tgoop.com/eotcy/2320
Last Update:
ለ2 ደቂቃ ቦታ ሰጥታችሁ አንብቡት
ከዕለታት አንድ ቀን ምድር የመሬት መንቀጥቀጥ ደረሰባት፤ መንቀጥቀጡ መሬት ላይ ያለውን ሁሉ ማነቃነቁ አይቀርምና ሁሉም ተናወጠ። በወቅቱ ከዛፍ ላይ አንድ የወፍ ጎጆ ነበረች፤
ይህች የወፍ ጎጆ በውስጧ እንቁላሎችን ይዛ ነበር። መሬቱ ሲንቀጠቀጥ ግን እንቁላሎቹን ይዛ ከነበረችው ጎጆ ውስጥ አንዱ እንቁላል ከዶሮዎች መንደር ወደቀ። ዶሮዎቹ እንቁላሉን እንደ እራሳቸው ተንከባክበውና ታቅፈው እንዲፈለፈል አደረጉ። ወፉ እንደ ዶሮ ዶሮዎቹ ጋር ተቀላቅሎ ማደግ ጀመረ። እነሱን መስሎ ዶሮነቱን አምኖ ኑሮውን መግፋቱን ቀጠለ። አንድ ቀን ከዶሮ ቤተሰቦቹ ጋር አንድ ላይ ሆነው በመሬት ሺንሸራሸሩ ወፎች በሰማይ ሲበሩ ተመለከቱ። ይሄኔ ወፉ, እኒህ በሰማይ በነፃነት የሚበሩት ወፎች ምንኛ የታደሉ ናቸው፤ ምናለ እኔም እንደነሱ መብረር ብችል "ሲል እራሱን እየተመለከተ ተናገረ። አብሮ አደጎቹ ዶሮዎች በወፉ ተሳለቁበት "አንተ እኮ ዶሮ ነህ እንደት እንደወፍ ለመብረር ታስባለህ ብለው ሃሳቡን አጣጣሉበት።
ወፉ ምንም እንኳን መብረር የሚችል ወፍ ቢሆንም እንደ ዶሮ ከዶሮ መሃል ስላደገ ዶሮ ነኝ ብሎ አምኗል። ማንነቱን ለውጦ አቅሙን አሳንሶ እራሱን ሳያውቅ ሌሎች ዶሮዎች በነገሩት ብቻ አለመብረሩን አምኖ ኖረ። ክንፎቹን ታቅፎ ሌሎች ወፎች ሲበሩ እየቀና እድሉን እያማረረ ኖሮ ሞተ።
መብረር ተፈጥሮው ሆኖ አልበርም ብሎ በማመኑ ብቻ ወፍ ሆኖ ተወልዶ ዶሮ ሆኖ ምድርን ተሰናበታት። የዚህ ወፍ ታሪክ የሁላችንም ታሪክ ነው። የምንመኘውን ነገር ለማድረግ ሁሉ ተሰጥቶን እያለ ሌሎች አይቻልም ስላሉን ብቻ አንችልም ብለን በማመን የፈለግነውን ኑሮ ሳንኖር እንሞታለን። እንደዛ ምስኪን ወፍ ከሌሎች መሃል ወድቀን ሌሎችን እንሆናለን። ማንነታችን ሌሎች እየነገሩን ራሳታችን ሳናውቅ እድሜያችን ይገፋል። አቅማችንን ሌሎች እየለኩት ችሎታችንን እና ተሰጥዖዋችንን ሳንጠቀምበት ህይወታችን ያልፋል። እስቲ እራሳችሁን ጠይቁት የወደቃችሁት ከማን መካከል ነው❓
ይቻላል ይሳካል ከሚሉት ወይስ አይቻልም አይሳካም ከሚሉት❓ ወፍ መብረር እየቻለ ከዶሮ መሃል ስላደገ እና ዶሮ ነኝ ብሎ ስላሰበ መብረር ምንም እንኳን ቢመኝ ሳይበር ቀረ።
የብዙዎቻችን ሕይወት ከዚህ ብዙም አይለይም። ሁሉ ነገር እያለን ሌሎች ሲሞክሩት ስላላየን ብቻ የማይቻል መስሎን ምኞታችን ምኞት ብቻ ይሆንብናል።
ይህን ነገር አስታውስ በባነነበት ሰዓት የሮጠ ሁሉ አረፈደ አይባልም። ነቅተን ዙሪያችንን እንመልከት፤ የከበቡንን እናስተውል። በዙሪያችን ያሉት አይቻልም ስላሉ ብቻ አይቻልም ብለን እራሳችንን ወደ ኋላ አናስቀረው። ከዶሮ መሃል እንደ ወደቀ ወፍ አትሁን። አቅምህን ተጠቀምበት፤ ፍላጎትህን ኑረው፤ ምኞትህን እውን አድርገው፤ ራስህን መመልከት ከቻልክ አንተ ከምታስበው በላይ ታላቅ ሰው መሆንህን ትደርስበታለህ። ማህበረሰብ ፣ ቤተሰብ ፣ ጓደኛ ባወጣልህ መስፈርት እና መመዘኛ እራስህን አትመዝን፤ ይልቁንም እራስህን በራስህ ፈትነው። ብዙዎች እንደ ወፍ ተወልደው እንደዶሮ ሞተዋል። ያ ክፉ እድልእኛን እንዳይገጥመን ሁላችንም የወደቅንበትን እንመልከት.....ሌሎች መብረር ካልቻሉ አንተ መብረር አትችልም ማለት እኮ አይደለም።
#ኦርቶዶክሳዊ_ትምህርቶች
አስተማሪ ሁኖ ካገኙት Like Share አስተያየትዎ
💚 https://www.tgoop.com/eotcy 💚
💛 https://www.tgoop.com/eotcy 💛
❤ https://www.tgoop.com/eotcy ❤
ወሰብሐት ለእግዚአብሔር!
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2320