tgoop.com/eotcy/2327
Create:
Last Update:
Last Update:
እናቶቻችን አሃዱ ሳይባል ውስጥ ለመግባት ነው የሚሮጡት
እኛሳ ወደዬት ይሆን የምንሮጠው ፡፡
ልሩጥ አይደክመኝም!
©ታደለ ሲሳይ
==============
ጉልበቴ ቢደክም፣ ቢዝል ሰውነቴ
የነፍሴ ብርታቷ፣ ናት እና እመቤቴ
ልሩጥ ወደ ቤቷ፣ ትቀደስ ሕይወቴ።
....................
ልሩጥ አይደክመኝም፣ ልሂድ ስሟን ልጥራ
የጨለመው ልቤ፣ በእመቤቴ ይብራ።
......................
ነፍሴ ብትቆሽሽ፣ ቢከስም ምግባሬ
አኑሮኛልና፣ ከዱሮ እስከዛሬ
ከእናቱ ጋራ ነው፣ ውሎዬና አዳሬ።
..................
ልሩጥ አይደክመኝም፣ ልጓዝ ወደ ቤቱ
ነፍሴን ያድሳታል፣ ቅዳሴ ማእጠንቱ።
.................
ቢዘል ከንቱ ጉልበት፣ ቢደክም ተፈጥሮ
ያፈረ ሰው የለም፣ ከእርሷ ጋራ ኖሮ።
......................
ሞት መጥቶ ሳይቀድመኝ፣ ሥጋ ሳይሆን አፈር
ነፍሴ ከሥጋዬ፣ በዕድሜ ሳትባረር
ልሩጥ አይደክመኝም፣ ልሂድ ወደ እግዚአብሔር።
...................
ሞት መጥቶ ሳይቀድመን፣ ሳንሆን ሬሳ
ኑ አብረን እንሩጥ፣ አብረን እንነሳ።😍🙏
https://www.tgoop.com/eotcy
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/Yy7XtpW_i3gvrUEuMNzrBWGdYUOcvoQW4M7b4GTw9cyF5YTeWCaI33L3UAwf8gfaiUVe1ajQmyyShdQ0R5oIkzPM4wllB9uFe16jvS1RdWVL0VM_KA_cvAVkxn7jjiDDrMNf7alBnJF-LN-cJlg8MNl7FZkQrwTjUK8PewJ0mJbtYQHQPyl_CpblkV4bB5lD4hWTyBJVZOhN3d9OxNa2yGX_K1bu59lCeuwaewUImm3GSjyY6MK50cZrH85DVlDEQaBAgJlUmXs1bWXvx6ejrmqVkmYH7P0Wuur3OeL6B6LgsXUCNu8P1lOku9L5iUh8mkVf7fTMHlLe7d0tTw0uhA.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2327