tgoop.com/eotcy/2333
Last Update:
በጣም አስተማሪ ታሪክ🙏
ይነበብ ‼️
አንድ ሰው በበረሃ እየተጓዘ እያለ የያዘው ውሃ አልቆበት በውሃ ጥም ይያዛል ቀስ በቀስ ውሃ ጥሙ ሰውዬውን እያደከመው ይመጣል በስተመጨረሻ ከአንድ የውሃ ጉርጓድ ጋር ይደርሳል ጉርጓዱ በጣም ጥልቅ ነበረ ውሃ ይኑረው አይኑረው አይታይም፡፡
ከዚያም ከጉርጓዱ ጎን አንድ አሮጌ የውሃ መሳቢያ ሞተር አለ ሞተሩ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ሰፍሯል፡፡ ‹‹ይህ የውሃ መሳቢያ ሞተር የሚሰራው በውሃ ነው›› ይላል፡፡
ከሞተሩ ጎን አንድ ጆግ ሙሉ ውሃ ተቀምጧል ጆጉ ላይ እንዲሁ አንድ ጽሁፍ ሰፍሯል ‹‹ወዳጄ ሆይ ይህንን ጆግ ውሃ ሞተሩ ውስጥ ጨምረው ሞተሩ ብዙ ውሃ ያወጣልሃል ታዲያ አደራ አንተም እንዳንተ ላለ ሌላ መንገደኛ ይጠቅማልና ውሃው ከጉርጓዱ ሲወጣልህ ጆጉን ሞልተህ ማስቀመጥን አትርሳ›› ይላል፡፡
በጆግ ያለውን ውሃ ሞተሩ ውስጥ ልጨምረው ወይስ ልጠጣው❓ እዚጋር ሰውዬው በሁለት ሃሳብ ተወጠረ ‹‹አንደኛ ይህ ሞተር አርጅቷል ጨምሬው ባይሰራ ይህንንም ውሃ አጣሁ ማለት ነው ሞትኩ ማለት ነው☹️ ስለዚህ ልጠጣውና ህይወቴን ላድን ፡ ደሞ ማሳሰቢያውስ ውሃው ያለሞተር አይሰራም እንደኔ ውሃ የተጠማ ሰው ቢመጣ ይህንን ማንቀሳቀሻ ከጠጣሁት ይሞታሉ›› 😭😭ብሎ ለራሱም ለሌሎቹም አሰበና በሃሳብ ተወጠረ በስተመጨረሻ በብዙ ጭንቀት ተወጥሮ ትልቅ ውሳኔ ወሰነ እንዲህ አለ ወደሞተሩ ብጨምረው ይሻላል ከሰራ ጥሩ ካልሰራ ግን እሞታለሁ እንጂ በፍፁም ‹‹ውሃውን ይህንን ጆግ ውሃ ጠጥቼ ሄጄ ዘለዓለሜን ስለዚህ ጉርጓድና ይህንን ውሃ አተው ስለሚሞቱ ሰዎች እያብኩ መኖር አልፈልግም›› ❌አለ፡፡
ከዚያም የጆጉን ውሃ ወደ አሮጌው ሞተር ውስጥ ጨመረውና የሞተሩን ማስነሻ ተጫነው፡፡ ሞተሩም ድምፅ እያሰማ ውሃ የማውጣት ስራውን ጀመረ፡፡ ሰውዬው ተደነቀ🤭 የሚፈልገውን ያህል ጠጣ አካባቢው በሙሉ በውሃ እራሰ ከጠበቀው በላይ አካባቢው ሁሉ ውሃ በውሃ ሆነ😃 ከዚያም በተባለው መሰረት እሱም ጆጉን በውሃ ከሞላው ቦሃላ ጆጉ ላይ ፅሁፍ ጨመረበት ‹‹እመኑኝ በትክክል #ይሰራል›› አለ፡፡
🟢🟡🔴
እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ለራስ ማሰብ በህይወት መኖር ነው ለሌላው ማሰብ ግን ሰው መሆን ነው‼️ያለህን ሳትሰስት ከሰጠህ በእጥፍ ድርቡ ፈጣሪ ይሰጥሃል፡፡ ሰውዬው ጆግ ውሃ ሰቶ አካባቢን የሚያርስ ውሃ እንደተቸረው አንተም የምትሰጣት ጠብታ ከልብህ ከሆነ በእጥፉ ይሰጥሃል፡
ቅዱሱ መጽሐፍ እንዲ ይለናል
በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል። 1ኛ ቆሮንቶስ 13÷1-8
መስጠትን ብቻ ሳይሆን አሰጣጥህ ወሳኝነት አለው፡፡ አንዳንዴ ከመንጠቅ የማይተናነስ መስጠትም አለ‼️
ምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በፍቅር ይሁን
መልካም ቀን
꧁ ይ🀄 ላ 🀄ሉ ꧂
https://www.tgoop.com/eotcy
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2333