tgoop.com/eotcy/2336
Last Update:
✔ በምጸልይበት ጊዜ ሐሳቤ አይሰበሰብም
✔ እንዲህ ከሆነ መጸለይ ቢቀርብኝስ❓
አጭር አስተማሪ ታሪክ ነው አንብቡት
https://www.tgoop.com/eotcy
☞︎︎︎ ልቡናውን ሰብስቦ መጸለይ ያቃተው አንድ ደቀ መዝሙር አረጋዊውን አባት እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል፡- “አባቴ የጸሎት መጽሐፍ ይዤ ስጸልይ ልቡናዬ አይሰበሰብልኝም፤ አፌ ቢያነበውም ልቡናዬ ግን ይበታተናል፡፡ እኔ ደግሞ ዝም ብዬ ሳስበው፦ ቅዱሳን በፍጹም ሐሳባቸው እያሰቡና እያራቀቁ እንባንና ጸጸትን እየጨመሩ የጻፉትን እኔ በልቤ ሌላ እያሰብኩ በአፌ ብቻ ባነበንበው እንደ ገደል ማሚቶ ፊደሉ አፌ ላይ እየነጠረ ይሄዳል እንጅ ጸሎትም አይሆንልኝም ፡፡
☞︎︎︎ ስለዚህ አባቴ የአፍ ብቻ ጸሎቴ ቅድመ እግዚአብሔር የማይደርስ ከሆነ ጸሎቴን ብተወው ይሻላል ወይስ ባልተወው ይሻላል?" ብሎ ጠየቃቸው። አረጋዊው አባትም እንዲህ ሲሉ አስረዱት፡-
☞︎︎︎ “አየህ ልጄ ዐይነ ስውር ሰው በዘንጉ ምድር እየመታ ሲሄድ ከመንገድ ላይ ያለ እባብ ለጊዜው የበትሩን ድምጽ ሰምቶ ይመታኛል ብሎ ይሸሻል እንጅ ዐይነ ስውር ነው አላየኝም ብሎ ባለበት አይጠብቀውም። ስለዚህ አንተም አስተውለህ ብትጸልይ መልካም ቢሆንም ለጊዜው ግን ጭራሽ ከምታቆመው በአፍህ ውስጥ ያለው የቃለ እግዚአብሔርን መንኳኳት የሚሰሙ አጋንንት መሸሻቸው አይቀርምና መቼም ቢሆን ጸሎትህን አትተው፡፡ አጋንንትንም ማባረር አንድ ታላቅ ጥቅም ነውና፡፡ ብዙ ከመጸለይህም አንጻር አንዳንድ ጊዜ ልብህ የሚወድቅባት ቃል ተጠራቅማ ወደ እግዚአብሔር ታደርስሃለች።
☞︎︎︎ እናም ልጄ ልብህ ምንም ዝርው ቢሆንም አፍህም የልዑል እግዚአብሔር ፍጥረትነውናይህንንምእንዳታቆመው። አሁን አንዱን ይዘህ ወደፊት ደግሞ ሁለቱንም ለማገናኘት መጣር ይኖርብሃል እንጅ አንተው በዳይ አንተው አኵራፊ ሆነህ ጭራሽ ከአምላክ ርቀህ የጠላት ሰይጣን መጫወቻ እንዳትሆን በማለት መለሰለት:: ስለዚህ እኛም በምጸልይበት ጊዜ ልቤ አይሰበሰብም እንዲህ ከሆነ መጸለይ ቢቀርብኝስ ❓ ብላቹሁ እንዳታቆሙ እህት ወንድሞቼ
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
https://www.tgoop.com/eotcy
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2336