Telegram Web
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
🌹ልደታ ለማርያም🌹፦ ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግንቦት አንድ ቀን (የግንቦት ልደታ) የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ‹‹የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት›› ያላት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ…
[ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ]

የብርሃን እናት ዛሬ ተወለደች

         "ሐና አንቺን ያፈራችባት
      ኢያቄምም  አንቺን ለሕይወት ያፈራባት
     የደስታ ሰዓት ምንኛ የተባረከች የተቀደሰች ናት
      የዓለሙ ሁሉ መድኃኒት አንቺ ነሽና
     አንዲት ርግቤ ሆይ ተአምርሽን አመሰግናለው "
                              ማኅሌተ ጽጌ


የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት ቀን ለክርስቲያኖች ሁሉ የደስታ ዕለት ናት ቅዱስ ያሬድ " ከኢያቄምና ከሐና ስለተወለደች ስለማርያም ልደት ዛሬ ደስታ ሆነ የብርሃን እናት በእውነት ተወለደች" እንዳለ ይህ ቀን የደስታችን ቀን ነው ለምን ቢሉ የመመኪያችን ዘውድ የንጽሕናችን መሠረት ድንግል ማርያም የተወለደችበት ዕለት ነውና፣ የነቢያት የትንቢታቸው ፍጻሜ የዓለም ብርሃን የተባለ መድኃን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን የምትወልድን የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ዕለት ነውና ነው ፡፡
የእመቤታችን ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሃ ፈሳሽ በድንገት የሆነ አይደለም አስቀድሞ በነቢያት ትንቢት የተነገረለት በአበው ሕይወት ውስጥ ምሳሌ የተመሰለለት ነው ለአብነትም
~ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት " መሠረቷቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው "መዝ 86፡-1 ብሎ በዝማሬው የተቀኘው ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላጆች ንጽህና ነው  የተቀደሱ ተራሮች ያለውም የእመቤታችን ሥርወ ልደት ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ከሆኑት ከተቀደሱት ከኢያቄምና ከሐና የመሆኑን ነገር ሲያመለክት ነው፡፡ ይህንን ትንቢትና እውነተኛውን የእመቤታችንን የትውልድ ሀረግ አስማምታ ቤተክርስቲያን ‹‹የእመቤታችን ማርያም ትውልዷ በአባቷ በኩል ከንጉሡ ከዳዊት ወገን ነው፤ በእናቷም በኩል ከካህኑ ከአሮን ወገን ነው፤ የአባቷ ስም ኢያቄም ነው፤ የእናቷም ስም ሐና ነው፡፡›› ብላ ታስተምራለች፡፡
~ ጠቢቡ ሰሎሞንም "ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ" መኃ 4፡8 ብሎ ሙሽራ የምትባል ድንግል ማርየም የት እንደምትወለድ ጭምር አስቀድሞ በትንቢት ነግሮናል
@eotcy
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት መሰረት የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለው ተራራማ ሀገር ነው፡፡ የዚህ ትንቢት ምስጢርም የእመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን ያስረዳሉ ትንቢቱም ሲፈጸም ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት 1 ቀን በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች
~ እናት እና አባቷ እርሷን ከመውለዳቸው በፊት በተቀደሰ ትዳር እየኖሩ ልጅ አጥተው እግዚአብሔርን ደጅ በመጥናት የሚኖሩ ቅዱሳን ነበሩ  እግዚአብሔር ከልጅ ሁሉ በላይ የሆነች አምላክን የምትወልድ ልጅን ሰጣቸው ስሟንም ማርያም ብለው ጠርተዋታል ጸጋ ወ ሐብት ማለት አስቀድማ ጸጋ /ስጦታ፣ ሐብት /በረከት ሆና ለእናት እና አባቷ ተሰጥታለች በፍጻሜ ግን መድኃኒት የተባለ ክርስቶስን ወልዳለች እና ለሰው ሁሉ ስጦታ ናት ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳያስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር እንዳለ ጠፍተን እንዳንቀር ምክንያተ ድኂን የሆነችን ድንግል ማርያም ስጦታችን ናት ፡፡

 ቅዱስ እንድርያስ የከበረ ስለሆነው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ታላቅነት ‹‹ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌው በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል፤ የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ ዕለት (ጌታ) መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነው፡፡” በማለት ገልጾታል፡፡ የእርሷ ልደት የልዑል ማደሪያው መቅደስ የተሰራበት ዕለት ነውና ሁላችን እናከብረዋለን፡፡ በዚህም ዕለት ‹‹ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም/ እነሆ ዛሬ በእመቤታችን ልደት ደስታ ሆነ›› እያልን እንዘምራለን
   
" ኢያቄምና ሐና  በጸለዩ በአለቀሱ ጊዜ
  ለሁላችን ምእመናን መጠጊያ የምትሆን
  ኃጢአት ይቅር የምታስብል ሴት ልጅ አገኙ
  ሁለቱ ሽማግሌዎች ሰማይን ወለዱ
  ሰማያቸውም ጸሐይን አስገኘች "

                         ነግሥ ዘልደታ
@eotcy
ምን ላድርግ..

" የዝሙት አሳብ እኔ ሳልፈልገው ይመጣብኛል ከዛም ወደሱ እሳባለሁ.. ምናልባትም ከሃሳብም ዘልዬ የሆኑ ነገሮችን አደርጋለሁ.. ልክ ሲያልፍ መጸጸት እጀምራለሁ..
ምን ላድርግ"

1. ሚስት ከሌለህ በጭራሽ ስለ ግንኙነት አታስብ

2. የምታየውን ነገር በጣም ምረጥ.. ፊልም የምታይ ከሆነ ፊልሙ ወደ እንደዚህ አይነት ሙድ ውስጥ የሚከት ነገር በፍጹም ሊኖረው አይገባም.. ትንሽ እንኳን ካለው በቃ አእምሮህ ላይ ተቀምጦ ለወደፊትህም ሌላ ፈተና ይሆንብሃል.. ስለዛ ገና ከጅምሩ አሳቦቹ እንዳይመጡ ተከላከል

3. አንተ ባትፈልገውም አዎ አሳቡ ሊመጣ ይችላል ግን ደግሞ ለዛ አሳብ ተባባሪ አትሁን.. አልወድቅም ብለህ በማሰብ ወይም ማሰቡ ብቻ ችግር የለውም ብለህ ተዘናግተህ በአሳብ ወደዛ አትወሰድ.. ይልቁንም ገና አሳቡ ሲመጣ ራስህን በሌላ ነገር ቢዚ አድርግ..

4. ፈተናው በጣም የከበደ ሲመስልህ የጌታን የስቅለት ስእል እያየህ እንዲህ ብለህ ተናገር፡ "አዎ ፈተናው ብርቱ ነው.. አንተ ግን ከፈተናዎችም ሁሉ በላይ የበረታህ ነህ" ስለዚህም የመስቀሉን ኃይል ትታጠቃለህ

5. ጦርነት ሜዳ ውስጥ ነህና ሁሌም ክርስቶስ በአንተ ኖሮ እንዲዋጋልህ ፍቀድለት.. እርሱ በአንተ ይኖር ዘንድ ንስሐ እየገባህ ከቅዱስ ምስጢር(ቁርባን) ደጋግመህ ተሳተፍ.. ሁሌም አጫጭርም ቢሆን ጸሎት አድርግ..

እና ደግሞ ብቻችሁን አትሁኑ ከሰው ጋር መቀላቀል ያስፈልጋል

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

🟢 @eotcy 🟢
🟡 @eotcy 🟡
🔴 @eotcy 🔴
እርቃን_ገላዎች

      አንብቡት  #ሼር

ሁለት ወጣት ሴቶች ግማሽ አካላታቸውን ብቻ የሚሸፍን ልብስ ለብሰው ስብሰባ ቦታ ደረሱ ። የስብሰባው መሪ በጥሩ ፈገግታ ተመለከታቸውና እንዲቀመጡ ጋበዛቸው ። ከዚያም እነዚህ ሴቶች በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ሊረሱት የማይችሉትን መልዕክት ተናገራቸው ። ትኩር ብሎ አይናቸውን እያየ እንዲህ አላቸው ፣ "ሴቶች ፈጣሪ የፈጠራቸው በጣም አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ በሚገባ የተሸፈኑና እንዲሁም ለማየትና ለማግኘት ብዙ ጥረት የሚጠይቁ ናቸው ።https://www.tgoop.com/eotcy

፩ አልማዞችን የት ነው የምታገኙአቸው ? ከመሬት በታች ከብዙ ጥልቀት በኋላ ተሸፍነውና ተደብቀው ።

፪ ወርቆችን የት ነው የምታገኟቸው ? ከማዕድናቶች በታች በትላልቅ ድንጋዮች ተሸፍነው ነው ። እነሱን ለማግኘት ወደታች ብዙ ርቀት ጠንክራችሁ መቆፈር ፣ መስራትና መፈለግ አለባችሁ ።https://www.tgoop.com/eotcy

ከዚያም ፊታቸውን ትኩር ብሎ እያየ ንግግሩን ቀጠለ ። "የእናንተ ሰውነት አስፈሪና ልዩ ነው ። የእናንተ ሰውነት ከአልማዝ ፣ ከወርቅና ከሌሎች የበለጠ ውድና ማራኪ ነው ። ስለዚህ እናንተም በሚገባ ልትሸፈኑ ይገባል ። ንግግሩን ቀጠለ ፣ ይህንን ውድ ሃብታችሁን ልክ እንደ አልማዝና ወርቅ በሚገባ ከሸፈናችሁና በቀላሉ እንዳይገኝ ካደረጋችሁ ታማኞችና አስፈላጊውን የማዕድን ማውጫ መሳሪያዎች ያላቸው ማዕድን አውጪ ድርጅቶች እናንተን ለማግኘትና ለዘመናት የማዕድን ማውጣት ስራቸውን ለመስራት ወደ እናንተ ይጎርፋሉ ።

በመጀመሪያ ከሃገራችሁ መንግስት( ቤተሰባችሁ) ጋር ይገናኛሉ ፣ ፕሮፌሽናልና ህጋዊ ፊርማ (ህጋዊ ጋብቻ) ይፈራረማሉ ። ነገር ግን የህንን ውድና ማራኪ ሃብታችሁን በሚገባ ባትሸፍኑትና ባትጠብቁት ሁልጊዜ ህገወጥ ማዕድን አውጪዎች ወደ እናንተ እንዲመጡና ውድ ማዕድናችሁን በህገወጥ መንገድ እንዲያወጡት ትማርካላችሁ ። ከዚያም ምንም ሳይጥሩና ሳይደክሙ በቀላሉ ውድ ሃብታችሁን ይወስዳሉ ማለት ነው ።
https://www.tgoop.com/eotcy
ስለዚህ ሴቶች እባካችሁ ሰውነታችሁን በሚገባ ሸፍኑ ። ይህን ካደረጋችሁ ፕሮፌሽናሎችና ህጋዊ ማዕድን አውጪዎች እናንተን ያሳድዳሉ ።"  እህታቹሁ ፍቅርተ ኢየሱስ

እስቲ ሁላችንም ወንዶች እህቶቻቹሁ፤ሚስቶቻችንን ፣ ጓደኞቻችንንና
ልጆቻችንን እንድሸፍኑ አስተምራቸው ።
      የቅዱሳን አምላክ ማስተዋልን ይስጠን🙏
ሰናይ ቀን ተቀላቀሉ ቴሌግራም👇

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
አንድን ህጻን ልጅ ማሙሽዬ ድንግል ማርያም ላንተ ምንድን ናት
ብዬ ጠየኩት
."ድንግል መርያም ፊደሌ ናት " አለኝ
አንዲት ወጣትንም ድንግል ማርያም ላንቺ ማን ናት ብዬ ጠየኳት
."የደናግል መመኪያ ናት " አለችኝ ።
አንድንም ወጣት ጠየኩት
" ውበት ናት " አለኝ ።
.....
ስደተኛም ሰው አግንቼ ጠየኩ
" እሷ የስደተኞች ስንቅ ናት " አለኝ ።
....@eotcy
አንዲት እናትንም ጠየኩ
" እሷ የአለም ሁሉ እናት ነች " አሉኝ ።
የቆሎ ተማሪውንም ጠየኩት
" ድንግል ማርያም መመኪያ ናት ስሟን ይዘህ አታፍርም " አለኝ ።
..
ዶክተሩንም ጠየኩት
" የመዳኒት እናት ነች " አለኝ
አናጢውንም ድንግል ማርያም ላንተ ምንድን ነች ብዬ ጠየኩት
.
"የአለም ሁሉ መሰላል ነች " አለኝ
.
አገልጋዩንም ጠየኩት
" የጻድቃን እመቤት ነች" አለኝ
ችግረኛ ድሀውንም ጠየኩት
" የሁሉ ሀብት ነች " አለኝ
.
ባለጸጋውንም ጠየኩት
"ድንግል ማርያም በረከት ነች " አለኝ
ወታደርም አግንቼ ጠየኩ
" ድንግል ማርያም ጋሻ መከታ ናት " አለኝ
.
ያረጁ አዛውንትም አግንቼ ጠየኩ
" ድንግል ማርያም ምርኩዝ ናት " አሉኝ
.........
....
በመጨረሻ ራሴን ጠየኩ
.
አይምሮዬም እንዲህ ብሎ መለሰልኝ
.....
የመስቀል ስር የአደራ ስጦታህ
.
የህይወትህ እንጀራ የተዘጋጀባት መሶብህ
የህይወትህ መጠጥ የተዘጋጀባት ፅዋህ
ከዘላለማዊ ፍዳ ወደ ዘላለማዊ ምህረት የተሻገርክባት መሰላልክ
እንኳን አንተ ቅዱሳን ምሳሌ ያጡላት ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን
እርሷን የሚመስል የሌለ ንግስተ ሰማይ ወምድር ናት።
ድንግል ማርያም የሁሉ መማሪያ ናት" አለኝ
ሁሉ ይማርባታል ፦ ፊደል መጽሀፍ እውቀት ነች ፡
ሁሉ ይማርባታል ፦ምህረት ታስገኛለች ታማልዳላች ።

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

@eotcy
ድንቅ ልዩነት ተመልከቱ

https://www.tgoop.com/eotcy

በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ፈርዲናንድ ማጄላን ዓለምን በመርከብ ዞረ።

👉ሐዋርያቱ ደግሞ መርከባቸውን ጥለው ዓለምን ዞሩ!

ዛሬ ይዘንባል እያሉ ትንቢት የሚተነብዩ ሜትሮሎጂስት ሞልተዋል።

👉እንደ ኤልያስ ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን የዘጋ ዳግመኛም ዝናብን ያዘነበ ከቶ የለም።

በላብራቶሪው ተመራምሮ ህሙማንን የፈወሰ ሞልቷል።

👉እንደ ጴጥሮስ ጥላው ድይው የፈወሰ ከቶ አላየሁም።

በዘፈኑ አጋንንትን የጠራ እንደ ማይክል ጃክሰን ሞልቷል።

👉እንደ ዳዊት በበገና መዝሙር አጋንንትን ያስወጣ እስከ ዛሬ አልተገኘም።

ኮረቫትና ሱፉን ለብሰው የምንጎራደዱ ሞልተዋል።

👉የልብሱ ቁራጭ አጋንንት ያስወጣ እንደ ጳውሎስ ከቶ አልተገኘም።

የግብፅ ነገስታት አፅማቸው በክብር ይቀመጣል።

👉ዐጥንቱ ሙት ያስነሳ እንደ ኤልሳዕ ከቶ አላየንም።

በአሜሪካ የነገሥታትን ምሥጢር የሚሰልሉ ድርጅቶች ሞልተዋል።

👉እንደ ኤልሳዕ በእስራኤል ሆኖ በሶሪያ ቤተመንግሥት የሚደረገውን ምሥጢር ያወቀ አልተገኘም።

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃን በእግሩ የረገጠ ዩሪ ጋጋሪ ዛሬ ብዙዎቹ አድንቀውታል።

👉 እንደ ኢያሱ ፀሐይን ያቆመ ከቶ አልተገኘም።

ሼር

ጥበብን ለቅዱሳን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን
አንዲት ሀይማኖት ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር~
https://www.tgoop.com/eotcy
በአንድ ወቅት አንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል ፊት ቆሞ ጌታየ ሆይ! አንተ ከእኔ ምን ትፈልጋለህ? ምንስ ባደርግልህ ደስ ትሰኛለህ?...እስቲ ንገረኝ ረጅምና በቁመቴ ልክ የሆነ ከሰም የተሰራ ሻማ እንዳመጣልህ ትፈልጋለህ? አለው። ጌታም መልሶ "ለሻማው መስሪያ የሚሆነው ሰሙም የእኔ ነው፤ ሰሙ የሚገኝበት የማር እንጀራውም የእኔ እኮ ነው"አለው።

ሰውየውም መልሶ "ይሁን እንግዲህ ወይ ለሰንበት ቅዳሴ የሚሆን ለሥጋ ወደሙ የሚሆን መገበሪያ ይዤልህ እመጣለሁ አለ።
ጌታችንም መልሶ "የሥጋ ወደሙ የሚዘጋጅበት ስንዴም ቢሆን የእኔ እኮ ነው" አለው።
@eotcy
ያም ሰው ቀጥሎ "እንግዲውስ ድሆችን ለመርዳት ይሆን ዘንድ 1000,000 ብር እሰጥሃለሁ አለው። ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ "
አንተ አለኝ ያልካቸው ነገሮች ሁሉ የእኔ ናቸው፤ ምድርና መላዋ ለእግዚአብሔር ናት ፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ። መዝ.24:1) አለው።

ሰውየውም እንዲህ አለ " ጌታዬ ሆይ እሺ ምን እንዳመጣልህ ነው የምትፈልገው?
@eotcy
ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ፣ ስለአንተ ብየ ተጠምቻለሁ ፣ ስለአንተ ፍቅር መስቀል ላይ ወጥቻለሁ አለው።

እግዚአብሔር ካለን ነገር በፊት እኛን ይፈልገናል። ራሳችንን ሳንሠጠው ብንደክም ብንለፋ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው" (ሉቃ. 10:42) ይለናል ይህም ልባችንን  ለእርሱ  በቃሉ ለመኖር መሥጠት ነው።

እውቀታችንን ሠጥተን ፣ ገንዘባችንን ሠጥተን ፣ ጉልበታችንን ሠጥተን እኛ የእርሱ ካልሆንን ምን ይጠቅማል? ኃጢአት ከእርሱ ለይታናለችና ፣ በንስሐ ልባችንን እንዲንሠጠው በመንፈሳዊ ምሥጢራት ከእርሱ ጋር አንድን እንድንሆን ይሻል። ራሳችንን በንስሐ አቅርበን ልባችንን ለፈጠረን አምላክ እንስጠው።
ወሰብሐት ለእግዚአብሔር

꧁  ይ🀄🀄ሉ ꧂

🟢  @eotcy  🟢
🟡  @eotcy  🟡
🔴  @eotcy  🔴
#ለምን_አንጾምም?

ተወዳጆች ሆይ የተሃድሶ መናፍቃን በዓለ ሃምሳን ለምን አትፆሙም ሲሉ ይደመጣሉ ከዛም አልፎ በዓቢይ ጾም የጾማችሁትን ለማካካስ ነው በማለት ይተቻሉ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንስ ምን ትላለች?

ጥያቄ:- በበዓለ ሃምሳ ለምን አንጾምም?
በፍትሐ ነገሥት ላይ እንዲህ የሚል ትዕዛዝ አለ፦ "ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር" /ዐንቀጽ 15:566/።

"የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ" /ዐንቀጽ 15:603/። የዐቢይ ጾምን ፍቺ ተከትሎ ለ50 ቀናት የማንጾምበት ምክንያት ብዙ ጥልቅ ምሥጢር ያለው ሥርዓተ ሃይማኖት ነው። በምሳሌ ለማስረዳትም ፦ ከትንሣኤ በፊት ያለውን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ብለን የምናስበው ዘመነ ኦሪት እንደሆነ በማሰብ ነው።

በዚኸ ሳምንት ከሌሎች ድርጊቶች በተጨማሪ መስቀል አንሳለምም። ይኸ የሆነበት ምክንያት በዘመነ ኦሪት መስቀል በክርስቶስ መለኮታዊ ደም ተባርኮ አልተሰጠም'ና ነው። ልክ እንደዚሁ ከትንሣኤ ዕለት ጀምሮ አስከ በዓለ ጰራቂሊጦስ (አስከ የሐዋርያት ጾም መግቢያ ድረስ) ያሉት 50 ቀናት እንደ አንድ ቀን ነው የሚታዩት። ይህም ማለት ሰው ከትንሣኤ በኃላ ፍጹም ያለ ድካም እንደሚኖር ለማስተማር ጾም እና የንስሐ ቀኖና አይሰጡም።
https://www.tgoop.com/eotcy
. ⛪️ #በዙፋኑም_መካከል: በዙፋኑም ዙሪያ በፊትና በሁዋላ ዓይኖች የሞሏቸው አራት #እንስሶች_ነበሩ:: ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል:: #ሁለተኛውም_እንስሳ ጥጃን ይመስላል:: #ሦስተኛውም_እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው:: #አራተኛውም_እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል:: #አራቱም እንስሶች #እያንዳንዳቸው_ስድስት ክንፎች አሏቸው::(ራዕይ 4:6)🙇‍♀🦋


(፰🕯) አርባዕቱ እንስሳ 🙏

#አርባዕቱ_እንስሳ ማለት⛪️

#የቅድስት_ሥላሴን_መንበር_የሚሸከሙ #የእግዚአብሔር_ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ #ዙፋን_ፊት_በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት #እንስሶች_አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።

አንድም የራሳቸውን #ክብርና_ተፈጥሮ ያስረዳል ገጸ ሰብእ አስተዋይነታቸውን ፤ ገጸ #አንበሳ_ግርማቸውን ፤ ገጸ ላሕም ተገዢነታቸውን ፤ ገጸ ንስር ተመስጧቸውን ያስረዳል ።https://www.tgoop.com/eotcy

አንድም ነገረ #እግዚአብሔርን_ያስረዳሉ ይኸውም ገጸ #ላሕም_ለሥጋዌው ፣ ገጸ ንስር ለተራዳኢነቱ ፣ ገጸ አንበሳ ለኀያልነቱ ፣ ገጸ ሰብእ ለመግቦቱ ምሳሌ ነው ።

አንድም ገጸ #ሰብእ_ሰው መሆኑን ፤ ገጸ አንበሳ ድል አድራጊነቱን ፤ ገጸ ላሕም #መሥዋዕትነቱን ፤ ገጸ ንስር #ትንሣኤውንና ዕርገቱን ያስረዳል

አንድም #በዐራቱ_ወንጌላውያን ይመሰላሉ ገጸ ሰብእ #በማቴዎስ ፣ ገጸ አንበሳ #በማርቆስ ፣ ገጸ ላሕም #በሉቃስ ፣ ገጸ ንስር #በዮሐንስ ይመሰላላል🙏

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

🤲 🤲 🤲
https://www.tgoop.com/eotcy
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የእናት ምልጃ ፊት አያስመልስ አንገት አያስቀልስ

በማቴ 15÷21-28 ላይ አምልኮተ እግዚአብሔር ከማያውቁ አህዛብ መካከል የሆነች ኃጢአተኛ የነበረች አንዲት ከነናዊት ሴት ወደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀርባ ጌታ ሆይ የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል ብላ ጮኸች። ይቺ ሴት ለልጅዋ አማላጅ ሆና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት በመምጣቷ እንደዳነችላት ተገልጧል። እስኪ አስተውሉ በጌታ አንደበት ውሻ የተባለች አህዛባዊት የሆነችው ይህቺ ኃጢአተኛ ሴት ለልጇ አማላጅ ሁና ድኅነት ካሰጠች ሰማያዊ ንጉስ እግዚአብሔር ፍፁም ንጽሕናዋን ቅድስናዋን የወደደላት ቅድስት ድንግል ማርያም እንዴት አታማልድም ተብሎ ይነገራል እንደት የእናት አማላጅ አትሆንም ተብሎ ይነገራል

እሷኮ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አንደበት ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ጌታ ካንች ጋር ነው አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ.. ሉቃ 1÷28 ተብላ የተመሠገነች የከበረች እግዚአብሔር እናት ናት።

በእርግጥ እውነት ነው አዎ እመቤቴ አታማልድም እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል ያለችው ትውልድ ለሆኑት እንጂ ላልሆኑትማ እንዴት ልታማልድ ትችላለች የምትመሰገነውስ ትውልድ ነኝ ብሎ ለሚያምነው እንጂ ለማያምነውማ እንዴት ሁኖ ይቻለዋል።

የእናት ምልጃ ፊት አያስመልስ አንገት አያስቀልስ መባሉ እውነት አይደለምን

የእመቤታችን የእናትነት ፍቅሯን በልባችን ጣሟን በአንደበታችን ያኑርብን
#ሼር

@eotcy
@eotcy
@eotcy
ይህን ያውቁ ኖሯል

አርፈው መቃብራቸው ያልተገኘ ቅዱሳን

፩..ሊቀ ነቢያት ሙሴ
፪..ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
፫..ጻድቁ ዮሴፍ (አረጋዊው ዮሴፍ)
፬..መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
፭..የቅዱስ ዮሐንስ አባት (ካህኑ ዘካርያስ)
፮..ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ

እስከ አሁን በሕይወት በብሔረ ሕያዋን ያሉ እና ሞትን ያልቀመሱ ግን ወደፊት የሚሞቱ ተሰውረው ያሉ አባቶች።

፩..ኢትዮጲያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ (ግንቦት 11 ቀን ተሰውሯል)
፪..አብነ አረጋዊ ዘሚካኤል (ጥቅምት 14 ቀን ተሰውሯል
፫..ርዕሰ አበው ሄኖክ (ሐምሌ 25 ቀን ተሰውሯል)
፬..ርዕሰ ነቢያት ኤልያስ (ጥር 6 ቀን ተሰውሯል)
፭..ነቢዩ እዝራ
፮..ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ ፣ ነባቤ መለኮት (ጥር 4 ቀን ተሰውሯል)
፯..ንጉሥ ነአኩቶ ለአብ (ሕዳር 3 ቀን ተሰውሯል)
፰..አቡነ ክፍለ ማርያም ዘትግራይ (የካቲት 20 ቀን ተሰውረዋል)
፱..አቡነ ገሪማ ይስሐቅ (ሰኔ 17 ቀን ተሰውረዋል)
፲..አቡነ አፍጼ (ግንቦተ 29 ቀን ተሰውረዋል)
፲፩..አቡነ ሊቃኖስ (ሕዳር 28 ቀን ተሰውረዋል)
፲፪..የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ልጅ ዳግማዊ ቂርቆስ (ታኅሣሥ 12 ተሰውረዋል)
፲፫..አባ ገብረ ሕይወት በአስቦት ገዳም (በ1945 ዓ.ም ተሰውረዋል)
፲፬..አባ በላይ ወ/ሚካኤል በአስቦት ገዳም (ሐምሌ 7 ቀን ዓ.ም (ተሰውረዋል)

በዚህ በተጨማሪ ስማቸው ያልተጠቀሱ እናንተ የምታውቋቸው የተሰወሩ ቅዱሳን ካሉ በኮሜንት መስጫው ላይ ጻፉልን!

የቅዱሳን ምልጃቸው በረከታቸው ከሁላችን ህዝበ ክርስቲያን ጋር ይሁን አሜን አሜን አሜን💒
Https://www.tgoop.com/eotcy
ግንቦት 12 -  ዕረፍቱ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ።

ቅዱሳን የማይታየው እግዚአብሔርን በሕይወታቸው አጉልተው የሚያሳዩን ናቸው።

የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ የዓለም ሁሉ መምህር የኾነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያረፈው በ407 ዓ.ም በስደት እያለ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በሕዝቡ ዘንድ ይወደድና ይከበር የነበረ አባት ስለ ነበር ገና በስድሳ ዓመቱ ማረፉ እጅግ መራራ ኀዘን ነበር። ይህም ዘወትር በልቦናቸው ሰሌዳ በኀሊናቸው ጓዳ ይኖር  ነበር።

በ434 ዓ.ም የቁስጥንጥንያ ፓትሪያርክ የኾነውና
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደቀመዝሙር የነበረው ቅዱስ ጵሮቅለስ  አንድ ቀን በሃጊያ ሶፊያ እያስተማረ ሳለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን እያመሰገነ ሰበከ  "ዮሐንስ ሆይ መላ ዘመንህን በሀዘን በመከራ አሳለፈክ ዕረፍትህ ግን የተወደደችና የተከበረች ኾነች! ቅዱሱ ሰውነትህ ያረፈበት መካን ንዑድ ክብርት ናት። ፍቅርህ የቦታን ወሰን አለፈ መታወስህ ይህን አጥርና ድንበር አፈረሰ…

ቅዱስ ፖትሪያርክ ጵሮቅለስ ይህን እየተናገረ እያለ ቃሉን ያደምጡ የነበሩ ሁሉ ማልቀስ ጀመሩ  ትምህርቱንም ሊያስጨርሱት አልተቻላቸውም። ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስን እጅግ ይወዱት ነበርና!

"እኔም ስለ እርሱ እላለሁ በእውነት አፈወርቅ አፈ እንቁ……በእውነት አፈ ጳዝዮን ነው በድርሰቶቹ ቤተክርስቲያንን የሚያስጌጣት አፈ ባሕርይ። በእውነት አፈ መዐር በቃሉ ጣፋጭነት ምዕመናንን የሚያለምለም በእውነት አፈ ሦከር በእውነት በትምህርቱ መዓዛ  የምስጢር በጎችን ደስ የሚያሰኛቸው አፈ ሽቶ አፈ ርኄ ነው። በእውነት በውግዘቱ ሥልጣን ከሐዲዎችን የሚቆርጥ አፈ ሰይፍ አፈ መጥብሃ ነው። በእውነት የማይናወጥ አምድ፣ የማይፈርስ መሠረት፣ በእውነት ከሞገዶች መነሣት የተነሣ የማይሰበር መርከብ በሃይማኖት ባሕር ውስጥ የሚዋኝ ዋናተኛ ነው። በእውነት የማይፈርስ ግንብ በጠላት ፊት የሚፀና አዳራሽ ነው።"
[መፅሐፈ ምስጢር - አባ ጊዮርጊስ
https://www.tgoop.com/eotcy
*ምክረ አጋንንት*

በቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ዘላስታ

📌ልጹም ትላለህ ፤ ተው አትጹም ይልሃል!አንተም ትተወዋለህ።
📌ልመጽውት ትላለህ ፤ ተው አትመጽውት ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ።
📌ንስሐ ልግባ ትላለህ ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ።
📌ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ
📌ላስቀድስ ትላለህ ፤ ትንሽ ተኛ ይልሃል። አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ።
📌ጸበል ልግባ ትላለህ ፤ ጤነኛ ነህ ይልሃል።
📌ገዳም ልባረክ ልሂድ ትላለህ ፤ ተው ስራን ስራ ይልሃል፡፡ አንተም ሳትሄድ ስትቆጭ ትኖራለህ።
📌አስራት በኩራት ልስጥ ትላለህ ፤ ተው አትስጥ የለህም ይልሃል። አንተም
ትተወዋለህ።
📌በአንድ ልወሰን ትላለህ ፤ ተው ቆንጆዎቹ ያልፉሃል ይልሃል። አንተም በዝሙት ትወድቃለህ።
በመጨረሻም የተወሰነልህ ግዜ ያልቃል ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ
ይወስዷታል።😢
📌ልጠጣ ስትል ፤ ጠጣ ይልሃል። ያሰክርሃል።
📌 ልዝፈን ስትል ፤ዝፈን ይልሃል። ያስጨፍርሃል
📌ልስረቅ ስትል ስረቅ ይልሃል። ያሰርቅሃል!
📌 ልጣለው ስትል ተጣላ ይልሃል። ያጣላሃል።
📌ልዋሽ ስትል ዋሽ ይልሃል። ያስዋሽሃል! ስጋዊ ተድላን ይሰጥሃል። ይመችሃል፡ስጋህ ወፍሮ፣ ቀልቶ ፣ ወዝቶ በጓደኞችህ ‹ ተመቸህ እኮ ! › ያስብልሃል። አንተም ደስ ይልሃል! በዛው ትገፋበታለህ።
ሃሳብህ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ቀርቶ ወደ ጅምናዝየም ቤት መሔድ
ይሆናል።
📌ሃሳብህ ሁሉ የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ይሆናል። ሃሳብህ ሁሉ ሳውና ባዝ ፣ስቲም ቤት ፣ማሳጅ ቤት ሂደህ መታሸት እና መዝናናት ይሆናል። እግርህ ሁሉ ወደ ሲኒማ ቤት ፣ ወደ ናይት ክለብ ቤት ፣ ወደ ሆቴል ቤት ፣ ወደ ግሮሰሪ ቤት ፣ ወደ ሱፐር ማርኬት ፣ ወደ ምናምን ቦታ ይሆናል።😭😭😭
በእነዚህ ሁሉ ስጋህ ሲመቸው
ቁሞ መጸለይ ይደክምሃል።
መስገድ ያቅትሃል።
መጾም ይከብድሃል።

ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይጨልምሃል።
ስጋህ በአጋንንት መረብ ይጠመዳል።
ደም ብዝት አስይዞ ሴት ያዝልሃል።
ደም ብዛት አሲይዞሽ ወንድ ያዝልሻል።
የነርቭ በሽታ አስይዞ መቆምና መሄድ ያስቅትሃል።
ስኳር በሽታ አሲይዞ ከጾም ይከለክልሃል።
ጨጓራ በሽታ አስይዞ ጾምን ይከለክልሃል።
❗️ምላስህ እግዚአብሔርን ማመስገንን ሳይሆን ዘወትር ስለ በሽታህ እንድትዘምር
ያደርጋታል።
❗️በጣም ብዙዎች ሃብት ሞልቷቸው በሽተኛ ያደርጋቸዋል። ገና ከጥዋቱ እነዚህ ሰዎች
የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው ቢሄዶ ኖሮ ፤ እንደ አብርሃም ፣እንደ ይስሐቅ እና እንደ ያዕቆብ በምድር ሃብታም እንደ ሆኑ ሁሉ በሰማይም እንደ ቅዱሳኑ የገነት ባለቤት በሆኑ ነበር።
📌 ሰይጣን ክፉ ነው! ሃብታሙን በሽተኛ ፣ ድሃውን ደግሞ ጤነኛ አድርጎ አምላክን ወቃሽ ያደርገዋል።
እንዲህ እንዲህ እያለ የመሰናበቻ ጊዜ ይደርሳል። በኃጢአት የዳበረው ስጋችን
አፈር ነውና በቅጽበት እሬሳ ተብሎ ወደ አፈር ይገባል። ነፍስ ግን እያዘነችና እየተፀፀተች ወደ ሲዖል ትወረወራለች።
📌የምናያቸው ቆንጆ ሴቶች ፣ የምናያቸው ቆንጆ ወንዶች ፣ የምናየው የልኳንዳ ስጋ ፣የምናየው መጠጥና ምግብ ሁሉ ያምረናል። ስጋችን ያሸንፈናል፥ ነፍሳችን ትሸነፋለች።
ለገነት ተፈጥረን ለሲዖል እንሆናለን።ሁላችንም ወደ እግዚያብሔር ተመልሰን ንሰሀ እንግባ።

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
+።።። ተሸክሜህ ነው ።።።።።+
...
በበርሃ ይሄድ የነበረ ሰው ወደ ኋላው ዞሮ ሲያይ ከእርሱ ሌላ አንድ ጥላ ይመለከታል:: የዚህም ጥላ ነገር አሳስቦት የማን እንደ ሆነ ያመለክተው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
እግዚአብሔርም :- "ከኋላህ የተመለከትከው ጥላ የእኔ ነው። አንተን እየጠበኩህ እንደሆነ ታውቅ ዘንድ ይህን ምልክት አሳየውህ" አለው። ያም ሰው ፈጣሪው ከእርሱ ጋር እንዳለ በመስማቱ እጅግ ደስ እያለው ጉዞውን ቀጠለ። ጥቂትም እንደተጔዘ ወጣ ገባ የሆነ በጣም አስቸጋሪ መንገድ አጋጠመው:: ሰውየውም ያን አስቸጋሪ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ለመውጣት ታገለ። በትግሉ መካከል ግን ወደ ኋላው ዞር ብሎ ቢመለከት ቀድሞ ያየውን ጥላ አጣው። ከዚያም ፈታኝ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ከወጣ በኋላ፣ በታላቅ ኃዘን ሆኖ እየተበሳጨ ፈጣሪውን እንዲህ ሲል ጠየቀው :- "ምንም ችግር ባልገጠመኝ በሰላሙ ጊዜ "ከአንተ ጋር ነኝ ስትል ጥላህን አሳየኸኝ፣ የአንተ እርዳታ በሚያስፈልገኝ ጊዜ ግን ራስህን ሰወርክብኝ:: ይከተለኝ የነበረውን ጥላም ዘወር ብዬ ባየው አጣኹት። ለምን ተውከኝ ?" ::

እግዚአብሔርም :- "በመከራህ ጊዜ ጥላዬን ያጣኸው ትቼህ እኮ አይደለም። ተሸክሜህ ነው!" ብሎ መለሰለት።

ክፉውን ዘመን በክንፈ ረድኤቱ ተሸክሞ የሚያሻግረን እግዚአብሔር ነው። እርሱ አይተወንም፤ አይንቀንም። እኛም ከእርሱ ውጭ ተስፋ የምናደርገው የለንም።

ጌታ ሆይ ስንት ዘመን ተሸክመኸኝ ምነው ተውከኝ ብዬህ ይሆን? ደካማው ልጅህን ይቅር በለኝ።

https://www.tgoop.com/eotcy
🙊🙊ስድብ በቀጠሮ🙊🙊
▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️

🗣ሴትየዋ በሰፈሩ ውስጥ የታወቀች ተሳዳቢና ተንኳሽ ናት። ወቅቱ የአቢይ ጾም መግቢያ አካባቢ ነው "አሁንስ በጾም በጸሎት ተወስኜ መኖር አለብኝ" ብላ ለራሷ ቃል ትገባና የንስሐ አባቷን ታማክራለች።

🕯 የንስሐ አባቷም በውሳኔዋ ተደስተው መልካም ማድረጓን ገልጸው እንዲህ ሲል ይመክሯታል። "ልጄ አደራሽን ይህ የሱባዔ ወቅት ሁላችን በጾምና በጸሎት ወደ ፈጣሪያችን የምንመለስበትና ስለ ኃጥያታችን የምናለቅስበት ነው እኛ ክርስትያኖች በይኽ ጊዜ እንኳንስ እርስ በእርስ ልንጣላ ይቅርና ጠላታችንን የምንወድበት፣ ስንበድል ይቅርታን የምንልበት የንስሐ ጊዜ ነው።ስለይኽ እንኳን አንቺ ቀድመሽ ልትናገሪ ቢናገሩሽም እንኳን በትእግስት ማለፍ ይኖርብሻል። አደራ ልጄ በርቺ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይሁን። ብለው ባርከው ያሰናብቷቷል።

💎ጾሙ ተጀመረና በሦስተኛው ቀን ሴትየዋ የከሰዓቱን ቅዳሴ አስቀድሳ ወደ ቤቷ ስትገባ "አንዴ ሌባ ካሏት ብትቆርብም አያምኗት" እንደተባለው የመንደሩ ሴት በነገር ጠመዳት። እስኪ ተመልከቷት አሁን ላያት ሰው እውነተኛ ክርስቲያን አትመስልም?? ወገኛ......እያሉ ዘለፏት እሷ ግን የንስሐ አባቷ የመከሯትን አስታውሳ እንዳትሳደብም ጾም በመሆኑ እንዲህ አለች "እሺ አሁን ስደቡኝ ግድ የለም ይኽ ጾም ይፈታና እያንዳንድሽን ልክ አስገባሻለሁ። .......

😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊
ሁሌም ቢሆን ተናግሮ አናጋሪውን ያዝልኝ ማለት ደግ ነው ቢሆንም ግን የብዙዎች ክርስትና እንደ ፋብሪካ ሠራተኛ በሺፍት(በፈረቃ) ነው። በጾም ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ይገሰግሳሉ ለፋሲካ ግን የመጠጥና ጭፈራ ቤቱን ያጨናንቁታል።

👉👉የሁዳዴ ክርስቲያን የፋሲካ ዘፋኝ መሆን አይገባንም ።
     "በጊዜውም አለጊዜውም ጽና "
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
ኪዳነ_ምሕረት

ስላንቺ ላወራ ስል እንባዬ ይቀድመኛል😥
ፍቅርሽን ውለታሽን ምገልጽበት ቃላት ያጥረኛል ከደጅሽ መጥቼ አለቀስኩ አቀረቀርኩም ግን አንቺ የልጅሽ ሀዘን አቶጂምና ቀና አረክሽ ችግሬን ላይመለስ ከእኔ አራቅሽው ታድያ በየትኛው አንደበትና ቃል አንቺን ላመሥግንሽ🙏
አንቺን ለምኜ የአጣሁት የለም

እናቴ

እኔማ አሁንም ደግሜ ደጋግሜ ኅጥያት መስራት አላቆምኩም፤ አንቺንም ማፍቀሬን አላቆምኩም
ይገርመኛል የአንቺ ትሕትና እደዚ ኅጥያተኛ ሆኜ ከኔ አትለይኚም እንዴት አይነት ፍቅር ❤️ ቢሆን ነው እንዴትስ ያለ መውደድ ነው፤ እንዴትስ ብዬ ላውራው ምንስ ቃል ተጠቅሜ ስላንቺ ፍቅር ልናገር እመቤቴ፤ ያንቺስ ደግነት በዛብኝ ከአይምሮ በላይ ሆነብኝ እናቴ አንቺን ሳመሰግን ነፍሴ ከሥጋዬ ልትለይ ትደርሳለች ገና ለማመስገን ስምሽን ስጠራው እንባዬ ይመጣል😢 የፍቅርሽ ኃይሉ በጣም ከባድ ነው። ሊመጠን፤ ሊለካ፤ ሊመዘን...ጭራሽ አይቻልም እና አንቺ ለኔ ያለሽ ፍቅር ልዩ ነው ኪዳነ_ምህረት እናቴ

👉 እናቴ በስንፍናዬ ላላመሰግንሽ እችላለሁ በስምሽ ላልጸልይ እችላለሁ መቼም ግን ስምሽን ሳልጠራ አልውልም

እ_ወ_ድ_ሻ_ለ_ሁ

꧁  ይ🀄🀄ሉ ꧂

https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
ኃጢአቷን የምትጽፈዉ ሴት

አንዲት ሴት ነበረች ኃጢአቷን የምትጽፍ
ልቧ በኃጢአት የሰከረ ለኃጢአትም ተገዥ የሆነች ይች ሴት የተለያየ ኃጢያት የምትሰራ ናት ትዘሙታለች፣ ትዋሻለች፣ ታማለች፣ ተሰርቃለች፣ ትገድላለች፣ በአል ትሽራለች፣ በትእቢት የተሞላች ሴት ናት ልቧ ኃጢአት ነበር። ነገር ግን የምትሰራዉን ኃጢአቷን ሁሉ እየጻፈች ታስቀምጥ ነበር።

ከእለታት አንድ ቀን የጻፈችዉን ኃጢአቷን ብታየዉ ስንክሳር አክሎ ተመለከተችዉ ስንክሳር ማለት በ365 ቀኖች የሚለዉ የቅዱሳን ታሪክ ሰብስቦ የያዘ ትልቅ መጽሐፍ ነዉ። የዚች ሴትም ኃጢአትም ይህን አክሎ ነበር እንዳየችዉ ደነገጠችና ኃጢአቷን ተሸክማ አባት ወደ አለበት ወደ አንጾኪያ ሄደች አባ ባስልዮስን አገኘችዉ አባቴ በዚህ ያለዉ ኃጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችዉ።

አባ ባስልዮስም ይፋቅልሽ አላት ገልጣ ብታሳየዉ ሁሉ ተፍቆ አንዲት ኃጢአት ብቻ ቀርታ አየቻት። በጣም ከባድ ኃጢአት ነበረች ሊፈሩዋት የምትከብድ ሊነግሯት የምታሳፍር ነበረች አባቴ ይችሳ አለችዉ አባ ባስልዮስም ይችን ኃጢአትሽንስ ማስተሰረይ የሚችል ልጄ ቅዱስ ኤፍሬም ነዉ ሂደሽ ለእርሱ ንገሪዉ አላት።
አባ ባስልዮስ ይሄን ያላት ኃጢአቷን መፋቅ አቅቶት አይደለም የራሱ ክብር ከሚገልጥ የቅዱስ ኤፍሬም ክብር እንዲገለጥ ፈልጎ ነዉ። ደግሞም ስትመላለስ ንስሐ እንዲሆናት ጭምር ነዉ።
እሷም አባ ባሰስልዮስ እንዳላት ቅዱስ ኤፍሬም ወዳለበት ወደ ሶሪያ ሄደች በባዶ እግሯ እንቅፋቱ እየመታት እሾሁ እየወጋት እግሯ ሲደማ ልብሷን ቀዳ እየጠመጠመች ተጉዛ ከቅዱስ ኤፍርም ደረሰች።

አባቴ በዚህ ያለዉ ኃጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችዉ ቅዱስ ኤፍሬም ግን ይሄ ለኔ አይቻለኝም ለአባቴ ለአባ ባስለዮስ እንጂ አላት ቅዱስ ኤፍሬም ግን ኃጢአቷን መደምሰስ አቅቶት አይደለም በፈሊጥ ቀኖና ሲሰጣት እንጂ ስትመላለስ ኃጢአቷ እንዲቀልላትም ነዉ። ሂደሽ ለአባ ባስለዮስ ንገሪዉ ይደመስስልሻል አላት እሷም አግኝቸዉ እኮ አይሆንልኝም ብሎ ወደ አንተ ልኮኛል ሳትል እሽ ብላ መንገድ ስትጀምር እንደ ቀድሞዉ በህይወት አታገኝዉም ሙቶ ካህናት ሊቀብሩት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይዘዉት ሲሄዱ ታገኝዋለሽ ሳትጠራሪ የተጻፈዉ ኃጢአትሽን ከአስክሬኑ ላይ ጣይዉ አላት እሷም እሽ ብላ ሄደች የቀኑ ሙቀት የሌሊቱ ብርድ እያሰቃያት ደረሰች ሙቶ ካህናት ፍትሀት እየፈቱት አየች።

የእግዚአብሔር አገልጋይ ባስልዮስ ሆይ የባሪያህን ኃጢአት ደምስስልኝ ብላ ከአስክሬኑ ላይ ጣለችዉ አስክሬኑም ድምጽ ወጥቶ ኃጢአትሽ ተደምስሶልሻል አላት ገልጣ ብታይ ተደምስሶላታል። አምላኳን አመሰገነች በደስታ ዘመረች በዚህ በኋላ ዓለምን ንቃ ገዳም ገብታ መኖር ጀመረች።

እንደዚች ሴት ኃጢአቱን የሚያስታዉስ ማነዉ?
ወደ ካህን ሂዶ ንስሐ የገባስ ስንቱ ነዉ?
ስለ ኃጢአቱ በረሃ የተከራተተ ማን ይሆን?

የዚችን ሴት መጨረሻ ያሳመረ የሁላችንም መጨረሻ ያሳምርልን ኃጢአቷን የደመሠሠ የሁላችንም ኃጢአት ይደምስስልን!

ለንስሐ የሚሆን ፍሬ አድርጉ

የዉዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2

🟢 @eotcy 🟢
🟡 @eotcy 🟡
🔴 @eotcy 🔴
እስኪ ልጠይቃችሁ

አንድ ሰው የተጣራ ወርቅ ልሰጣችሁ እመጣለሁና የሆነ ቦታ [ ለምሳሌ ተራራው ሥር ] ጠብቁኝ ቢላችሁ ምን ታደርጋላችሁ ? ወደዚያ ቦታ [ ወደ ታራራው ለመውጣት ] ለመሔድ አስፋላጊ ነው የምትሉትን [ ቅድመ ዝግጅት ] ሁሉ አታደርጉምን ? [ እንዳያመልጣችሁ በጊዜ ሔዳችሁ ]  ቀኑን ሙሉም ቢሆን ቁጭ ብላችሁ አትጠብቁትምን ? 

እግዚአብሔር እሰጣቹዃለሁ ያለው አንድ ሺህ ቅንጣት ወርቅ አይደለም ወይም ምድርን ሁሉ አይደለም።  ከእነዚህ ሁሉ የምትበልጠዋን መንግስተ ሠማያትን ነው እንጂ ...

ታድያ ከዚያ የሚበልጥ ስጦታ ምን አለ ? 🤷🏾‍♂
[ ምንም የለም ]  ይሕን ስጦታ ለማግኘት የማይደክሙ [ ወደ ተራራው የማይወጡ ] ሰዎች እንደምን ያሉ ምስኪኖች ናቸው
| ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ክርስቶስን ያከበሩ ፣ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፣ እውነትን የመሠከሩ ፣ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፣ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ ፣ ታላላቅ የምድር ነገስታትን፣ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፣ ከዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ።

ቅድስት ሆይ አንች እኮ:- ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ፣ ዓለምን ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የመለሰ፣ መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚንቀጠቀጡለት ፣ የሁሉ ፈጣሪ የሁሉ አምላክ እናት ነሽ። በፊትም አሁንም ወደፊትም ካንቺ በቀር ፈጣሪዋን ልጄ ብላ የምትጠራ ሴት አልነበረችም  የለችም አትኖርምም ክርስቶስም እናቴ ብሎ የሚጠራት ብቸኛዋ ሴት አንቺ ነሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ።

እናት ስትሆኝ ድንግል ድንግል ስትሆኝ እናት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ብሎ የሚጠራሽ ብቸኛዋ ሴት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ። እግዚአብሔር መርጦና ጠብቆ ያስቀረሽ ዘር በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ።
ለዓለም ሁሉ ድህነት ምልክት የሆንሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ።

እናቴ እንግዲህ እኔ ምን ልናገር ሺህ ቃላትን ብደረድር ያንቺን ክብር ልገልፀውስ እንደምን እችላለሁ አዎ አሁንም እላለሁ መልካም ያደረገ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ። ምሳ.31:29

የቃልኪዳኗ እመቤት ምልጃዋ አይለየን

https://www.tgoop.com/eotcy
2024/09/26 04:56:06
Back to Top
HTML Embed Code: