tgoop.com/ethio_physics/763
Last Update:
ጨረቃ ላይ ውሃን ለማግኘት እየሰሩ የሚገኙት ኢትዮጵያዊ የናሳ ተመራማሪ
ኢትዮጵያዊው የናሳ ተመራማሪ ኢንጂነር ብርሃኑ ቡልቻ (ዶ/ር) በጨረቃ ላይ ያለውን ውሃ የመለየት ችግር መፍትሄ ለመስጠት ከቡድን አጋሮቹ ጋር በመስራት ላይ የሚገኙ ሳይንቲስት ናቸው፡፡
ተመራማሪው ከዚህ በፊት ጨረቃ ላይ ውሃ ለማግኘት የሚያስችል በመጠን አነስተኛ የሆነ ቁስ የኳንተም ፊዚክስ ቀመርን በመጠቀም መስራታቸው ይታወሳል።
"ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ስመጣ የባህል ልዩነቱ እና የሚደግፈኝ ባለመኖሩ ተቸግሬ ነበር" የሚሉት ኢንጂነር ብርሃኑ፤ "ሁሌም የማስበው ጠንክሮ መሥራት እና በትምህርት ስኬታማ መሆንን ነበር" ይላሉ፡፡
አሁን ላይ በጨረቃ ላይ ያለውን ውሃ የመለየት ችግር መፍትሄ ለመስጠት እና ሰዎች ጨረቃ ላይ መኖርን እንዲያልሙ የሚያስችል አስደናቂ ምርምር በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ከሰሞኑ በሜሪላንድ የሚገኘው የናሳ የጠፈር በረራ ማዕከል ኢንጂነሩ፤ በዚሁ የምርምር ማዕቀፍ ውስጥ ያበለፀጉትን ፕሮቶታይፕ ለማጠናቀቅ የሚያስችላቸው 2.5 ሚሊዮን ዶላር ፈንድ እንዳቀረበላቸው የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል።
በፕሮቶታይፑ ላይ የሚሰራውን የቴክኒካል ሥራ ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመት ሊፈጅ እንደሚችል ኢንጂነር ብርሃኑ ይገልጻሉ።
ውሃ ከምድር ወደ ጨረቃ ሊጓጓዝ ቢችልም ወጪው የማይቀመስና ሥራው ውጤታማ ባለመሆኑ የኢንጂነር ብርሃኑ ቡድን ምርምር ትልቅ ውጤት የሚያስገኝ ነው፡፡
ቀደም ሲል በተደረጉ ጥናቶች ጨረቃ ላይ አነስተኛ መጠን ውሃ መኖሩ ቢረጋገጥም የውሃ ውህዶችን በትክክል መለየት ግን ሳይቻል ቆይቷል።
በጨረቃ ላይ ያሉትን የውሃ አካላት ከውህዳቸው ለመለየት እና ብሎም በትክክል ቦታውን ለማመላከት የሚያግዘው የኢንጂነር ብርሃኑ የምርምር ሥራ ለብዙ ጥያቄዎች መልስ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡
Join👉 T.me/ethio_physics
BY Ethio Physics 🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/ethio_physics/763