tgoop.com/ethiofeker/436
Create:
Last Update:
Last Update:
የዕለቱ መልእክት 📝
°°°°°°°ህሊናህን ጠብቅ°°°°°°°°
ውሸት እየጎላ - እየተንፀባረቀ በሰዎች ማንነት፣
ጊዜያቶች ነጎዱ - ሳይጨበጥ እውነት፣
ሁሉም ሆኖ ልዝብተኛ - ባየው ተማራኪ፣
አምላኩን ዘንግቶ ለሰይጣን ትእዛዝ ሆነ ተላላኪ፣
ነገ ለኔ ሳይል - የሌላውን ዛሬ አበላሽቶ፣
ደልቶት ኖሮ ያልፋል- ባለው ተገምቶ፣
ሰርቶ አዳሪው - ፈርቶ አየተጨቆነ፣
ከሰራው ተነፍጎ - ሲነጥቁት እያየ፣
ሁሉም ያልፋል ብሎ - ውስጡን አሳመነ፣
አፈር ነህና ወዳፈር ትመለሳለህ የሚለውን ረስቶ፣
ይበልጠኛል ብሎ - ያሰበውን ከሌላው አባልቶ፣
ቢያልፍም ያወርሳል - ቤት አጥር ገንብቶ፣
መንገድህን አትልቀቅ - ጠብቅ ሚሰጥህን፣
ጉዳትህን እወቅ - አንግብ ሚጠቅምህን፣
የፈጣሪ ሰማይ - የፍትህ ዝናብን ካልጣለ፣
ማንም ሠው አይመጣም - ካንተ የተሻለ
ዙፋን ቢሻ እንጂ ....
ከተንኮል የፀዳ - ፈልግ'ስቲ የት አለ።
SHARE ❣ SHARE
@ethiofeker
BY Ethio Feker ኢትዮ ፍቅር
Share with your friend now:
tgoop.com/ethiofeker/436