tgoop.com/ethiokeld1/418
Last Update:
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች (Face Masks) !
(በዶክተር መክብብ ካሳ - ከCOVID-19 RRT)
የኮቪድ-19 ቫይረስ በምናወራበት፣ በምንስልበትና በምናስነጥስበት ጊዜ ከአፍና አፍንጫችን በሚወጡ ጥቃቅን ጠብታዎች (droplets)አማካኝነት እንደሚተላለፍ ይታወቃል፡፡
በርካታ ጥናቶች አንደሚያሳዩት ጭንብሎችን መጠቀም በቫይረሱ እንዳንያዝ አንዲሁም እኛም ወደ ሌሎች እንዳናሰተላልፍ በተለይም በማህበረሰብ ውስጥ ሊፈጠር የሚችልን ስርጭት (community spread)ለመቀነስ ያግዛል::
በተለይ እንደኛ አብዛኛው ህዝብ ቤት መቀመጥ ባልቻለበት ሁኔታ ጭንብሎችን መጠቀም እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ምልክት ባይኖራቸውም ቫይረሱን ማስተላለፍ ይችላሉ ስለዚህ መጠንቀቅ ያለብን የሚያስሉ ወይም የሚያስነጥሱትን ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም ግለሰብ ነው፡፡
ሌሎች በተደጋጋሚ የተነገሩ የመከላከያ ዘዴዎችን ጭንብሎችን ከመጠቀም ጋር አብረው መከወን ይኖርባቸዋል እንጂ የተወሰኑትን ብቻ ተግባራዊ ማድረግ በቫይረሱ እንዳንያዝ አያደርገንም፡፡
ጭንብሎችን ከማድረጋችን በፊት እጃችንን በአግባቡ ማፅዳት፣ አፍና አፍንጫችንን በደንብ መሸፈኑን ማረጋገጥ፤ ከማውለቃችን በፊት በድጋሚ እጃችንን ማፅዳትና የጭንብሉን መያዣ ክሮች ብቻ በመጠቀም ማውለቅና አካባቢን በማይበክል መንገድ ማስወገድ፡፡
የህክምና ባለሙያዎች የሚጠቀሙባቸውን ጭንብሎች ባለመጠቀም እጥረት እንዳይፈጠር የበኩላችንን እንወጣ፡፡
በምንጠቀምበት ጊዜ ምቾት ላይሰማን ይችላል ነገር ግን ለጋራ ደህንነታችን ሲባል ለተወሰነ ጊዜ እንቸገር::
የአንድ ሰው ጥንቃቄ ጉድለት መዘዙ ለብዙኀን ይተርፋል፤ እንተሳሰብ!
@ethiopiagovernmentcovid19
BY Ethio Qeld
Share with your friend now:
tgoop.com/ethiokeld1/418