Happening Now: Attending CSO Research Forum @ African Leadership Excellence Academy
Forwarded from Ethiopiawinnet members, volunteers & supporters group
ሰላም የኢትዮጵያዊነት ድርጅት አባላት እና ደጋፊዎች
በሃገራችን ሰላም ሊያመጣ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት የሃገራዊ ምክክር ላይ አጀንዳ መሰባሰብ በይፋ ተጀምሯል። በመኾኑም በአጀንዳነት መቅረብ አለባቸው የሚባሉ ነጥቦች ዙሪያ የህዝብ ጥቆማ እና ድምጽ ማሰባሰብ እንዲቻል በእርስዎ እይታ መሰረታዊ የሚባሉ አጀንዳዎች ምን መሆን እንዳለባቸው የጥቆማ መልዕክት እንዲልኩልን እንጠይቀለን !

በዌቢናሩ ላይ ለመሳተፍ አሁኑኑ በቀጣዩ ሊንክ ይመዝገቡ: https://us06web.zoom.us/webinar/register/WN_WAmXXs0NQt2pqKzg8APQZw
በማኅበራዊ ሚድያዎቻችንን ያግኙን
ፌስ ቡክ: https://www.facebook.com/ETHIOPIAWINNET.AA
ቴሌግራም፡ https://www.tgoop.com/ethiopiawinnetaa
ሊንክደን፡ https://www.linkedin.com/company/79367322/
ዩትዩብ : https://youtube.com/@voiceofethiopiawinnet3661

👍3
በቀጣዩ ማስፈንጠሪያ በዩትዩብ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን። https://www.youtube.com/live/VGqo55tGsGs?feature=share
YouTube
Ethiopic Script in the Modern Era: Prospect, Challenges, and Opportunities
Ethiopic Script in the Modern Era: Prospect, Challenges, and Opportunities: የግዕዝ ስክሪፕት በዲጂታል ዘመን፡ ተግዳሮቶች፣ ተስፋዎች እና እድሎች
Contents
-- TIMESTAMPS --
00:00 Dr. Hailemarkos Worke, Moderator
00:01:13 Dr. Erku Yimer, Opening Remarks
00:12:38 Dr. Bahiru Kassahun…

👍2
በግእዝ/በአማርኛ/ ፊደላት እና ቋንቋ ለዘመናዊነት ያለው ምቹነት ዙሪያ ላይ በማተኮር ድርጅታችን በተከታታይ ያዘጋጀው ዌቢናሮች አስመልክቶ የጀርመኑ ዶቼዌሌ(DW) ያቀረበውን ዘገባ በቀጣዩ ማስፈንጠሪያ እንዲያነቡ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡
https://www.dw.com/am/የአማርኛ-ሊቃውንት-ጥናታዊ-ሥራዎች-ላይ-ያተኮረ-ጉባዔ/a-65218352
https://www.dw.com/am/ዐማርኛ-ቋንቋን-በአፍሪቃ-ደረጃ-ለመጠቀም-ባለው-አቅምና-ብቃት-ላይ-ምሁራዊ-ውይይት-ተካሄደ/a-65796700?fbclid=IwAR0BQCB_s_snhd4d6Il6UdRT-AZRe6H8B9TWcCBHL90KiZGGZEAhhiSFY8s

Forwarded from GhionMagazine ግዮን መጽሔት (ቀ ቁ)
በቋንቋ ዙሪያ የፀደቀው የትምህርት ፖሊሲ “ህጋዊነት” በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጥያቄ አስነሳ
ባለፈው ሳምንት የትምህርት ሚንስትሩ የተቋማቸውን የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሲያቀርቡ በም/ቤቱ አባላት የትምህርት ፖሊሲው አጸዳደቅ ጥያቄ ተነስቶበታል።
የካቲት 20፤ 2015 ዓ.ም. በሚንስትሮች ም/ቤት የጸደቀው የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ወደ ተግባር መግባቱን ትምህርት ሚንስቴር ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች በደብዳቤ አሳውቋል።
ሞላ ፈለቀ (ዶ/ር) የተባሉ የም/ቤቱ አባል በረቂቅ ፖሊሲው ላይ በነበረው ሀገራዊ ውይይት እንደተሳተፉ ገልጸው፤ የፖሊሲውን ይዘት ብቻ ሳይሆን የህግ ጥያቄም አንስተውበታል።
የም/ቤቱ አባል በዋናነት ቋንቋ የተመለከተ ፖሊሲ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ስልጣንና ኃላፊነት መሆኑን አንስተዋል።
ፖሊሲው ከአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀጥሎ የሁለተኛ ቋንቋ መረጣ ሀገራዊ መግባባትን የሚፈጥር አለመሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህም የጋራ መግባቢያ ቋንቋ ባለመካተቱ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ማህበረሰብ ለመገንባት ያለውን ፈተና ገልጸዋል።
“ለምሳሌ በሲዳማ አፉን የፈታ ህጻን ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ ከአምስቱ [ቋንቋዎች] አንዱን ቢመርጥ ወይም ኦሮምኛን ቢመርጥ፤ በወላይተኛ አፉን የፈታ ተማሪ አማርኛን ቢመርጥ፤ እነዚህ ሁለት ኢትዮጵያዊያን በምን የጋራ ቋንቋ ነው ሀገራዊ የጋራ ጉዳዮችን በጋራ ሊመክሩ፣ ሊዘክሩና ሊግባቡ የሚችለው?” ሲሉ ጠይቀዋል።
የም/ቤቱ አባል በዚህ ሳያበቁም ፖሊሲው በሚንስትሮች ም/ቤት ብቻ ጸድቆ ገቢራዊ መደረጉ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትን ስልጣንና ኃላፊነት የሚጥስ ነውም ብለዋል።
ለዚህም የሚንስትሮች ም/ቤትን ስልጣንና ተግባር የሚደነግገውን የህገ-መንግስቱን አንቀጽ 77 በመጥቀስ ም/ቤቱ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን “ይነድፋል፤ ያስፈጽማል” የሚለውን አንስተዋል።
“ራሱ [የሚንስትሮች ም/ቤት] ያመነጨውን ፖሊሲ ራሱ ህግ አድርጎ ራሱ እንዴት ፈጻሚ ይሆናል? እንደዚህ አይነት ሀገራዊ ፖሊሲዎች በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርበው አለመጽደቃቸው አሳሳቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ” ብለዋል።
የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፖሊሲውን ህጋዊነት በሚመለከት “የፖለቲካ ችግር” ውስጥ መግባት እንደማይፈልጉ በመጥቀስ ከእርሳቸው በተሻለ የም/ቤቱ አፈ-ጉባኤ ያብራሩታል በሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
አል ዐይን አማርኛም የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው ሲጸድቅ የእንደራሴዎች ም/ቤት ስልጣን ተገፍቷል ወይ? ፖሊሲን የማጽደቅ ስልጣንና ኃላፊነት ያለው የትኛው ም/ቤት ነው? ሲል የህግ ባለሞያዎችን አነጋግሯል።
የህግ ባለሞያዎች ፖሊሲ የፖለቲካ ሰነድ መሆኑን ጠቅሰው፤ የህጎች ምንጭ የሆነ፣ አንድ ፓርቲ ሀሳቡን ለመሸጥ የሚያዘጋጀውና አመለካከቱና አስተሳሰቡ የሚገልጽበት እንዲሁም በፓርቲ ጽ/ቤት የሚወጣ መሆኑን ተናግረዋል። ሆኖም ፖሊሲዎች ህገ-መንግስቱን ታሳቢ አድርገው ሊወጡ እንደሚገባቸው ገልጸዋል።
የህግ ባለሞያ ሆኑት ሞላልኝ መለሰ የትምህርት ፖሊሲው በሚንስትሮች ም/ቤት መጽደቅ እንደሚችል ተናግረዋል። በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ደግሞ ከፖሊሰው የተቀዱ ህጎች ቀርበው እንደሚጸቁም ተናግረዋል። ፓርላማው ያጸደቃቸውን አዋጆች ማስፈጸሚያ የሚሆኑ ደንብና መመሪያዎችን ደግሞ በሚንስትሮች ም/ቤት እንደሚጸድቅ ገልጸዋል።
“ፖሊሲዎች ፖለቲካዊ አንደምታ አላቸው። የህዝብ ጥቅም ታይቶ፣ ህዝብም ውይይት አድርጎበት ሊወጡ ይችላል። ይሄ የሪኦት ዓለም ጉዳይ ነው። ማህበራዊ ስሪትንም የሚያይ ነው” ሲሉ የህግ አማካሪና ጠበቃ ቢንያም ከበረ ተናግረዋል።
የፖሊሲ ማሻሻያ ከሆኑ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መጽደቅ አለበት የሚሉት የህግ ባለሞያው፤ ለውጦች የፓርላማን ብቻ ሳይሆን የህዝብን ይሁንታ ማግኘት አለባቸውም ይላሉ።
ፖሊሲዎች ሲወጡና ሲጸድቁ “ምንድ ነው መሰረታዊ ለውጡ? ወይስ ቀድሞ ነበረውን ማስፈጸም ነው? የሚሉ ጉዳዮች አሟጋች ናቸው። ለምሳሌ ከ10ኛ ክፍል የሆነውን [ብሄራዊ ፈተና] 12ተኛ ክፍል ካለ መሰረታዊ ለውጥ ነው። ይሄ በአስፈጻሚው አካል አይሆንም” በማለት አብራርተዋል።
የፌደራል የስራ ቋንቋ በህገ-መንግስቱ የተደነገገ ሲሆን፤ በትምህርት ፖሊሲው የፌደራሉን የስራ ቋንቋ ማስተማር ግዴታ መሆን አለበት ሲሉ ሞላልኝ መለሰ ገልጸዋል።
የፖሊሲው አስተሳሰቦች ህገ-መንግስቱን የሚቃረኑ አሊያም የሚጋጩ ከሆነ ተፈጻሚ እንደማይሆኑ ህገ-መንግስቱን በመጥቀስ ገልጸዋል።
“ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ ህጎች ተፈጻሚነት የላቸውም” የሚሉት የህግ ባለሞያው፤ ጉዳዩ ለህገ-መንግስት አጣሪ ጉባኤ መቅረብ እንዳለበት አስምረዋል።
“ትምህርትን ስናነሳ የምንነጋገረው ስለ አምስት ዓመታት ስርዓት ብቻ አይደለም። አንድ ፓርቲ ስልጣን ላይ ሚቆየው ለአምስት ዓመት ነው። የትምህርት ፖሊሲ በየአምስት ዓመቱ የሚቀየር ከሆነ ሀገር እየተገነባ አይደለም።
ስለዚህ እነዚህ ሰነዶች ከመጽደቃቸውና ስራ ላይ ከመዋላቸው በፊት ምን ስርዓት ልንከተል ይገባል የሚለውን ነገር በደንብ መፈተሽና መነጋገር ይጠይቃል" በማለት ሀሳብ ሰንዝረዋል።
AlAin

ጀግናው ታንክ ማራኪው ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ !!!
የዚያድባሬን ወረራ ለመመከት የሚያዚያ 4/1969 ዓ.ም የፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለማርያምን የእናት ሀገር አድን ጥሪን አዋጅ በመቀበል ከቀድሞ ወለጋ ክፍለሀገር አሶሳ አውራጃ ቤጊ ወረዳ ወደ ኦጋዴን በመዝመት በአቡሸሪፍ ግንባር የወራሪው የሶማሊያ ሀይል T-55 ታንኮች በእጅ ቦምብ ደጋግሞ ያጋየው የሀገር ባለውለታው የጀግና ሜዳይ ተሸላሚው ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ በመጨረሻ ተሸነፈ።
ድርጅታችንም በዚህ ጀግና የሃገር ባለውለታ ህልፈት የተሰማውን ሃዘን ይገልጻል፡፡🙏
ክብር እና ዘላለማዊ ዕረፍት ለጀግናው አሊ በርኬ !!!

❤6
አትሌት ለሜቻ ግርማ የ3 ሺሕ ሜትር መሰናክል የዓለም ሪከርድ ሰበረ
አትሌት ለሜቻ ግርማ ትላንት ምሽት በፓሪስ በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ ውድድር የ3 ሺሕ ሜትር መሰናክል ሩጫ ውድድር የዓለም ክብረወሰን በመስበር አሸነፈ።
7:52.11 በሆነ ደቂቃ የገባው ለሜቻ ግርማ በሳይፍ ሳኢድ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ከአስራ ስምንት ዓመታት በኋላ የግሉ ማድረጉን ከዓለም አትሌቲክስ ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
ሌላኛው በርቀቱ የተካፈለው ኢትዮጵያዊው አትሌት አብርሃም ስሜ 8:10.73 በሆነ ደቂቃ አራተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
በሌላ በኩል ትናንት ምሽት በተካሄደው የፓሪስ ዳይመንድ ሊግ 5 ሺሕ ሜትር ሩጫ ውድድር አትሌት ለተሰንበት ግደይ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡
ሌላኛዋ አትሌት እጅጋየሁ ታየ ደግሞ በርቀቱ 3ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን የወርልድ አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡

👍4❤1
📣 የግንቦት ወር 2015 ዓ.ም የድርጅታችንን ዜና መጽሔት ካልደረስዎት ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ (link) በመጠቀም እንዲያነቡ በአክብሮት እንጋብዛለን። ከዚህ ቀደም የነበሩ ዜና መጽሔቶችን( Past Issues) በሚለው ዘርፍ በመንካት ማግኘት ይችላሉ።
https://mailchi.mp/9fff6a4d4637/1bnk5keu58-9368159?e=4198e66800#LinkNine
በማኅበራዊ ሚድያዎቻችንን ያግኙን
ዌብሳይት፡- https://www.ethiopiawin.net