Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
852 - Telegram Web
Telegram Web
🔈Notice/ ማስታወቅያ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገራዊ ምክክሩ ዙርያ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር የበይነ መረብ (Zoom) ውይይት ለማድረግ ጥሪ አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት በሐምሌ 1 እና 2፣ 2015 በሚካሄዱት ውይይቶች ላይ ለመሳተፍ የሚከተለውን ሊንክ በመጠቀም ከሰኔ 20 እስከ 29፣ 2015 ድረስ መመዝገብ እንደሚቻል ኮሚሽኑ በአክብሮት ያሳውቃል፡-

https://forms.gle/D1bAYTVqjv79tm2r9

#የኢትዮጵያሀገራዊምክክር #ሀገራዊምክክር #ethiopiannationaldialogue #NationalDialogue #Ethiopia
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
በአሜሪካዋ ከተማ ላስቬጋስ ውስጥ ‘ሊትል ኢትዮጵያ’ የሚባል ወረዳ ተሰየመ።

በአሜሪካ ኔቫዳ ግዛት፣ ላስቬጋስ ውስጥ በምትገኘው ክላርክ ካውንቲ ‘ሊትል ኢትዮጵያ’ [ትንሿ ኢትዮጵያ ] የሚባል አካባቢ መሰየሙ ተገልጿል።

የዘመቻው አስተባባሪ አቶ ግርማ ዛይድ ለቢቢሲ እንደገለፁት ከ120 በላይ አገራት ዜጎች በሚኖሩባት ኔቫዳ ግዛት በአገረ ገዢ ደረጃ አዋጅ ወጥቶለት ሲጸድቅ ይህ የመጀመሪያው ነው።

ለኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አንድ ሰፈር ማሰየም ከባድ ነው የሚሉት አቶ ግርማ፣ ፋይዳው ግን ዘርፈ ብዙ መሆኑን ይጠቁማሉ። የዓለም ቱሪስቶች ማዳረሻ በሆነችው ላስቬጋስ የትንሿ ኢትዮጵያ መመሥረት ኢትዮጵያን ለሰፊው ዓለም ማስተዋወቅ ዋነኛው ዓላማ ተደርጓል።

አቶ ግርማ በቀጣይም ሌሎች ዕቅዶች እንዳሏቸው የገለጹ ሲሆን አንደኛው በላሊበላ ውቅር ቤተ ክርስቲያን አምሳያ 'እንኳን ወደ ትንሿ ኢትዮጵያ በደህና መጣችሁ' [ ዌልካም ቱ ሊትል ኢትዮጵያ] የሚል ሐውልት ማስቀረጽና ወደ ቱሪስት አካባቢው በሚወስደው አውራ መንገድ ላይ 'ሊትል ኢትዮጵያ' ብሎ ማሰየም ነው ብለዋል።

በኔቫዳ ግዛት ውስጥ በኢትዮጵያ ስም የተሰየመ አካባቢ የሚገኝበት ክላርክ ካውንቲ ውስጥ ቢያንስ 17 የኢትዮጵያ ምግብ ቤቶችን ጨምሮ ከ50 በላይ የኢትዮጵያውያን የንግድ ተቋማት እንደሚገኙ የላስ ቬጋስ ሪቪው ጆርናል ዘገባ ያመለክታል።

ይህንን ስያሜ ለማግኘት እንቅስቃሴ የተጀመረው ከ40 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ባሉበት ከተማ እንዴት አንድ የባህል ማሳያ አካባቢ አይሰየምም በሚል መነሻ ነበር። ሐሳቡን የጀመሩትም በላስቬጋስ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ሴንተር ሰብሳቢ አሌክሳንደር አሰፋ ነበሩ። ሒደቱም አራት ዓመታትን ወስዷል። (BBC)

www.tgoop.com/tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Tere
ለሁላችንም የእኩል እናት እና ቤት የሆነች ኢትዮጵያ ነው የምታስፈልገን!!

1. እንደ መንደርደሪያ


ከሰሞኑን ለአንድ የቢሮ የመስክ ሥራ የሶማሊ ክልል መስተዳድር ዋና ከተማ በሆነችው ጅግጅጋ ነው ያለሁት። ታዲያ አንድ አመሻሽ ላይ ከመሃል ከተማው ወደ አረፍኩበት ሆቴል እንዲወስደኝ ከተሳፈርኩበት የባጃጅ አሸከርካሪ ጋር የትውውቅ ሰላምታ አደረገን ነበር። በነገራችን ላይ ጅግጅጋ ከተማ ውስጥ ለመንቀሳቀስ አብዛኛው ሕዝብ የሚጠቀመው ባጃጅና "Force" የሚባል ከባጃጅ ከፍ የሚል የታክሲ አገልግሎት በሚሰጥ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ነው። እናም ከዚህ የባጃጅ አሽከርካሪ ወጣት ጋር ከትውውቃችንና የሰላምታ ጥቂት የቃላት ልውውጣችን የባጃጁ ባለቤትና ሹፌር የሆነ ወጣት ከሰሜን ኢትዮጵያ የመጣ፤ ትግራዋይ እንደሆነ ተረዳሁኝ።

ባለፉት የሁለት ዓመት የእርስ በርስ አሰቃቂ ጦርነት በብዙ ዋጋ የከፈለችውን ትግራይን በአእምሮዬ እያመላለስኩ፤ የባጃጁን ሹፌር ወደ ጅግጅጋ መቼና እንዴት እንደመጣ ጠየኩት። ወጣቱ የትግሪኛ ቅላጼ በተጫነው አማርኛ ወደ ጅግጅጋ እንዴት እንደመጣና ስለ ቆይታው እንዲህ አወጋኝ፤

"... ከትግራይ መጥቼ አዲስ አበባ፣ ቃሊቲ ሰፈር ለ5 ዓመት ባጃጅ ላይ ነበር የሠራሁት። ባለፈው ጊዜ ከተማ ውስጥ ባጃጅ አትሠሩም ብለው ሲከለክሉን ባጃጄን ሽጬ እዚህ ሶማሊ ክልል፣ ጅግጅጋ መጣሁ። እዚህ ከትግራይ የመጡ ሁለት ጓደኞች አሉኝ። እናም እዚህ ና ከእኛ ጋር ትሠራለህ ሲሉኝ መጣሁ። ወደዚህ ከመጣሁ ገና ሁለት ወሬ ነው። ግን ዋአይ ለሥራም ለኑሮም ከአዲስ አበባ ይልቅ ጅግጅጋ ትሻላለች። የኑሮ ውድነቱ ቢከብድም ወንድሜ ጅግጅጋ ለኑሮ ጥሩ ናት ተስማማታኛለች አለኝ...።" በፈገግታ በታጀበ ድምፀት።

መቼ ይሆን ለሁላችንም እኩል እናትና ቤት የሆነች የኢትዮጵያን በተግባር እውን የምናደርገው?!

ከዚህ ትግራዋይ የባጃጅ ሹፌር ጋር ያደረግነውን የሐሳብ ልውውጥ እያወጣሁና እያወረድኩ... መቼ ይሆን ያለ ምንም ሰቀቀንና ሥጋት ሁሉም ኢትዮጵያ በፈለገው የሀገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሶ መኖርና መሥራት የሚችልበት ሙሉ ነጻነት የሚኖረው?! አልኩ... ይሄ የባጃጅ አሽከርካሪ ከተወለደባት ምድር ትግራይ ይልቅ አዲስ አበባ ትሻለኛለች ብሎ ሸገር ላይ ከተመ። አዲስ እንደፈለገው ሳትሆንለት ስትቀር ደግሞ "ምን ዕዳ አለብኝ?!" ኢትዮጵያዊ አይደለሁ እንዴ ብሎ ከአዲስ አበባ ብዙ ኪሎ ሜትር ተጉዞ ሶማሊ ክልል ጅግጅጋ ላይ ኑሮውን መሠረተ።

በቀደመው ዘመን የዚህን ወገናችንን ዓይነት የኑሮ ዕጣ ፈንታ የሚጋሩ ብዙ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፤ ዛሬ ግን ይህን የአብሮነት ታሪካችንን በነበር እናስታውሰው ዘንድ ተገደናል። በእኛ ዘመን ያለንበትን አስፈሪ እውነታ ስንታዘብ (በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን- አባቶች፣ እናቶች፣ አረጋውያን፣ ሴቶችና ሕፃናት የሰቆቃ ድምፅ በጆሮዬ እያቃጨለና የመከራ ሕይወታቸው ፊቴ ላይ ድቅን ብሎ እየታየኝ- የትናትናው የአብሮነት ታሪካችን፤ በኢትዮጵያዊነት ፍቅርና አንድነት መንፈስ የተሳሰርንበት ውሉ እንዲህ መላላቱ፣ መሳሳቱ አስተከዘኝ።

ለነገሩማ ተግባራዊነቱ ጥያቄ ውስጥ የወደቀም ቢሆንም ቅሉ አሁን በሥራ ላይ ያለው የኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት ከላይ ባነሳሁት ገጠመኜ በተንደረደርኩበት ሐሳብ ጋር በተያያዘ እንዲህ የሚል ድንጋጌ/አንቀጽ አለው።

ማንኛውም ሰው በማንኛውም ስፍራ በሰብአዊነቱ እውቅና የማግኘት መብት አለው፤ (አንቀጽ 24 ቁ. 3) በሌላ ስፍራም፤ "ማንኛውም ኢትዮጵያ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል የመንቀሳቀስ፣ የመኖርና ሀብት የማፍራት መብት እንዳለው፤" ይደነግጋል።

ይሁን እንጂ የዛሬዋ ኢትዮጵያችን እውነታ ግን ከዚህ በጣሙን የተለየ ከሆነ ሰነባብቷል። እናም ያለፉትን ዓመታት የእናት ኢትዮጵያን ስቃይዋን፣ የሕዝቦቿን ሰቀቀንና መከራ ቆም ብለን ማሰላሰል ያስፈልገናል።

"... ከክልላችን ውጡልን፣ ይህ አለን የምትሉት ሀብትና ንብረት ሁሉ በእኛ መሬት ላይ ያፈራችሁት ሀብት ነውና ሰባራ ሳንቲም ከክልላችን ይዛችሁ መውጣት አትችሉም፤ ይህና ያ ሕዝብማ እንዲህ አድርጎናል... እናንተና እኛ እኮ..." በሚል ተአማኒነቱ ባልተረጋገጠ የቂም በቀል ታሪክና የብሔር/የዘውግ/የጎሳ ፖለቲካ ነጋዴዎች/Ethnic Enterpreuner የጥላቻ ትርክት በግፍ የተገደሉ፣ በጅምላ የተጨፈጨፉ፣ በአንድ ጀምበር ሀብት ንብረታቸው ለእሳት የተዳረገባቸው፣ ሀገሬ/ወገኔ ብለው ከኖሩበት ቀዬ በግፍ የተፈናቀሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የግፉአን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን የሰቆቃ ድምፅ፣ መከራና ሰቆቃቸውን ማሰላሰል ያዝኩኝ።

በዚህ ስሜት ውስጥ ሆኜ ይህን ጽሐፍ እየከተብኩበት ባለሁበት ካፌ በረንዳ ላይ ከአገረ ሶሪያ በእርስ በርስ ጦርነት ጦስ ተፈናቅለው- ብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠው ወደ ሀገራችን የመጡ ሁለት ሶሪያውያን እናቶች መንገድ አቋርጠው በካፌው በረንዳ ላይ ወደተቀመጥነው ተስተናጋጆች ሲመጡ አስተዋልኩኝ።

አንደኛዋ እናት በግምት የ6 ዓመት ዕድሜ ያላትን ሕፃን ልጇን ጭምር የሚሸጡ ዕቃዎችን አስይዛ በካፌው የሚስተናገዱ ሰዎች እንዲገዟቸው አንጀትን በሚበላ ሁኔታ ተስተናጋጆችን በዓይናቸው ይለማመጣሉ። ሌላኛዋ ሶርያዊት እናት ደግሞ ጸሐይ ያዛላቸውን ሁለት ሕጻናትን በእቅፏና በእጇ ይዛ ወዲህና ወዲህ እያለች ለልመና እጇን እየዘረጋች ነው። የጽሐፌ መነሻ ሐሳብና ይህ ግጥጥሞሽ ገረመኝ።

እናም እኛስ ብንሆን ፖለቲካዊ ልዩነቶቻችንና ቁርቁሳችንን ገደብ ካላደርግንበት አሁን በተያያዝነው የእልኽና የመጠፋፋት መንገድ የነገ ዕጣ ፈንታችን እንደ እነዚህ ሶሪውያን ስደተኞች ላለመሆናችን ምን ዋስትና ይኖረናል?! በየቀኑ በሀገራችን ላይ እየሆነ ያለውን ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ስናይ- ኢትዮጵያስ የሶሪያንና የመንን የመፍረስ፣ የውድመት ታሪክ ላለመጋራቷ ምን ዋስትና ይኖራታል?! ስል ራሴን ጠየቅኹ።

እንደሚታወቀው በአንድ ወቅት በእርስ በርስ ጦርነት ከፈራረሱት የመንና ሶሪያ በልጠን በዓለም አቀፍ ደረጃ በሀገር ውስጥ መፈናቀል/Internal Displacement የአንደኝነት ረድፍ የያዝንበት ታሪካችን የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው። ለአብነትም የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት/UN - IOM National Displacement Report 12- እ.አ.አ. በመጋቢት ወር 2022 ባወጣው ሪፖርት፤ "በኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር 2.75 ሚሊዮን መድረሱን አመላክቶ፤" ነበር። አንባቢዎቼ ይህ ሪፖርት የትግራይ ክልልን እንዳላካተተ ልብ ይሏል።

እንግዲህ ይህ ሪፖርት የብዙዎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን መከራና ሰቆቃ የሚያሳይ መሬት ላይ በተጨባጭ ያለ ሐቅ ነው። ዛሬም በመፈናቀል ሥጋት ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን ቁጥር ጥቂት አይደለም። ግና መቼ ይሆን ከላይ በገጠመኜ ለማንሳት እንደ ሞከርኩት ከሰሜን ኢትዮጵያ ተነስቶ ኑሮውን ጅግጅጋ እንዳደረገው የባጃጅ ሹፌር ወገናችን ሁሉ፤ በዚህ ዘመንስ መሼ ይሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በፈለገበት ቦታና አካባቢ የመኖር፤ የመንቀሳቀስና ሀብት የማፍራት መብቱ እንዲከበር ከቃል ያለፈ ተግባር ማየት የምንችለው?!

መቼ ነው ለሁሉም በእኩልነት እናትና ቤት የሆነች ኢትዮጵያን ዕውን የምናደርገው?! ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በማንነታቸውና በቋንቋቸው የተነሳ የሚደርስባቸው ግፍ፣ ግድያና መፈናቀልስ ማቆሚያው መቼ ይሆን?! ይህን በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን ከመርግ የከበደ ግፍና መከራ በመቃወም- መቼ ይሆን በቃ! እረ በቃ! የሚለው የጋራ ድምፃችን ጎልቶ የሚሰማው?!

2. እንደ መውጫና መደምደሚያ
Forwarded from Tere
ጠረፋማ የሚባሉ እንደ ሶማሌና ጋምቤላ ያሉ ክልሎች ከአጎራባች ሀገራት የሚጋሯቸው በርካታ ነገሮች አሉ። ከታሪክ እስከ ባህል፤ ከቋንቋ እስከ ጎሳ ዝምድና፤ ከንግድ ትስስር እስከ የጋራ ማንነትና ሥነ-ልቦና ድረስ በብዙ ነገር የተጋመደና የተሰባጠረ ሕዝብ ነው ያለባቸው። በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ሶማሊ ከሌላው አጎራባቹ የሶማሊያ ሕዝብ ጋር በብዙ ነገር ላይለያይ የተሳሰረ ነው። ከዚህ ባሻገር ግን በሶማሊ ክልል ከሀገራችን ኢትዮጵያ ከአራቱም ማእዘን የመጡ የተለያዩ ሕዝቦች በሰላም ይኖራሉ።

እንደውም ጅግጅጋ ምድር ላይ "የሐበሻ ሰፈር" የሚባል ሁሉ አለ። በዚህ ሰፈር ውስጥ በአብዛኛው ወይም ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ  ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የመጡ ሕዝቦች ናቸው የሚኖሩበት (ኦሮሞው፣ አማራው፣ ትግራዋዩ፣ ወላይታው፣ ሐረሪው ወዘተ.)። ታሪኩ፣  ሃይማኖቱ፣ ባህሉ፣ ንግዱ፣ የማኅበራዊ ኑሮውና ሥነ-ልቦናዊ መስተጋብሩ ... ወዘተ ላይለያይ አስተሳስሮታል።

ከነቢዩ መሐመድ እስከ ነቢይ ሙሴ፤ ከግሪክ ጠቢባንንና ባለ ቅኔዎች- ከሆሜር እስከ ሄሮዱተስ፤ ከአፍሪካውያኑ የነጻነት አባቶች ከጆሞ ኬንያታ እስከ ጋናዊው  ንኩሩማ፣ ከማንዴላ እስከ ታቦ እምቤኪ... ወዘተ የእንግዳ ተቀባይ አገር፣ የስደተኞች ቤትና ተስፋ፤ የአንድነትና የወንድማማችነት ተምሳሌት ተድርጋ የተሳለች አገር ዛሬ ምነዋ እርስ በርስ የምንገፋፋባትና የምንጠላላባት አገር ሆነች...?!

ይህን የአንድነት፣ የፍቅርና የመተሳሰብ ውብ ታሪካችንን ዛሬስ ማስቀጠል ስለምን ተሳነን...?! እናስ መቼ ነው ለሁሉም በእኩልነት እናትና ቤት የሆነች ኢትዮጵያን ዕውን የምናደርገው?! ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንስ በማንነታቸውና በቋንቋቸው የተነሳ የሚደርስባቸው ግፍ፣ ግድያና መፈናቀል ማብቂያው መቼ ይሆን...?! ዛሬም የቀጠለው ይህ የኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ግፍና ሰቆቃ በአንድ ድምፅ- በቃ! እረ በቃ! ሊባል ይገባዋል።

እናም ዛሬም ነገም የምንመኛት ኢትዮጵያ- ለዜጎቿ/ለሁላችንም የእኩል እናት እና ቤት የሆነች አገር መሆን ይኖርባታል!!

ሰላም ለኢትዮጵያ!!
📣 የሰኔ ወር 2015 ዓ.ም የድርጅታችንን ዜና መጽሔት ካልደረስዎት ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ (link) በመጠቀም እንዲያነቡ በአክብሮት እንጋብዛለን። ከዚህ ቀደም የነበሩ ዜና መጽሔቶችን( Past Issues) በሚለው ዘርፍ በመንካት ማግኘት ይችላሉ።
https://mailchi.mp/85ff57c54a96/1bnk5keu58-9387959?e=4198e66800#LinkNine

በማኅበራዊ ሚድያዎቻችንን ያግኙን
ዌብሳይት፡- https://www.ethiopiawin.net
ፌስ ቡክ: https://www.facebook.com/ETHIOPIAWINNET.AA
ቴሌግራም፡ https://www.tgoop.com/ethiopiawinnetaa
ሊንክደን፡ https://www.linkedin.com/company/79367322/
ዩትዩብ : https://youtube.com/@voiceofethiopiawinnet3661
Happening now: Taking part in consultative workshop on. CSOs National Dialogue Agenda Collection
በአማራ ክልል በተፈጠረው ግጭት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

ነሃሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም

አዲስ አበባ፦


የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ከቅርብ አመታት ወዲህ በሀገራችን እየተከሰቱ የሚገኙ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እልባት እንዲያገኙ በተከታታይ ሲያሳስብ እና የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች እየተስተዋሉ ያሉ ግጭቶች መልካቸውን እና አይነታቸውን እየቀየሩ በህዝብ እና በሀገር ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት እያደረሱ ይገኛል፡፡

በቅርቡም በአማራ ክልል የተከሰተውን የትጥቅ ግጭት እና አጠቃላይ ሁኔታውን ምክር ቤቱ በአንክሮ ሲከታተል ቆይቷል፡፡ የተከሰተው ግጭትምበአብዛኛው ህዝብ ተሰባስቦ በሚኖርባቸው ከተሞች የሚካሄድ፤ የንጹኃንን ሕይወት እየቀጠፈ የሚገኝ፤ የዜጎችን መሰረታዊ መብቶች የገደበ፤ የክልሉን ሰላም በእጅጉ ያወከ፤ ከፍተኛ ማህበራዊ እና ሰብአዊ ቀውስ እያስከተለ መሆኑን ለመገንዘብ ችለል፡፡

በመሆኑም በክልሉ ያለው የትጥቅ ግጭት በአጭር ጊዜ ሰላማዊ መፍትሄ ካላገኘ በአሁኑ ወቅት እየፈተኑን ከሚገኙ ተደራራቢ ችግሮች ጋር ተዳምሮ በሀገራዊ የፀጥታና ደህንነት ሁኔታ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ቀውስ በመገንዘብ ምክር ቤቱ የሚከተለውን ጥሪ ለሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ያስተላልፋል፡-

1. የሀይል አማራጭ መፍትሄ እንደማይሆን ከትናንት የመከራ ተሞከሮች በመማር ሰላማዊ እና ዘለቄታዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ሁሉም የግጭት ተዋናይ አካላት ቅድሚያ ለሰላም እንዲሰጡ፤

2. መንግስት በአማራ ክልል የተፈጠሩ ግጭቶችን ለመፍታት በጅምር ላይ የነበሩ የሰላም እንቅስቃሰዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ጥረት እንዲያደርግ፤ እንዲሁም የታጠቁ ሀይሎች የግጭት አማራጭን በመተው ለሰላማዊ መፍትሄ ቅድሚያ እንዲሰጡ፤

3. የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ምሁራን እና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ሰላማዊ ጥረቶችን እንዲደግፉና ርብርብ እንዲያደርጉ

4. በመንግስት የታወጀው የአስቸካይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ፤ ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች እንዲሁም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት እውቅና የተሳጣቸው እና በማንኛውም ሁኔታ የማይገደቡ መብቶች ተገቢው ጥበቃ እንዲደረግላቸው፤ የፀጥታ ኃይሎች አላስፈላጊ እና ተመጣጣኝ ያልሆነ ሃይል ከመጠቀም እንዲቆጠቡ፤

5. የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ በማቅረብ እንዲረባረቡ፤ በሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ሽፋናቸው እየጨመረ እና መጠነ ሰፊ ጉዳት እያደረሱ የሚገኙ ግጭቶች እንዲያበቁና ዘለቄታዊ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት በመስጠት ርብርብ እንዲያደረጉ፤

6. የሚዲያ ተቋማት፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ እና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች፤ በሃላፊነት እንዲንቀሳሱና ግጭቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ እንዲሁም ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ እያቀረብን፤

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፤ የሚፈጠሩ ግጭቶች እና አለመግባባቶች ሁሉ በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲያገኙ የጀመረውን ሁለንተናዊ ጥረት አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ለማረጋገጥ ይወዳል ፡፡



ስለ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 በአንቀጽ 85 መሰረት የተቋቋመ ገለልተኛ ተቋም ሲሆን የሲቪል ማህበረሰብ ዘርፉን በመወከል በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲንቀሳቀስ በአዋጁ ኃላፊነት ተሰጥቶታል። በአሁኑ ወቅትም ከ4600 በላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የምክር ቤቱ አባላት ናቸው።

-----------------------
በአማራ ክልል በተፈጠረው ግጭት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ
📣 የሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም የድርጅታችንን ዜና መጽሔት ካልደረስዎት ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ (link) በመጠቀም እንዲያነቡ በአክብሮት እንጋብዛለን። ከዚህ ቀደም የነበሩ ዜና መጽሔቶችን( Past Issues) በሚለው ዘርፍ በመንካት ማግኘት ይችላሉ።
https://mailchi.mp/50acdc74b4a7/1bnk5keu58-9392003?e=4198e66800#LinkNine
በማኅበራዊ ሚድያዎቻችንን ያግኙን
ዌብሳይት፡- https://www.ethiopiawin.net
ፌስ ቡክ: https://www.facebook.com/ETHIOPIAWINNET.AA
ቴሌግራም፡ https://www.tgoop.com/ethiopiawinnetaa
ሊንክደን፡ https://www.linkedin.com/company/79367322/
ዩትዩብ : https://youtube.com/@voiceofethiopiawinnet3661
ርዕሰ አንቀጽ
ኢትዮጵያዊነት የኢትዮጵያ መድኃኒት
ሀገራችን በሰው ብንመስላት ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ ድረስ ታማለች፡፡ ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ ከምእራብ እስከ ምሥራቅ ጫፍ ድረስ ታማለች፡፡ ደኅና የሚባለው አካባቢ እንኳ በነጋታው ግጭት ዘርቶ ያድራል፡፡ እዛም እዛም የግጭት ዜና የመፈናቀል ዜና መስማት የተለመደ መሆኑ አንስቶ እስከለየለት ጦርነት ድረስ ሀገራችን አሁን እያስተናገደች ትገኛለች፡፡ ይኽ በእውነት ያማል፡፡ ዛሬ በአንጻራዊ ሰላም ያለው ዜጋም ቢሆን ግጭት ውስጥ ባለው ወገኑ ምክንያት ኑሮው ሰላማዊ አይሆንም፡፡

አሁን ባለው ለትውልድ የዘለቀ የጥላቻ እና የከፋፋይ አስተሳሰብ በሥራ ላይ ያለው ሕገ መንግሥት ጥሩ መደላድል ሆኖት፤ የአመራሩ የዜጎችን ደኅንነት ለማስጠበቅ በግልጽ እያሳየ ባለው ደካማነት ምክንያት በሰላም ወጥቶ መግባትን ትልቅ ተልዕኮ ፈጽሞ እንደመመለስ ያህል ብርቅዬ ሆኗል፡፡ ከለላ አጥተው በታጣቂዎች እና በሰፈር ዱርዬዎች ሁሉ ሳይቀር የሚታገቱበት ክስተት የከተማዋ እንብርት ድረስ ተንሰራፍቷል፡፡ ይህ የፖለቲካዊ ሥርዐት እየፈረሰ መሆኑን ማሳያ ምልክት መሆኑን የሌሎች ሀገራት ታሪክ ማጥናት በቂ ነው፡፡ ይህም ክስተት ተዛምቶአዊ ጠባይ ያለው በመሆኑ ለማኅበራዊ ሥርዐት መናድ (Social disorder) ቀን በቀን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል፡፡
ሀገራችን እንደ ሀገር እንድትቀጥል ፍላጎት ያለው አካል በዚህ ወቅት ሊያደርገው የሚችለው ነገር ቢኖር የጋራ ማንነትን በማስታወስ ላይ የተመረኮዘ ይሆናል ብለን እንጠብቃለን፡፡ እይታውና ትንታኔው በጋራ አብሮነት እንጂ በግል እና ጊዜያዊ ጥቅም አይቃኝም፡፡ መንግሥት ደግሞ በብዙ ባለሙያዎች እና አማካሪዎች የሚሠራ እንደመሆኑ ይኼ ይጠፋዋል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው፡፡ ይሄ በሥልጣን ላይ ያለውም ሆነ የተገፋ ቡድን ሊያስበው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊነት በማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃትን በማንነት ተደራጅቶ ለማስጠበቅ መጣር እስከዛሬ ከመጣንበት አካሔድ የተለየ ውጤትን ያስገኛል የሚል እምነት የለንም፡፡ ኢትዮጵያዊነት እና ሰብአዊነት ላይ እንደሚሠራ ድርጅት፤ ሰብአዊነትን እና ኢ ፍትሐዊነትን ብንታገል ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ሊረዱን፣ ለዛላቂና ለወደፊት አብሮነታችን ለማይቀረው ኢትዮጵያ ወሳኝ መሠረት ማስቀመጥ ይቻላል፡፡
አለበዛ የምትከፋፈል መንግሥት አትጸናም እንደሚለው ቅዱሱ መጽሐፍ፤ የሚከፋፈል የሕዝብ ሥነ ልቦናም ዘላቂና አመርቂ ውጤት አያመጣም፡፡ መንግሥትም የጀመረውን እልህ የመጋባትና ለሕዝብ የገባውን ቃል ማጠፍ ተግባሩን በማመን ለሕዝብ ይቅርታ በመጠየቅ ወደ ውይይት መምጣት አለበት፡፡ ኢትዮጵያዊነትን አንዱን ቡድን ለማጥቃት ሌሎችን ለማስተባበር መጠቀም ሳይሆን የሐሳብ ልዩነት ያለውንም ለመረዳት ወንበር ስቦ መቀመጥን ቅድሚያ የሚያሰጥ እንጥፍጣፊ የሞራል መሠረብ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

የሀገር ሽማግሌዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የሃይማኖት አባቶች ይህንን በማስገንዘብ እንቆምለታለን የምንለው ሀገርና ሕዝብ ከመጥፋቱና አሁንም ሌላ የታሪክ ጠባሳ ከመተው በፊት ልንረባረብ ያስፈልጋል፡፡ ይህንንም በኢትዮጵያነትና በሰብዓዊነት መነጽር በመቃኘት የትኛውንም ቡድን ማቀራረብ እንደሚቻል ድርጅታችን ያምናል፡፡
ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
🇪🇹እንኳን ደስ አለን !🇪🇹 በአለም አቀፍ አትሌቲክስ ሻምፕዩና ጠንካራ የቡድን ስራ በመስራት እንቆዎቻችን በ19ኛዉ የቡዳፔስት የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና በሴቶች ማራቶን ውድድር አማኔ በሪሶ ወርቅ እና ጎይተቶም ገብረስላሴ ብር ለሀገራችን አስገኝተዋል አስገኝተውልናል።

በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!
🌼🌼 በአዲሱ ዓመት የኢትዮጵያዊነት ድርጅት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የእኔና የእርስዎ ድጋፍ ያሻል። 🌼🌼 እኔ የአዲሱ ዓመት ስጦታዬን ለኢትዮጵያዊነት አበርክቻለሁ እናንተስ

🇪🇹 ኢትዮጵያዊነት ለእኛ
እኛ ለኢትዮጵያዊነት 🇪🇹
ድርጅታችን ለመላው ኢትዮጵያውያን መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንልን ይመኛል ።🌻🌻🌻
2025/07/05 23:53:58
Back to Top
HTML Embed Code: