ETHYAS Telegram 1351
Forwarded from Deleted Account
(የበኲረ አብ መድኃኔ ዓለም ዋሻ ፍጹማን ገዳም ቅዱሳን አባቶች።)
ነሐሴ ፳፱ ቀን ፲ ፱፻፺፱ ዓመተ ምሕረት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ። አሜን።
ለተወዳጅ ልጆቻቸውና በአለ ቤታቸው ወለተ ሰንበት እንዲኹም የአለቃ አያሌው ተአምሩ ወልደ ጊዮርጊስ
ልጆችም ሆነ የልጅ ልጆች። በጣም የአለቃ አያሌው ተአምሩ ከዚህ ዓለም መለየት ማለት ለመላው ኢትዮጵያ ሞት
መሆኑ ግልጽ ነው። የሃይማኖት መሪ፤ የማተባችን ተከራካሪ፤ የጾም የጸሎታችን አዘውታሪ፤ የሊቀ ሊቃውንት
አስተማሪ፤ የመናፍቃን ተከራካሪ፤ የመጻሕፍት ፈታች የቅኔው ገበሬ፤ የድጓው የመቋሚያው በሬ፤ ወይ አለቃ
አያሌው ነሐሴ ፲ ፯ ተቀበረ ዛሬ። የኢትዮጵያ ዐይኗ ወጣ ዛሬ። እዘኑ እንዘን ዋእኔን ምእመናት ምእመናን፤ ጠፍቷል
ዐይናችን። እኛ እንደምናውቀው ሁሉ ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቈጠረ ጀምረው ሊቁ አለቃ አያሌው ተአምሩ
የመጽሐፉ ጌታ አዋጠው ጠቅላላ ለሁሉም ተስማሚ የሆነውን በአስተዳደር ሊቀ ሊቃውንት ተመለሱ ይህ ሕግ
የኮተሊክ ሕግ ቢሉ የተነሡ የጥቅም ፈላጊ ምሁር ነኝ የሚሉ የመናፍቅ ተከታይ ወይም ተባባሪ ሕጉን በመጣስ
እንቢ ቢሉአቸው ከራሴ ውርድ ነኝ ብለው ደጉ አባታችን አለቃ አያሌው ተአምሩ ወልደ ጊዮርጊስ በመሪነታቸው
አውግዘው እንደ አርዮስ ለይተው የፍራት መንፈስ ወይም የአፍቅሮ ንዋይ ሳይከተሉ የሃይማኖት መሪ የሆኑት ለግል
አራሳቸውን ሞት ሳይፈሩ ስለ ሃይማኖት ሲዋጉ መቈየታቸው ግልጽ ነው። ለኛ በጹሑፍ ተገልጾልን ስናዝን
ቈይተናል። ሞታቸውን በሰማነ ጊዜ ብቻቸውን አይደለም የሞቱ ሀገሪቱ ናት የሞተች። አሁንም ክቡር ሞቱ ለጻድቅ
በቅድመ እግዚአብሔር ነው። ለወደፊቱ ልጆች ሆይ! እንደሳቸው እንድትሆኑ ነው የምንለው። ኢየኀድግ ወልድ
ግብረ አቡሁ። የሆነው ሁኖ ጽፈውልን የነበረው ሦስት ገጽ ለልጆቻቸው ልንል እናንተም እንደሳቸው ያርጋችሁ
ከአባታችን ረድኤት በረከት ከመጻፉም ሆነ ከመቋሚያው ወይም ከልብሳቸው በዚህ ገዳም ቋሚ ተጠሪ ነበሩ።
ምኞታቸው የነበረው ብዙ ነው። አራቱን ገጽ ምንጣፍ ከአብራኬ ከወጡትም ሆነ ከመንፈስ ቅዱስ ልጆቸ ተቀብዬ
እችለውአለሁ ብለው ነበረ። አሁንም እኛ ግን ለዘለዓለም ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ለነፍሰ አቡነ ወልደ ጊዮርጊስ
ያድኅኖ እመአተ ወልዳ፤ ለወለተ ሰንበት ይዕቀባ እመአተ ወልዳ ሳይባል አይውልም። እኛ ያለንበት ቦታ ሽቅብ
ቢአዩት ሰማዩ እሩቅ ነው ቁልቁል ቢአዩት ምድሩ ጥብቅ ነው። ድምፀ አራዊት፥ ግርማ ሌሊት ነው። ክቡር
አባታችን ከዋሻው ታቦቱ ሲወጣ ቦታውን ስለሚአቁት በአለፈው ጊዜ ስምንት ሺሕ ብር ሰጥተው መንበር
አሠርተው ገብቶአል። አሁንም ምኞታቸው የነበረ ገና ምንጣፍ ሁለተኛ መቋሚያ ጸናጽል ሦስተኛ መጻሕፍት
አራተኛ መቀደሻ ልብስ ነበረ። መራኁት ማለት ደወል ነበረ። እራሳቸው ሠርተው አሰማርተው ሃይማኖት መርተው
የተራበ አብልተው የተጠማ አጠጥተው ገዳማትን እረድተው ነው የአለፉ። በጣም የማይዘነጋው የአባታችን ለሦስት
መቶ ሰባት ዓመት የቆዩት አባት ነሐሴ ፯ ቀን ተገልጸው ወልደ ጊዮርጊስ ብላችሁ ስም ጥሩ ተብሎ ተነግሮናል።
ለራሳችሁ እዘኑ እንጂ ለአባታችን አትዘኑ። እናታችንን መጥናችሁ ጠውሩ። ለእኛም በአታችንን እረጅ ስለ አጣነ
እዘኑልን እንላለን የበኲረ አብ መድኃኔ ዓለም ዋሻ ፍጹማን ገዳም። ሰላመ እግዚአብሔር ለሁሉም የእግዚአብሔር
ጸጋ አይለያችሁ።»

tgoop.com/ethyas/1351
Create:
Last Update:

BY ኢትዮጵያ የስላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር

Share with your friend now:
tgoop.com/ethyas/1351

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

4How to customize a Telegram channel? Unlimited number of subscribers per channel To view your bio, click the Menu icon and select “View channel info.” In 2018, Telegram’s audience reached 200 million people, with 500,000 new users joining the messenger every day. It was launched for iOS on 14 August 2013 and Android on 20 October 2013. To upload a logo, click the Menu icon and select “Manage Channel.” In a new window, hit the Camera icon.
from us

Telegram ኢትዮጵያ የስላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር
FROM American