Telegram Web
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ተመስገን ጌታቸው የተሰጣቸውን መንግሥታዊ ኃላፊነት በስኬት እያከናወኑ ይገኛሉ።

ተመስገን ጌታቸው ከጥቅምት 11/2014 ዓ.ም. እስከ የካቲት 28/2017 ዓ.ም. የጎፋ ዞን ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል፤ በዚህ ኃላፊነታቸውም በ2016 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉ 12 ዞኖች ውስጥ ሶስተኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ይኽም የተሰጣቸውን መንግሥታዊ ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጡ መሆኑን ያመለክታል።

ተመስገን ጌታቸው የተሰጣቸውን መንግሥታዊ ኃላፊነት በስኬት፣ በሕግ አግባብ እና ከሌብነት በፀዳ መልኩ እየተወጡ በመሆኑ ኢዜማ የተሰማውን ኩራት እየገለፀ፤ ከየካቲት 28/2017 ዓ.ም. ጀምሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በምክትል ቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የመልካም አሰተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ በመሆን የተቀበሉትን አዲስ ኃላፊነት የሀገርን ጥቅም ባስከበረ መልኩ በተለመደው ትጋትዎ እንዲያገለግሉ መልዕክቱን ከአደራ ጋር ያስተላልፋል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
በጠራራ ፀሐይ የሚፈፀም አስገዳጅ የፓርቲ ዝርፊያ በቸልታ የሚታለፍ አይደለም፤ በግልጽ እምቢ ሊባልም ይገባል!


የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የመንግሥት እና ፓርቲ አለመለያየት ለሀገራችን ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ዋንኛው እንቅፋት መሆኑን ደጋግሞ ለማስረዳት ሞክሯል፤ በተግባርም ድርጅቱን ሲያዋቅር ይህን ታሳቢ በማድረግ የድርጅት እና የመንግሥት ክንፎችን ለይቶ እምነቱን በተግባር ማሳየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በተቃራኒው ብልፅግና ፓርቲ በተደጋጋሚ መንግሥት እና ፓርቲ መለየት ሲሳነው ባስተዋልንባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ደጋግመን አሳስበናል፡፡ ነገር ግን ፓርቲው ከዚህ ስህተቱ ከመታረም ይልቅ ከጊዜ ወደጊዜ እየባሰበት መሆኑን ስናይ ሆነ ተብሎና ታስቦበት በማወቅ የሚፈፀም ታቅዶ የሚከናወን ሥራ ነው እንድንል አድርጎናል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ባለፈው ጥር ወር ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤው ካሳለፋቸው ውሣኔዎች አንዱ “ፓርቲውን ማጠናከር” የሚል ውሳኔ ይገኝበታል፡፡ ይህንኑ ውሳኔ መሠረት በማድረግ በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ጉዳያቸውን ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሱ ዜጎቸ በውድም ሆነ በግድ የፓርቲ ማጠናከሪያ ገንዘብ እንዲያዋጡ እየተደረገ እንደሆነ ካሰባሰብናቸው ማስረጃዎች ለማወቅ ችለናል፡፡ ከፓርቲ አባላት ውጭ ያሉ ዜጎች ብልፅግናን ፓርቲ ጨምሮ ለየትኛውም ድርጅት በፈቃደኝነት የፈለጉትን ድጋፍ ማድረግ መብታቸው እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ እንዲሁም ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ዜጎች ሃሳባችንን ይወክሉልናል ለሚሏቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ያለምንም ፍርሃት መደገፍ እንዳለባቸውም እምነታችን ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዜጎች አገልግሎት ለማግኘት በሚሄዱባቸው የመንግሥታዊ ተቋማት ይህን ተግባር መፈፀም በፍፁም ሕገወጥ ተግባር ነው፡፡

በመሠረቱ ብልፅግና ፓርቲ 17 ሚሊዮን በላይ አባላት አሉኝ” ሲል በአደባባይ ቢሰማም ለፓርቲው ማጠናከሪያ አሉኝ ክሚላቸው አባላት ማሰባሰብ ሲገባው አባል ካልሆኑ ዜጎች በመንግሥት ተቋማት አገልግሎት ጋር አያይዞ መዋጮ ማሰባሰብ ምንም ዓይነት የሕግም ሆነ የሞራል መሠረት የለውም። ብልጽግና ይህንን ዓይነት አሳፋሪ ተግባር የሚፈፅሙ አባላቱንም ቆጥሮ ከሆነ “በአባላት ብዛት ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ሁለተኛ ሆኛለሁ” የሚለው መዋቅሩን በድጋሚ ሊያጤነው ይገባል፡፡

ብልፅግና ፓርቲ ዋና ዋና የሚባሉት የፓርቲው አባላት በመንግሥት መዋቅር በሹመት ግፋ ሲል ደግሞ በዴሞክራሲ ተቋማት ማስተባበሪያ በሚል የሙሉ ጊዜ የአንድን ፓርቲ የፖለቲካ ሥራ የሚሠሩት ሁሉ ከሕዝብ ከሚሰበሰብ ታክስ ደሞዝና ጥቅማ ጥቅም የሚተዳደሩ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር በሆነበት ሀገር አሁን ደግሞ አባል ያልሆኑ ዜጎችን ጭምር ለአገልግሎት ወደ ማንኛውም መንግሥታዊ ተቋማት ሲሄዱ የፓርቲ መዋጮ መሰብሰብ የመንግሥት መዋቅርን ለአንድ ፓርቲ አገልግሎት መጠቀም መሆኑን አለመረዳት ሳይሆን የማናለብኝነት ስሜቱ የት እንደደረሰ እንደማሳያ የምንወስደው ነው፡፡

በሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ይኑር የሚል ቁርጠኛ አቋም አለኝ የሚል ፓርቲ እንዲህ ዓይነት አሳፋሪ ተግባር ውስጥ መገኘቱ ዓይን ያወጣ አድልኦ እየሠራ መሆኑ ሊያወቀው ይገባል፡፡  ገዢው ፓርቲም አሁን አለኝ ከሚለው ግዝፈት በላይ ለመለጠጥ የሚሄድበት መንገድ ቅጥ ያጣ እራስ ወዳድነት እና አልጠግብ ባይነትን የሚያሳይ እንደሆነ ማስገንዘብ እንወዳለን፡፡ በዚህ መንገድ የምንጓዝ ከሆነ በሀገራችን ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫም ይደረጋል ብሎ ማሰብ ዘበት ይሆናል፡፡ ዜጎች በኑሮ ውድነት፣ በሙስና እና በመልካም አስተደዳደር እጦት መንገላታተቸው ሳያንስ ይህን ዓይነት በጠራራ ፀሐይ በፓርቲ መዋጮ ስም የሚፈፀም ዝርፊያ በቸልታ የሚታለፍ አይደለም፤ ዜጎችም በግልፅ እምቢ እንዲሉ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

በመጨረሻም መንግሥት በማንኛውም ደረጃ እና ተቋም ይህ ሕገወጥ ተግባር እንዳይፈፀም አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግ እና ሥርዓት እንደዲያስከብር እየጠየቅን ይህን ድርጊት የሚፈፅሙ የብልፅግና ፓርቲ አባላትም ይህን ዓይነት አቅጣጫ ከየትኛውም አካል ቢወርድ ህገወጥ መሆኑን በመረዳት ለሀገራችን ዴሞክራሲዊ ሥርዓት ግንባታም ጸር መሆኑን በመገንዘብ ከዚህ ሥራቸው እንደዲታቀቡ እናሳስባለን፡፡

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ይህን ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ በማጣራት በመንግሥት ተቋማት ከአገልግሎት ጋር ተያይዞ የሚሰበሰብ የብልፅግና ፓርቲ ማጠናከሪያ ገንዘብ ማሰባሰብ በአስቸኳይ እንዲያስቆም እና ፓርቲው ላይ የወሰደውን የእርምት እርምጃ ለሕዝብ በግልጽ እንዲያሳውቅ እንጠይቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
መጋቢት 02/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ፌደራል መንግስቱ በትግራይ ክልል የሚታየውን ውጥረት በአስቸኳይ ሊያስቆም ይገባል፣ ዘላቂ መፍትሔም ያስፈልገዋል!


የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ከፕሪቶሪያው ሥምምነት መፈጸም በኋላ አንጻራዊ ሰላም እየታየበት የነበረው የትግራይ ክልል ሁኔታ የፌደራል መንግሥቱ በፕሪቶሪያ ሥምምነት መሠረት ታጣቂ ኃይሎችን ትጥቅ የማስፈታት ኃላፊነቱን በአግባቡ ባለመወጣቱ፣ አካታች የሆነ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት አለመመስረቱን ተከትሎ ህወሓት የእርስ በእርስ ፍትጊያ ውስጥ ገብቶ በትግራይ ክልል ውጥረት መንገሱን ይገነዘባል፡፡ በእርግጥ ይህ ሁኔታ እንዳይፈጠር በመስጋት የፕሪቶሪያ ስምምነት በአግባቡ ተተግብሮ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ደጋግመን ያቀረብነውን ማሳሰቢያ ሳይሰማ በዝምታ ያለፈው ፌደራል መንግስቱ አሁን ለተፈጠረው ቀውስ ድርሻውን መውሰድ እንዳለበት ሊያውቅ ይገባል፡፡

ኢዜማ በፓርቲው የውስጥ ጉዳይ ላይ የትኛውንም አስተያየት የመስጠት ፍላጎቱ የለውም፡፡ ሆኖም በህወሓት ውስጥ የተፈጠረውን የውስጥ የስልጣን ሽኩቻ ተከትሎ በክልሉ ያሉ የታጠቁ ኃይሎች እየሄዱበት ያለው ግትር፣ ግጭት ቀስቃሽ ህገወጥ እንቅስቃሴ ግን በጠቅላላው እንደሀገር በተለይ ደግሞ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ ንፁሀን ዜጎች ላይ የሚያመጣውን ምጣኔ ኃብታዊ፣ ማኀበራዊ ብሎም የሰላምና የደኀንነት አስከፊ አደጋ በቅጡ እንረዳለን፣ ያሳስበናልም፡፡

ትግራይ ክልል አሁን ላለበት ውስብስብ ችግር የተዳረገው መሳሪያ ማንሳትን የተሻለ አማራጭ አድርጎ በሚወስደው ህወሓት የተነሳ መሆኑ እየታወቀ አሁንም የፓርቲው አመራሮች ምንም ሳይፀፀቱ ስልጣንን ጠቅልሎ በመያዝ ግብግብ ውስጥ ገብተው ለሌላ ዙር ግጭት የሚጋበዙ ከሆነ በተለይ በትግራይ ውስጥ ያሉ ዜጎች ሊረዱት የሚገባው መሠረታዊ ጉዳይ ይህ ስብስብ በምንም አይነት ሁኔታ ለማኅበረሰቡ ጥቅም የቆመ እንዳልሆነ ነው፡፡ በዚህ የፖለቲካ ሥልጣን ጥምን ለማርካት በሚደረግ መገፋፋት ውስጥ ባለመሳተፍ እንዲሁም ግጭት የሚቀሰቅሰውን የትኛውንም ኃይል በግልፅ በመቃወም የክልሉ ነዋሪ በአንፃራዊነት ያገኘውን ሰላም ሊያስጠብቅ ይገባል፡፡ በተግባር መሬት ላይ በግልፅ እንደሚታየው ጥቂት ግለሰቦች የዜጎች ሰላምና ደኀንነት ሳያስጨንቃቸው የግል ሥልጣን ለመጨበጥ ህገወጥ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ ሰላም ወዳድ ዜጎች ሁሉ በአንድ ላይ በመቆም ይህ ቡድን ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ማስጠንቀቅ ደግሞም የትኛውም ፀብ አጫሪ ተግባሮቹ ላይ ባለመሳተፍ የህዝብ ድጋፍ እንደሌለው ማሳየት አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡

በተለይ የፌደራል መንግሥቱ ጉዳዩ እዚህ ደረጃ ከመድረሱ በፊት በክልሉ የተፈጠረውን ትርምስ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ሊያስቆም ሲገባ ይህን አለማድረጉ ሳያንስ አሁንም ራሱን እንደሩቅ ተመልካች በመቁጠር በጉዳዩ ላይ ተጨባጭ መፍትሔ እንዲመጣ አለመስራቱ ብሎም የፕሪቶሪያው ስምምነትን በአግባቡ እንዲፈፀም ባለማድረጉ ንፁሀን ዜጎች በህይወታቸው እና በአካላቸው ዋጋ እየከፈሉ መምጣቱ ተገቢነት የሌለው ተግባር መሆኑን አውቆ አሁንም ለጉዳዩ ተገቢ ትኩረት በመስጠት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ በሚያስችል ህጋዊ እና ሰላማዊ መንገድ ብቻ የመንግስትነት ሚናውን እንዲወጣ እናሳስባለን፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
መጋቢት 05/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) የፓርቲው ምርጫ ክልሎችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ሥልጠና እና የአቅም ግንባታ መድረክ በተለያዩ ዞኖች አከናውኗል።

በዚሁ መሠረት በድሬድዋ ከተማ አስተዳደር እና በሐረሪ ክልል ለሚገኙ የምርጫ ክልል ተወካዮች ሥልጠና ተሠጥቷል።

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ፣ በአሪ ዞን ጂንካ እና በጉራጌ፣ስልጤ እና ሐላባ ዞኖች ወልቂጤ ላይ በቀጣይ ሳምንታት ሥልጠናው የሚቀጥል ይሆናል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) የፓርቲው ምርጫ ክልሎችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ሥልጠና እና የአቅም ግንባታ መድረክ በተለያዩ ዞኖች አከናውኗል።

በዚሁ መሠረት በደቡብ ኢትዮጵያ እና ሲዳማ ክልል ለሚገኙ ምርጫ ክልሎች ሐዋሣ እና ዲላ ከተማ ላይ ከየምርጫ ክልሉ ለመጡ ተወካዮች ሥልጠና ተሠጥቷል።

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ፣ በአሪ ዞን ጂንካ እና በጉራጌ፣ስልጤ እና ሐላባ ዞኖች ወልቂጤ ላይ በቀጣይ ሳምንታት ሥልጠናው የሚቀጥል ይሆናል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) የፓርቲው ምርጫ ክልሎችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ሥልጠና እና የአቅም ግንባታ መድረክ በተለያዩ ዞኖች አከናውኗል።

በዚሁ መሠረት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ በወላይታ ዞን ስር ለሚገኙ ከየምርጫ ክልሎች ለተወከሉ የሥራ አሥፈፃሚ አባላት በወላይታ ሶዶ ከተማ ሥልጠና ተሰጥቷል።

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ፣ በአሪ ዞን ጂንካ እና በጉራጌ፣ስልጤ እና ሐላባ ዞኖች ወልቂጤ ላይ በቀጣይ ሳምንታት ሥልጠናው የሚቀጥል ይሆናል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
2025/07/13 19:14:51
Back to Top
HTML Embed Code: