Telegram Web
ከተለያየ ዓይነት ማንነቱ በበለጠ አንድ ኢትዮጵያዊነቱ ያስተባበረው፤ የአንዲት ሀገሩንም የግዛት አንድነት ያስከበረ በወርሃ የካቲት የተፈጸመ ሌላ የጋራ መስዋዕትነት እና አኩሪ ታሪክ!! አንድ ሕዝብ እንጂ ሕዝቦች እንዳልሆንን ማሣያ ግማድ፤ ካራማራ!!

እንኳን ለ 47ኛው የካራማራ የድል በዓል መታሠቢያ ቀን አደረሣችሁ።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
ለፖለቲካ ፍጆታ በሚል የሚደረጉ የሴቶች ተሳትፎን ኢዜማ እንደማይቀበል ያሣውቃል!!


የሰው ልጆች ሰው በመሆናቸው ብቻ ከሚጎናጸፉት ሰብዓዊ መብት ባሻገር የአንድ ሀገር ዜጋ ከመሆን የሚመነጩ ዴሞክራሲያዊ መብቶችም አሉ።

እንደ አጠቃላይ የሰው ልጆች እንደ ሁኔታው በተለያዩ ጊዜያት እነዚህን መብቶች በቅጡ ባለመከበራቸው እነዚህን መብቶች ለማስከበር ከፍተኛ ትግል እና መስዋዕትነት ተከፍሏል።

እነኚህ ከፍተኛ ትግሎች ቢደረጉም የሴቶች መብት መከበር ከተወሰኑ መሻሻሎች ባሻገር አሁንም ገና ብዙ የሚቀረው ሆኖ እናገኘዋለን።

ሴቶች የዓለምን ግማሽ በመቶ የሚሆን ቁጥር ቢይዙም ይህንን የሚመጥን በቂ እና ውጤት የሚያመጣ ውክልና ግን ኖሯቸው አያውቅም፤ ይልቁንም በዓለም ላይ ባሉ ሰው ሰራሽም ሆነ ተፈጥሯዊ አደጋ ከፍ ያለውን ዋጋ ከሕፃናት ጋር ሲወስዱ እንመለከታለን። ከዚህ በተጨማሪም እንደ መደፈር፣ ጠለፋ እና የመሣሠሉ የተለያዩ አይነት ጥቃት ሰለባዎችም ናቸው።

ለዚህ በዋነኛነት የማኅበረሰብ አረዳድ እና የመንግሥት አስፈላጊው የሕግ ሽፋን አለመሥጠት በመሠረታዊነት የሚነሱ ሲሆኑ ከእነዚህ ሁለቱ የመነጩ ታሪካዊ ኢፍትሐዊነቶች ሴቶች መብቶቻቸውን በተሟላ ሁኔታ ለመጠየቅ የሚያስችላቸው አቅምን እንዳያጎለብቱ ከፍ ሲል ለእነርሱም ምቹ የሆነ ሥርዓት መገንባት አለመቻል ምክንያት ሆኗል።

የዘንድሮ ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን ጭብጥ (Theme) "ሁሉም መብቶች፤ ለሁሉም ሴቶች" በሚል ይከበራል።

ይህም ጭብጡ ካለፉት ጊዜያት ውስን ጉዳይ ላይ ካተኮረ ጭብጥነት ይልቅ ሰፋ ያሉ ጉዳዮችን የሚመለከት ሆኖ ተቀርጿል።

ይህ መሠረታዊ የሆኑ የመብት እና እኩልነት ጥያቄዎችን አንግቦ የተነሣው ጭብጥ በይደር የሚቆይ ሳይሆን ባለው አቅም ሁሉ ዛሬ ላይ እየተተገበረ መሔድ ያለበት ሆኖ እናገኘዋለን።

ይህንን ተግባር በእውነት ተፈፃሚ ለማድረግ ግን በመጀመርያ ስለችግሩ አንገብጋቢነት ጆሮ ሰጥቶ ከመስማት አንስቶ እስከ በበቂ ሁኔታ ችግሩን ለማስወገድ ፍላጎት ማሣደር እና አቅምን መገንባት ይሻል፤ ለዚህም በዚህ ውስጥ የሚመለከታቸው የሲቪክ ማኅበራት እንደ አጠቃላይ በሴቶች መብት ላይ በቂ ግንዛቤ መፍጠር፣ አስፈላጊ የሕግ ማዕቀፎችን በማነሳሳት እንዲወጡ ግፊት ማድረግ እና የመሣሠሉት ይጠበቃል፤ መንግሥት ችግሩን የሚመጥን የፖሊሲ እና ሕግ ማዕቀፍ አበጅቶ ሴቶች ለሀገራቸው እንደማንኛውም ዜጋ ሊያበረክቱ የሚገባቸው ላይ እንዲያተኩሩ ማድረግ እና ማኅበረሰቡ ሴቶች በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የሚገጥሟቸውን ፈተናዎች አብሮ በመቆም ፍትሐዊ እና የተረጋጋ ማኅበረሰብ መፍጠር ላይ ሁሉም የድርሻቸውን እንዲወጡ ይጠበቃል።

ኢዜማ በማኅበራዊ ፕሮግራሙ በግልጽ እንዳስቀመጠው ሴቶችን ያገለለ ማንኛውም ዓይነት ፖሊሲ ውጤታማ እንደማይሆን ይገነዘባል፡፡ በተለይ የሴቶች በፖለቲካው መስክ መሳተፍ የራሳቸውን ጉዳይ በጥልቅ ያገናዘበ ፖሊሲ ለመቅረፅ ፋይዳው የጎላ እንደሚሆን ያምናል፡፡ ትምህርት ለእኩል ተሣትፎ ወሣኝ መሣሪያ በመሆኑ ሴት ልጆች ከትምህርት ገበታ የሚያስቀሩ ማነቆዎችን በማስወገድ ዘላቂ የሆነ የሴቶች ተሳትፎን ለማረጋገጥ ይሠራል፡፡ ሴቶች አሁን ያለው የፖለቲካ ምህዳር የፈጠረው አፈና ሲነሣ ሙሉ ኃይላቸውን ሊጠቀሙ የሚችሉበት እድል እንደሚፈጠር ኢዜማ ያምናል፡፡ ለይስሙላ ለፖለቲካ ፍጆታ በሚል የሚደረጉ የሴቶች ተሳትፎን #ኢዜማ እንደማይቀበልም ያሣውቃል።

እንኳን ለዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን አደረሣችሁ!!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ኢዜማ ሴቶች መምሪያ ኃላፊ ሠናይት ዘውዴ  የእንኳን አደረሣችሁ መልዕክት
“የተቋማት ግንባታው ይበልጥ ወደፊት መራመድ ሲገባው ወደ ኋላ የተመለሰበትን አግባብ እያስተዋልን ነው”


ቃልኪዳን ከበደ የኢዜማ በጀትና ፋይናንስ/ትሬዥረር መመሪያ ኃላፊ


በኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የምትዘጋጀው የዜጎች ልሳን መጽሔት ቅጽ 02_ቁ: 11 ትኩረቷን በተቋማት ግንባታ ላይ አድርጋ የተሠናዳች ሲሆን የወሩን እንግዳ ጨምሮ የተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮችን ታሥነብበናለች፤ ማስፈንጠሪያውን በመጫን ሙሉውን ይዘት ያንብቡ።

https://drive.google.com/file/d/1mo5NeeWewZ79jZc_twPEX0OuajVGqTVq/view?usp=drivesdk

#ኢዜማ
#የዜጎች_ልሳን
2025/07/13 11:28:29
Back to Top
HTML Embed Code: