Telegram Web
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንዴት አድርገን በጋራ ለልጆቻችን እንሰራለን ብለን የምናስብበት ጊዜ ነው!

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፖለቲካ ማለት ማኅበረሠብን ወደተሻለ ቦታ ለመውሰድ የሚደረግ ሙከራ እንጂ ማኅበረሠብን ሊያጠፋ የሚችል ነገር ዕያየን አብሮ ሲጠፋ ማየት አይደለም!

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
በኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የምትዘጋጀው የዜጎች ልሳን መጽሔት ቅጽ 02_ቁ: 12 ባለፉት ሁለት ዓመታት በመጽሔቷ የተዳሰሱ ጉዳዮችን ታወሳናለች፤ ማስፈንጠሪያውን በመጫን ሙሉውን ይዘት ያንብቡ።

https://drive.google.com/file/d/1MC-aVkGR2D2T614KNLS8OUQ7IX7k5gkn/view?usp=drivesdk


#ኢዜማ
#የዜጎች_ልሳን
የቀድሞ ፖለቲካ አሁን ባለው ላይ ያሣረፈው አዎንታዊ እና አሉታዊ ተጽዕኖ ምንድነው በሚል ርዕስ በሴቶች መምሪያ የተዘጋጀው የውይይት መርኃግብር ተካሔደ።

የውይይቱን መነሻ ሐሣብ የፓርቲው ም/ሊ ማዕረጉ ግርማ ያቀረቡ ሲሆን ተወያዮች ሐሣቦችን በማከል እና ጥያቄዎችን በማንሣት ሰፊ ውይይት እንዲካሔድ አስችለዋል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ( #ኢዜማ )
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ)
ዘንድሮ በኢትዮጵያ ለ50ኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ136ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሰራተኞች ቀን ‹‹ the impacts of digitalization and artificial intelligence (AI) on workers' safety and health›› በሚል መሪ ቀን እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዓለም ታሪክ እንዲሁም በሀገራችን አንቱታ ካተረፉ የመብት ትግሎች መካከል አንዱ የሆነው ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን የሚከበርበት ነው፤ በመሆኑም ፓርቲያችን በተለያየ ዘርፍ ተሠማርታችሁ ለዕለት ተዕለት ሕይወታችሁ እና ለሀገር እድገትና ልማት ለምታበረክቱት አስተዋጽኦ ልናመሠግን እንዲሁም እንኳን ለዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን አደረሣችሁ ለማለት ይወዳል።

አንድ ሀገር ያለ ሥራ እና ሠራተኞች አንድ እርምጃ ፈቀቅ የሚል እድገት እንደማይኖራት ይታወቃል። በሀገራችን ያለው የሥራ ዕድልና ሠራተኛ ፍላጎት እና አቅርቦት ምጥጥኖሹ እጅጉን በተዛነፈበት ይህንንም ተከትሎ የመጡ የሠራተኛውን ዕውቀቱን እና ወዙን የሚመጥን ክፍያ አለመኖር፣ የቅጥር አድሎ፣ ምቹ የሥራ ቦታ አለመኖር፣ የኑሮ ውድነት እና በመሣሠሉት ውስጥ ሆነው በተለይም በግብርና፣ ምርት፣ ግንባታ፣ ሕክምና፣ ትምሕርት እና መደበኛ ባልሆኑ ዘርፎች ተሠማርተው ለሀገር እድገት የሚሠሩ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞችን ደግሞ በተለየ ሁኔታ ማክበር ይገባል።

ኢዜማ እነኚህ የሠራተኛውን ሕይወት ከባድ ያደረጉ መሠረታዊ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት ፓርቲያችን ይዞት የተነሣው የማኅበራዊ ፍትሕ ጽንሰ ሐሣብ እና ይህንን መሠረት አድርገው ተሰናስለው በሚዘጋጁ ሕጎች እና ፖሊሲዎች እንደሆነ በጽኑ ያምናል።

እነዚህ ሕጎች እና ዋና የፖሊሲ ሐሣቦች ፍትሐዊ ክፍያ፣ የሠራተኞችን መብት በተሻለ ሁኔታ መጠበቅ በተለይም የአካል ጉዳተኞች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ማስከበር፣ የሥራ ቦታዎች ምቹነትን ማረጋገጥ የሚችሉ አፈፃፀሞች እና የመሣሠሉትን መያዝ ዋነኛ ናቸው።

ፓርቲያችንም ፖሊሲውን በዚህ መሠረት ቃኝቶ የያዘ የሠራተኞችን መብት ለማሥከበር ከፍተኛ ቁርጠኝነት ያለው መሆኑን ለማሣወቅ ይወዳል። በሀገራችን የሚገኙ ሁሉም የሥራ ቦታዎች ለሠራተኞቻቸው ምቹና ጤናማ አካባቢን መፍጠር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

እንደሀገር በተስማማንባቸው ድንጋጌዎች መሠረት የሠራተኛ ማህበራት ፌደሬሽኖች እና ኮንፌዴሬሽን ለሚነሱ የመብት፣ የዝቅተኛ የሥራ ክፍያ ጣሪያ፣ የሥራ ላይ ጉዳት ዋስትናና የካሣ ጥያቄዎች መንግስት ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ ማንኛውም ያለሠራተኛው ፍቃድ የሚደረግ ጫናና ማዋከብ እንዲቆም ፣ የታዳጊ ልጆች የጉልበት ብዝበዛን ማስቀረት፣ የሥራ ላይ አድሎና መገለል እንዲቆም ጥሪያችን እናስተላልፋለን።

ለዚህ መሣካት ሚና ካላቸው የሠራተኛ ማኅበራት እንዲሁም የሙያ ማኅበራት ጋር በቅርበት ጣልቃ ገብነት ባስወገደ መልኩ አብሮ ለመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት ያለው ሲሆን ፓርቲያችን ለማኅበራቱ ሁልጊዜም በሩ ክፍት እንደሆነ ለመግለጽ ይወዳል።

የኢዜማ የሙያና ሠራተኛ ማህበራት መምሪያ
ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የውይይት መድረክ

የኢዜማ የሠራተኛ ፖሊሲ ቅኝት

የመነሻ ሐሣብ አቅራቢዎች

የኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት እንቅስቃሴና ተግዳሮቶቹ በዳዊ ኢብራሒም (የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት የኢንዱስትሪ ግንኙነት አማካሪ)

የኢዜማ የሠራተኛ ፖሊሲ ቅኝት በንጋቱ ወልዴ (የኢዜማ ትይዩ ካቢኔ ፀሐፊ)

ቀን: ነገ ቅዳሜ ሚያዚያ 25/2017 ዓ.ም.

ሰዓት: 8:00

ቦታ: ስታዲየም በሚገኘው የ #ኢዜማ ዋና ጽ/ቤት ፕ/ር መሥፍን ወ/ማርያም አዳራሽ
የመርኃግብር ማሥታወሻ!

የውይይት መድረክ

የኢዜማ የሠራተኛ ፖሊሲ ቅኝት


የመነሻ ሐሣብ አቅራቢዎች

የኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት እንቅስቃሴና ተግዳሮቶቹ በዳዊ ኢብራሒም (የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት የኢንዱስትሪ ግንኙነት አማካሪ)

የኢዜማ የሠራተኛ ፖሊሲ ቅኝት በንጋቱ ወልዴ (የኢዜማ ትይዩ ካቢኔ ፀሐፊ)

ቀን: ዛሬ ቅዳሜ ሚያዚያ 25/2017 ዓ.ም.

ሰዓት: 8:00

ቦታ: ስታዲየም በሚገኘው የኢዜማ ዋና ጽ/ቤት ፕ/ር መሥፍን ወ/ማርያም አዳራሽ
#ኢዜማ የሠራተኛ ፖሊሲ ቅኝት በሚል በኢዜማ ሙያ ማኅበራት መምሪያ የተዘጋጀው መርኃግብር በትላንትናው ዕለት ተካሔደ።

በመርኃግብሩ የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት አማካሪ የሆኑት ዳዊ ኢብራሒም በዓለም አቀፍ እና በኢትዮጵያ የሠራተኛው የመብት ጥያቄዎች እንቅስቃሴ መነሻውን፣ በእንቅስቃሴው የተከፈለውን መሥዋዕትነት፣ የተጎናፀፋቸውን ስኬቶች እና ከዚህ በኋላ ትኩረት ሊያደርገባቸው ስለሚገቡ እንቅስቃሴዎች ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል።

እንዲሁም የኢዜማ የሠራተኛ ፖሊሲ ቅኝት በሚል የኢዜማ ፖሊሲ ላይ ማብራርያ የሠጡት የኢዜማ ትይዩ ካቢኔ ጸሐፊ ንጋቱ ወልዴ ሲሆኑ ፖሊሲው ሲዘጋጅ ከላይ ተነሱ የተባሉ የመብት ጥያቄዎችን በሒደት ለመመለስ በሚያስችል እንዲሁም እንደ ሀገር በተለያዩ ዘርፎች ሠራተኛው የሚያደርገውን አስተዋጽኦ ከፍ እንዲያደርግ ባለመ መልኩ መሆኑን ገልጸው ፖሊሲው ፓርቲው ይዞት የተነሣው ማኅበራዊ ፍትሕ እሳቤ ላይ ያጤኔጠነ እንደሆነ ገልጸዋል። እንዲሁም ከሌሎች ፖሊሲዎች ጋር የተሠናሠለ መሆኑን በቅጡ የተረጋገጠ እንደሆነም አንስተዋል።
እንኳን ለ 84ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች መታሠቢያ ቀን አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ኢዜማ 6ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል ን እና የኢዜማ አካዳሚ ምርቃትን አስመልክቶ የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ ያቀረቡት ንግግር።
ኢዜማ ከመንግሥት ጋር አብሮ መስራቱ መርህ የለሽ ሊያስብለው አይችልም


አሰፉ ተረፈ (የኢዜማ ብሔራዊ ኦዲት ኮሚቴ አባል)

በኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የምትዘጋጀው የዜጎች ልሳን መጽሔት ቅጽ 02_ቁ: 12 ትኩረቷን ፖለቲካ እና መርህ ላይ አድርጋ የተሠናዳች ሲሆን የወሩን እንግዳ ጨምሮ የተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮችን ታሥነብበናለች፤ ማስፈንጠሪያውን በመጫን ሙሉውን ይዘት ያንብቡ።

https://drive.google.com/file/d/1ciHhYDVU-IojlXWD1UkAp1rC7aTA5pjx/view?usp=drivesdk

#ኢዜማ
#የዜጎች_ልሳን
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በኢዜማ አካዳሚ ምርቃት መርኃ ግብር ላይ የአካዳሚው አስተባባሪ ሐሮሌ ዮሴፍ ያደረጉት ንግግር።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ፀሐፊ ደስታ ዲንቃ በ #ኢዜማ አካዳሚ ምርቃት ላይ ያደረጉት ንግግር።
2025/07/13 22:50:57
Back to Top
HTML Embed Code: