Telegram Web
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) የፓርቲው ምርጫ ክልሎችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ሥልጠና እና የአቅም ግንባታ መድረክ በተለያዩ ዞኖች አከናውኗል።

በዚሁ መሠረት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፤ በሐዲያ እና ከንባታ ዞን ስር ለሚገኙ ከየምርጫ ክልሎች ለተወከሉ የሥራ አሥፈፃሚ አባላት በሆሣዕና እና ዱራሜ ከተማ ሥልጠና ተሰጥቷል።

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ፣ በአሪ ዞን ጂንካ እና በጉራጌ፣ስልጤ እና ሐላባ ዞኖች ወልቂጤ ላይ በቀጣይ ሳምንታት ሥልጠናው የሚቀጥል ይሆናል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በሚያተባብሩን ጉዳዮች ላይ ከሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አብረን እንሰራለን!!

ኢዜማን ይወዳጁ

👉 ፌስቡክ: https://bit.ly/Ezema_FB

👉 ትዊተር (X): https://bit.ly/3XgzDbH

👉 ዩቲዩብ: https://bit.ly/Ezema_YT

👉 ቲክቶክ: https://bit.ly/EzemaT_T

👉 ቴሌግራም: https://bit.ly/Ezema_TG

👉 ዋትስአፕ: https://whatsapp.com/channel/0029Vb4gZHl9sBI4OBw49p2z

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠ/ሚ ዓብይ አሕመድ ዛሬ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም. በፌዴራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከም/ቤቱ አባላት ለተነሡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን በ ሕ/ተ/ም/ቤት አባል (የኢዜማ ተመራጭ) የተከበሩ ባርጠማ ፍቃዱ የሚከተለውን ጥያቄ አቅርበዋል፤

#የዜግነት_ፖለቲካ
#ማኅበራዊ_ፍትህ
#ዴሞክራሲያዊ_ፌደራሊዝም
#ኢዜማ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፓርቲ ውስጥ ያልተለማመድነውን ዴሞክራሲ ከፓርቲው ውጪ ልናመጣው አንችልም!!

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
የኔ ፖለቲካ
            
የውይይት መድረክ


የውይይት ርዕስ:
የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት እድሎቿ እና ተግዳሮቶች


የመነሻ ጽሁፍ አቅራቢ የሺጥላ ወንድሜነህ (ዶ/ር)

ቀን: መጋቢት 20/2017 ዓ.ም

ሰዓት: 8:00

ቦታ: የኢዜማ ዋና ጽ/ቤት፤ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም አዳራሽ

በኢዜማ ወጣቶች መምሪያ የተዘጋጀ

#ኢዜማ
#የኔ_ፖለቲካ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የተሻለ ህይወት ለልጆቻችን ከሰጠንም ማድረግ የምንችለው እንደ ኢትዮጵያዊ ማሰብ ስንችል ነው!!

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
የመርኃግብር ማሥታወሻ!!

የኔ ፖለቲካ
            
ለሁሉም ዜጋ ክፍት የሆነ የውይይት መድረክ


የውይይት ርዕስ:
የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት እድሎቿ እና ተግዳሮቶች


የመነሻ ጽሁፍ አቅራቢ የሺጥላ ወንድሜነህ (ዶ/ር)

ቀን: ነገ ቅዳሜ መጋቢት 20/2017 ዓ.ም

ሰዓት: 8:00

ቦታ: የኢዜማ ዋና ጽ/ቤት፤ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም አዳራሽ

በኢዜማ ወጣቶች መምሪያ የተዘጋጀ

#ኢዜማ
#የኔ_ፖለቲካ
የመርኃግብር ማሥታወሻ!!

የኔ ፖለቲካ
            
ለሁሉም ዜጋ ክፍት የሆነ የውይይት መድረክ


የውይይት ርዕስ:
የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት እድሎቿ እና ተግዳሮቶች


የመነሻ ጽሁፍ አቅራቢ የሺጥላ ወንድሜነህ (ዶ/ር)

ቀን: ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 20/2017 ዓ.ም

ሰዓት: 8:00

ቦታ: የኢዜማ ዋና ጽ/ቤት፤ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም አዳራሽ

በኢዜማ ወጣቶች መምሪያ የተዘጋጀ

#ኢዜማ
#የኔ_ፖለቲካ
#ኢዜማ ወጣቶች መምሪያ የሚዘጋጀው #የኔ_ፖለቲካ መርኃግብር በዛሬው ዕለት በኢዜማ ዋና ጽ/ቤት ተካሔደ።

በውይይቱ ዓለም አቀፍ እና ሀገራዊ ሁኔታን መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት ላይ ያሉ እድሎች እና ተግዳሮቶች በዘርፉ ምሁር የሺጥላ ወንድሜነህ (ዶ/ር) የመነሻ ሐሣብ አቅራቢነት እና በተወያዮች ተጨማሪ ሐሣብ እና ጥያቄዎች ሠፊ ውይይት ተደርጓል።

ሙሉ ውይይቱን በፓርቲው የዩቲዩብ ገጽ (https://bit.ly/Ezema_YT) በቅርቡ ይፋ የምናደርግ ይሆናል።

ሌሎች የኢዜማ የማኅበራዊ ትስስር ገፆችንም ይወዳጁ።

👉 ፌስቡክ: https://bit.ly/Ezema_FB

👉 ትዊተር (X): https://bit.ly/3XgzDbH

👉 ቲክቶክ: https://bit.ly/EzemaT_T

👉 ቴሌግራም: https://bit.ly/Ezema_TG

👉 ዋትስአፕ: https://whatsapp.com/channel/0029Vb4gZHl9sBI4OBw49p2z
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ 1446ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል አደረሳችሁ!

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
መጋቢት 22/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሰጠ መግለጫ
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ በዛይሴ ወዘቃ፣ ፃናኦ ቀበሌ በግለሰብ ቤት ላይ በተፈፀመ የቤት ማቃጠል ጥቃት ቤት ንብረት መውደሙ እና የሁለት ህፃናት ህይወት ማለፉን ለማወቅ ችለናል፡፡
በዚህ አሰቃቂ ሕገወጥ ድርጊት ድርጅታችን ኢዜማ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ የክልሉ መንግስት ድርጊቱን የፈፀሙትን አካላት ሕጋዊውን መንገድ ተከትሎ እንዲያጣራ እና በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን ለፍርድ እንዲያቀርብ እንጠይቃለን፡፡ከዚህ አሳፋሪ እና አስነዋሪ ተግባር ጀርባ ያለ የትኛውም አካል ቢሆን በጋራ ሊወገዝ የሚገባው መሆኑንም ኢዜማ በፅኑ ያምናል።
ይህን በጭካኔ የተሞላ አስነዋሪ ድርጊት ተከትሎ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያዎች እና የመንግስት አካላት የድርጅታችንን ስም አላግባብ እያነሱ መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህን መሰል ስም ማጥፋት በቸልታ የማናየው መሆኑ እንዳለ ሆኖ ኢዜማ በእንደዚህ አይነት ሕገወጥ ተግባር ውስጥ የማይገኝ ብሎም ከቆመለት የሰላማዊ ትግል መርሆ ውጪ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ሳናነሳ የማናልፈው ጉዳይ ቢኖር ወንጀል የፈፀሙ አካላትን ለፍርድ በማቅረብ ሂደት ውስጥ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ አይነት የፖለቲካ ልዩነትን መሰረት ያደረጉ ንፁሐንን ከአጥፊዎች ያለየ የጅምላ እስርና ህገወጥ አፈና እንዳይኖር የህግ አስከባሪ አካላትም ሕግና ሕግን ብቻ መሰረት አድርገው እንዲሰሩ በአፅንኦት ለማሳሰብ እንወዳለን ፡፡
ስለሆነም ይህን አሰቃቂ ወንጀል የፈፀሙ አካላት በአስቸኳይ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ የፀጥታ አካላትም የደረሱበትን ግኝት ደረጃ በደረጃ ለሕብረተሰቡ እንዲያሳውቁ እየጠየቅን ኢዜማም ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ እንደሚከታተል ለማሳወቅ እንወዳለን።
በተፈፀመው ሕገወጥ እና በጭካኔ ለተሞላ አስነዋሪ ተግባር ቤት ንብረታቸውን እና ህፃናት ልጆቻቸውን ላጡ ቤተሰብ፣ ወዳጅ እና ዘመድ መፅናናትን እንመኛለን፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
መጋቢት 22/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የፌደራል መንግሥት በክልል ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁ: 359/1995 ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮችች ም/ቤት አባል (የ #ኢዜማ ተመራጭ) የሆኑት አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ያቀረቡት ሐሣብ

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የፌደራል መንግሥት በክልል ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁ: 359/1995 ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮችች ም/ቤት አባል (የኢዜማ ተመራጭ) የሆኑት አብርሃም በርታ (ዶ/ር) ያቀረቡት ሐሣብ

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ ውስጥ የማንነት ፖለቲካ ያመጣብንን ችግር ከሌላ ቦታ አጣቅሰን የምንረዳው ሣይሆን፤ በራሣችን ያየነው ነው!

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ
2025/07/13 15:23:33
Back to Top
HTML Embed Code: