የተከበራችሁ የኢዜማ 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ተሳታፊዎች
የተከበራችሁ የኢዜማ የየመዋቅሩ አመራሮችና አባላት
የተከበራችሁ የኢዜማ ደጋፊዎችና ኢትዮጵያዊያን
ዛሬ ወደ እናንተ ቀርቤ መልዕክት የማስተላልፈው በከንቱ እንድትደግፉሽ ብቻ ሳይሆን በኢዜማ የፖለቲካ ሥራ ላይና በሀገራችን እንዲሰፍን ከሚፈልገው የፖለቲካ አሰራር መሻት የመነጨ ህልሜን ነው የማጋራችሁ። ይህ የኔ የግል ራዕይ ሳይሆን ለፓርቲያችን ህልውና የሚቀጥልበት እና ሀገራችን የሚፈውሰውን ፖለቲካ የምንሰራበት ራዕይ ነው።
ዛሬ ይህንን ዕድል አግኝቼ በፊታችሁ ለመመረጥ በዕጩነት ስቀርብ በቀጣይ ዓመታት በተወዳደርኩበት የአገልግሎት ቦታ የሀገራችን ኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲ አሰራር ለማዘመን ነው። ይህ ለእኛ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው። በመንታ መንገድ ላይ ለተወዛገበው የፖለቲካ ትግላችንና ለመፃዒው የሀገራችን ዕድል ፋንታ የምንቀይስበት የታሪክ እጥፋት ነው። ዜጎች አጥብቀው የሚሹትን የፍትህ ስርዓት እንዲሰፍን: በየፊናው የሚሰማውን የድረሱልን ተማፅኖ: በቅርቡ እየተንሰራፋ የመጣውን ተስፋ የመቁረጥ አዝማሚያ ምላሽ እንዲያገኝ የተደራጀና የዘመነ የፖለቲካ ትግል ማድረግ አንድ አማራጭ ነው። የሀገራችን ጥያቄዎች ለመመለስ ለምናቀርበው የፖለቲካ ጥያቄ ራሱን የቻለ ዘመናዊ የፖለቲካ ፓርቲ አሰራሮችን መንደፍ ይጠበቅብናል። ለዚህ ደግሞ ጊዜው አሁን ነው።
ይህን የምናሳካው በፓርቲያችን ጥንቃረ: አደረጃጀት: የውስጥ ሥራና ህዝባዊ አንድነት ነው። ኢዜማን እንደገና የምናደራጅበትና ወደ መነሻ ዓለማው የምንመልስበት ወቅት ዛሬ ነው።
ክቡራንና ክቡራት
ኢዜማን እንደገና በማለት እዚህ በፊታችሁ ስቀርብ የፓርቲያችን ገፅታ ከቀደመው በተሻለ መልኩ ለማስተካከል የፓርቲው ማዕጰላዊ ጽ/ቤት ገፅታን ማዘመን ተገቢ ነው። የፖለቲካ ፓርቲ ሥራን ከዋና ጽ/ቤት በሚሰራው ስራ ያማረና የተሻለ ለማድረግ በቁርጠኝነት ልንሰራ ይገባል። የፓርቲያችን ጽ/ቤት የየዕለት ተግባር መተግበር: መረጃ ማደራጀት: ስብሰባዎችን ማመቻቸት ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ የዜግነት ፖለቲካ እና ማህበራዊ ፍትህ ጥያቄዎች የልብ ማረፊና እምነት የሚጣልበት ተቋም መገንባት ነው። በቀጣይ ምርጫ በፓርቲያችን የከፍተኛ ስልጣን ባለቤት በሆነው በጠቅላላ ጉባዔያችን ይህንን ታላቅ አደራና የቤት ሥራ ስትሰጡኝ ፓርቲያችን ጉልህ: የሚታይ ራዕይና ተጠያቂነትን መርሁ ያደረገ የፖለቲካ ትግል ማዕከል እናደርገዋለን።
ኢዜማን እንደገና!
ከቢሮክራሲ እስራት ወደ ልህቀት
በህገ ደንባችን ላይ በተሰጠን ሀላፊነትና ተግባር ከማዕከላዊ ቢሮው በተጨማሪ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተጠናከረ አደረጃጀት እንዲኖረን ጽ/ቤቶችንና ቢሯቸውን ያለማቋረጥ የሚደረግ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ወደ መደበኛ የሰላማዊ ፖለቲካ ትግል እናስገባቸዋለን። በዋና ቢሮም ሆነ በየመዋቅሩ የሚወሰኑ የተለያዩ ውሳኔዎችን ክትትል በማድረግ አፈፃፀማቸውንና ተግባራዊነታቸውን በቋሚነት መከታተል። በሀገራችን እንዲኖር የምንፈልገውን ተጠያቂነት በመጀመሪያ በፓርቲያችንና በራሳችን እንጀምረዋለን። ተጠያቂነት የሌለውን የፖለቲካ ፓርቲ የሚመርጠው አካል ስለሌለ በቅድሚያ ከራሳችን መዋቅሮች በማስጀመር ተጠያቂነትን እናሰፍናለን።
ይህንን ለማሳካት
1, በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ: በሰለጠኑና ብቁ በሆኑ ባለሙያዎች: ግልፀኝነት በተሞላው አሰራር: ተጠያቂነትን እናሰፍናለን
2, ብያንስ የማዕከላዊ ቢሮው የሚቆጣጠረው በእያንዳንዱ የክልል ከተሞችና የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የፓርቲያችን አደረጃጀቶችን የሚደግፍ የጽ/ቤት ቢሮ እንዲኖር እንሰራለን
3, በየመዋቅሩ አጋዥ ቢሮ ለመክፈት የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ እናስጀምራለን
4, የኢዜማ ቅርጫፍ ጽ/ቤቶችን እንቅስቃሴ ለአባሉ በየጊዜው ለማድረስ የመረጃ ማሰራጫ መንገድ እንፈጥራለን
የተጠናከረና የጎላ አስተዋፅዖ ያለው የፖለቲካ ፓርቲ ለማድረግ የዜጎች: የማህበራት: የመደብና ሌሎች የትግል አቅጣጫዎችን በመከተል ሀገራችንን ያቆረቆዛትን የብሔር: የጎሳና ተመሳሳይ የፖለቲካ ትግሎችን በጋራ እናከስማቸዋለን።
ክቡራንና ክቡራት
ኢዜማን እንደገና ለማጠናከር የፓርቲው ጽ/ቤቶችን ማጠናከር ቅድሚያ የምሰጠው ጉዳይ ነው። በተቻለን መጠን በዋና ቢሮ ስር የሚደራጁ የክልል አጋዥ ጽ/ቤቶች የየራሳቸው የሚያስፈልጋቸውን ተቋማዊ ቁሳቁሶችን ከተለያዩ አካላት ጋር በመነጋገር እናሟላቸዋለን። በዋና ቢሮ ደረጃም የቬርችዋል የርቀት ስብሰባ ማከናወኛ smart room ወደ ሥራ እናስገባለን። ከአባላትና ከየምርጫ ክልሉ የሚመጡትን ጥያቄዎችን በ48 ሰዓታት ውስጥ ምላሽ እየሰጠን የፍትህ ጥያቄውን እናሳልጣለን።
ይህን ለማድረግ እና በጋራ ለማሳካት የሚከተሉትን መንገዶች እንጠቀማለን
ስትራቴጂካዊ የአመራር ጥበብ
የፓርቲያችን ዋና ፀሐፊ ከሆንኩ ትልቁ ሥራዬ የኢዜማን ሀሳብና ራዕይ ወደ ተግባር የመቀየር ስራ ነው። በዋና ጽ/ቤት የሚገኙ መምሪያዎች ጋር በጥምረት በመሆን ፈጣን: ቀልጣ እና ተደራሽ አገልግሎት መስጠት ነው።
የመፈፀም ብቃት ማሳደግ
ፓርቲያችን ባለው ውስን የሰው ሀይል በመጠቀም በየዕለቱ የሚሰጡንን ስራዎችን በተገቢው መንገድ መፈፀም ትልቁ የስኬት ቁልፍ ነው። የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴውን ውሳኔ በመከተል ተግባራዊነታቸውን እየተከታተልኩ መደገፍ እችላለሁ።
የተጠናከረ ወዳጅነት
የሀገራችን የማህበራዊ ፍትህ ጥያቄ ለማስፈፀም ብዙ የሰው ሀይል የሚጠይቅ ስራ ቢሆንም ካሉን ሁሉም የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች ጋር የተጠናከረ ወዳጅነት በመፍጠር የፓርቲ ተልዕኳችን ከወረቀትና ከምዕናብ ሀሳብ ወደ ተግባር እቀይረዋለሁ።
ውጥረትን ማርገብ
ሀገራዊ የፖለቲካ ውጥረቶችን ለማርገብ የፓርቲያችን ውጥረቶችን መክሰም ይቀላልና በተቻለ መጠን በኢዜማ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ውጥረቶችን ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት ሰላማዊ የሥራ ከባቢን እፈጥራለሁ። ይህ በተለያዩ ውጥረቶች ምክንያት እየተራዘመ ያለውን የህዝባችን ፖለቲካዊ ጥያቄ የሚመለስበት ጊዜ ያሳጥራል።
ቁርጠኝነትን ማጉላት
ሁሉም የኢዜማ አባል ላመነበት ፍትሃዊ ጥያቄ እስከመጨረሻም የሚታገል ቁርጠኛ እንደሆነ ይታወቃል። ለዚህማ ማሳያነት እስከዛሬ ኢዜማን በሙሉ ጊዜዬ ሳገለግል አንዳች ቀን እንኳን ሰንፌ አላውቅም። ይህን በነፃ ለኢትዮጵያ የማደርገውን በዋጋ የማይተመን ትግል በቀጣይም ለሌሎች አርዓያ በሚሆን መልኩ በቁርጠኝነት አገለግላለሁ።
ክቡራንና ክቡራት
ኢዜማን እንደገና ስንል የፖለቲካ ፓርቲን የመምራትና ተቋማዊነትን ማዘመን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል በአዲስ ገፅታ መገንባት ማለታችን እንደሆነ ይታወቅልን። ለዚህም የህዝባችን ክብር በሚመጥን መልኩ የዘመነና የተጠናከረ የፖለቲካ ፓርቲ እናደርገዋለን ማለታችን ነው።
በቀጣይ በዋና ፀሐፊነት ሳገለግላችሁ የሚከተሉትን ዓበይት ተግባራትን እንደምተገብርላችሁ ለማረጋገጥ እወዳለሁ:
ሀ/ በአሁኑ ወቅት ያለውን እጅግ የተዳከመ እና ልል ተጠያቂነት ያለውን የኢዜማ ማዕከላዊ ቢሮ ዘመኑን በዋጀ የአገልግሎት ጥራት: ተጠያቂነቱ የተንሰራፋ በባለሙያ የሚመራ ተቋም: እና መረጃ እና መርህ ተኮር የአሰራር ስርዓት እዘረጋለሁ።
ለ/ የጽ/ቤት የአፈፃፀምና የማስፈፀም አቅምን የሚመዝን ወራዊ የተግባር ምዘና ስርዓት እዘረጋለሁ: የፓርቲው ውሳኔዎች: የአባላትና የመዋቅር ጥያቄዎችን: የሦስተኛ ወገን የደብዳቤ ግንኙነቶችን በብቃት አሳልጣለሁ

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለ #ኢዜማ ን በልኩ ከተሠጡ የድጋፍ ድምፆች በጥቂቱ ይመልከቱ።
ማጠቃለያ!
⚖️
ከሰኔ 2-26/2017 ዓ.ም በሚቆየው የኢዜማ 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የከፍተኛ አመራሮች የምርጫ ቅስቀሳ ስናካሂድ ቆይተናል። በእነዚህ የቀስቀሳ ቀናት በተቻለን መጠን ኢዜማ እንደገና መታደስ አለበት በሚለው ሀሳባችን በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የኢዜማ መዋቅሮች ጥያቄ መሆኑን በመረዳት ፓርቲያችን ሊያደርጉ የሚገባቸውን የማሻሻያ ሀሳቦችን ጠቁመናል። የፓርቲያችንም ከፍተኛ ስልጣን ያለው የጠቅላላ ጉባዔው በዕለቱ በማሻሻያና ሪፎርም ሀሳቦች ላይ ትኩረቱን እንዲያደርግ በመላው ኢትዮጵያ የምንገኝ ኢዜማዊያን በአንድ ድምፅ አሰምተናል። በዚህም ታሪካዊ ጉባዔ ላይ ኢዜማ ራሱን ገምግሞ እንደገና ወደ ሰፊው ህዝብ እንዲቀርብ ጥያቄ ሰንዝረናል።
ሪፎርም እና ተሃድሶ አስፈላጊ በመሆናቸው ፖለቲካዊ ማሻሻያዎች: መዋቅራዊ ማሻሻያዎችና ተቋማዊ ማሻሻያዎች እንደሚያስፈልጉን አምነን ሁሉም የኢዜማ አባላት ባቀረብነው ሀሳባችን ላይ እንዲወያይ አድርገናል። የጉባዔው ይሁንታ ካገኘ የኢዜማን ማሻሻያ የሚመሩ አካላትን ለመጠቆም እንወዳለን። ከታች ወደ ላይ የቀረበውን የኢዜማን ማሻሻያ ሀሳብ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ ሊመራው ይችላል። ሪፎርሙ ላይ ከመግባባት ከተደረሰ የፓርቲው መሪ ወይም ጉባዔው የሚሰይመው የሪፎርም ቋሚ ኮሚቴ ወይም ገለልተኛ የፖለቲካ ሙያ ኤክስፐርቶች በጥንቃቄ ሊመሩት ይችላሉ።
ይህን ተከትሎ ኢዜማ እንደገና ማሻሻያ የማድረግ ፍላጎቱ በጠቅላላ ጉባዔው ተቀባይነት ካገኘ ኢዜማን ለመጪው ዘመን ጊዜውን የዋጀ ተራማጅ የፖለቲካ ፓርቲ የማድረግ ፍላጎታችን ይሰምራል።
በዚህ የማሻሻያ ሀሳብ አስፈላጊነት የምታምኑ የጉባዔ ተሳታፊዎች የኢዜማን እንደገና ማሻሻያ ሀሳብ አስፈላጊነት የሚያምኑ አመራሮችን በምስጥራዊ የካርድ ድምፅ አሰጣጥ እንድትመርጡ አሳስባለሁ!
ለዚህ የውስጠ ፓርቲ ምርጫ ስኬት ድጋፍ ያደረጋችሁ አካላት ማለትም የኢዜማ 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አዘጋጅ ኮሚቴ: የአስመራጭ ኮሚቴ: ዕጩ ተወዳዳሪዎች: የጉባዔ ተሳታፊዎች: የኢዜማ አባላትና አመራሮች እና ሌሎች በዚህ ታሪካዊ ጉባዔ ላይ ላደረጋችሁት አስተዋፅዖ ከልብ አመሰግናለሁ!
የማሻሻያ ሀሳቡን ይዘው ከቀረቡት ውስጥ
ጌታቸው ጳውሎስ-ለሊቀመንበርነት
ኤልሳቤጥ ሉቃስ- ለምክትል ሊቀመንበርነት
ዶ/ር ካሣሁን ደለነ-ለዋና ፀሐፊነት
እንድትመርጡ በአክብሮት እጠይቃችኋለሁ!
ሙሉ የቃል ኩዳን ሰነዳችን ለማግኘት
https://www.tgoop.com/ethzema/4751
https://drive.google.com/file/d/1wscQokq5GqXMs6ORl5XiXsPUWuFzDdRn/view?usp=drivesdk

Telegram
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለ #ኢዜማ ን በልኩ ከተሠጡ የድጋፍ ድምፆች ይመልከቱ።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሰኔ 28-29/2017 ዓ.ም. የሚደረገውን የ #ኢዜማ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ አስመልክቶ ከጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ስብሳቢ ዮሐንስ መኮንን የተላለፈ መልዕክት።