Telegram Web
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዕጩ ሊቀመንበር ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ መልዕክት

“ሰላም ጤና ይስጥልኝ የተከበራችሁ የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች!
ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ ነኝ፡፡

ኢዜማ በዚህ ወር መጨረሻ በሚያከናውነው ኹለተኛ መደበኛ ጉባኤ ለሊቀመንበርነት ለመወዳደር በዕጩነት ቀርቤያለሁ። እንደሚታወቀው ላለፉት ኹለት ሳምንታት ኢዜማን በልኩ በሚል መሪ ቃል የምረጡኝ ቅስቀሳ እያከናወንሁ ነው፡፡

ፓርቲያችን ኢዜማ ራዕዩን መሸከም የሚችል ጥንካሬ ላይ እንዲደርስ በልኩ መንቀሳቀስ እንዳለበት አምናለሁ፡፡

የኢዜማ ልክ ትጋት፣ ዲሲፕሊን እና ልኅቀት ነው፡፡ የኢዜማ ልክ ዘመኑን የዋጀ እና ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች ምላሽ መስጠት የሚችል ኾኖ መገኘት ነው፡፡

ኢዜማ በልኩ እንዲኾን ከዚህ ቀደም ያጋጠሙትን ተግዳሮቶችና ድርጅታዊ ድክመቶችን በመመርመር ስትራቴጂያዊ አመራር ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ፡፡

ኢዜማን በልኩ ብለን የተሰባሰብነውን አመራሮች ማለትም እኔ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅን ለሊቀመንበርነት፣ አቶ ማዕረጉ ግርማን ለምክትል ሊቀመንበርነት፣ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬን ለዋና ጸሐፊነት እንዲሁም ወይዘሮ አሰፉ ተረፈን ለፋይናንስ/ትሬዠረር ኃላፊነት እንድትመርጡ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡

#ኢዜማን በልኩ! ትጋት፣ ዲሲፕሊን፣ ልኅቀት”
ኢዜማን እንደገና!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ-ኢዜማ ከተመሠረተበት ግንቦት 2011 ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ ሀገራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች በፅንሰ ሀሳብ መሪነት የሀገራችን ፖለቲካ እያዘመነ ይገኛል። ፓርቲያችን ከአመሠራረቱ ጀምሮ ከምርጫ ክልሎች ወደ ላይ የተደራጀ በመሆኑ ሁላችንም የምንኮራበትና ዜጎች ተስፋ ያደረጉበት ስብስብ መሆኑ ይታወቃል። ኢዜማ አዲስ የአደረጃጀት ቅርፅ ይዞ በመምጣት በመንግስት እና በፓርቲ ደረጃ የነበረውን ቁርኝት በመለያየት የፖለቲካ መሪ ክንፍና የፓርቲ ሊቀ መንበር ዘርፍ ለየብቻ የሚሰሩበትን አሰራር በመተግበር ለብዙ የፖለቲካ ድርጅቶች አርዓያ መሆን ችሏል።

ፓርቲያችን ሰኔ 28-29/2017 ዓ.ም በሚያደርገው 2ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቅቋል። በዚህ ከመላው ኢትዮጵያ በሚወከለው ጉባዔ ላይ የፓርቲውን ትላልቅ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይታወቃል። በዚህ የጉባዔ ሂደት የሚያከናውነው የፓርቲው የከፍተኛ አመራሮች ምርጫ አንዱ ነው። በዚህ የጉባዔ ተመራጮች ላይ በአስመራጭ ኮሚቴው ተመልምለው ለውድድር የቀረቡ ዕጩዎች ለፓርቲያችን አባላትና ለጉባዔ ተሳታፊዎች ራሳቸውን እና የሚሰሩትን ስራ አስተዋውቀው ወደ ምርጫ ሂደቱ ይገባሉ።

እኛ 'ኢዜማን እንደገና!' በሚል መሪ ቃል የተሰባሰብን ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለፓርቲያችን ዘመን ተሻጋሪነት ያስፈልጋሉ የሚሉ ሀሳቦችን ይዘን ቀርበናል።

ከላይ የተጠቀሱትን ሀሳቦች: ጥያቄዎችና ዕጩ አመራሮቻችን በአጭሩ የሚገልፅልን የጋራ የቃል ኪዳን ሰነድ በማስፈለጉ ለተከበሩ የኢዜማ አባላትና የጠቅላላ ጉባዔ ተሳታፊዎች ይህንን ሰነድ አቅርበናል።

https://drive.google.com/file/d/1wscQokq5GqXMs6ORl5XiXsPUWuFzDdRn/view?usp=drivesdk

ኢዜማን እንደገና!

ጌታቸው ጳውሎስ - ዕጩ ሊቀመንበር
ኤልሳቤጥ ሉቃስ- ዕጩ ምክትል ሊቀመንበር
ዶ/ር ካሳሁን ደለነ- ዕጩ ዋና ፀሐፊ
የኢዜማ እንደገና ማሻሻያዎች

ኢዜማን እንደገና ለማሻሻል በጠቅላላ ጉባዔው ይሁንታን ካገኘንና ፓርቲያችንን የምናሻሽልበት አጋጣሚው ከተፈጠረ ምን ዓይነት ማሻሻያዎችን ለማድረግ አስበናል? የምናሻሽልበት ምክንያቶቻችን ላይ ከተስማማን ለምን እንደምናሻሽል ከተግባባን በቀጣይ ደግሞ ዋና ዋና ማሻሻያዎቻችን ምንድን ናቸው?

ከምርጫ ክልል ጀምሮ መሠረቱን ያፀና ትልቅ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ በየጊዜው ራሱን እያሻሻለ እስካልሄደ ድርስ ከግብ መድረስ አይቻለውም። ይህን ተከትሎ እኛ በመረጮቻችን በጎ ፍቃድ የፓርቲ ማሻሻያ ስራ እንድንሰራ አደራው ከተሰጠን በቀጣይ

1, ፖለቲካዊ ማሻሻያዎች
2, ድርጅታዊ (መዋቅራዊ) ማሻሻያዎች
3, ተቋማዊ ማሻሻያዎችን እንተገብራለን።

በሦስቱ ዓበይት የማሻሻያ ሀሳቦቻችን ዝርዝር ትንታኔዎችን የምንሰጥ ሲሆን ለአንባቢ በሚጠቅም መልኩ በአጭሩ ለማብራራት እንወዳለን።

1, ፖለቲካዊ ማሻሻያዎቻችን

ኢዜማ በፖለቲካ መስመር ጥራትና ቁርጠኝነት በሰፊው ህዝብ ዘንድ የታመነበት ፓርቲ መሆኑ ይታወቃል። ይህ የጠራ የፖለቲካ አረዳድ እና አቅጣጫ ላይ የተመሰረተ የተሀድሶ አተገባበር ይከተላል። በጥንቃቄ የሚመራ የፖለቲካ ተሀድሶ ዋና መዳረሻው የዜግነት ፖለቲካ እና የማህበራዊ ፍትህ ማስፈን ሲሆን በሀገራዊ ሉዓላዊነት ላይና በዜጎች ደህንነት ላይ የተመረኮዘ ይሆናል። ኢዜማ በተሃድሶ ፕሮግራሙ የውስጠ ፓርቲ ፍትሃዊነትን: ስብጥርንና ዝግጁነትን ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ የአርቆ አሳቢዎች ቡድን (Think Tank) ቡድኖች ጋር በትብብር የሚሰራ: የማህበራዊ ፍትህ ተደራሽነትን በገለልተኝነት የሚከታተል አካል እና የኢትዮጵያን ሰላማዊ የውጭ ግንኙነቶችን የሚደግፍ የተልዕኮ ማዕቀፍ ያስፈልገዋል። ይህን ማድረጉ በቀጣይ ጊዜውን ለሚመጥን የፖሊሲ ዝግጅት ግብዓት ይሆነናል። ኢዜማ ያሉትን ፖሊሲዎችን ለአባላት ከማሳወቁ በፊት ከአሰላሳይ ቡድኖች ጋር በመምከር ለሀገር ያለውን ጠቀሜታ በዝርዝር ለየመዋቅሮቾ እንዲያደርስ እናደርጋለን።

ኢዜማን እንደገና ለማደስ የተሃድሶ ስትራቴጂ ቀርፀን ፓርቲው የነበሩበትን ክፍተቶችን በማስተካከል ለአዲሱ የፖለቲካ ትውልድ መዳራሻ እናደርገዋለን። የጠቅላላ ጉባዔዎች ውሳኔዎቻችን እንደገና በመገምገም ከጊዜውና ከወቅቱ ጋር የሚሄዱትንና ከእኛ የሚጠበቁትን ውሳኔዎቻችን እናስቀጥላለን። በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያሳጡንን ውሳኔዎች ካገኘን የህዝብን ድምፅ በማክበር ውሳኔዎቻችን ዳግም እናጤናቸዋለን።

ፓርቲያችን የመሃል ከተማ ፓርቲ ብቻ እንዳይሆን ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመቅረብ ሰላማዊ ስልጡን ፖለቲካን እናራምዳለን። አባላት ብቻ ሳይሆኑ ደጋፊዎቻችንም በቀጣይ ስትራቴጂካዊ ዕቅዶቻችን ላይ አሻራቸውን እንዲያኖሩ ሁኔታዎችን እናመቻቻለን።

በሀገራችን ከሚገኙ ከተለያዩ አሰላሳይ ቡድኖች ጋር በመተባበር ኢዜማን ከሚገዳደሩ የዘርና የጎሳ ፖለቲካ ትርክቶች የሚያስወጡንን አሰላሳዮችን በማድመጥ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ዴሞክራሲ እንተጋለን።

2, ድርጅታዊ ( መዋቅራዊ) ማሻሻያዎች

የፓርቲያችን ህልውና የሚፀናው ባለን መዋቅራዊ አደረጃጀቶች እንደሆኑ ይታወቃል። የኢዜማ አደረጃጀት ከምርጫ ክልል የሚጀምር እና በተያዩ ደጋፊ: አስተባባሪና አጋዥ መዋቅሮች መደገፋቸው ፓርቲውን የሚያጠነክረው አካሄድ ነው ብለን እናምናለን። ለዚህ የሥራ ዘርፍ ሃላፊነት የሚታጨው አመራር ግን በብስአኮ የሚሾም ከሚሆን በፓርቲያችን የጠቅላላ ጉባዔ ተመራጭ ሆኖ ተወዳድሮ እንዲመረጥ ምክረ ሀሳብ እናቀርባለን። የድርጅት ጉዳይ ዘርፍን የሚመራው አካል የጉባዔ ተመራጭ ሆኖ በምርጫ እንዲሰየም እንጠይቃለን። ይህን የፓርቲያችን የጀርባ አጥንት የሚመራው አካል እንደሌሎች የስራ ክፍሎች በግለሰቦች በጎ ፍቃድ ላይ መወሰኑን አግባብነት የሌለው እንደሆነ እንረዳለን።

ፓርቲያችን በሚያንቀሳቅሳቸው የመዋቅር አደረጃጀቶች በሙሉ የምንስማማበት ሲሆን በተጨማሪነት የሚርጫ ክልሎችንና ለአሰራር እንዲመች ተብለው የተደራጁ የዞን ማስተባበሪያዎችን በቅርበት የሚያግዝ በክልል እና በከተማ አስተዳደሮች የሚንቀሳቀስ ተጨማሪ አጋዥ ጽ/ቤቶችን በመክፈት በቅርበት የምናግዝበት መንገድ እንፈጥራለን። ይህን በማድረግ በቀጣይ ለሚከናወነው ሀገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ ብቡ አጋዥ መዋቅር እናደራጃለን።

የአዳዲስ አባላት ምልመላና ጥሪ ግብዣን በቋሚነት በየመንፈቅ ዓመቱ በየመዋቅሩ በዘመቻ መልክ እንዲሰራ እናደርጋለን። ጠቅላላ ጉባዔው ለሚቀጥሉት ጊዜያት በትጋት እንድናገለግለው ይሁንታ ከሰጠን በአባልነት መስፈርቶች ላይ ማሻሻያ እናደርጋለን። ለአብነት ያኽል ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ካለባቸው የፋይናንስ እጥረት በመነሳት በየምርጫ ክልላቸው ከሌሎች አባላት በግማሽ ያነሰ የአባልነት መዋጮ እንዲከፍሉ በማድረግ የወጣቶችን ተሳትፎ እናበረታታለን። ይህ ኢዜማ በአዲሱ ትውልድ ላይ ለሚሰራው የፖለቲካ ስራ አመቺ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አኳያ እንተገብረዋለን።

ዓለም ከደረሰበት የቴክኖሎጂ ለውጥ አብዛኛው የሰው ልጅ ህልውና በዲጂታል ስርዓት የታገዘ በመሆኑ እኛ ከተመረጥን 'ዲጂታል ኢዜማ' የሚል ፕሮግራም በመቅረፅ ሰፊዎን መራጭ ህዝብ በስነ ዜጋ: በምርጫ: በዴሞክራሲ: በመብቶችና ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲ ስራዎች ላይ በተከታታይ የሚሰራ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ንቅናቄ በፓርቲ ደረጃ እንተገብራለን። የፓርቲው ድረ ገፅ በቀላሉ ከማሰራት በተጨማሪም አባላት በቀጥታ ስለፓርቲያቸው ሙሉ መረጃ የሚያገኙበትን መንገድ እንፈጥራለን። የሞባይል መተግበሪያዎችን በማሰራት የአባልነት ጋር ተያይዞ የሚሰሩ ማናቸውም ነገሮች በዲጂታል ኢዜማ ክፍል እንዲሰራ እናስደርጋለን። በፓርቲያችን ዋና ጽ/ቤት የመረጃ ማከማቻ ቋት Cloud Archive ወደ ስራ በማስገባት ከወረቀት ንክኪ ነፃ የሆነ አገልግሎት እንዲሰጥ እናደርጋለን።

3, ተቋማዊ ማሻሻያዎች

ፓርቲያችን እስካሁን የመጣበትን ተቋማዊ ቅርፅ የበለጠ ጉልህና የሚታይ ለማድረግ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን ማድረግ ተገቢ ነው ብለን እናምናለን። ለዚህ እንዲረዳ ተቋሙ በዋና ቢሮ ያሉትን የመምሪያ እና የስራ ክፍሎችን አዲስ በምናዋቅረው አጋዥ የክልሎችና የከተማ አስተዳድሮች ጽ/ቤቶች እናስፋፋለን። እነዚህ የጎንዮሽ ትዪዩ መምሪያዎች ወደ አጋዥ ቅርንጫፍ መዋቅሮቻችን የሚተባበሩበትንና በትስስር የሚሰሩበትን መመሪያዎችን የፓርቲያችን የህገ ደንብ ተርጓሚና አስፈፃሚ ኮሚቴ ካፀደቀልን ወደ ተግባር እንገባለን።

የሚደራጁ ጽ/ቤቶች ተቋሚ ይዘታቸውን ሳይለቁ ፈጣን ተደራሽ የመረጃ መለዋወጫ መስመር በመዘርጋት በየመዋቅሩ የሚደረጉ ፖለቲካዊ ተሳትፎአችን እናጠናክራል። በየደረጃው ያሉ መመሪያዎች: ደንቦና አሠራሮችን እጅግ ፈጣንና ለስራ ምቹ በሚሆኑ መልኩ ማሻሻያ እናስደርግባቸዋለን።

ኢዜማ እስከዛሬ ድረስ የፓርቲውን ፋይናንስ ስራ ከሌሎች አቻ ፓርቲዎች በተሻለ ሁኔታ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን የኢዜማ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር (Treasurer) በሁለት የተከፈለ ስራ ሲኖረው የፋይናንስ እና የንብረት አስተዳደር ክፍሎች ብቻ ናቸው። ይህ በሁለት ዘርፎች የተከፈለውን አሰራር በነበረበት በባለሙያ ብቻ እንዲመራ በማድረግ መምሪያውን ከፖለቲካ ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ የባለሙያ ስራ እናደርገዋለን። ከዚህ ጋር በተቀራረበ ሁኔታ አብሮት የሚሰራ 'የሀብት አሰባሳቢ መምሪያ' ራሱን ችሎ እንዲደራጅና እንደሌሎች የሥራ ክፍሎች የሙሉ ጊዜ ስራው የኢዜማን ገቢ የማሳደግና ሀብት የማሰባሰብ ስራን የሚሰራ ራሱን የቻለ መምሪያ እንዲኖር እንሰራለን።
የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ሃላፊን ከፖለቲካ አመራርነት ይልቅ በብቁ ባለሙያዎች እንዲመሩት እናስደርጋለን። የፋይናንስ ሃላፊውም ከጉባዔ ተመራጭነታቸው ይልቅ በሙያ ታምኖባቸው በግልፅ የማስታወቅያ የሚቀጠሩ የዘርፉ ሀላፊ እንዲኖሩት የጠቅላላ ጉባዔውን እንጠይቃለን።

ኢዜማን እንደገና!

ጌታቸው ጳውሎስ-ዕጩ ሊቀመንበር
ኤልሳቤጥ ሉቃስ-ዕጩ ምክትል ሊቀመንበር
ዶ/ር ካሣሁን ደለነ-ዕጩ ዋና ፀሐፊ

የቃል ኪዳን ሰነዳችን ሙሉውን ለማንበብ ከታች በተቀመጠው የቴሌግራም መስፈንጠሪያ በመግባት ማገኘት ይችላሉ።

https://www.tgoop.com/ethzema/4751

https://drive.google.com/file/d/1wscQokq5GqXMs6ORl5XiXsPUWuFzDdRn/view?usp=drivesdk
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ኢዜማ ን በልኩ ከተሠጡ የድጋፍ ድምፆች በጥቂቱ ይመልከቱ።
ሐ/ ደረጀውን የጠበቀ የጎንዮሽ ትስስር ከተለያዩ መምሪያዎች ጋር እፈጥራለሁ። ለአብነት ያኽል የህዝብ ግንኙነት መምሪያ: የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር መምሪያ: የወጣቶች ሴቶችና አካል ጉዳተኞች መምሪያ: የሙያና የሠራተኛ ማህበራት መምሪያዎችና ሌሎች መምሪያዎች ጋር የጠበቀ የሥራ ግንኙነት በማድረግ ለትጋት እታትራለሁ

መ/ በዋና ቢሯችን የዲጂታል መረጃ አርካይቭ በማደራጀት ከዚህ በኋላ ያሉ ማንኛውም የኢዜማ ስራዎችን በዲጂታል መልኩ እንዲቀመጥና በተፈለገ ሰዓት አገልግሎት ላይ እንዲውል አደርጋለሁ።

ሠ/ በየሩብ ዓመቱ የጽ/ቤት ስራዎችን ምዘና ለብስአኮ እና ለአባላት ይፋ በማድረግ ግልፀኝነትን አሰፍናለው።

ረ/ በክልል ደረጃ ለሚደራጁ አጋዥ ጽ/ቤቶች የተሟላ ቁሳቁስ እንዲኖር ከረድዔት ድርጅቶችን ረጂ ግለሰቦች ጋር በመነጋገር ሁሉም የኢዜማ መዋቅር አጋዥ ጽ/ቤቶች የቢሮ ቁሳቁስ እንዲሟላ እሰራለሁ።

ሰ/ አዲስ ለምናዋቅራቸው የክልል አጋዥ ጽ/ቤቶች ድጋፍ የሚውሉ 'መቶ ብር ለፍትህ!' የሚል ዘመቻ በማስተባበር በየአካባቢው ከሚገኙ አባላት እና ደጋፊዎች ጋር የገቢ ማሰባሰቢያ በማድረግ ጽ/ቤቶቹ እንዲጠናከሩ እሰራለሁ!

ሸ/ የፓርቲያችን የሆሉም ጽ/ቤት ፀሐፊዎች በየ4 ወሩ በኢዜማ አካዳሚ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እንዲወስዱና ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲጨብጡ እሰራለሁ።

የተከበራችሁ የኢዜማ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ተሳታፊዎች

ከላይ በመግቢያዬ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ይህ የእኔ ህልም ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢዜማዊ የጋራ ራዕይ ነውና ይህን ዕቅዳችን ለመተግበርና አተገባበሩን ለመከታተል በጉባዔው ዕለት በሚደረገው የዋና ፀሐፊነት ቦታ ላይ እንድትመርጡኝ ስል በታላቅ ትህትና እጠይቃችኋለሁ!

ኢዜማን እንደገና!

ዶ/ር ካሣሁን ደለነ
ዕጩ ዋና ፀሐፊ

የቃል ኪዳን ሰነዱን ለማገኘት

https://www.tgoop.com/ethzema/4751

https://drive.google.com/file/d/1wscQokq5GqXMs6ORl5XiXsPUWuFzDdRn/view?usp=drivesdk
2025/07/11 22:56:00
Back to Top
HTML Embed Code: