Telegram Web
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ኢዜማ መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በዝክረ ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ መርኃግብር ላይ የነበራቸውን ወዳጅነት እንዲህ አስታውሰዋል፤ እንዲሁም በዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ አጭር የሕይወት ታሪካቸው ቀርቧል።
የውይይት መድረክ


የመወያያ ርዕስ: አሁናዊ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት በኢትዮጵያ

የመነሻ ሐሣብ አቅራቢ: ዶ/ር ዳዊት በለው (የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) ፖሊሲ ጥናት እና ምርምር መምሪያ ኃላፊ)

ቀን: ቅዳሜ የካቲት 01/2017 ዓ.ም.

ሰዓት: 8:00 ሰዓት

ለሁሉም ዜጋ ክፍት የሆነ መድረክ
የመርኃግብር ማስታወሻ!!

የውይይት መድረክ


የመወያያ ርዕስ: አሁናዊ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት በኢትዮጵያ

የመነሻ ሐሣብ አቅራቢ: ዶ/ር ዳዊት በለው (የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ( #ኢዜማ ) ፖሊሲ ጥናት እና ምርምር መምሪያ ኃላፊ)

ቀን: ነገ ቅዳሜ የካቲት 01/2017 ዓ.ም.

ሰዓት: 8:00 ሰዓት

ለሁሉም ዜጋ ክፍት የሆነ መድረክ
የመርኃግብር ማስታወሻ!!

የውይይት መድረክ

የመወያያ ርዕስ: አሁናዊ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት በኢትዮጵያ

የመነሻ ሐሣብ አቅራቢ: ዶ/ር ዳዊት በለው (የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ( #ኢዜማ ) ፖሊሲ ጥናት እና ምርምር መምሪያ ኃላፊ)

ቀን: ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 01/2017 ዓ.ም.

ሰዓት: 8:00 ሰዓት

ለሁሉም ዜጋ ክፍት የሆነ መድረክ
የዜጎች ልሳን



#ኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የምትዘጋጀው የዜጎች ልሳን መጽሔት ቅጽ 02_ቁ: 010 የወሩን እንግዳ ጨምሮ  በዚህ ዕትም

👉 የኑሮ ውድነቱን እያባባሰ ያለው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ

👉 ብልጽግና ፓርቲ እና ሰሞነኛው ጠቅላላ ጉባኤው

👉 አወዛጋቢው የንብረት ማስመለስ አዋጅ ያስከተለው ስጋት የሚሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ታስነብበናለች

ማስፈንጠሪያውን በመጫን ሙሉውን ይዘት ያንብቡ።

https://drive.google.com/file/d/1HArivJ-5f8No7lqUzyKO5jPSM3ZKyEKN/view?usp=drivesdk

#ኢዜማ
#የዜጎች_ልሳን
#የማኅበረሰብ_አስተያየት


የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) ሀገራዊ ምክክሩን በተመለከተ #የማኅበረሰብ_አስተያየትን እየሰበሰበ ይገኛል፤ በመሆኑም ከታች ያለውን ማስፈንጠርያ በመጫን አስተያየትዎን ይስጡን።

መጠይቁን ከዛሬ የካቲት 07/2017 ዓ.ም. እስከ የካቲት 17/2017 ዓ.ም. ባለው ጊዜ መሙላት እንደሚቻል እያሣወቅን ስለሚደረግልን ትብብር ሁሉ ከወዲሁ እናመሠግናለን።

https://ee.kobotoolbox.org/x/WlMMRUv5
የኢትዮያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የየካቲት 12 ሰማዕታት በተገቢው መልኩ መዘከር አለባቸው ብሎ ያምናል።

#ኢዜማ በዘመናት ለሀገራችን የተከፈለውን ውድ ዋጋ ያከብራል፤ ይዘክርማል!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ
የካቲት 12/2017
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) ሀገራዊ ምክክሩን በተመለከተ #የማኅበረሰብ_አስተያየትን እየሰበሰበ ይገኛል፤ በመሆኑም ከታች ያለውን ማስፈንጠርያ በመጫን አስተያየትዎን ይስጡን።

መጠይቁን እስከ የካቲት 17/2017 ዓ.ም. ባለው ጊዜ መሙላት እንደሚቻል እያሣወቅን ስለሚደረግልን ትብብር ሁሉ ከወዲሁ እናመሠግናለን።

https://ee.kobotoolbox.org/x/WlMMRUv5
ፍትሐዊ ሽግግርን ማጠናከር ለተረጋጋ ቀጣይነት (Strengthening a Just Transition for a Sustainable Future)


ዛሬ በዓለምአቀፍ ደረጃ የሚከበረው የማኅበራዊ ፍትሕ ቀን "ፍትሐዊ ሽግግርን ማጠናከር ለተረጋጋ ቀጣይነት" (Strengthening a Just Transition for a Sustainable Future) በሚል ጭብጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል።

ዓለም ባለፉት ዓመታት በተለያየ መስክ ዕያሣየቻቸው ያሉ ለውጦች እና እያጋጠሟት ያሉ ችግሮች መነሻ በማድረግ ትኩረት እንዲሠጥበት ታላሚ ያደረገ ጭብጥ ነው።

ለውጦች ከሚባሉት መካከል፤ ዓለም ከከርሰ ምድር የነዳጅ ኃይል ተጠቃሚነት ወደ አረንጓዴ ኃይል ተጠቃሚነት እያደረገች ያለው ሽግግር እና ዓለም በቴክኖሎጂው ረገድ እንደ የሰው ሰራሽ ልኅቀት (AI) ላይ ዕያሳየችው ያለው እድገት ተጠቃሽ ሲሆኑ እንደ ችግር የሚነሱት ደግሞ ዓለም የገጠማት ያልተረጋጋ የምጣኔ ሀብት ሁኔታና ይህንን ተከትሎ የተፈጠረ የምጣኔ ሀብት ኢ-ፍትሐዊነት ያመጣው የማኅበረሰብ አለመረጋጋት፣ አመፃ እና የአየር ንብረት ለውጥ ሲሆን በተጨማሪም ይህንን ተከትሎ የመጣ ፍልሰት እና መፈናቀል በዚህ ውስጥ ይካተታሉ።

እነኚህ ለውጦች እና ችግሮች ይዘው ሊመጡ የሚችሉትን አሉታዊ ውጤቶችን ቀደሞ በማሰብ በማኅበራዊ ፍትሕ እሳቤ አርቆ መግዛት ካልተቻለ ዓለም ለከፍተኛ አደጋ እየተጋለጠች መሄዷ እንደሚቀጥል መረጃዎች ያሣያሉ።

ሀገራችንም ከዓለም የተነጠለች እንዳለመሆኗ እና በተጨባጭም ካለችበት የማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብት (በተለይም የቴክኖሎጂ እድገት)፣ ፖለቲካዊ እና የሰላምና ደኽንነት እድገት እና ሁነት አንፃር ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች አሳሳቢነት ደረጃ የሚለያይ ሲሆን ነገር ግን ወደፊትን አስቦ የሚደረግ ተገቢ ዝግጅት እንደሚያስፈልግ አያጠራጥርም።

ለአብነትም ኢትዮጵያ እየገጠማት ያለው የምጣኔ ሀብት አለመረጋጋት ካለባት የብድር ጫና ጋር ተዳምሮ ለማኅበረሰብ የሚሠጡ አገልግሎቶች እና መሠረተ ልማቶች ላይ የበጀት ፈሰስ ለማድረግ መንግሥት ላይ እክል የሚፈጥር በመሆኑ የኑሮ ውድነትን በመጨመር እና የብር የመግዛት አቅም በመቀነስ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ከባድ አድርጎታል። 

በእርግጥ መንግሥት ከአበዳሪ ተቋማት ጋር የብድር ማሸጋሸግ ሥምምነት ሙከራ ቢያደርግም የወሰዳቸው የወጪ ቅነሣ እርምጃዎች ለማኅበረሰቡ ሊውሉ የሚችሉ አገልግሎት እና ሊሟሉ የሚገባቸው መሠረተ ልማቶችን በመገደብ እንዲሁም ተደራራቢ ግብር በመጣል ገቢ ለመሰብሰብ ላይ ትኩረት ማድረጉ ለዘላቂ ልማት እንቅፋት ከመሆኑ ባሻገር ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች ላይ ሕይወትን የበለጠ ከባድ ያደርጋል። 

#ኢዜማ ይህንን ችግር ለመፍታት የምጣኔ ሀብት ማሻሻያዎች ለማኀበራዊ ፍትሕ ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው ያምናል በዚህም መሠረት ከላይ ለተጠቀሰው ችግር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች የእዳ ቀውሶችን እንዳይሸከሙ ማድረግ ያሻል ብሎ ያምናል፤ ሌሎች ተመሣሣይ ለውጦችና ችግሮችም እንደየሁኔታቸው በተመሣሣይ የምላሽ ማዕቀፍ ውስጥ ፍትሐዊ ሽግግርን የተረጋጋ ቀጣይነት ባረጋገጠ መልኩ መፍትሔ ሊሠጣቸው ይገባል ብሎ ያምናል።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) ሀገራዊ ምክክሩን በተመለከተ #የማኅበረሰብ_አስተያየትን እየሰበሰበ ይገኛል፤ በመሆኑም ከታች ያለውን ማስፈንጠርያ (Link) በመጫን አስተያየትዎን ይስጡን።

መጠይቁን እስከ የካቲት 17/2017 ዓ.ም. ባለው ጊዜ መሙላት እንደሚቻል እያሣወቅን ስለሚደረግልን ትብብር ሁሉ ከወዲሁ እናመሠግናለን።

https://ee.kobotoolbox.org/x/WlMMRUv5
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) ሀገራዊ ምክክሩን በተመለከተ #የማኅበረሰብ_አስተያየትን እየሰበሰበ ይገኛል፤ በመሆኑም ከታች ያለውን ማስፈንጠርያ በመጫን አስተያየትዎን ይስጡን።

መጠይቁን እስከ የካቲት 17/2017 ዓ.ም. ባለው ጊዜ መሙላት እንደሚቻል እያሣወቅን ስለሚደረግልን ትብብር ሁሉ ከወዲሁ እናመሠግናለን።

https://ee.kobotoolbox.org/x/WlMMRUv5
#የማኅበረሰብ_አስተያየት

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) ሀገራዊ ምክክሩን በተመለከተ #የማኅበረሰብ_አስተያየትን እየሰበሰበ ይገኛል፤ በመሆኑም ከታች ያለውን ማስፈንጠርያ በመጫን አስተያየትዎን ይስጡን። 

መጠይቁ ዛሬ የካቲት 17/2017 ዓ.ም.  የሚያበቃበት ቀን ሲሆን ባለው ጥቂት ጊዜ መጠይቁን በመሙላት ትብብር እንዲያደርጉልን እየጠየቅን ስለሚደረግልን ትብብር ሁሉ  ከወዲሁ እናመሠግናለን።

https://ee.kobotoolbox.org/x/WlMMRUv5
በሕግ መጠየቅ ያለበት የትኛውም ዜጋ በሕግ ሊጠየቅ የሚገባው ሕጋዊ በሆነ መንገድ ብቻ ነው!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ባለፉት ጥቂት ቀናት በአዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ወጣቶች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እየታፈኑ የት እንደገቡ ሳይታወቅ መሰወራቸውን ከቤተሰቦቻቸው እና ከተለያዩ አካላት ለመገንዘብ ችለናል።

ይኽን የመንግሥት ተግባር ይበልጥ አስከፊ የሚያደርገው እነዚህ ታፍነው የተወሰዱ ወጣቶች የት እንደሚገኙ አለመታወቅና ቤተሰቦቻቸውም በመንግሥት አካል የተያዘ ግለሰብ ሊገኙባቸው ይችላሉ የሚሏቸውን ቦታዎች ቢያስሱም ለማግኘት አለመቻላቸው ነው። በተጨማሪም አንዳንዶቹ ከተወሰኑ ቀናት መሰወር በኋላ በድንገት የት እንደነበሩ እንኳ መናገር በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ወደቤታቸው መመለሳቸው ነው።

ይሕ ሕጋዊ መንገድን ያልተከተለ የመንግሥትን ተግባር በሕግ ተጠያቂ መሆን ያለበትን አካል በቁጥጥር ሥር ማዋል ሳይሆን በወንበዴ የሚፈፀም አይነት አፈና እንደሆነ እና ይኽም ሕዝብን ለማስተዳደር ሥልጣን ላይ ካለ አካል የማይጠበቅ አስፀያፊ ተግባር መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

አሁንም በዚህ አይነት አፈና ውስጥ ያሉ ወጣቶች እንዳሉ ፓርቲያችን ያረጋገጠ ሲሆን ቤተሰቦቻቸውም በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንዳሉ ለማወቅ ችለናል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 4 ማንኛውም ዜጋ፣ የመንግሥት አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማኅበራት እንዲሁም ባለሥልጣኖቻቸው ሕገመንግሥቱን እንዲሁም ኢትዮጵያ ላፀደቀቻቸው ሥምምነቶች ተገዢ መሆን እንዳለባቸው ቢገልጽም የመንግሥት ተግባር ግን ሀገራችን ያወጣቻቸውን ሕጎች እንዲሁም አባል የሆነችባቸውን ሥምምነቶች የሚጥስ ሆኖ እናገኘዋለን፤ ለአብነትም፡

1) የኢፌዴሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 17 ንዑስ 2 ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጪ ሊያዝ ክስ ሳይቀርብበት ወይም ሳይፈረድበት ሊታሰር አይችልም፤ 

2) የኢፌዴሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 19 ወንጀል ፈጽማችኋል በመባል የተያዙ ሰዎች የቀረበባቸውን ክስና ዝርዝር ወዲያውኑ ማወቅ፣ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍ/ቤት የመቅረብ፣ የያዛቸው የሕግ አስከባሪ በዚህ የጊዜ ገደብ ምክንያቱን ካላስረዳ ፍ/ቤት የአካል ነፃነታቸው እንዲያስከብርላቸው የመጠየቅ እና በመረጡት የሕግ ጠበቃ የመወከል መብት እንዳላቸው፤

3) ከላይ የተጠቀሱትን የሕገመንግሥት ሕግጋት ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው ዓለምአቀፍ ሥምምነቶች የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃና ዓለምአቀፍ የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ቃልኪዳን ሥምምነት አንቀጽ 9፣ የአፍሪካ ሕብረት ሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ አንቀጽ 6 ቢያትቱም መንግሥት ከላይ እንደተገለጸው ከእነዚህ ሕጎች እና ሥምምነቶች በሚጣረስ መልኩ ሲንቀሳቀስ ይስተዋላል።

በመሆኑም፤

1) መንግሥት አፍኖ የያዛቸውን ወጣቶች የት እንደሚገኙ ይፋ እንዲያደርግ

2) አፍኗቸው ያሉ ወጣቶች የወንጀል ተጠያቂነት አለባቸው ካለ ክሱን በግልጽ መሥርቶ እራሣቸውን የመከላከል መብታቸው እንዲያከብር አልያም በቶሎ እንዲፈታቸው

3) ያፈናቸውን ወጣቶች ቤተሰብ እንዲጎበኛቸው፣ የሕግ ጠበቃ እንዲቀርብላቸው እና አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላቸው

4) ሕገወጥ ተግባሩን የፈፀሙ የመንግሥት አካላትን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት አካላትን በማሳተፍ ተጠያቂነት እና የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን እንዲያደርግ እንጠይቃለን።

ይህን አለማድረግ ግን ሥርዓት አልበኝነትን መጋበዝ፣ ለሕገወጥ ተግባራት ሽፋን መስጠት ብሎም ድጋፍ በማድረግ ቡራኬ እንደመስጠት የምንቆጥረው መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

ከላይ የተዘረዘሩት እንዳሉ ሆኖ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጉዳዩን ተመልክቶ የሚመለከተውን አካል ተጠያቂ እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን።

ኢዜማ ይህን የመሰሉ የማናለብኝነት ሕገወጥ ተግባራትን አምርሮ የሚያወግዛቸው መሆኑን እያሳወቅን፤ አምርረን የምንታገለው መሆኑንም ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ( #ኢዜማ )
የካቲት 18/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ
የእናት የአባቶቻችንን ድል የብሔር ሸማ ለማልበስ መድከም መሥዋዕትነታቸውን ማሳነስ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል!

ኢትዮጵያ ሀገራችን በሕዝቧ መሥዋዕትነት ኢትዮጵያዊ ማንነቱን አስጠብቀው፣ ነፃነቱን አጽንተው ወደ ትውልድ ያስተላለፉ እናትና አባቶች ልጆች መሆናችንን እያሰብን የዛሬን ድል ማክበር ትልቅ ኩራት ነው።

የዚህ ድል ምንነት ሲገለጥ ድሉ ከሀገራችንም ተሻግሮ ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሰማነው ነው፡፡ ይህ እውነት ሆኖ ዝንት ዓለም የሚኖር መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህን ድል ስናከብር ልናስታውሰው የሚገባው በዚህ ድል ቀደምት እናት አባቶቻችን ያስተላለፉልንን አንድነት፣ እኩልነት ነፃነት እና ሉዓላዊነት የሚባሉ አዕማዳትን ነው።

እነኚህ በከፍተኛ ተጋድሎ የተሻገሩልን መሠረታዊ ሐሣቦች አሁን ላይ ምን ያህል እንደ ዕሴት አቆይተናቸዋል የሚለውን ቆም ብሎ አስቦ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል።

ከዚህ አዕማድ አንፃር ሀገራችን የተከፈለው መሥዋዕትነት ለበለጠ አንድነት መሠረት የሚሆን ሆኖ ሳለ አሁን ላይ የዘውጌ ማንነት ላይ በተንጠለጠለ ፖለቲካ ሳቢያ መሠረቱ እየተነቀነቀ መሆኑን ስናስተውል በመሥዋዕትነት የተገኘ ድል ብለን ከምንገልጽባቸው ምክንያቶች አንዱን ጥያቄ ውስጥ እንዳለ ማሰብም ብሎም መፍትሔ መፈለግም ይኖርብናል፡፡

ሌላው መሠረታዊ ሐሣብ እኩልነት ሲሆን የሰው ልጅ የተለያየ ማንነት መገለጫ የሆኑት እንደ ቀለም ያሉት የእኩልነት መመዘኛ መስፈርቶች ልክ እንዳልሆኑ በማሣየት ረገድ ይህ ድል ትልቅ ነፀብራቅ ቢሆንም ሀገራችን ባለፉት ዓመታት ይህንን ማጽናት በማይችል የዘውጌ ማንነት ላይ በተንጠለጠለ ፖለቲካ ውስጥ በመውደቋ ለተለያዩ ዕድሎች እኩል መጫወቻ ሜዳ ከሚሠጥ ሥርዓት ውጪ ሆና ስናገኛት መልስ ልንፈልግለት እንደሚገባ ማሠብ አለብን።

በተጨማሪም ማሰብ ያለብን ስለ ነፃነት ሲሆን በተለይ ሀገራችን ዜጎቿ በማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳይ ተደራጅተው ለመንቀሳቀስ አስቻይ ያልሆኑ አምባገነናዊ ሥርዓት በተደጋጋሚ መዘወር እንዲሁም ከዚህ አምባገነናዊ ሥርዓት ላይ የዘውጌ ማንነት ላይ የተንጠጠለ ፖለቲካ ተደምሮበት ስንት መሥዋዕትነት በተከፈለባት ሀገር ላይ በነፃነት መዘዋወር አለመቻላችን ስናይ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ የሚለውን እንድናስብ ያስገድደናል።

ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች እና ሌሎች ጉዳዮች ተዳምረው ዝቅተኛ የምጣኔ ሀብት ደረጃ ላይ የምትገኝ ሀገር መሆኗ እና ዜጎቿ በድህነት አረንቋ ውስጥ መገኘት ሉዓላዊነቷን የምታመቻምችበት (compromise) ኢትዮጵያ መሆኗንም ሳይዘነጉ ምላሽ ይፈልጋል።

ለዚህ ደግሞ ሁላችንም ተጠያቂ መሆናችንን በመረዳት ከውይይት የተነሣ መፍትሔ ላይ ያተኮረ ተግባርን በመከተል የራሣችንን ዓድዋ እናሣካ ስንል ጥሪ እያስተላለፍን፤ በዓሉ ሲከበር የእናት የአባቶቻችንን ድል የብሔር ሸማ ለማልበስ መድከም መሥዋዕትነታቸውን ማሳነስ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል!

ድሉም ልዩነታችንን በማጉላት ሳይሆን አንድነታችንን በሚመጥን መልኩ መከበር አለበት እንላለን፡፡ በተጨማሪም በዓሉ በሀገር መከላከያ ኃላፊነት መከበሩ መልካም ሆኖ በዚያው ልክም ሕዝቡ በአደባባይ በነፃነት ተሳትፎ የሚያከብረው የድል በዓል ይሁን እንላለን፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ)
የካቲት 23/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ
ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሰጠ መግለጫ


የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ከተማ ከየካቲት 22 እስከ የካቲት 24/ 2017 ዓ.ም. ሲያደርግ የነበረው ስብሰባ በድርጅቱ አሠራር ሒደት እና ወቅታዊ ሀገራዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በቀጣይ ስለሚኖሩ ድርጅታዊ ተግባራት ላይ ተወያይቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡

1) ድርጅታዊ ጉዳዮች፤

1.1) የፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ: በኢዜማ መተዳደርያ ደንብ መሠረት ጠቅላላ ጉባኤ የፓርቲው ከፍተኛ የሥልጣን አካል ሲሆን የሥልጣን ዘመኑም 3 ዓመት መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ይህ ጉባኤ የሥልጣን ዘመኑ ሊገባደድ ጥቂት ወራት የቀረው መሆኑን ከግንዛቤ በመውሰድ ሥራ አስፈጻሚው በድርጅታዊ መተዳደሪያ ደንቡ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ መሠረት ጉባኤውን ለማካሄድ ወደ ዝግጅት እንዲገባ ውሳኔ አስተላልፏል።

1.2) የፓርቲ መዋቅሮችን ማጠናከር፡ ሰኔ 2013 ዓ.ም. ከተካሔደው 6ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ወዲህ ባሉት ጊዜያት በፍጥነት ተለዋዋጭ የሆነው የቀጠናው እና የሀገሪቱ ፖለቲካ እና የጸጥታ ችግር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ተዳምረው ባለፉት ዓመታት የድርጅታችንን መዋቅሮች እና አባላት የታለመለትን ያህል የፖለቲካ ተሳትፏቸውን ለማሳደግ ተግዳሮት ገጥሞን ቆይቷል። በመሆኑም ይህንን ችግር በሚያርቅ መልኩ ከፍ ያለ ትኩረት የሚሰጠው የድርጅት መዋቅር ግንባታ ሥራ አጠናክሮ መቀጠል ይደር የሚባል ተግባር እንዳልሆነ በመገንዘብ በዲጂታል ሥርዓት ማጠናከርን ጨምሮ ዘመኑ በሚፈቅደው ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ወስኗል።

1.3) የኢዜማ አካዳሚ እና ተከታታይ አቅም ማጎልበቻ ውይይቶች፡ ኢዜማ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ተቀዳሚ ተግባር ማኅበረሰብን ወደተሻለ ቦታ የሚያደርስ የጠራ አስተሳሰብ መያዝ፣ ይህን አስተሳሰብ መሬት ላይ ማውረድ የሚችል ዘመን ተሻጋሪ ድርጅታዊ መዋቅር መገንባት እንዲሁም በየጊዜው ተለዋዋጭ የሆኑ ሀገራዊም ሆነ ዓለም አቀፋዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን ስልታዊ በሆኑ ዘላቂ ግብ ላይ ተመስርተው እየተነተኑ ውሳኔዎችን ማሳለፍ የሚችሉ አመራሮችን ማፍራት መቻል ትክክለኛ የሆነው መንገድ ከመሆኑም ባሻገር ዘላቂ የሆነ የሕዝብ ይሁንታን ያስገኛል ብሎ የሚያምን ፓርቲ ነው። ይህንን ሕልም በሀገራችን እውን ማድረግ ግን እንደሚታሰበው ቀላል የሚባል እንዳልሆነ በቅጡ ይረዳል፤ ረዥም ጊዜ እንደሚያስፈልገውም ይገነዘባል፡፡ በተለይ ልኂቃን የሚባሉት የሀገሪቱ ዜጎች በፖለቲካው ላይ ትርጉም ያለው ተሳትፎ ለማድረግ ያላቸው ተነሳሽነት ደካማ መሆን እና በሀገራችን ታሪክ ውስጥ ሥልጣን በሃሳብ የበላይነት ሳይሆን በጡንቻ መፈርጠም ላይ የተመሠረተ መሆኑን የተቀበለ የአስተሳሰብ ውቅር የበላይነት መያዙ ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ፖለቲካ ላይ የዳር ተመልካች እንዲሆኑ ከመግፋቱም በላይ አምባገነን የሆኑ ሥርዓቶችም በሥልጣን ኮረቻ ላይ ተፈናጥጠው ለመቆየት ምቹ ሁኔታ አድረገው እንዲወስዱት አድርጓል።

ይህንን አስተሳሰብም ሆነ አሠራር በሂደት ሊያርቅ በሚችል መልኩ የፖለቲካ አመራሮችን ማብቃት እንደ ተቀዳሚ ሥራ መውሰድ ይገባል። በዚህ ረገድ ኢዜማ አባላቱንም ሆነ ፍላጎቱ ያላቸውን ሀገር ወዳድ ዜጎች ለማሰልጠን ዝግጁ የሆነ አካዳሚ ገንብቶ መጨረሱን ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ሠልጣኞችን ወደ አካዳሚው ለማስገባት ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተመዘገቡ አባላት በመመልመል ላይ ይገኛል። ከአካዳሚው ዘላቂ የአቅም ግንባታ ሥራ ጎን ለጎን ከዚህ ቀደም ሲያደርገው ከነበረው የፖለቲካ ውይይቶች በተለየ ትኩረት ለአመራርነት እና ለጠራ ግንዛቤ አስተዋጽኦ ባላቸው የተመረጡ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ተከታታይ የውይይት መድረኮች በተለያዩ አማራጮች እንዲካሄድ ወስኗል።

2) ሀገራዊ ጉዳዮች

2.1) ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ፡ በውይይቱ በልዩ ትኩረት ከታዩት አጀንዳዎች መካከል ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ አንዱ ሲሆን ውስጣዊ የጸጥታ ችግሮች፣ የኑሮ ውድነት እና ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮችን በየፈርጁ ተመልክቶ አሁናዊ ሀገራዊ ፖለቲካችን ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ ሁኔታ እየተለወጠ መምጣቱን ፓርቲው ተገንዝቧል። ከ2010 ዓ.ም. ለውጥ በኋላም ቢሆን በዘውግ ማንነት ላይ የተመሰረተው የፖለቲካ ሂደት የሀገራችንን እድገት እና ዴሞክራሲ ወደኋላ በማስቀረት ዛሬም እልባት ስላላገኘ ለዜጎቻችን መፈናቀል፣ ሞት እና ሰላም ማጣት መንስኤ መሆኑን ቀጥሏል፡፡ በእንደዚህ አይነት ሃገራዊ ሁኔታና በሚለዋወጡ ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ምክንያት ሀገር ወዴት እየሄደች ነው የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ባለመቻሉ ህዝባችን በከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ መሆኑን እና ማህበረሰባችንን ከዚህ ግራ መጋባት በማውጣት ሁሉም ዜጋ በእኩልነት የሚኖርባትን ሀገር ለመፍጠር የሚያስችል የፖለቲካ ስርዓት ለመዘርጋት ይቻል ዘንድ ፓርቲያችን ይህን ተለዋዋጭ የሆነ የፖለቲካ ሥርዓት በተረዳ መልኩ ለህዝቡ ጠንካራ የፖለቲካ አማራጭ ሆኖ ሊሰራ እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ወቅቱን የሚመጥን የፖለቲካ አስተሳሰብ እና አሠራር ማስፈን ይረዳ ዘንድ የአጭር እና የረዥም ጊዜ ተግባራት የለየ ሲሆን ይህንንም አስመልክቶ በቅርቡ የተብራራ ሰነድ ይፋ እንደሚያደረግ ያሳውቃል።

ፓርቲያችን ኢዜማ ከድርጅታዊ መርኆዎቹ ቀዳሚው የሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ሁሌም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል። የፖለቲካ ፓርቲ (የቡድኖች) ጥቅም ከሀገር በታች የሆነ ፍላጎት መሆኑን በመገንዘብ የሀገርን ጥቅም ጉዳይ በምንም መልኩ በሁለተኛ ደረጃ የሚያየው እንዳልሆነ ዛሬም በድጋሚ ለማረጋገጥ ይፈልጋል። ላለፉት ሠላሳ ዓመታት በተለይ በዘውግ ማንነት ላይ የተንጠለጠለው የፖለቲካ አስተሳሰብ እና መዋቅር እስካሁን ሀገራዊ አንድነታችን በማላላትም ሆነ ለዘላቂ ሀገራዊ ጥቅማችን ስጋት የሆኑ አያሌ ችግሮችን ያጋለጠን መሆኑ ሳያንስ በዚህ ስሁት አስተሳሰብ የተለከፉ ኃይሎች ከባእዳን ጋር ሳይቀር በመሰለፍ ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ እንቅስቃሴዎቻቸውን በጥንቃቄ እየተከታተላቸው ይገኛል። በኢትዮጵያ ወስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ኃይሎች ምንም እንኳን የተለያየ አመለካከት እና ፍላጎቶች እንዳሉን ብናምንም የሀገራችንን ሉዓላዊነት የሚፈታተኑ እና የሕዝብን ሰላም የሚነሱ ጉዳዮች ሲከሰቱ ግን ከሁሉም ሀገር ወዳድ ኃይሎች ጋር በጋራ የምንቆም መሆኑን በድጋሚ ለማረጋገጥ ይወዳል።

2.2) ሀገር አቀፍ ምርጫ፡ ኢትዮጵያውያን ምንም እንኳን በበርካታ ውስጣዊ እና ውጪያዊ ችግሮች የተከበብን ቢሆንም የፖለቲካ ሥልጣን ማግኛው ብቸኛ መንገድ በሃሳብ ፉክክር ላይ የተመሠረተ ነጻ እና ገለልተኛ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ብቻ መሆኑ ላይ አቋማችን የማይናወጽ ነው። በሀገራችን ወደ ሥልጣን መውጫ መንገድ ምርጫና ምርጫ ብቻ እንዲሆንም አብክሮ ይሰራል፡፡በዚህም መሠረት አሁናዊ ሀገራዊ ፖለቲካ ላይ ፓርቲው እንደ አንድ ዋነኛ ባለድርሻ የሚጠበቅበትን ገንቢ ሚና ለመጫወት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊደረጉ ከሚገባቸው ፖለቲካዊ ተሳትፎዎች መካከል በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ መቅረብ አንዱ ነው። ይህንንም ማሳካት እንዲያስችለው በቅርቡ በፓርቲው መሪ የሚመራ የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰይሞ ወደ ሥራ የሚገባ መሆኑን ያሣውቃል።
2.3) ሀገራዊ ምክክር፡ ሀገራችን ውስጥ ለዘመናት የዘለቀው የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ኋላቀርነት ምክንያቶች አንዱ እስካሁንም ያልተጠናቀቀው የዘመናዊ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት የፈጠራቸው ውስብስብ ችግሮች መሆናቸውን ግልፅ ነው። ከእነዚህ ችግሮች ጋር የተያያዙ የተለያዩ የታሪክ ዕይታዎችና ቁርሾዎች የሀገራችንን የፖለቲካ ሁኔታ ከድጡ ወደማጡ እንዲዘፈቅ በማድረግ ፍትሕ፣ ነጻነት እና እኩልነት የሰፈነባትን የተረጋጋች ኢትዮጵያን በጋራ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል። ከዚህ ችግር በዘላቂነት ለመላቀቅ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነትን ለድርድር ሳያቀርብ ቢያንስ መሠረታዊ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ የተለያየ እምነት እና ፍላጎት አለን የሚሉ ኃይሎችን ወደ ጋራ ሥምምነት የሚያደርስ ሀገራዊ ምክክር ማድረግ እንደሚያስፈልግ ፓርቲያችን ቀደም ሲል ባጸደቃቸው ድርጅታዊ ሰነዶቹም ሆነ የአቋም መግለጫዎቹ ሲያስገነዝብ ቆይቷል፡፡

ሀገራችንም ለዚህ ጥሩ መደላድል የመፍጠር እድል ያለው የሀገራዊ ምክክር ከሦስት ዓመታት በፊት መጀመሯ ይታወሳል። ሀገራዊ ምክክሩ የሚመራበትን ሕግ በመደንገግም ሆነ ኮሚሽነሮቹን በመሰየሙ ሂደት በርካታ እክሎች የነበሩበት ቢሆንም እንኳን ጉድለቶቹ እንዲስተካከሉ ግፊት እያደረጉ በምክክሩ ሂደት መሳተፍ የተሻለው አማራጭ መሆኑን በማመን ኢዜማ ለሀገር አንድነት፣ ለሕዝብ ሰላም እና እድገት ይበጃል የሚላቸውን ምክረ ሃሳቦች የያዘ ሰነድ አዘጋጅቶ በሀገራዊ ምክክሩ ላይ በሙሉ ልብ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ገዢው ፓርቲ በአንድ አንድ አካባቢዎች እንደተስተዋለው የተለያዩ ጣልቃ ገብነቶችን በመፈጸም አመኔታውን ከመሸርሸር እንዲቆጠብ ለማሳሰብ እንወዳለን። ከዚህ ባለፈ ከፍተኛ ሀገራዊ ሀብት ፈስሶበት የሚደረግ እና በስንት አንድ ጊዜ የሚገኝን ሀገራዊ ምክክርን የመሰለ እድል ከውስጥም ሆነ ከውጪ የሚመጡ ጣልቃ ገብነቶችን በጋራ መከላከል እንደሚገባም እናሳስባለን።

ሀገራዊ ምክክሩ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን በተለያዩ አከባቢዎች ነፍጥ አንስተው የሚፋለሙ ኃይሎች ተሳታፊ መሆን እጅጉን አስፈላጊ በመሆኑ መንግሥት ከመገናኛ ብዙኃን ጥሪ ባለፈ የሚያደርጋቸውን ሙከራዎች ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት በድርድር፣ በሽምግልና ብሎም በሌሎች ሰላም ማምጣት በሚችሉ ማናቸውም አማራጭ መንገዶችን ተጠቅሞ ግጭቶቹ የሚቆሙበት ሁኔታን እንዲያመቻች እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን። የፖለቲካ ፍላጎቶቻቸውን ለማሳካት በምንም ምክንያት ይሁን ነፍጥ አንስተው ጫካ የገቡ ኃይሎች ሊያስታውሱት የሚገባው ዋና ቁምነገር ያለፉትን ሁለት ትውልዶች የአመጽ መንገድ ልብ ካልን ከብዙ ሕይወት እና ንብረት ውድመት በኋላ ምናልባት የመንግሥት ለውጥ ማምጣት ይቻል እንደሆነ እንጂ የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓትም ሆነ የተሻለ ማኅበረሰብ የሚፈጥር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ማስፈን እንደማይቻል መገንዘብ ያሻል። በመሆኑም በየትኛውም የሀገራችን አካባቢ ነፍጥ ያነሳችሁ ኃይሎች እንታገልለታለን ለምትሉት ማኅበረሰብም ሆነ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ጦርነት ጥፋት እንጂ አንዳች እርባና እንደማያመጣ በመገንዘብ ለሰላም ድርድር በራችሁን ክፍት እንድታደርጉ እና በሀገራዊ ምክክሩ ላይ እንድትሳተፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በድጋሚ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ለሀገራዊ የጋራ ጥቅሞቻችን በጋራ እንድንቆም በውስጣዊ ችግሮቻችን ሳቢያ በምንም ሁኔታ ቢሆን ለውጭ ኃይሎች በር እንዳንከፍት ሀገራዊ ጥሪ ማስተላለፍ እንፈልጋለን፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
የካቲት 25/2017 ዓ.ም.
2025/07/13 20:19:00
Back to Top
HTML Embed Code: