Telegram Web
ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም : ገብረ ሕይወትም ይባላሉ:: [562] ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል:: በዚህም በሚሊየን [አእላፍ] ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል::
የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮዽያ ልዩ ፍቅር አላቸው:: ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ ፻ [100] ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል:: ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው::

በሃገራችን ውስጥ ከ [2,000] በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት:: በ8ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት ፭ [5] ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል::

እንኳን ለአባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓለ እረፍት በሠላም አደረሰን
🙏                                    🙏

@Ewntegna
@Ewntegna
@Ewntegna

             
😔ትክክለኛ 🎁old group ገዢ 🙏

♻️የሆነ ሰው inbox ኑ ብዛት አለን🏃 @abenezersolomon1

💧💧💧💧💧💧💧

🙈እንዲሁም old group ያላቺሁ 😌
😳ሰዎች መሸጥ የምትፈልጉ በ አርፍ ዋጋ እንገዛለን 🧐

🔰Inbox ኑ @abenezersolomon1

😎ሙሉ ኃላፊነት ይሄ ቻናል ይወስዳል🤓
እባካችሁ scam ለማረግ አትምጡ
መጻጉዕ

የዐብይ ጾም ፬ተኛ ሳምንት

<< እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዓራተ ሕማሙ ወይመይጥ ሎቱ ኩሉ ምስካቤሁ እምደዌሁ አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ >> መዝ.፵፥፫

<< እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል እኔስ አቤቱ ማረኝ >> መዝ.፵፥፫

የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት ሰንበት መጻጉዕ ይባላል  በዚህ እለት ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን ፈውሷል ጎባጣዎችን አቅንቷል እውራንን አብርቷል አንካሶችንም አድኗል ለምፃሞችንም በመለኮታዊ ሃይሉ አንጽቷል ቤተ ክርስቲያናችንም በዚህ ዕለት ስለ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገቢረ ተዓምራትና ስለ ድውያን ፈውስ በሰፊው ታስተምራለች። የዮሐ.ወንጌል ፭:፩-፳፭

ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያነ ሥጋን በተአምራት ድውያነ ነፍስን በትምህርት የማዳኑ ጉዳይ ጎልቶ ከሚነገርባቸው ጊዜያት አንዱ ይህ “መፃጉ’’ የተሰኘው ሳምንት ነው፡፡

“መፃጉ” ማለት በሽተኛ ማለት ነው አምላካችን በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ በዚህች ምድር ሲመላለስ ከደዌ ዳኛ ከአልጋ ቁራኛ የገላገላቸው መኾኑን የሚያሰረዱ የምስክርነት ቃሎች የሚሰሙበትን ጊዜ ቅዱስ ያሬድ “መፃጉ” በማለት ጠርቶታል፡፡

በመፃጉ ሳምንት የሚሰበከው ምስባክ፡-

‹‹እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ፤ ወይመይጥ ሎቱ ኵሎ ምስካቤሁ እም ደዌሁ፤ አንሰእቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ›› የሚለው ነው  በመዝሙር 40 ላይ የሚገኘውን ይህንን ቃል ዲያቆኑ ከፍ ባለ ዜማ ከሰበከ በኋላ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 5 ላይ ያለው ይነበባል ይተረጎማል  በደዌ ሥጋም ኾነ በደዌ ነፍስ የተያዝን የሰው ልጆች የፈጣሪያችንን ምሕረትና ቸርነቱን እንደምናገኝ ተሰፋ የምናደርግባቸው ገቢረ ተአምራት ይሰማሉ እኛም ከዚህ ታሪክ ብዙ ነገሮችን እንማራለን የመጀመርያው ሰውን መውደድን ማፍቀርን ለሰው ድኅነት ብሎ ዝቅ ማለትን ትሕትናን እንማራለን፡፡

የክርስትና ሕይወት የፍቅር የሠላም የአንድነት ሕይወት ነው ለራስ ብቻ የሚኖሩት ሕይወት ሳይሆን ለሌሎችም መዳን ዝቅ ማለት ነውና እኛም ይህን በዓልን ስናከብር ጾሙንም ስንጾም ይህን ታሳቢ ማድረግ ይኖርብናል፡፡

ወርሃ ጾሙን በሰላም አስፈጽሞ ለብርሃነ ትንሳኤው ያድርሰን አላዛርን ከሞት መፃጉዕን ከአልጋ ቁራኛ ያስነሳ አምላክ ለታመሙት ወገኖቻችንም በምህረት እጁ ይፈዉስልን  ሰላሙን ፍቅሩን ያብዛልን አሜን።

@Ewntegna
@Ewntegna
@Ewntegna
Forwarded from ELOHE PICTURES ♱ (Elohe pictures)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ELOHE PICTURES ♱ (Elohe pictures)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
                    መጻጒዕ

ይህ ሣምንት መጻጒዕ ነው

ይህ ዓመትም መጻጒዕ ነው

ይህ ጊዜም መጻጒዕ ነው

ይህ ሕይወት መጻጒዕ ነው

የዚህ ዘመን ሰውም መጻጒዕ ነው

ሠላሳ ስምንት ዓመት ሙሉ ተኝቶ

ያልተለወጠ ሰው ሁሉ መጻጒዕ ነው።
አይ መጻጒዕ?
             ጌታ ያስበን  🙏 😭

@Ewntegna
@Ewntegna
@Ewntegna
(ትንቢተ ሚክያስ ምዕራፍ 6)
----------
6፤ ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን?

7፤ እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጎች ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? ወይስ የበኵር ልጄን ስለ በደሌ፥ የሆዴንም ፍሬ ስለ ነፍሴ ኃጢአት እሰጣለሁን?

8፤ ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?

አዎ እግዚአብሔርን የሚያስደስተው ፦
ወርቅና ብር አይደለም።
እግዚአብሔርን ለማስደሰት፦
ፍርድን ምሕረትን ትሕትናን ማድረግ ነው ።

          ( አንድ ቀን አንድ ቃል)

@Ewntegna
@Ewntegna
@Ewntegna
ነገሮችን የምሸከምበትን ጥንካሬን እንዲሰጠኝ እግዚአብሔርን ለምኜው ነበር እርሱ ግን በእርሱ ላይ እንድደገፍ የሚያደርገኝን ድካም ሰጠኝ።
        
                (አቡነ ሺኖዳ)

@Ewntegna
@Ewntegna
@Ewntegna
Forwarded from ELOHE PICTURES ♱ (Elohe pictures)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
(ትንቢተ ኢዮኤል ምዕራፍ 2)
----------
13፤ ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቁጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።

14፤ የሚመለስና የሚጸጸት እንደ ሆነ፥ ለአምላካችሁም ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቁርባን የሚሆነውን በረከት የሚያተርፍ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?

           (አንድ ቀን አንድ ቃል)

@Ewntegna
@Ewntegna
@Ewntegna
ሰው ራሱን ቢያሳዝን፣ አንገቱንም እንደ ቀለበት ቢያቀጥን፣ ማቅ ለብሶ በአመድ ላይ ቢተኛም ይህ ጾም እግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠ አይደለም፡፡” “ታዲያ እግዚአብሔር የመረጠው ጾም እንዴት ያለ ነው?” ትሉኝ እንደኾነም ነቢዩ ኢሳይያስ የእግዚአብሔር አፈ ንጉሥ ኾኖ እንዲህ ሲል ይመልስልናል “የበደልን እስራት ፍታ፤ ለተራበው እንጀራህን አጥግበው፤ ድኾችን ወደ ቤትህ አስገብተህ አሳድራቸው፡፡” እንዲህ ስታደርግ፡- “ያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፡፡ ፈውስህም ፈጥኖ ይወጣል”  (ኢሳ.58፥5-8)፡፡

       (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

@Ewntegna
@Ewntegna
@Ewntegna
(ትንቢተ አብድዩ ምዕራፍ 1)
----------
3፤ በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር፥ ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ፥ በልብህም። ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? የምትል አንተ ሆይ፥ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።

4፤ እንደ ንስር መጥቀህ ብትወጣ፥ ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

          (አንድ ቀን አንድ ቃል)

@Ewntegna
@Ewntegna
@Ewntegna
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ (£itsum)
ደብረ ዘይት ( mount of olives )

+ የአምስተኛ የዓቢይ ፆም ሳምንት
+ የዘይት ተራራ (የወይራ ዛፍ ያለበት) ማለት ነው
+ ዳዊት ፳፩ መዝሙር እያዘነና እየጸለየ  ያለ ጫማ የወጣበት ተራራ ነው ። ፩ሳሙ ፲፭- ፴
+ ምሥጢረ ምጽአቱ የተነገረበት ተራራ ነው ። ማቴ ፳፬-፫
+ ቅዱሳን ሐዋርያት ልዩ ምስጋና ያቀረቡበት ተራራ ነው ። ሉቃ ፲፱-፴፯
+ ጌታችን ያድርበት የነበረ ተራራ ነው ሉቃ ፳፩-፴፯
+  ምሥጢረ እርገቱ የታየበት ተራራ ነው ። ግብ ፪-፲፫

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ
Forwarded from ELOHE PICTURES ♱ (Elohe pictures) via @dooxbot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በእናንተው ደጋፍ የተጀመረው እዚህ ደርሷል አሁንም ድጋፋችሁ አይለየን 🙏🙏🙏
የቤተክርስቲያኑ የባንክ አካውንት
💰 👉 1000265718063 👈
ገላን ቅዱስ ሚካኤል

ሁላችንም 100 ብር ብናስገባ ብዙ ነገር መሸፈን እንችላለን የቅዱስ ሚካኤል ምልጃው እና ጥበቃው አይለየን 🙏🙏🙏

ለበለጠ መረጃ የደብሩ ስልክ

+251950008283

የቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ የሆናችሁ
የአቅማችሁን ሼር በማድረግ ማገዝ ለሚችሉ እናድርስ

T.me/Elohe_picture
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
📍 ሕማማት 📍

📍በዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ ተጽፎ በ ቢኒያም ብርሃኑ የተተረከውን ሕማማት የተሰኘውን መጽሐፍ በትረካ ለማግኘት
👇👇👇
2025/03/29 19:02:03
Back to Top
HTML Embed Code: