Telegram Web
ራስን ድል መንሳት 
የስጋ ምኞትንና ፍላጎትን አስመልክቶ ጾምና ድንግልናን ራስን ድል የመንሳት መንገዶች
ናቸው። ነፍስን አስመልክቶ የሚጠቀስም ሌላ መንገድ አለ።ራሱን የሚገዛና እርሱነቱን ወደ
ዓለማዊ ደስታ ከማዘንበል የሚያግድ ሰው ብጹዕ ነው።
ማንነት ልታይ ልታይ ሲል፡ ጉራውን ሊገልጥ ሊተብት ይችላል።በዚህ ሁሉ ግን ልንቃወመው
ይገባናል። ለእኛ #ከእግዚአብሔር ጋር መደሰትና መልካም የሆነው ነገር ለመጪው ህይወት
ብናቆይ የሚሻለን መሆኑን ራሳችንን ልናሳምነው ይገባናል፡፡ በዚህ ዓለም ድስታን ለማግኘት
በሚፈልጉ ሰዎች ላይ #የመድኋኒ_ዓለም ቃል ይመሰክርባቸዋል፡- " . . . እውነት
እላችኋለው፡- ዋጋቸውን ተቀብለዋል።"ማቴ6፡5፡፡
ስለዚህ በምድር ላይ ያሉ መብቶችህን ሁሉ ለማግኘት አትሞክር እግዚአብሔር እያንዳንዱ
ዕንባህን ከዓይኖችህ ላይ የሚጠርግበት በወድያኛው ዓለም ቢሆንልህ ይሻልሃልና።
ማንነትህ ወይም ስጋህ አሁን ላለህበት ዓለም ደስታ የሚያዘም ከሆነ በርትተህ ተከላከላቸው።
በራስህ ወይም በስጋህ ላይ የምይወስደው ይህ እርምጃ ጭካኔ አደለም፡ለእነርሱ ዘላለማዊ
ሕይወትን ማረጋገጫ እንጂ!
ራሱን በዚህ ዓለም ሳለ የሚንከባከባት ያጠፋታል። ራሱን በጥብቅ ከመቆጣጠር ችላ የሚል
ሰው በእርሱ ላይ ኋይል እንዲኖረው ያደርጋል።ሰለሆነም ራሱን ለጽድቅ ከሚያለማምደውና
#የእግዚአብሔር መንገድ ከሚተገብረው ሰው በተለየ ሁኔታ በመንፈሳዊ ጠባዩ ላይ
እንዲያምጽ ያደርገዋል።
ራስን ድል መንሳት የሚሰጠው መንፈሳዊ ደስታ ከስጋ ደስታ ጋር እንደማይነጻጸር እርግጠኛ
ሁን። ከሁሉ በጣም የሚያስደንቀው የራስ ጉራ ሙሉ ለሙሉ መጥፋት በሚገባው በመንፈሳዊ
አገልግሎት ውስጥ ከፍ ከፍ ማለቱ ነው።
#ቅድስነታቸው_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
(መንፈሳዊ ውግያዎች ከሚል መጽሓፋቸው የተወሰደ ተጽሓፈ በእግዚአብሔር ፍቅር ነው።)

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር››
   ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ
Forwarded from Smart ፕሮፋይል Pictures (𝚆𝚎𝚗𝚍𝚒🦁)
‼️አሰቸኳይ የ እርዳታ ጥሪ‼️

ይህቺ ልጅ ሜሮን ካፒታ ትባላለች የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪ ስትሆን የሶስተኛ አመት የፊርማሲ ተማሪ ነበረች አሁን ካይ ግን የኩላሊት ታማሚ ሆና በአልጋ ካይ ትገኛለች። በአዲስአበባ ታዝማ የዉስጥ ደዌ የህከምና ማአከል ዉስጥ የምትገኝ ሲሆን ሁለቱም ኩላሊቷ መስራት ስላቆሙ በአጥበት ካይ ትገኛከች።
አናም ይሀ እጥበት ብቻ በቂ ባለመሆኑ ወደ ህንድ በመሄድ የኩላሊት ንቅለ ተከካ አንድታደርግ ተብላለች።
ቤተሰቦቿም የተጠየቁትን ገንዘብ ማግኘት ባለመቻካቸው ለእርዳታ አጃቸዉን ዘርግተዋል አናንተም የተቻላችሁን አንድታደርጉ በፈጣሪ ስም አንጠይቃቹሃለው

አህታችን ሜሮንን አናድናት።

JOIN US 👉 @wendi_officiall🌼
https://www.tgoop.com/+J0ynCyKIZu85N2Y0
አንተ ሐሳብህን ልትመራዉ እንጂ፤ ሐሳብህ አንተን ሊመራ ቦታ አትስጠዉ፥ እዉነተኛ ክርስቲያን ስሜቱ የሚመራዉ ሳይሆን ስሜቱን የሚመራ ነዉ።
        አቡነ ሸኖዳ ሣልሳዊ

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
#ቅዱስ_መስቀል

#ቤተ_ክርስቲያን_ከመሠረቷ_እስከ_ጉልላቷ_ያጌጠችው_በመስቀል_ነው

በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከማኅሌት እስከ መቅደሱ የመስቀል አገልግሎት እጅግ ብዙ ነው ማኅሌቱን ስንመለከት ሊቃውንቱ ገና ስቡሕ ብለው የሚጀምሩት በመስቀል ሲሆን እንዲሁም የመስቀልን ክብር በሚያወሳ ጣዕመ ዝማሬ በየዚቁ መሐል በማቅረብ ነው ።

በመቀጠልም ዲያቆኑ የምልጣን ምስባክ በሚሰብክበት ሰዓት መስቀልን ይዞ ነው እስመ ለዓለሙና አንገርጋሪው የሚቃኘው ስለዚህ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን #መስቀል_የማኅሌቱ_ጌጥ_ነው

በቅድስት ውስጥ በሚቀርበው አገልግሎት ውስጥ ስንመለከት ደግሞ መልክአ ሥዕሉ የሚጀመረው በመስቀል ነው ተአምረ ማርያም የሚነበበው በመስቀል ነው ኪዳን የሚደረሰው በመስቀል ነው ።

ወደ መቅደሱ ውስጥ ስንገባ ደግሞ ቅዳሴው የሚጀመረው በመስቀል ነው ገና ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት የመቀደሻ ንዋያተ ቅድሳት መጀመሪያ በመስቀል ተባርከው ነው ለአገልግሎት የሚውሉት ለምሳሌ ጻሕሉ ፣ ጽዋው ፣ ዕርፈ መስቀሉ ፣ ሙዳዩ ፣ መሶበ ወርቁ ፣ ዕጣኑ ፣ ልብሰ ተክህኖው ፣ መጎናጸፊያው ፣ ማኀፈዱ ወዘተ በመስቀል ይባረካሉ ።

ቅዳሴው ሲጀመር ደግሞ ረቡዕ ዓርብና ቅዳሜ ሲሆን ገና መግቢያው የሚታወጀው በመስቀል ዜማ ነው ይኸውም « መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ እምኵሉሰ ፀሐየ አርአየ ። መሰቀል አበራ ከሁሉ ይልቅ ፀሐይን አሳየ #ለፀሐይ_ፀሐይዋ_ሆነ » የሚለውን ዜማ እያዜሙ ወደ መቅደስ ይገባሉ ።

ከዚያም ዲያቆናቱ የመጾር መስቀል ካህናቱ የእጅ መስቀል ይዘው ቅዳሴውን ያከናውናሉ በእያንዳንዱ የጸሎት አንጓ የመስቀል ቡራኬ አለ መልእክት ከመነበቡ በፊት ዲያቆናቱ መስቀል ይሳለማሉ ።

እንዲሁም በንዋየ ቅድሳቱ ላይ መስቀል ይሳላል ፤ ይቀረጻል ፤ ይጠለፋል ለምሳሌ በካህናት ልብሰ ተክህኖ ላይ በጽዋው ክዳን ላይ በዕርፈ መስቀሉ ጫፍ ላይ ፤ በማኅፈዱ ላይ በመሶበ ወርቁ ላይ ፣ በጽናው ላይ በአጎበሩ ላይ ፤ በመጻሕፍት ድጉሰት ላይ መስቀል ይደረጋል ።

ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጥምቀት የምትፈጽመው በ40ና በ80 ቀን ሀብተ ወልድ ስመ ክርሰትና የምታድለው ፤ ልጅነት የምታጎናጽፈው በመስቀል ነው ሥርዓተ ጋብቻ ሲፈጸም ሙሽራውና ሙሽሪት እጆቻቸውን በመስቀሉ ላይ አነባብረው ቃለ መሐላ የሚፈጽሙት ቃል ኪዳናቸውን የሚያረጋግጡት በመስቀል ነው ።

ምእመናን የእንግድነታቸውን ኑሮ ጨርሰው በሞት ከዚህ ዓለም ሲለዩ ቤተ ክርስቲያን ክብርት ነፍሳቸው ለፈጣሪያቸው ክቡር ሰውነታቸውን ለመቃብር የምታረካክበው በመስቀል ባርካ ነው የምትሸኘው ።

አባቶቻችን የመስቀልን ክብር በብዙ መንገድ እንዲገለጥ አድርገዋል ዓመታዊና ወርኃዊ በዓል ሰይመውለታል መልክ ደርሰውለታል #መልክአ_ሕማማት ጽላት ቀርጸውለታል ፤ ቤተ ክርስቲያን አንጸውለታል መስተብቁዕ ደርሰውለታል #መስተብቁዕ_ዘመስቀል
ውዳሴ ደርሰውለታል ፤ ድርሳን ጽፈውለታል #ድርሳነ_መስቀል ክርስቲያኖች በስሙ እንዲጠሩ አድርገዋል ለምሳሌ ብርሃነ መስቀል ፣ ገብረ መስቀል ፣ ወለተ መስቀል፣ ኀይለ መስቀል ፤ወልደ መስቀል ፤ መስቀል ክብራ ወዘተ እያሉ ስመ ክርስትና ተሰይሞለታል ።

ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ከመሠረቷ እስከ ጉልላቷ  ያጌጠችው በመስቀል ነው

#እንኳን_ለብርሃነ_መስቀሉ_በሰላም_አደረሰን_አደረሳችሁ

@ewuntegna
ንግሥት እሌኒን እናወድሳት ዘንድ ይገባል፡፡ ክብር የሚገባውን የአምላካችንን የጌታችንን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክቡር መስቀል አገኝ እንደሆነ ብላ በእምነት ለመፈለግ ተግታለችና፡፡

የጌታችን መስቀል ቅዱስ ስጋው የተቆረሰበት ክቡር ደሙ የፈሰሰበት ከሁሉ የተለየ ከሁሉ የተቀደሰ ሁሉንም የሚቀድስ እንደሆነ አስቀድማ ተገንዝባለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፡፡

ንግሥትነቷን በዓለማዊ ቅምጥልናና ምቾት ታሳልፈው ዘንድ አልወደደችም፤ ይልቁንስ የተወደደውን መስቀል ትፈልግ ዘንድ በመንፈስ ብርቱ ሆና በስጋ ደከማለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

እጅግ የከበረውን መስቀል ትፈልግ ዘንድ ስትጀምር በራሷ መታመን አልታበየችም ይልቁንስ ሁሉን ስለክርስቶስ ትቶ የወጣ ባህታዊ ኪራኮስን ታማክር ዘንድ ወዳለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

በተዋህዶ የከበረ የአብ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ይዞ እንዳላስቀረው ሞትንም ድል አድርጎ እንደተነሳ ሁሉ ክቡር መስቀሉም ተቀብሮ ለዘላለም እንደማይኖርና ከተቀበረበትም እንደሚወጣ አምናለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

ከጌታችን መስቀል ጋር የተቀበሩት መስቀሎች ብዙ ናቸው የጌታየን እንዴት እለየዋለሁ? ብላ ሳትጨነቅ የክርስቶስ መስቀል ክብሩን ራሱ እንደሚገልፅ በልቧ ተማምና እስክታገኝው ደክማለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፡፡

@ewuntegna
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!!


"በመስቀሉ ደም ሰላምን አደረገ"። ቆላ.1÷20

       መስቀል ማለት የተመሳቀለ "ተ" ፊደል ቅርጽ ያለው ማለት ነው። በፊት መስቀል የተረገሙ የተወገዙ የሆኑ የዘራፊዎች  የወንበዴዎች መቅጫ  ነበረ። ይሄንንም ተግባር በመስቀል ላይ ወንበዴዎችን መቅጣት የተጀመረው በፋርስ ሀገር ነው። ይኸውም የፋርስ ሰዎች ጣኦት አምላኪዎች ነበሩና ቅጣቱ በመሬት ላይ ከሆነ የመሬት አምላክ "አርሙዝድ" የሚሉት እንዳይቆጣን በማለት ሰዎችን ከመሬት ከፍ አድርገው ይሰቅላሉ።
      በመስቀል ላይ ወንበዴዎችን መቅጣት ይህ አድራጎት  በሮማ ግዛት እንደ ልምድ ሕግ ሆነ።
ሎቱ ስብሐት ንጹሐ ባሕሪ ጌታችን መድኃኔአለም ክርስቶስም እንደ ወንበዴ ተቆጥሮ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ተሰቀለ።

      የርጉማን፣ የወንበዴዎች፣የኃጢተኞች፣የቀማኞች መሰቀያ የነበረው እንጨት፥
ንጹሕ ጌታ ተሰቀለበት።
የረከሰ ደም ይፈስበት የነበረ እንጨት፥
የጌታ ክቡር ንጹሕ ደም ፈሰሰበት፣ የአማኑኤል ቅዱስ ስጋ ተቆረሰበት።

           አዳም በዕጽ/በእንጨት/ ትዛዝ ማፍረስ ምክንያት ከፈጣሪው ተጣልቶ ወደ ምድር ተሰዶ በኋላም በሲኦል ወድቆ ሲኖር ነበረ፥
        መድኃኒታችን ክርስቶስ በዕጽ/በመስቀል/ ተሰቅሎ ከተፈረደበት መርገም ከወደቀበት ሲኦል ከሰይጣን ባርነት ቀንበር ነጻ አውጥቶ ልጅነትን ሰጥቶ ወደ ቀደመ ክብሩ ወደ ርስቱ ወደ ገነት አስገባው።

         አዳም ዕጽዋ ላይ ያለውን ፍሬ በልቶ የሞት ሞት አገኝቶት ከእግዚአብሔር የነበረውን ኅብረት ሲያጣ፥
            መድኃኔአለም ክርስቶስ በዕጸ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ቅዱስ ስጋውን፡ክቡር ደሙን ሰጥቶ ዘለአለማዊ ሕይወትን፡ ኅብረቱን አደለን። ዮሐ.6÷53

በዕጸ በለስ መርገም፣ ኩነኔ ፣ ጉስቁልና ሲሆን፥
በዕጸ መስቀል ሰላም ፍቅር አዲስ ሕይወት ተሰጠን።

   " በመስቀሉ ደም ሰላም አደረገ" የአምላካችን ንጹሕ ደም አለምን ሁሉ ቀደሰ ፣ ከኃጢአትም ሁሉ አነጻን።
“ደሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ያነጽሐነ እም ኩሉ ኃጣውኢነ፤ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።”
      1ኛ ዮሐንስ 1፥7
  ቅዱስ ደሙን መላእክት በአለሙ ሁሉ ረጭተውታል። "ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ፤ ምድር ጸዳች ሐሴት አደረገች በክርስቶስ ደም ስለ ታጠበች"

  ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በመስቀል ነው። "መስቀል ብርሃን መሰረተ ቤተርስቲያን" ደሙ በነጠበበት ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ትታነጻለች።

       ክብር ይግባውና ቅዱስ አምላካችን አማኑኤል በመስቀል ላይ ሆኖ ሳለ የመጨረሻ የሰውን ልጅ የማዳንን ስራ "ተፈጸመ" አለ ድኅነታችን የተፈጸመው በመስቀል ነው። በመስቀሉ ሳለ ጥንተ ጠላታችንን ዲያብሎስን በአራቱ ማዕዘን በነፋስ አውታር አሰሮ እንደቀጠቀጠው ሁሉ እኛም ቅዱስ መስቀሉን ጋሻ አድርጎ ስለሰጠን መስቀሉን ይዘን ሰይጣንን እንዋጋበታለን ድል እናደርገውማለን።

    መስቀሉን በአንገታችን አስረን ስናየው፡ በመስቀሉ ስናማትብ፡ መስቀሉን ስንሳለም፥ የመስቀልን በዓል ስናከብር ሁል ጊዜ ትዝ የሚለን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ብሎ በመስቀል ላይ የከፈለውን ውለታ እናስታውሳለን።

መስቀል የጌታን የእለተ አርብ ውሎ የምናይበት መስታዎት ነው።

በመስቀሉ ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን ተሰጠን!
በመስቀሉ እመቤታችን ቅድስት ማርያም ተሰጠችን!
መስቀል የእግዚአብሔር ኃይል የጠላት ጋሻ ሆኖ ተሰጠን!
በመስቀሉ ረድኤት ፍቅር ሰላም አንድነት ሰፈነልን!

ሞገሰ መስቀሉ ወሀብተ ረድኤቱ ይድር በላዕሌነ የሀሎ ምስሌነ አሜን!!!

"መልካም የመስቀል በዓል"
ዲ/ን ደሳለኝ ወርቄ

@ewuntegna
@ewuntegna
Psalms 22 (አማ) - መዝሙር
1: አምላኬ፡ አምላኬ፡ ለምን ተውኸኝ?
እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ቃል ሩቅ ነህ።
2: አምላኬ፥ በቀን ወደ አንተ እጠራለሁ፥ አልመለስህልኝም፤
በሌሊትም እንኳ ዕረፍት የለኝም።
Job 34 (አማ) - ኢዮብ
4: ቅን የሆነውን ነገር እንምረጥ፤
መልካሙንም ነገር በመካከላችን እንወቅ።

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
ዕንባቆም ፩፥፩-፫

እግዚአብሔር ሆይ፤ ለርዳታ እየተጣራሁ፣
አንተ የማትሰማው እስከ መቼ ነው?
“ግፍ በዛ” ብዬ እየጮኽሁ፣
አንተ የማታድነው እስከ መቼ ነው?
3 ስለ ምን በደልን እንዳይ አደረግኸኝ?
እንዴትስ ግፍ ሲፈጸም ትታገሣለህ?
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
"እኔ በስምሽ አምናለሁ፥ አንቺም ስለእኔ ትማልጃለሽ፥ ልጅሽም ስለአንቺ የልመናዬን ዋጋ ይሰጠኛል።"
— ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
“ወዳጄ ሆይ!
የትዕቢት መርዝ ተጠራቅሞ አብጦብሃልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ስለ ወዳጆቹ ሲል አርአያ ገብርን የነሣ ትሑቱ ጌታም ትሕትናን ያስተምርሃል፡፡

የስግብግብነት ትኩሳት አስቸግሮሃልን? ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ደግነትንም ትማራለህ፡፡

የምቀኝነት ብርድ አስቸግሮሃልን? እንኪያስ ወደ ሰማያዊው መዓድ ቅረብ፤ ምህረት ማድረግንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡

ትዕግሥትን የማጣት እከክ ይዞሃልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ራስን መግዛትንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወትህ ልል ዘሊል ብትሆን ይህን መንፈሳዊ መዓድ ተመገብና ብርቱ ትሆናለህ፡፡

ቆሽሸሃልን? እንኪያስ ወደዚሁ መብልና መጠጥ ቅረብ ብዬ እመክርሃለሁ፤ ንጽሕናንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡”

ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 46)
----------
1፤ አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።

2፤ ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም።

@Ewunetgna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
አንዲት ክፉ ቃል መልካሙን ሰው እንኳ ክፉ ታደርገዋለች፤ አንዲት መልካም ቃል ግን ክፉውን ሰው መልካም ታደርገዋለች፡፡
አባ መቃርዮስ

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ (£itsum)
+ ዕረፍታ ለቅድስት አርሴማ +

ሴቶች እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ
(ዕብ 1፥35)

ቅድሰት አርሴማ ሰማዕቷ ። በአርመንያ ታኅሣሥ 6 ቀን ሐሙስ ዕለት ተወለደች ። አባቷ ቴዎድሮስ አትናስያ ይባላሉ ። የነበረችበት ዘመን ዘመነ ሰማዕታት በመባል ይተወቃል ። ዲዮቅልጥያኖስ ቆንጆ ሴት ፈልጋችሁ አምጡልኝ ብሎ ሠራዊቱን በየሀገሩ ላከ አምጡልኝ ሲላቸው አርሴማ በተራራ ተቀምጣ ነበር ፤ እርሷም የእግዚአብሔር መንፈስ ተገልጦላት ወደ አርመንያ ሄደች ። ይህንን ሰምቶ ለንጉሡ ለድርጣድስ አሰፈልገህ ላክልኝ ብሎ ላከበት አስፈልጎ አገኛት እርሷም መልከ መልካም ሴት መሆኗን አይቶ ይህችንስ ለማንም አሳልፌ አልሰጥም ብሎ ዶርታንን ለምኚልኝ አላት ለመንግሥተ ሰማያት የታጨሽ ነሽና ይህ አላዊ እንዳያረክስሽ አለቻት መልኳን አይቶ በስሜት ተሸንፎ ዘሎ ያዛት ከእግዚአብሔር ኃይል መንፈሳዊ ተሰጥቷልና ጎትታ ከመሬት ጣለችው ። በሰይፍ መስከረም 29 ቀን አሰቆረጣት በ27 ዓመቷ በሰማዕትነት በዚህ ዕለት አረፈች ። ( ፍኖተ ስብከት ሊቀ ስዮማን አዲሱ ላቀው ገጽ_37 )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
2 Peter 3 (አማ) - 2 ጴጥሮስ
9: ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna
2025/01/01 00:00:49
Back to Top
HTML Embed Code: