Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
ከክፉ ሰዎች መራቅ ጉዞ ወደ መልካምነት ።


በህይወትህ የሚጋጥሙህ ሰዎች ሶስት አይነት ናቸው። አንዳንዶቹ አንተ የምትፈልጋቸው ናቸው። ሌሎቹ እነሱ አንተን የሚፈልጉ ናቸው ። ቀሪዎቹ ደግም እርስ በርስ የምትፈላለጉ ናቸው።

የምትፈላለጉ ከሆነ ጥሩ ነው። ነገር ግን በጣም መጥፎው ነገር እየፈለካቸው የማይፈልጉህ አይደሉም። በጣም መጥፎዎቹ እነሱ ፈልገው እንድትፈልጋቸው ካደረጉ በኋላ የማይፈለጉህ ሰዎች ናቸው። መጥፎ ሰው ማለት እየፈለከው የማይፈልግህ ሳይሆን ሳትፈልገው ፈልጎህ የመፈለግ ስሜት ፈጥሮ የማይፈለግህ ሰው ነው።

በሂወትህ የሚያጋጥሙህን መጥፎ ሰዎች እንደሌሉ ቁጠራቸውና ተዋቸው። ምንም እንኳን በከባዱ ቢጎዱህም እንዳልቱፈጠሩ ቁጠራቸውና እርሳቸው። አዎ በላይህ ላይ የፈጠሩት ቁስል በላይህ ላይ የፈጠሩት ጠባሳ ከባድ ቢሆንም አንተ እነሱ በላይህ ላይ ያስቀመጡትን ጠባሳና ቁስል ሳይሆን ፈጣሪ በውስጥህ ያኖረውን ስጦታ ለማየት ሞክር። ያኔ ህይወትህ ያምራል። ልብህን ከቂም በቀል ስታጸዳው ህይወትን እንደገና መኖር ትጀምራለህ።

አዎ እብድ ውሻ ሲነክስህ መልሰህ ውሻውን አትነክሰውም። ከነከስከውማ ከውሻው በምን ተሻልህ? በሂወት ጉዞህም የሚያጋጥሙህ ብዙ አቁስል ሰዎች አሉ። ግን እነሱ በጎነተሉህ ቁጥር እየዞርህ መልስ የምትሰጥና አተካሮ ውስጥ የምትገባ ከሆነ እመነኝ አቅምህን ታጣለህ። ካቆሰሉህ በላይ ቁስልህን እየነካካህ ታመረቅዘዋለህ። ህይወትህም የሀዘን ይሆናል።

አንተ ግን እንዲህ አይነት ሰዎች ሲያጋጥሙህ "ተዋቸው" በጣም ከባድ ቢሆንም "እርሳቸውና አንተ ከነሱ የተሻልህ መሆንህን አሳያቸው"
ሁሌ በአዲስ ጎዳና ስንጓዝ አዲስ መውጫ በር፤አዲስ መሻገሪያ ድልድይ እናገኛለንና ያለፈውን ትተን ያለፈውን ረስተን እንደገና ህይወትን "ሀ" ብለህ ጀምር፡፡

ሰው ሁን ከሰውም ሰው

@tobiya_kinet
@eyorkis
የሰዎችን ህይወት ራሳቸው እንዲወስኑ ብንተውላቸው ፍላጎታቸው እኛን እስካልነካ ድረስ ብናከብርላቸው ጥሩ ነው ሁሉም ነገር ላይ ሀሳብ ካልሰጠን የሁሉንም ሰው አመለካከት ካላስተካከልን ባንል…

አንዳንዴ አንድን ነገር አጥብቀው ሚቃወሙ እና እዛ ነገር ላይ ችክ ሚሉ ሰወች ራሳቸው በዛ ህይወት ውስጥ ያሉ የዛ ነገር ሰለባ ናቸው ያሉበት ነገር ኮሽታ ፈጥሮባቸው ነገሮችን ለመሸፈን ኦቨር አክት ያደርጋሉ

ሰወች ላይ የሙጥኝ በዚ ካልሄድክ እንደኔ ካላሰብክ አትበሉ የእነሱን ለእነሱ እንተውላቸው ሁላችንም ብዙ ሚያሳስበን ያልተስተካከለ የሚያስጨንቀን ነገር አለን እሱ ላይ ብንሰራ 👍
  @mekdela
@eyorkis
እንደምትወዳት ንገራት,

(በእውቀቱ ስዩም)
ሕይወት የብድር በሬ፥መቼ ሁሌ ይጠመዳል
ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል
የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወሰዳል::

ቀለበት፥ አምባር አይደሉም
እጅህ ላይ ሁልጊዜ የሉም
-ቀናት ሳምንታት ወራት
ዛሬውኑ ፥አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት::

አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ
ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ
ያጸድ በሮች ሳይቆለፉ
በንቦች ጎዳና ላይ፥ተርቦች ሳይሰለፉ
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ
ሕይወት የላምባ መብራት
አሁንኑ ዛሬውኑ ፥እንደምትወዳት ንገራት፤

ርቃ ሳትገሰግስ
ገና ስንቋን ስትደግስ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደማትቀባው አመድ
ወደማትስበው አየር
ሳትቀየር
አንትም አንደበት ሳለህ፥ እሷም ጆሮ ሳያጥራት
ዛሬውኑ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት።

@eyorkis
(ከመጽሐፉ የጀርባ ገጽ የተወሰደ -ከውስጥ)


የደስታ ቀናት እንደ ሰማይ ሲርቁ... ክፋ ቀናት እንደ አጀብ ሲከቡን... የተጠበቀው ቀርቶ የልተጠበቀው ሲሆን... ሞት አንድ አማራጭ ሆኖ ሲቀርብ... ውስጣዊ ሰላማችን ሲረበሽ... አርጋታ ፈጽሞ ሲጠፋ....

...ያን ጊዜ “ጌታ ሆይ እስከመቼ?” እንላለን፡፡ ደግሞም በልጅነት ሰቆቃ በአባቶቻችን አንደበት “እስከማዕዜኑ?” እንላለን፡፡ አንባችን አንደ መጠጥ፣ ሀዘናችንም እንደ መበል ይሆንበናል፡፡ የቀናት ጠንሳሽ የሆነው አባታችን እግዚአብሔር ግን “ታገስ፣ የመጠበቅን ፍሬ ትበላለህ” ማስቱን ይቀጥላል፤ እኛም “አምላኬ ሆይ፣ እንዴት ልታገስ? እሰከመቼስ ልጠብቅ?” አንላለን፡፡ ከዚያም ቃሉን ያስታውሰናል፣ የቀደሙ ቅዱሳኑን አብነት ይዘክርልናል፡፡

“እንደ ልጄ እንደ ዳዊት ቀና ሁን፣ እንደ ታላቁ ታጋሽ እንደ ኢዮብ ሁንልኝ፣ የቀጠርኩልህ ቀን ሲደርስ የመከራህን ቀናት አስረሳሃለሁ! እንደ ተወዳጁ ልጄ እንደ ወልድ ትንሳኤህ እስኪገለጥ እርጋታን ገንዘብህ አድርግ!'' ይለናል፡፡ በቅዱስ ቃሉ ያባብለናል፡፡

የህማማት ቀናቶቻችን እንደ ግዮን ወንዝ የረዘሙ ሲመስሉ፣ የህዝባችን እፎይታ፣ የሀገራችን ሰላምና መረጋጋት እንደ ጌታችን መምጫ ቀን ሲርቁብን፣ ህይወት ከንቱ፣ መኖርም ምናምንቴ መስሎ ሲታይ... የምድረ በዳው መንከራተት ከንዓናችንን ሊያስረሳን ሲደርስ፣ መራርነት ተስፋችንን ሊያስጥስን ሲተጋ፣ የስጋ ድካም ከዘለዓለማዊው እጣ ፈንታችን ሊያናጥበን ሲል... ያን ጊዜ የታላላቅ አባቶች ምክር፣ የቅዱሳን ጥበብ፣ የታጋሾች ምስክርነት ያስፈልገናል፡፡


"እስከማዕዜኑ"

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ


ምንጭ፦እስከመንገድ የቴሌግራም ቻናል

@eyorkis
ኮብላይ ተስፋ

ጊዜ ነፋስ ነው - የባሕር አውሎ
ወጀቡ ጤዛ እየዘራ....
ይንከራተታል በየትም - ነፍስ የሚበርድ ቆፈን አዝሎ።
ተስፋ ያ'ረኩት ነገ - ያልፋል በነፋስ ታዝሎ
ጊዜ ይጠድፋል ከአውሎ
ይከስማል ጥላው ቸኩሎ።

ግብብ መስኮቴን ብከፍተው - የንጋት ጮራ እንዲገባ
ቀኑ ድንግዝግዝ ለብሷል...
ሳታፈራ እረግፍለች - ርጥብ አደይ አበባ።

ሳይነጋ ዳግም ጨልሟል - ዞሯል የአመሻሽ ጥላ
ነፍሴ እሽ ሩሩ ስትል - ተስፋ ጉጉቷን አዝላ፤
ተስፋዋ በእቅፏ ሞተ  - ጠለቀች በዋዛ ጀንበር
ሁሉም ከንቱነት ሆነብኝ - ድካም ነው ነፋስን ማስገር።
እንደ እፉዬ ገላ ከስሞ - ገና በአበባው ጉጉቴ
በየት ጥሎኝ አለፈ - ከነፋስ ፈጥኖ ልጅነቴ...
            ```
አሻግሬ ባይ ዱር ለብሷል - የመጣሁበት መንገድ
ይግባኝ አይሉት ለሸንጎ - ጊዜ ሳይነጋ ሲረፍድ።

እንዴት ተጣጣሁ ከኅልሜ
ዋ! ልጅነት ቀለሜ
ላልደርስ እባክናለሁ - ላልችለው ጊዜን ተሸክሜ።

ቀና ብል ለዓይኖቼ ራቀ - እንደ ጉም ተ'ኖ ጠፋ
በሸካራ መዳፌ...
ከጠወለገ እንባ ጋር - ታበሰ በዋዛ ተስፋ።

እንባዬን ከፊቴ ሊጠርግ - ቢነሣ ይቡስ መዳፌ
ክንዴን ዝሎ አገኜውት - የሞተ ተስፋ ታቅፌ።

መንገደኛ ነፋስ ነው - ኅልማችን ሁሉ ከንቱ
የመኖር ቆፈን፥ ውሽንፍር - የጊዜ ብርዱ እትቱ..

እንደ ክረምት ቁልቁለት
እያዳለጠችኝ ሕይወት
ስንት መከራ ልሸከም - ለአንዲት ዓለም - ለአንዲት ኑረት..?



           ༺❀༻
`` አንዳንድ ግንኙነቶች ፈውሳቸው መፍረሳቸው ነው። ያ መፍረስ ሊጎዳህ ይችላል ፀፀት እና ህመም ሊሰማህ ይችላል፤ ትዕግስትህን ብሎም የህይወት ዘመንህን ያቃጥለዋል፤ መዳንህ ግን ከዚህ ይጀምራል። ``

-ቪክቶር ሁጎ
ሕይወት አይደለም አዝነንባት ፤ ተደስንባትም አትበቃም ።

ነገር ግን ሕይወት አጭርና አፍታ እንደመሆኗ ዓለም ግን ሰፊ ነች ። ለዚያም ነው ጥልቁ የሕልም ባሕር ከክሱተ ዓለም የሚፈልቀው ።


ብቻ አምላክ ዘመናችንን ይባርክ❤️


♡‿︵  Fasikaw ♡︵‿

@lomi_teratera
አይ እንደልቡ😁😁

ግን ይቺ ጠጠር ጠጠር ብቻ ነች?🤔

@tobiya_kinet
@eyorkis
ጀግናው የታክሲ ሹፌር ስምኦን አደፍርስ
(1905 -- 1929)

በእጅጉ አስገራሚ ታሪክ ነው። አስገራሚ ያልኩት በብዙ ምክንያት ነው። አንደኛው ኢትዮጵያ ውስጥ የታክሲ ስራ መቼ ተጀመረ ብለን ብንጠይቅ በ 1920ዎቹ ነው የሚል መልስ እናገኛለን። በ 1928 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ስምንት ታክሲዎች ብቻ ነበሩ።

ከነዚህ የስምንቱ ታክሲዎች አንደኛው ባለቤት ስምኦን አደፍርስ ይባላል። የያኔው ዘመናዊ ሰው። መኪና ሲነዳ እንደ ብርቅ እና ተአምር የሚታይ ነበር። ከተለያዩ የታሪክ መዛግብት ያገኘሁትን የዚህን ጀግና ኢትዮጵያዊ ታሪክ እንኮምኩመው፡፡

ስምኦን አደፍርስ ፣ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ግራዚያኒ ላይ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም ቦምብ ሲወረውሩ የተባበራቸው ጀግና ነው። በታክሲው ይዟቸው መጭ ያለ ልበ ደፋር ሰው ነው። በኢትዮጵያ የታሪክ አለም ውስጥ ስለ እሱ ብዙ አልተባለለትም።
ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ስለዚሁ ስምኦን አደፍርስ ስለሚባለው አስገራሚ ኢትዮጵያዊ ሰፋ አድርገው ከጻፉ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው።

ስምኦን ከአባቱ ከአቶ አደፍርስ አድጎ አይቸውና ከእናቱ ከወይዘሮ ሙሉ ብርሃን መሸሻ በሐረርጌ ክፍለ ሀገር በሐብሮ አውራጃ በአንጫር ወረዳ ልዩ ስሙ ጉባ ላፈቶ በሚባለው ሥፍራ በ 1905 ዓ.ም ተወለደ። እድሜው ለትምህርት ሲደርስ በመጀመሪያ እዚያው ላፍቶ በሚገኘው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ደብር ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በሕፃንነቱ በመምጣት በልደታ ማርያም ካቴድራልና በአሊያንስ ፍራንሴዝ ትምህርቱን በሚገባ አጠናቀቀ። ከዚያም በታክሲ ነጂነት ወደ ግል ሥራ ተሠማርቶ ይኖር ነበር።.......

ሙሉውን ታሪክ
👇
www.facebook.com/share/p/1JKUmZzf5p/

#ታሪክን_ወደኋላ
የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም

#በዛሬዋ_ዕለት

ከ 81 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በአብርሃም ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም መሪነት በኢጣልያኑ የጦር አዛዥ ጄነራል ግራዚያኒ ላይ በቦንብ ያደረጉት የግድያ ሙከራ ምክንያት የኢጣሊያን ወታደሮች በቂም በቀል በመነሳት በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ለ 3 ተከታታይ ቀናት ዘግናኝ እና ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በህዝቡ ላይ ጭፍጨፋ ያደረሱበት ዕለት ነበር።

የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም በፋሺስት ኢጣሊያ በግፍ የተጨፈጨፉ ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት ሲታወሱ......

የካቲት 12 ቀን በኢትዮጵያ ታሪክ የተለየ ቀን ነው፡፡ የኢጣሊያዋ ኔፕልስ ግዛት ልዑል ልጅ መውለዱን ለመዘከር ግራዚያኒ በዚህ ቀን የአዲስ አበባን ደሃዎች ሰብስቦ ለመመጽወት ባደረገው ጥሪ መሰረት ከ 3ሺ የሚበልጡ አቅመ ደካሞች በጥዋቱ በ 6 ኪሎው ቤተመንግስት ተገኝተዋል፡፡

በዚህ ቀን ኢትዮጵያውያን ጥቃት ሊያደርሱ ይችላሉ የሚለው መረጃ እስከ ሮም በመሰማቱ የቤተመንግስቱ ውስጥና ዙሪያ መትረየስ በታጠቁ ልዩ ወታደሮች እንዲጠበቅ ተደርጓል፡፡ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ይህንን ጠንካራ ጥበቃ አልፈው ውስጥ ገብተዋል፡፡

ከቀኑ ለስድስት ሩብ ጉዳይ አካባቢ ሲሆን ከፍተኛ ፍንዳታ በቤተ መንግስቱ ተሰማ፡፡ ከፍ ወዳለው የቤተመንግስቱ ደረጃ የተወረወረው ቦምብ ደግሞ ግቢውን በጩሀት አናጋው፡፡ የመጀመሪያው ቦምብ ባለመትረየስ ጠባቂውን አስወገደው፡፡ 2ኛው ቦምብ ከግራዚያኒ አጠገብ የነበረውን ምሰሶ አፈራረሰው፡፡......

ሙሉውን ታሪክ
👇
www.facebook.com/share/p/18eTRqoJUT/

#ታሪክን_ወደኋላ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ወይእዜኒ መኑ ተስፋየ
አንቺን ልጠብቅሽ
እንዴት ብየ ልይሽ
ስሚኝ የኔ እመቤት
የሳሎኔ ውበት
የሕይወቴ ድምቀት
በአካል ላላገኝሽ በርሃው አይሏል
ከየብሱ ለጥቆ ባህሩ ተኝቷል
ባህሩ ቢታለፍ አድማስ ተዘርግቷል
እንዴት ብየ ልኑር አይንሽን ሳላየው
በሃሳብ ሸራ ላይ ገላሽን እያየው
እንዴት ልንቋቋመው የናፍቆትን በትር
በምን ልሻገረው የለየንን ድንበር ?
መቸም እጅ አልሰጠም
መቸም ተስፋ አልቆርጥም
አይገድልም ህመም ነው የናፍቆት ውሃ ጥም
ተስፋ መቀመር ነው ተራርቆ ፍቅር
ፈንድቶ የማይለይ በልብ ውስጥ የሚቀር
ታዲያ እንዴት ልይሽ?ድንበሩን አልፌ ባህሩን ቀዝፌ
ከሃሳብ እንድድን ገላሽን አቅፌ
ጀምበር ገባች ፥ መሸ
ያጸዳሁት ቤቴም ፥ መልሶ ቆሸሸ
አልጠፋም መብራቱ
አልተበላም 'ራቱ
አሁንም ክፍት ነው በርና መስኮቱ ።
ለቁር ተጋለጠ ፥ ጓዳዬ እንደ ውጪው
መቼ ነው የምትመጪው ?

መጽሐፍ ገለጥኩና መልሼ ዘጋሁት
ልጽፍ አሰብኩና ብዕሬን ወረወርኩት
መቆም መንጎራደድ
መቆም መንጎራደድ
መቆዘም መተከዝ ፥ በሐሳብ መሰደድ
ደርሶ ብንን ብንን
ደሞ ቁጭ ብድግ
ካንቺ ውጭ አላውቅም ምን እንደምፈልግ ።

ምኞት ነው ያለኝ  ፥ ዝም ብሎ ምኞት
ወይ የማያኖር ፥ ወይ የማያስሞት

ትመጫለሽ እያልኩ በጉጉት ከምኖር
ምናለ በሞትኩኝ ለአንድ ለስድስት ወር ።
የቱንም ያህል ብቸኘነት ቢሰማህ ወደ ተወህ ሰው አትመለስ !

@eyorkis
ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለታላቁ ጾመ ኢየሱስ (የዐብይ ጾም) በሰላም አደረሳቹ።

ጾሙ የሰላም የበረከት እንዲሁም የፀሎታቹ ሁላ ምላሽ የምታገኙበት መልካም የጾም ወራት ይሁን እያልን መልካም ምኞታችን እንገልፃለን።

https://www.tgoop.com/tobiya_kinet
@eyorkis
Photo
2025/02/24 23:34:47
Back to Top
HTML Embed Code: