Telegram Web
የነቢዩ ﷺ ቀብር ዘራፊዎች

የነቢዩን ﷺ ቀብር በተለያየ ዘመን ለመውሰድ ተሞክሯል። ይህም ከፊሉ በአይሁድና ክርስቲያኖች ከፊሉ ደግሞ በሺዓዎች የተፈፀመ ነው። ምክንያቱ ደግሞ ሙሽሪኮቹ የኢስላምን ክብር ለማንቋሸሽ፥ ሽዓዎቹ ዶሪህ ሰርተው ገቢ ለመሰብሰቢያ ነው።

ከእነዚህ ሙከራዎች አንዱ ደግሞ በ557 ሒጅራ የተፈፀመው ነው።

በወቅቱ በዐባስያ ኸሊፋ በባግዳድ የነበረ ሲሆን ነገርግን በሱልጣኖቹ ሰልጁቆች እጅ ስለወደቀ አቅም የለውም። በዚያ ዘመን ጠንካራ የሚባለው ሱልጣን በሶርያ የሚገኘው ኑሩዲን ማህሙድ ኢብን ዘንኪይ ነው።

አንድ ሌሊት ኑሩዲን በህልሙ ነቢዩ ﷺ መጡና ፀጉራቸው ቀይ ወደሆኑ ሁለት ሰዎች እየጠቆሙ ❝ማህሙድ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ተከላከልልኝ!❞ አሉት። ኑሩዲንም ደንግጦ ተነሳና ሁለት ረከዓ ሰግዶ ተመልሶ ተኛ። ከዚያም ህልሙን ለሁለተኛ ጊዜ አየ። አሁንም ተነሳና ሰግዶ ተኛ። ለሶስተኛ ጊዜ አየ። በዚህ ጊዜ አማካሪውን ሸይኽ ጀማሉዲን አል-ሙውሱሊን አስጠራና ነገራቸው። እነሱም ህልሙ እውነት ስለሚመስል ለማንም ሰው ሳይናገር በፍጥነት ወደ መዲና እንዲሄድ አዘዙት።

ኑሩዲንም አማካሪውንና ሌሎች ጥቂት ሰዎችን አስከትሎ ከ16 ቀናት ግስገሳ በኋላ መዲና ገባ። ከዚያም ወደ ነቢዩ ﷺ መስጂድ በመሄድ ሶላት ከሰገደ በኋላ ለህዝቡ ሰደቃ መስጠት ስለሚፈልግ እንዲሰበስቡለት አዘዘ።

ህዝቡም ከተሰበሰበ በኋላ ሁለቱን ሰዎች ቢፈልጋቸው አጣቸው። እሱም ❝ሰደቃ ያልደረሰው ሰው አለ?❞ ብሎ ሲጠይቃቸው ❝ከመግሪብ ከመጡት ሁለት ዛሂዶች በቀር ሁሉም ደርሶታል። እነሱ ቀን የሚፆሙ ሌሊት የሚሰግዱ ሲሆኑ ለህዝቡም ሰደቃ ይሰጣሉ።❞ አሉት።

ኑሩዲንም ሰዎቹ እንደሆኑ አወቀና እንዲቀርቡለት አዘዘ። ሲቀርቡም በህልሙ ያያቸውን ሆነው አገኛቸው። ከዚያም ከየት እንደመጡ ሲጠይቃቸው ከሞሮኮ ለሐጅ የመጡ መሆናቸውን ነገሩት።

ኑሩዲንም ወዳረፉበት ቤት እንዲወስዱት ጠየቃቸው። ያረፉበት ቤት ከነቢዩ ﷺ ቀብር ቅርብ ሲሆን የተነጠፈውን ስጋጃ ሲያነሳው የተቆፈረ ዋሻ አገኘ። እሱንም ተከትሎ ወደውስጥ ሲገባም ከነቢዩ ﷺ ቀብር አጠገብ ደረሰ።

ሰዎቹን ማን እንደላካቸው ሲጠይቃቸው የስፔኑ ንጉስ እንደሆነና እነሱም ክርስቲያኖች መሆናቸውን ተናዘዙ። ኑሩዲንም ከቀብሩ ደርሰው ሳለ ምን እንዳገዳቸው ሲጠይቃቸው የመሬት መንቀጥቀጥና የጉርምርምታ ጩኸት መሆኑን ነገሩት። ከዚያም ሁለቱም በህዝብ ፊት አንገታቸው ተቀላ።

ኑሩዲንም ዋሻው እንዲደፈንና የመቃብሩ ዙሪያ እንዲታጠር አድርጎ ወደ አገሩ ተመለሰ።
(አል-መራጊይ - ተህቂቅ አን-ኑስራ 240 / ኢብን ዒያስ - በዳዒዕ አዝ-ዙሁር)

ሰል ማን



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
1👍1
Audio
#ኪታብ ዑምደቱል አህካም
#በፈትህ አባቦራ መስጂድ
#ዘወትር ረቡዕ እና ጁመዓ ከመግሪብ- ዒሻ #በኡስታዝ ካሚል ጣሃ   ደርስ በድምፅ ክፍል #53 መከታተልና መቅራት ትችላላችሁ። #እንዳያመልጥዎ
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 1⃣9⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣6⃣
ምዕራባውያን "እኛ የኢስላም ጠላት አይደለንም" ካሉን ያ ከሁለት አንዱ ነው። ወይ እነሱ የሚያወሩት ውሽት ነው፣ ወይ እኛ ያለንበት ትክክልኛ ኢስላም አይደለም።
ለተጋቢዎች የሚደረግ የመልካም ምኞት መግለጫ!

ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ፡ እንዲህ ይላል፦ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ሰዎች ጋብቻ በሚፈፅሙበት ግዜ እንዲህ በማለት ዱዓእ ያደርጉ ነበር፦

﴿بارَكَ اللهُ لك، وبارك عليك، وجمع بينَكما في خيرٍ﴾

“አላህ ባለቤትህን ይባርክልህ። አንተንም ይባርክህ። በመካከላችሁ የሚኖረው ትስስርም መልካም ይሁን።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 4729



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 2⃣0⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣6⃣
የማስነጠጥ ስነስርዓት!

ከአቡ ሁረይራ (رضيﷲ عنه) ተይዞ፡ ረሱል (ﷺ) ባስነጠሱ ጊዜ እንዲህ ያደርጉ ነበር፦

﴿كَانَ إِذَا عَطَسَ غَطَّى وَجْهَهُ بِيَدِهِ، أَوْ بِثَوْبِهِ، وَغَضَّ بِهَا صَوْتَهُ﴾

“አፋቸውን በእጃቸው ወይም በልብሳቻው ይከድኑ ነበር። ድምፃቸውንም ዝቅ ያደርጉ ነበር።”

📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል: 2745



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልስነይን 2⃣1⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣6⃣
ህልም ለሁሉም አይነገርም!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا تَقُصُّوا الرُّؤيا إلا على عالمٍ أو ناصحٍ﴾

“ህልም ካያችሁ ለማንም አትንገሩ። ለአሊም ወይንም ለምትወዱት መልካም መካሪ ሰው ካልሆነ በቀር።”

📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 119



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
👍1
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አሱለሳዒ 2⃣2⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣6⃣
ከቂያማ ቀን መድረስ ምልክቶች ውስጥ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿وَإِذَا رَأَيْتَ رِعَاءَ الْبَهْمِ يَتَطَاوَلُونَ فِي الْبُنْيَانِ﴾

“ጫማ የሌላቸው፣ የታረዙና ድሃ የሆኑ የፍየል እረኞች በህንፃ ግንባታ ሲፎካከሩ ትመለከታለህ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 10



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
👍1
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልዓርቢዓዐ 2⃣3⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣6⃣
Audio
#ኪታብ ዑምደቱል አህካም
#በፈትህ አባቦራ መስጂድ
#ዘወትር ረቡዕ እና ጁመዓ ከመግሪብ- ዒሻ #በኡስታዝ ካሚል ጣሃ   ደርስ በድምፅ ክፍል #54 መከታተልና መቅራት ትችላላችሁ። #እንዳያመልጥዎ
ከወንጀሉ ምህረት ይደረግለታል!

ከሰዐድ ቢን አቢ ወቃስ (رضي الله عنه) ተይዞ፡ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَنْ قَالَ حِينَ يَسْمَعُ الْمُؤَذِّنَ : أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ، رَضِيتُ بِاللَّهِ رَبًّا، وَبِمُحَمَّدٍ رَسُولًا، وَبِالْإِسْلَامِ دِينًا ؛ غُفِرَ لَهُ ذَنْبُهُ﴾

“የሙዓዚንን ጥሪ ሰምቶ ከጨረሰ በኋላ እንዲህ ያለ፦ ‘ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ የሌለና እሱም አንድና አጋር እንደሌለው፤ ሙሃመድም የአላህ ባሪያውና መልዕክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ። በአላህ ፈጣሪነት በሙሃመድ መልዕክተኝነትና በኢስላም ሃይማኖትነት ወድጃለሁ።’ ከወንጀሉ ምህረት ይደረግለታል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 386



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 2⃣4⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣6⃣
👍2
ማስታወሻ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إذا رَأَيْتُمْ هِلالَ ذِي الحِجَّةِ، وأَرادَ أحَدُكُمْ أنْ يُضَحِّيَ، فَلْيُمْسِكْ عن شَعْرِهِ وأَظْفارِهِ.﴾

“የዙልሂጃ ወርን ጨረቃ ካያችሁና ከናንተ መካከል አንዱ ኡድሂያን ለማረድ ካቀደ ፀጉሩንና ጥፍሩን ከመቁረጥ ይቆጠብ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1977

ማስታወሻ፡ የዙልሒጃ ወር የሚገባው ዕሮብ ግንቦት 20 ወይም ሐሙስ ግንቦት 21 ነው።


https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
👍1
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 2⃣5⃣ #ዙልቀዓዳ 1⃣4⃣4⃣6⃣
Audio
#ኪታብ ዑምደቱል አህካም
#በፈትህ አባቦራ መስጂድ
#ዘወትር ረቡዕ እና ጁመዓ ከመግሪብ- ዒሻ #በኡስታዝ ካሚል ጣሃ   ደርስ በድምፅ ክፍል #55 መከታተልና መቅራት ትችላላችሁ። #እንዳያመልጥዎ
2025/07/13 22:56:36
Back to Top
HTML Embed Code: