Telegram Web
ወዳጄ ልቤ በግራ በኩል ያለው ደረጄ ሀይሌ ነው ልበልህ... በቀኝ በኩል ያለውም ፍቃዱ ከበደ ነው ልበልህ .. መሀል ላይ ያለውን በእውቀቱ ስዩም ነው ብልህ እንዴት ታምነኛለህ?
@fikren
@Rasyisak
ፍቅር እዚህ ቦታ 😍

ካልከሰመ ፍቅር ካልጠበበ አይምሮ
ሰው አይደለም ከሰው በአምሳሉ ተፈጥሮ
ያድራል ከእንስሳው እንዲህ ተነባብሮ
@fikren
@Rasyisak
የፈጣሪ ቀመር

አንዳንዴ የምትወደውን ነገርና ስትሰራ ይበልጥ ከማተኮር ያለብህ አንተ የምትሰጠው ላይ ነው። የምትወደውን ሰው ስትንከባከብ የምትቀበለውን ሳይሆን የምትሰጠው ፍቅር ላይ አተኩር ፤ የፈጣሪ ቀመር ደስ የሚለው አንተ ቀንሰህ ስታካፍል እሱ በተቃራኒ ደምሮ እያባዛ መስጠቱ ነው
@fikren
@Rasyisak
They are simply amazing

Big respect!
ሀገር አለችን የሀገር አውራ
ባባቶቻችን አፅም ወጋግራ
በሥጋና በደም አሻራ
የታነፀች የተሰራች
በጥበብ የደመቀች
በአብሮነት የተዋበች

በአንድነትዋ ፅናት
ጠላት የማይደፍራት

እናም

አባቶች ሞተው የሰርዋት
እኛ በጥጋብ አናፍርሳት

ቢገባን ኖሮ ትርጉሙ
ኢትዮጵያ ማለት ወርቅ ሰሙ
ህብር ነው በቃ አንድነት
ከብሔር በላይ ሰውነት

ኢትዮጵያ ማለት ቅኔ ትርጉሙ
አንድ ነው የሰው ልጅ መላው አለሙ

ልዩነት ቢሻለን ኖሮ
ያበጁት ነበር ድሮ

ኢትዮጵያ አናፍርሳት
ለጠላት አሳልፈን አንስጣት
በአንድነታችን ስንንሸራተት
ያኔ ነው ጠላት የሚያገኛት

የኢትዮጵያ ትጥቅ ማለት
ነውና ህብረ ብሔራዊነት

ጉራጌ ብቻ
ትግራይ ብቻ
ኦሮሞ ብቻ
አማራ ብቻ
ቤንሻንጉል ብቻ
ሶማሌ ብቻ
ወላይታ ብቻ
ሲዳማ ብቻ
ምን ጥቅም አለው ከማነስ ሌላ
የጎጃም ማር ሸዋ ላይ ካልተበላ
የጅማ ቡና መቀሌ ላይ ካልተጠጣ
የወለጋ ቅቤ ሸገር ድረስ ካልመጣ
የሶማሌ ግመል አፋር ካልተሸጠ
አንዱን ያንዱን ፍሬ ካልተለዋወጠ

መለያየት ሞት ነው

እንዴት ለብቻ ይበላል ?
እረ እንዴት ለብቻ ይኖራል?
ሰው እንዴት ከሰው ይርቃል ?
ከሰው ወዴት ይሸሻል?

ሰው ነው የሰው መድኃኒቱ
እንዳለው የአበው ተረቱ

የአባቶችህን ታሪክ ሰልስ
ያገርህ ክብር መልስ

በጠላትህ አዙሪት አትሽከርከር
እንደ አባቶችህ አገርህ አክብር

አትቁም በልዩነት ላይ
አብራላት የአንድነት ፀሐይ

ወድቀህ እንዳትገኝ አደራ
አንድነት አጥብቅ ታሪክ ሥራ

እንደ አሉላ እንደ ቴዎድሮስ
እንደ ምኒልክ እንደ ዮሐንስ

እንደ አብዲሳ አጋ እንደ አባጅፋር
አክሱም ነህ ሲሉ ድረስ ወደ ጎንደር
ጅማ ላይ ክተም ሸገር ላይ እመር
አሥመራ ያንተናት ሂድ ተሻገር

በዛላንበሳ በደብረቢዘን
ሱባኤ ግባ ካሻህ በግሸን
አክሱም ፂዮን ላይ ሄደህ ተቀባ
ወደ ቤተመንግስት ዘልቀህ ልትገባ

ነፍስህን ስጣት ለውድ አገርህ
ተምረህ ተገኝ ከአያት ካባትህ
አገር ሽጦ የት ይታደራል?
የተሸመተው የትስ ይበላል?

አገር እያለልህ በጥበብ የተሰራ
ተው አይበጅህም አፍርሼ ልስራ ።


ብርሃኑ ኮሬ(እመጓ)27/10/2013

@fikren
@Rasyisak
ዛሬ ቀኑ በጣም ደስ ይላል 😍
😍
አንድ ነገር አስታውስ ሰወች የሚሰጡህ ዋጋ ራስህ ባወጣኸው መሰረት ነው፤ውድ ነሳኝ ብለህ አስበህ ራስህን አክብረህ ከኖርክ ሁሉም ውድ እንደሆንክ አምኖ ያከብርሀል። ራስህን ካረከስክ እና ለራስህ ያለህ ግምት ዝቅ ያለ ከሆነ ምን ትጠብቃለህ ሁሉም ሰው ዝቅ አርጎ ያይሀል፤ ምርጫው ያንተ ነው።

ራስህን ከፍ አርገህ ሰዎች ባይቀበሉህ እንኳን ላንተ ያላቸው ክብር አይቀንስም እንደውም "በውስጣቸው እሱ ግን ራሱን እንደማን ነው ሚያስበው? እኔ የእሱ ድፍረትና በራስ መተማመን ቢኖረኝ የት እደርስ ነበር" ይላሉ። ወዳጄ አይነግሩህም እንጂ ድብን አርገው ነው ሚቀኑብህ። እራስህን አክብረው ወዳጄ

ሸጋ እና የተባረከ የስኬት ቀን ይሁንልን 💚💛

@fikren
@Rasyisak
....በህይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምርት መውሰድ ነው። መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቁጥር ሁሌም እንማር ፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንሁን፣ሁሌም ብሩህ ተስፋ ይኑረን።
ብልህ ሰው ዛሬ ላይ አዋቂ ነኝ፣ትክክል ነኝ እኔ ብቻ የሚል ሳይሆን ዛሬ ላይ የህይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው። ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ የሚኖር ሲሆን በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይሆን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው።

👉ሜሎሪና ገፅ 184👈

ውብ አሁን 💚💛
@fikren
@Rasyisak
Start ብላቹ ተሸላሚ አድርጉኝ 🙏 ሽልማቱን አካፍላቹሀለው
እቺ ግጥም ለምሽታችን 💚💛 በዛውም ከላይ ያለውን link start እያላችሁ 🙏 ለመሸለም የቀረኝ 10 ሰው ብቻ ነው። እስቲ አታሳፍሩኝ start እንዳላችሁ ስልካቹን በውስጥ መስመር ላኩልኝ ሽልማቱ ሲደርሰኝ ካርድ ይሞላቹሀል.........
.
.
.
ከሰው አንሼልሽ
ጭራሽን ስከተል ያዩኝ ሰዎች ሀሉ።
ይመክሩኝ ጀመረ
ራስህን አትጣል አትነስ እያሉ
እስኪ ንገሪልኝ
"ሽንፈት" እንደሆነ የአፍቃሪ ሰው ድሉ።

@fikren
@fikren
@Rasyisak

#አንwar
My channel
2025/02/03 14:37:30
Back to Top
HTML Embed Code: