tgoop.com/fikrhn/1111
Last Update:
❤️ #እኔና_አንቺ ❤
የደወልኩላት ስለናፈቀችኝ ነበር።ለብዙ ጊዜያት ሞክሬው ከራስ ጋር እየተጣሉ መኖር እየደከመኝ፣ማረፍያዬ ከሷ ውጭ አልታይህ እያለኝ ስረበሽ፣ይቅርታ ልላት ነበር ስልኬን ያነሳውት
....ያኔ ለመጨረሻ ጊዜ ላያት በሰልስቱ ስንገናኝ ''ላንተነትህ ነፍሴን ባልሰስት ለእኔነቴ ግን ህመምን ሰጠኸኝ።'አለች ባለ ማጥፋቴ ስለቀጣኸኝ አዝኛለው።" አትሂድ አልልህም መንገድ ምንኛ ሸክም እንደሆነ እነዚህ ስብርባሪ ቀናቶች በቂ ናቸው።
ሀሳብህ ምንድነው ? አለች ከመሄድ በማያስቀሩኝ ተስፋዎቿ ውስጥ በስስት ምናልባት እያየችኝ......
'አላውቅም አላውቅም እየሆነ ላለው ነገር ግን አዝናለው'
'የመጨረሻ ቃልህ ኢሄ ነው...? እንድታስብ ጊዜ የሰጠውህ መልስ አለቀ..? አለች በትኩረት እያየችኝ
'አ...አዎ'
በቃ አትጨነቅ የኮበለለን ልብ እግር አያስቆመውም አይደል ዝም ብዬ ነዋ የለፋውት(የማጣት ፈገግታ)።በነፍስ ካልተጣመሩ ስጋኮ ፈራሽ ነው፤ይቀየራል።እንደማልጨክንብህና ላንተ ልከፍል የነበረውን የህይወቴን ዋጋ ታውቃለህ፣ ብዙ ባወራ ደስታዬ ነበር ግን ምን ሊጠቅም ብለህ.... በቃ ቻው አልያዝህ አለች ድካምና ስብራት ባዘለው ፊቷ ልታቅፈኝ እየቀረበች።
ያኔ እውነት የመሰለኝ አለም እንደ ጉም ተኖ ከእጄ ወጣ። የሄድኩባቸው መንገዶች በሙሉ ወደ እርሷ እየመለሱኝ፣የመለሱኝ መንገዶች ደግሞ ከእርሷ አላደርስህ አሉኝ።የተለየ የመሰለኝ ነገር የተለየውበት ወንፊት ሆነ እንደ ብናኝ እፍታ ገለባዬ ብቻ ቀረ ማምሻዬ ላይ የትዝታና የናፍቆቷ ንፋስ እየወሰዱኝ ክቡር ፍቅሯን፤ ክቡር ክብሯን አጉልተው አሳዩኝ...ዋጋ የለሽ፣ራስ ወዳድ፣አሁንን ብቻና ለብልጭልጭ የተሸነፍኩኝ ብኩን መሆኔን የስብእናዋ ምስል አሳየኝ።ከሷ ውጪ መኖር ህልም ሆነብኝ።የእውነት ናፈቀችኝ፣የእውነት ላያት ጓጓው......ስልኬን አንስቼ ደወልኩላት ዝምምምም.......'የደወሉላቸው ደንበኛ ቁጥር አገልግሎት ላይ አልዋለም'
ደጋግሜ ሞከርኩኝ ግን ተመሳሳይ መልስ አዲስ ነገር የለውም።
ከወራት በኋላ ግን.........በሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ በፈገግታ ታቅፋ አየኋት....ሌላ ህይወት...
.
.
.
#ሻሎም ትዝታዬ..... #ሻሎም የኔ ናፍቆት......Shalom.....😔
የሁላችንም ልክ በሀቃችን የተመዘነ ነው::
''ሌላ ለመሙላት አጉድለን ስንሄድ ነው የቀነስነው የሚወሰድብን።''
✍....... #Jo_ሊ
@fikrhn
@fikrhn
@fikrhn
BY እኔና አንቺ
Share with your friend now:
tgoop.com/fikrhn/1111