FIKRHN Telegram 1124
#ሰሎሜ

ልጅ ሆኜ ነው በዝግታ ስታለቅስ የምሰማት፡በዝምታዋ ውስጥ ተኮራምታ ስመለከት ገና በስድስት አመቴ ማንባትን እፈራ ነበር:: የሀዘን ቃልን ከሷ ፊት በላይ የሚገልጽ ማንንም አላየሁም "በወደቀ ህይወት ውስጥ የተገኘ ሴትነት" ትላለች በእሮሮዎቿ መሀል..... በተከፋችበት ቀን ሁሉ አባቷን ትናፍቃለች፤መነሻዋን አብርቶላት መዳረሻውን ላጠፋችበት የአባቷ ቃል ሰርክ በቁጭት እንደነደደች ነው።ብዙ ጊዜ የተነፈገቻቸውን ነገሮች አብዝታ እያሰበች፣ጣርያው ከተበሳሳው ታዛዋ ስር ቁጭ ብላ ስትተክዝ አያታለሁ።

መሞንጨር የጀመርኩት በእሷ ታሪክ ነው።የመጀመርያ ድርሰቴ እሷ ናት።በአይኔ ያየሁት ማንነቷን በብእር ማቅለም ህመሟን ስለሚያሳንስብኝ አልጽፈውም ነበር።
ልጅነቷን፣ሴትነቷን፣ቤተሰብ ማጣትን እሷን ሆኜ ነው ያደግኩት ጥንካሬና ስብራትን ዘወትር ሳትነግረኝ ከሁኔታዋ እማር ነበር።መለየትና ብቸኝነትን ነፍስ እስከማውቅበት ጊዜዬ ድረስ በደንብ አለማምዳኛለች።

በትኩስ ገላዋ በሙቀቷ ነደው በወጣትነቷ የተጣቧት፡ ከጭኖቿ ስር ለመገኘት የሚደረድሩትን የመሃላ ፍሬ አልባ ንግር፡ በስሜት የተወጠረ ስጋቸውን ለማስተንፈስ የክህደት ቃልን ሰጥቶ የከሸፈ ስጦታቸውን ሲቸሯት ከኛ ቤት አጥር ቀዳዳ አሻግሬ እያየሁ ነው የኖርኩት።የምታፈቅራቸው ወንዶች በሙሉ እንደ በረዶ አይበረክቱላትም ጸሃይ ይመስል ከፍላጎታቸው በኋላ ይቀልጣሉ ሁሉም በጊዜ ትተዋት ይበራሉ። በየዋህነት ትወዳቸዋለች እነሱ ግን በብልጠት ኑሮዋን ያከብዱባታል።ሁሉም የመንደራችን ሰዎች በሙሉ ውጣ ውረዷን ከመረዳት ይልቅ የፍርድ ሚዛናቸው ላይ ማስቀመጥ ይቀላቸዋል።
ሳይገባቸው ይረዷታል፡:" የአበባነት ዘመኗ ኮስምኖ የደረስኩበት ወጣትነቴ የመልካምነትን ኢ-አጸፋ አሳይቶኛል። ዘመኗ ዘግይቼም ቢሆን ተከትሎኛል። በህጻንነቷ ያጣቻት የእናቷን ጠረን ከቶ አታውቀውም ባላሳደገቻት የእናቷ ምትክ በጉስቅልና ዘመኗ የተነፈገቻቸው የኑረቷ ብሶት ሔዋንነቷን ከስሩ ሊቀጩባት ይታገሏታል።እናትነት ህልሟ ነበር።ከነ ህመሟ ጠንካራ ናት።

በውርስ ከምትኖርበት የቀበሌ ቤት ጎረቤታቸው ሆኜ በጉልምስናዋ ጎርምሻለው ነፍስ ባላወቅኩበት እድሜዬ እንባና መከፋቷን ከገላዋ ላይ እየተመለከትኩኝ፡እየሰማው ነው ያደግኩት።ሰዎችን በሚገባ ያወቅኳቸው በራሴ ትርምስ ሳይሆን በሷ ታሪክ ነው።
"ሳታውቅ ተረድቻት ሳልናገር ኖርኩት።" ከአመታት ቆይታ በኋላ ወደ እናቴ ቤት ሄድኩኝ የጓጋሁት ግን ሰሎሜን ለማየት ነበር::ትናንቷንና ዛሬዋን ላነጻጽር፡በአሮጌ ቆርቆሯችን አጥር እንደ ልጅነቴ በቀዳዳው ተመለከትኩኝ።እድሜዋ ገፍቷል ጸጉሯ:ቆዳዋ፡ሁናቴዋ እርጃናዋን እያጎሉት ነው...........#ሰሎሜ! እንባዬ መጣ አሁንም በረንዳዋ ላይ ተቀምጣለች......አሁንም ተክዛለች........

........ #ፍርድኤ(Joሊ)

@fikrhn
@fikrhn
@fikrhn

tgoop.com/fikrhn/1124
Create:
Last Update:

BY እኔና አንቺ

Share with your friend now:
tgoop.com/fikrhn/1124

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Healing through screaming therapy “[The defendant] could not shift his criminal liability,” Hui said. Channel login must contain 5-32 characters The administrator of a telegram group, "Suck Channel," was sentenced to six years and six months in prison for seven counts of incitement yesterday.
from us

Telegram እኔና አንቺ
FROM American