tgoop.com/finding_hubullah/797
Last Update:
ኢብራሂም ቢን አድሃም ረሂመሁሏህ ጋር የተደረገ ቃለ መጠየቅ:-
ሰውየው:- በረካ የሚባል ነገር ጠፍቷል የለም አላቸው::
ኢብራሂም ቢን አድሃምም ረሂመሁሏህ በዙሪያህ ውሻና በጎችን አይተሃልን? አሉት
ሰውዬውም አዎ! አለ::
ኢብኑ አድሃምም ረሂመሁሏህ የትኞቹ ናቸው በብዛት የሚወልዱት? አሉት::
ሰውየውም ውሻ እስከ ሰባት ትወልዳለች በጎች ግን እስከ ሶስት ነው የሚወልዱት አላቸው::
ኢብራሂም ቢን አድሃምም ረሂመሁሏህ በዙሪያህ ብትመለከት የትኞቹን በብዛት ታያለህ? አሉት::
ሰውዬውም በጎች በብዛት ይታያሉ አላቸው::
ኢብን አድሃምም ረሂመሁሏህ በብዛት የሚታረዱትና ቁጥራቸው የሚቀንሰው በጎች አይደሉምን? አሉት
ሰውዬውም አዎ! አላቸው::
ኢብን አድሃምም ረሂመሁሏህ በረካ ማለት ይሄ ነው አሉት::
ሰውዬውም ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል ? (በውሾች ፋንታ እንዴት በጎች ሊበዙ ቻሉ)? ይላቸዋል::
ኢብኑ አድሃምም ረሂመሁሏህ በጎች በግዜ ወደ በረታቸው ገብተው በሌሊቱ መጀመሪያ ላይ ይተኙና ከፈጁር ቀድመው ይነሳሉ::
የዛኔ የእዝነት ወቅት ስለነበር በረካ በእነሱ ላይ ይወርዳል::
ውሾች ግን ሌሊቱን ሙሉ ሲጮኹ ያነጉና የፈጁር ወቅት ሲገባ ይተኛሉ የእስዝነቱም ግዜ ያመልጣቸውና በረካውንም ያነሳባቸዋል አሉት::💚🙏🏽
ትምህርቱን ለእናንተ ተውኩት...!😋😊
https://www.tgoop.com/finding_hubullah
BY የአላህን ውዴታ ፍለጋ
Share with your friend now:
tgoop.com/finding_hubullah/797