tgoop.com/finottebiirhan/7752
Last Update:
ዓሣ አንበሪው ዮናስን በሦስተኛ ቀኑ ከነነዌ የባህር ዳርቻ ሲደርስ ተፋው። ዮናስ እግዚአብሔርን አመሠገነ። ወደ ነነዌ ከተማ ገባ ሕዝቡንም ሰበከ። ከህጻን እስከ አዋቂ፣ ከእንስሳ እስከ ሰው፣ ከሎሌ እስከ ንጉሥ ድረስ አዳመጡት። በክፋታቸው ተጸጸቱ። ጾሙ፣ ራሳቸውን ስለ እግዚአብሔር አዋረዱ። እግዚአብሔርም ማራቸው።
ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይኾን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡ ስለኾነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመኾኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ኾነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡
ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኀጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡
አምላካችን እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶ፣ ልመናችንን ተቀብሎና ጾማችንን አስቦ ምሕረትን ያድርግልን፤የነነዌ ህዝብን በምህረቱ የጎበኘ ቸሩ አምላካችን ሀገራችንን ህዝባችንንም በምህረት አይኑ ይጎብኝልን ቸርነቱን ያብዛልን ፆሙንም ለጥያቄያችን መልስ የምናገኝበት የበረከት ፆም ይሆንልን ዘንድ የአምላካችን ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን አሜን!!! 🙏
መገናኛ ብዙኅን ንዑስ ክፍል
🍁️️️️🌿🍁️️️️🌿✨✨✨🍁️️️️🌿🍁️️️️🌿✨✨✨
BY ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
Share with your friend now:
tgoop.com/finottebiirhan/7752