FINOTTEBIIRHAN Telegram 7826
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
🌹ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አድዋ ድል🌹
                     💚💛❤️
እንኳን ለታላቁ ሰማዕት የኢትዮጵያ ገበዝ ለሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል አደረሳችኹ!!!

ልመናው ጸሎቱ በረከቱ አማላጅነቱ በዕውነት ለዘለዓለሙ ይደረግልንና ቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረገው ተአምር ይኽ ነው፡፡

በዚያን ወራት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 1854 ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ በነገሡ በ26 ዓመት የምኒልክ የጦር አለቃ ገበየሁ ድል ከአደረጋቸው በኋላ እንደገና ምኒልክን ወግተው ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ሊገዙ የሮም ሰዎች መጡ፡፡

ከዚኽም በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ "ሀገሬ ኢትዮጵያን እወዳለኹ የሚል ኢትዮጵያዊ ኹሉ ባስቸኳይ ይነሣ መስቀለ ሞቱንም ተሸክሞ ይከተለኝ እግዚአብሔር የወሰነልንን የባሕር ወሰን አልፎ ሀገር የሚያጠፋ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት መጥቷልና" ሲሉ ዓዋጅ አስነገሩ፡፡

ዳግመኛም በፈረሶቻቸው መጣብር ላይ በጦራቸው አንደበት ላይ በጋሻቸው እምብርት ላይ የመስቀል ምልክት እንዲያደርጉ ጭፍሮቹን አዘዟቸው። መስቀል ጠላትን ድል አድራጊ እንደኾነ አስቀድሞ ያውቁ ነበርና፡፡ ከዚያም ተነሥተው ወደ ትግራይ ክፍለ ሀገር ዘመቱና ከትግራይ አውራጃዎች አንዷ የምትኾን አድዋ ከምትባል አገር ደረሱ፡፡

የሣህለ ማርያም ዳግማዊ ምኒልክ ሚስት ወለተ ሚካኤል እቴጌ ጣይቱም በንጉሡ ትዕዛዝ ታቦተ ጊዮርጊስን አስይዘው ከሊቀ ጳጳሱ ከአባ ማቴዎስ እንዲኹም ከቀሳውስቱና ከመነኮሳቱ ጭምር ከንጉሡ ጋር ወደ ጦርነቱ ተጓዙ፡፡
በዚኽም ጊዜ የአክሱም ጽዮን መነኮሳትና ካህናት የእመቤታችንን ሥዕል ይዘው ወደ ንጉሡ ወደ ምኒልክ መጥተው ከሊቀ ጳጳሱ ከአቡነ ማቴዎስ ጋር ተቀላቀሉ። ከዚያም ሌሊቱን ሙሉ ጸሎተ ምሕላ ሲያደርሱ አደሩ፡፡

ቅዳሜ ሌሊት ለእሑድ አጥቢያ የካቲት 22 ንጉሡ ሣህለ ማርያም ምኒልክ የጦር ልብሳቸውን ለብሰው ከሠራዊታቸው ጋር ወደ ጦር ግንባር ኼዱ፡፡ ከዚያም ከሮማውያን የጠላት ጦር ጋር ተገናኝተው ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጦርነቱን ጀመሩ፡፡ የንጉሡ የሣህለ ማርያም ምኒልክ ሚስት ወለተ ሚካኤል እቴጌ ጣይቱም ሌሊት በታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስና በእመቤታችን ሥዕል ፊት በጸሎትና በስግደት አድረው ሲነጋ ወደ ጦርነቱ ቦታ በመኼድ እጅግ በሚያስደንቅ አነጋገራቸው ኃይለ ቃል በጦርነቱ መካከል እየተገኙ ለንጉሡ ወታደሮች የሞራልና የብርታት ድጋፍ ይሰጡ ነበር፡፡ በዕውነትም ለተመለከታቸው ኹሉ እንደ ኃይለኛ ተጋዳይ አርበኛ ይመስሉ ነበር እንጂ የሴቶች የተፈጥሮ ባሕርይ በእርሳቸው ላይ አይታይባቸውም ነበር፡፡

የንጉሡም ወታደሮች የንግሥቲቱን የጀግንነት አነጋገር በሰሙ ጊዜ በእሳት ላይ እንደተጣደ የብረት ምጣድ ልባቸው ጋለ፤ ይልቁንም ላም እንዳየ አንበሳና የፍየል መንጋ እንዳየ ነብር እየተወረወሩ በጦርነት መካከል በመግባት የጠላትን ጦር በሰይፍ ይጨፈጭፉት ነበር፡፡ መጽሐፍ ሹመቱን ሽልማቱን ያየ አርበኛ ከጦርነት ከሰልፍ ወደኋላ አያፈገፍግም ብሎ ተናግሯልና፡፡

በዚያም ጊዜ ንጉሡ ሣህለ ማርያም ምኒልክ በጦርነቱ መካከል ሳሉ ሊቀ ጳጳሱ አባ ማቴዎስ እንዲኹም የአክሱም መነኮሳትና ሌሎቹ ካህናት በሙሉ ታቦተ ጊዮርጊስንና ሥዕለ ማርያምን ይዘው ከንጉሡ በስተኋላ በደጀንነት ቆመው ጸሎተ ምሕላ ያደርሱ ነበር፡፡ ንግሥቲቱ ወለተ ሚካኤል እቴጌ ጣይቱም በጸሎት ጊዜ በመዓልትም በሌሊትም ከእነርሱ አልተለዩም ነበር፡፡

የጽዮን አገልጋዮችም በእግዚአብሔር የሕጉ ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር፡፡
በዚኽም ዕለት ይኸውም የካቲት 23 ቀን በሮማውያንና በኢትዮጵያውያን መካከል ከፍተኛ ጦርነት ኾነ። በዚኽም ጊዜ በሰማይ ታላቅ ተአምር ተደረገ። ማለትም የቀስተ ደመና ምልክት ታየ። ከዚያም ከቀስተ ደመናው ውስጥ መልኩ አረንጓዴ የሚመስል ጢስ ይወጣ ነበር፡፡ ከዚኽም ጢስ ውስጥ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ያለ ድምጽ ተሰማ፡፡
ከዚኽም የነጎድጓድ ድምፅ የተነሣ በሮማውያን ወታደሮች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሽብር ኾነ። ለመዋጋትም አልቻሉም፤ ይልቁንም ኃያሉ ገባሬ ተአምር ማር ቅዱስ ጊዮርጊስ በአምባ ላይ ፈረስ ተቀምጦ ከነፋስ ሩጫ ይልቅ እየተፋጠነ በዓየር ላይ በተገለጸ ጊዜ በግምባራቸው ፍግም እያሉ ወደቁ፡፡

"የኢትዮጵያ ሕዝብ አምላካቸው ሊረዳቸው መጣ እንግዲኽ ማን ያድነናል?" አሉ። ምድር ጠበበቻቸው በዚኽም ጊዜ የኢትዮጵያ ሠራዊት የሮምን የጦር ሠራዊት ፈጁዋቸው፡፡ የተረፉትንም ማረኳቸው ፈጽመውም እስኪያጠፏቸው ድረስ በሮማውያን ላይ በእግዚአብሔር ሥልጣን የኢትዮጵያውያን እጅ እየበረታች ኼደች፡፡

ከዚኽም በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ሣህለ ማርያም ምኒልክ በእግዚአብሔር ኃይልና በቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት የሮማውያንን የጦር ሠራዊት በጦርነት ድል አድርገው የድል አክሊል ተቀዳጁ፡፡ ስለዚኽም በዳዊት የምስጋና ቃል "የድል ዘውድ ያቀዳጀኝን እግዚአብሔርን ባለ ዘመኔ አመሰግነዋለኹ፤ ለፈጣሪዬም እዘምራለኹ" አለ። ሕዝቡም ኹሉ "በክብር ከፍ ከፍ ያለ እግዚአብሔርን በፍጹም ምስጋና እናመሰግነዋለን፤ የሮማውያንን ኃይል ቀጥቅጦ አጥፍቷልና ሠረገሎቻቸውንም ሠባብሯልና ፤ ሠራዊቱንም ኹሉ በምድር ላይ በትኗልና!" እያሉ አመሰገኑ፡፡ በፈጣሪያቸው በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል በጦርነቱ መካከል የረዳቸውን ቅዱስ ጊዮርጊስንም በፍጹም ማድነቅ አደነቁት፡፡

የሮማም የጦር ሠራዊት በኢትዮጵያዊያን ፊት ተዋረዱ። ዳግመኛም በኢትዮጵያ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም፡፡ በምኒልክም ዘመነ መንግሥት ኢትዮጵያ ከጦርነት ለዓርባ ዓመት ያኽል ዓረፈች፡፡
የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ምኒልክም ከዓድዋ ጦርነት ከተመለሱ በኋላ አዲስ አበባ ከተማ መካከል በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ቤተክርስቲያን አሠሩ። ስሟንም "ገነተ ጽጌ" ብለው ሰየሟት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በጦርነት ቦታ ኹሉ ይረዳቸው ነበርና፡፡

ልመናው ክብሩ በእኛ ለዘለዓለሙ በዕውነት ይደርብን!!! ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን

ምንጭ፡ ተአምረ ጊዮርጊስ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

tgoop.com/finottebiirhan/7826
Create:
Last Update:

BY ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

Share with your friend now:
tgoop.com/finottebiirhan/7826

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Telegram iOS app: In the “Chats” tab, click the new message icon in the right upper corner. Select “New Channel.” A few years ago, you had to use a special bot to run a poll on Telegram. Now you can easily do that yourself in two clicks. Hit the Menu icon and select “Create Poll.” Write your question and add up to 10 options. Running polls is a powerful strategy for getting feedback from your audience. If you’re considering the possibility of modifying your channel in any way, be sure to ask your subscribers’ opinions first. In handing down the sentence yesterday, deputy judge Peter Hui Shiu-keung of the district court said that even if Ng did not post the messages, he cannot shirk responsibility as the owner and administrator of such a big group for allowing these messages that incite illegal behaviors to exist. Each account can create up to 10 public channels Telegram channels fall into two types:
from us

Telegram ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
FROM American