Forwarded from Deleted Account
«ወልዴ የኦርቶዶክሳውያን ቻናሎች ፕሮሞሽን አገልግሎት»
★ ቻናልዎን ማስመዝገብ ይፈልጋሉ ? እንግዲያውስ ፕሮሞሽናችንን ይቀላቀሉ።
➲ 100 - 500 አባላቶች
️➲ 500 - 1000 አባላቶች
➲ 1000 - 500 አባላቶች
➲ ️5000 - 10,000 አባላቶች
➲ ️10,000 - 20,000 እንዲሁም ከዛ በላይ አባላቶች ያሏቸው የቅድስት ቤተክርስትያን ደግሟን እና ቀኖናዋ፣ ትውፍትትዋን ጠብቀው መንፈሳዊ ትምህርት ለምእመናን የሚያቀርቡ ቻናሎች ተቀብለን እየመዘግብን እና በታማኝነት እያሳደግን እንገኛለን!
♥ ፕሮፕሮሞሽኑን ይቀላቀሉ ቻናልዎን ያስመዝግቡ ያሳድጉ !
🕊 • WELL የኦርቶዶክሳውያን ቻናሎች ፕሮሞሽን አገልግሎት • 🕊
@WeldyePromotion
@WeldyePromotion
Ⓜ ቻናልዎን ለማስመዝገብ : –
♡ @W43686155 ወይም
♡ @Enate_MaryamBot ይጠቀሙ ♡

Forwarded from Josy Quality Button
«ፎቶ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ» መንፈሳዊ ቻናል ድንቅ ድንቅ ስእለ አድኅኖ ይዞላችሁ ቀርቧል። የማንን ይፈልጋሉ ?
❖ መስከረም 29 በክርስቶስ ስም አንገቷን ለሰይፍ የሰጠችው የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ በቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ❖
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖✔💥 ስለ ቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ቀደምት ሊቃውንት መስክረዋል፤ ሥዕሏን ሥለዋል፤ መልክእ ደርሰውላታል፤ የዚኽች ቅድስት ሰማዕት አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትኖስያና ይባላሉ፤ በብፅዐት ያገኟት ልጅ በመኾናቸው በተወለደች በሦስት ዓመቷ በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተ ክርስቲያን አድጋለች።
💥 እጅግ መልከ መልካም ነበረች። ቅዱስ ጳውሎስ “ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፥34) ያለውን አስባ ራሷንም በድንግልና ሕይወት ለክርስቶስ ለይታ ነበር። ከ284- 305 በሮም የነገሠው ከሓዲው ድዮቅልጥያኖስ መልኳ ውብ የኾነች ድንግል ሊያገባ ፈልጎ ቆንጆ መርጠው ያመጡለት ዘንድ አገልጋዮቹን አዘዛቸው፡፡
❖✔💥 እነርሱም በፍለጋቸው በሮሜ አገር ባለች ቤተ ክርስቲያን ቅድስት አርሴማን በማግኘት ሥዕሏን ሥለው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ርሱም በእጅጉ ተደስቶ እንዲያመጧት በማዘዝ ወደ ሰርጉም እንዲመጡ ለመኳንንቱ ላከ፡፡
❖✔💥 ርሷና ዐብረዋት የነበሩትም ደናግል ይኽነን በሰሙ ጊዜ በማዘን ጌታችን በወንጌል “በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ” (ማቴዎስ 10፥23) ያለውን አስበው ድንግልናቸውን ይጠብቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በመለመን ከሮም ተነሥተው በስዉር የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደነበረችው ወደ አርመን ሸሽተው ኼደዋል፡፡
💥 ቅድስት አርሴማም ወደ አርመንያ ሀገር በገባች ጊዜ ከሓድያኑ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የሚያምኑትን ክርስቲያኖችን ላይ መከራን ሲያጸኑባቸው ተመለከተችና
አምላካችን ክርስቶስ "ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።" (ማቴ 10:32-33) ያለውን በማሰብ “እኔ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የማምን ክርስቲያን ነኝ” በማለት መሰከረች፡፡
❖✔💥 የመልኳን ደም ግባትም በማየት ንጉሥ ድርጣድስም ለራሱ ስለተመኛት አምልኮቷን እንድትተው፣ ክርስቶስን እንድትክድ በብዙ ሽንገላን ሊሸነግሏት ቢሞክሩም አልኾነላቸውም፤ ከዚያም ፈርታ ትክዳለች ብለው በማሰብ ክርስቲያኖች ለአናብስት ወደሚጣሉበት አደባባይ በመውሰድ የተራቡ አናብስትን ሲለቅቋቸው ነቢዩ ዳንኤል እንዳደረገው በጸሎቷ ኀይል አናብስቱ ወደ ንጉሡ ወታደሮች በመወርወር ብዙዎችን ገድለዋል፤ ከዚያም ከሥሯ ተንበርክከው ሰግደውላታል፡፡
❖✔💥 ንጉሡ በዚኽ ባይኾንለት በግድ ለጣዖታቱ እንድትሰግድ አሳስሮ አማልክቱ ወዳሉበት ቤተ ጣዖት ሲወስዳት፤ በመስቀል ምልክት ብታማትብ በጣዖታቱ ላይ ዐድረው ሰዎችን የሚያስቱ አጋንንት እየጮኹ ሲወጡ ጣዖታቱ በመላ እየተሰባበሩ ወድቀዋል፤ ከዚያም በረኀብ ለመቅጣት ወደ እስር ቤት ቢያኖሯት መልአኩ ኅብስትን እንደ ኤልያስ መግቧታል፡፡
❖✔💥 ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት እየጐተቱ ወሰዷት፤ “ወተንሥአ ንጉሥ እማዕከለ ዐውድ ወአኀዛ ከመ ያብኣ ውስተ ጽርሑ ለአርሴማ ድንግል ወሶቤሃ ኀደረ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕለ አርሴማ ቅድስት ወገደፈቶ ውስተ ምድር” ይላል፤ ንጉሡ ይዞ ወደ እልፍኙ ሊያስገባት ከአደባባይ ተነሥቶ ድንግል አርሴማን በያዛት ጊዜ፤ ዳዊት ጎልያድን በእግዚአብሔር ኃይል እእንዳሸነፈ ቅድስት አርሴማም እላይዋ ላይ ባደረው የእግዚአብሔር ኀይል በምድር ላይ ጣለችው፤ ያን ጊዜ በዐፍረት ኾኖ ራሷ ይቈረጥ ዘንድ አዘዘ።
💥 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ላይ "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።" (ሮሜ 8:35-36) እንዳለ ያደረሱባት መከራ ሁሉ ከክርስቶስ ፍቅር ሊለያት አልቻለም።
💥 ከዚያም የክብር ባለቤት ጌታችን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን አስከትሎ ተገለጸላት። በቅዱስ መጽሐፍ ላይ “አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ፤” (ዘዳግም 7፥9) እንደሚል
ስሟን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ምሕረትን እንደሚያደርግ ቃል ኪዳንን ከገባላት በኋላ መስከረም 29 በ290 ዓ.ም. አንገቷን ተቈርጣ የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጅታለች።
💥 አስቀድሞ በኢሳይያስ ዐድሮ "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" (ኢሳ 56:4-5) ብሎ እንደተናገረ በስሟም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ታኅሣሥ 6 ቅዳሴ ቤቷ ሲከበር፤ የከበረ ሰውነቷ ዛሬ ድረስ በአርመን አለ፡፡
❖✔💥 በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ እየታነጹ ከክርስቶስ አምላኳ በተቀበለችው አማናዊ ቃል ኪዳንም ብዙ ሕሙማን እየተፈወሱ በረከቷን እያገኘን እንገኛለን፡፡ ታቦቷ ካለባቸው እጅግ ብዙ በረከት ካላቸው የሰማዕቷን ገድል ከተረጎምኩባቸው ቦታዎች መኻከል በደቡብ አፍሪካ በረስተንበርግ፤ በዱባይ እና በአውሮፓ ስኮትላንድ ግላስኮ፤ በሰሜን አሜሪካ ቨርጂንያ መካነ ሰማዕት የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ይገኛሉ፨
❖✔💥 ካመሰገኗት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ሊቃውንት ውስጥ ሊቁ አርከ ሥሉስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሚጠቀሱ ሲኾኑ፦
❖✔💥 ሊቁ አርከ ሥሉስም ይኽነን የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ሲመሰክር፡-
✍️ “በጾታ ኅሩያን ዕደው እንዘ ተኀብሪ ጾታ
እንበለ ትፍርሂ ምንተ ብልኀተ ኲያንው ወሰይፍ ልሳነ መንታ
ዘፈጸምኪ ስምዐ በእንተ ኢየሱስ ንጉሠ ኤፍራታ
ሰላም ለኪ አርሴማ ምስለ እምኪ አጋታ
ወለደናግል ሰላም ምስሌኪ ዘሞታ”
(በተመረጡ ወንዶች ወገንነት ተባብረሽ ኹለት አፍ ያለው ሰይፍንና የጦሮችን ስለትን ምንም ሳትፈሪ የኤፍራታ ንጉሥ ስለሚኾን ስለ ኢየሱስ ምስክርነት የፈጸምሽ አርሴማ ከእናትሽ ከአጋታ ጋር ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ ካንቺ ጋር የሞቱ ለኾኑ ደናግል ሰላምታ ይገባል) በማለት በኅብረት አመስግኗቸዋል፡፡
❖✔💥 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን ታላቅ መጽሐፉ ላይ፦
✍️“ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ
ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ
ዘፈጸመት ገድላ በጻማ
ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡
(ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው) በማለት ያወድሳታል፨
❖✔💥 እኔም በዚኽ ጽሑፌ ላይ ሊቁ አርከ ሥሉስ ለቅድስት ጣጡስ ሰማዕት በሰጣት ምስጋና ለሰማዕቷ አርሴማ በመስጠት አመስግኜያት ጽሑፌን አበቃለሁ፨
❖✔💥 “ሰላም ለአርሴማ ሥርጉተ አፍኣ ወውስጥ
በምግባር ፍጹም ወበሃይማኖት ስሉጥ
አመ ኮነት ሰማዕተ እንበለ ተምያጥ
አሕምሞ ሥጋሃ ኢክህሉ አስዋጥ
ወጸበለ እግራ ለሐሱ አናብስት መሠጥ”
(በፍጹም ምግባርና በፍጹም ሃይማኖት በውስጥና በውጪ ያጌጠ

✔
ፍቅር ሲመነምን ውጤቱ የበዙ ጥፋቶችን ማስከተል ይሆናል!!
የፍቅር እጦት ቂም እና ጥላቻን ይፈጥራል። ይህ ደግሞ በኃጢአት ሐሴት ማድረግን ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ በመሰናከሉም ልብህ ሐሴት አያድርግ" ምሳ 24፥17
ሌላው የፍቅር እጦት ውጤት ቁጣ እና ክፋት ነው። እንዲህ ያለው ሁኔታ ስድብን፣ ጠብን፣ ግድያን፣ ነቀፋን፣ ማዋረድንና ስም ማጥፋት ማስፋፋትን ያስከትላል። ከዚህ በተጨማሪ የፍቅር እጦት ወይም ጉድለት ወደ ቅንዓት፣ ወደ አላዋቂነት፣ ወደ ኩራት፣ ወደ ጽናትን ማጣትና ወደ ጭካኔ ይመራል።
ለእግዚአብሔር የሚሆን ፍቅርን ማጣት በብዙ ጉዳዮች ውስጥ ሊገለጥ ይችላል፤ ከእርሱም መካከል ጸሎትን፣ መጽሐፍ ቅዱስንና ቤተ ክርስቲያንን መርሳት ጥቂቶቹ ናቸው። በእግዚአብሔር ፊት መቆምን ማጣት እና በእግዚአብሔር መንግሥት ፈጽሞ ሐሴት አለማድረግ ሌሎቹ ጉድለቶች ናቸው።
#ብጹዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

ምክረ አበው:
☞ የአንቀጸ ብፁዓን ቅደም ተከተል ☜
ጌታችን ትእዛዛቱን የሰጠን ወርቃማ በኾነ ቅደም ተከተል ነው፡-
✝ አስቀድሞ “በመንፈስ ድኻ” የኾነ ሰው በርግጥ ለገዛ ኃጢአቶቹ “ያዝናልና”፤
✝ “የሚያዝን” ሰውም “የዋህ”፣ “ጽድቅን የሚራብና የሚጠማ” እንደዚሁም “የሚምር” ይኾናልና፤
✝ “የሚምር”፣ “ጽድቅን የሚራብና የሚጠማ” እንደዚሁም “በልቡ የሚዋረድ” ሰውም በርግጥ “ልበ ንጹህ” ይኾናልና፤
✝ “ልበ ንጹህ” ሰውም “አስተራራቂ” ጭምር ይኾናልና፤
✝ እነዚህን ኹሉ ምግባራት የያዘ ሰውም መከራዎችን ድል መንሣት ይቻለዋልና፤ ነቀፋ ሲደርስበት አይታወክምና፤ ስፍር ቊጥር የሌላቸውን ፈተናዎችም መቋቋም ይችላልና፡፡
የማቴዎስ ወንጌል ፲፭፥፱

"አሀደ ለከ ወአሀደ ለሙሴ ወአሀደ ለኤልያስ ንግበር ማህደረ"
👉" ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 17:4)
2/ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው?
✔ቡሄ ማለት ብራ ፣ብርሃን ፣ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሀነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ ፣ብርሃን ደማቅ የሚል ፍች ተሰጥቶታል ፡፡
✔ አንድም ቡሄ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማዩም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡★ ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ
✔አንድም ቡሄ ቡኮ/ሊጥ ማለት ነው፡፡በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ /ሙልሙል ተጋግሮ የሚያደልበት በዓል ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
3/የደብረታቦርን በዓል ለምን እናከብራለን?
👉ደብረታቦር ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን ፣ዮሐንስንና ጴጥሮስን ወደ ታቦር ተራራ ካወጣቸው በኋላ በዚያም ብርሃነ መለኮቱ የተገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክ መሆኑን ያሳየበት ዕለት ስለሆነ እናከብረዋለን፡፡
4/በቤተክርስቲያናችን ቡሄ ህፃናት ሲዘምሩ የሚሰጣቸው ሙልሙል ምንን ምሳሌ ያደረገ ነው ?
✔በበዓለ ቡሄ ብዙ ታምራትና ሚስጢራት እንዲሁም ምሳሌዎች የተገለጡበት ዕለት ነው ፡፡ ከእነዚህም መካከል፦
➊ሙልሙል ዳቦ ፦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ እለት በደብረታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሠላቸው /ጌታችን አካባቢውን በብርሃን ሞልቶት ስለነበር/በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበኩ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሀን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያል፡፡
_አንድም እንደ ሀዋሪያት የምስራች ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው ቡሄ በሉ የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ፡፡ማቴ 10÷12በደረሳችሁበት ሁሉ ተመገቡ ብሏልና ጌታችን፡፡
➋ ህፃናቱ የደቀ መዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡
➌ የህፃናት መዝሙር የምስራች ወይም ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡
➍ችቦ ማብራት የጌታችን የብርሀነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡አንድም በደብረታቦር ተራራ የነበሩት ህፃናት ወላጆች ይዘውት የመጡት ችቦ ነው፡፡
➎ ጅራፍ ማጮህ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው 1/ ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋት ና ህማም እናስብበታለን
2/ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓዳማ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
/ማስታወሻ ፡ጅራፍን በርችት መቀየር ኢትውፊታዊ ነው፡፡የቡሄ በሉ ግጥም ስድብና ዛቻ ያዘለ መሆን የለበትም /
፡፡
➏በታቦር ተራራም እየሱስ ቅና ሚስጥሮችን አሳይቷል ፡፡ከእነዚህም መካከል
✔ቡሄን በተራራ ያረገበት ምክንያት ተራራ የወንጌል ፣የመንግስተ ሰማይ ፣ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡ተራራ ሲወጡት ይከብዳል ከወጡት በሀላ ግን ሜዳውንና ጭንጫውን ኮረብታውን ሁሉ ሲያሳይ ደስ ይላል፡፡ወንጌልንም ሲማሯት ታጽራለች ፥ከተማሯት በሀላ ግን ጽድቅና ሀጢያትን ለይታ ስታሳውቅ ደስ ታሰኛለች፡፡
✔አንድም ተራራን በብዙ ፃዕር እንዲወጡት መንግስተ ሠማይንም በብዙ መከራ ያገኟታልና ነው፡፡
➐ በዚህም ተራራ ከነቢያት ሁለቱን /ሙሴና ኤልያስን/ ከሀዋሪያት ሶስቱን/ ያዕቆብን ፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን/ ማምጣቱ በቤተክርስቲያናችን ብሉይና አዲስ እንዲነገር ለማጠየቅና አምስቱ አዕማደ ሚስጢር ለማጠየቅ
➑መንግስተ ሠማያት ሀዋሪያትና ነቢያት ፣ደናግላን እንደ ኤልያስ መዓስባን እንደሙሴ ያሉ ህያዋን እንደኤልያስ ና ምውታን እንደ ሙሴ ያሉ በአንድነት የሚወርሷት መሆኑንም ለማስረዳት ነው፡፡
➒ወልድ እየሱስ ክርስቶስ አብ በደመና መንፈስ ቅዱስ በብርሀን አምሳል በታቦር ተራራ ተገልጠዋል .
╔═★═══════📄══╗

‹‹ምሁራን ምርጥ ዘር ላይ መመራመር ሲያቅታቸው ሰውን በዘር ያባላሉ››
🎤መጋቢ ሀዲስ እሽቱ አለማየሁ
በቀደዱልን መፍሰስ የለብንም። እኛ ውሃ አይደለንም። እኛ ሰዎች ነን፤ ልባዊነት (አዋቂነት)
በውስጣችን መኖር አለበት። አዋቂነት ማለት ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ ባዮሎጂ ወይም አቋቋም፣
ድጓ፣ ቁርዓን መማር ማለት አይደለም። ይሄ ይሄ ከላይ የሚጨመር ነው። ምክንያቱም
አንዳንድ ጊዜ ማንበብ ያቋረጡ ሰዎች ንግግር የሚያልቅባቸው የተቀባው ድንጋይ ቀለሙ
ስለሚለቅ ነው።
አንዳንድ ሕንፃ ዝናብ በጣም ሲበዛበት ቀለሙ ይገፋል፤ ቀለሙ ሲለቅ ድንጋዩ ይወጣል።
ማንበብ ስናቆም ወደቀደመ ነገራችን ነው የምንመለሰው፤ ምክንያቱም ርሃብ እንጂ
ባህሪያችን ዕውቀት ባህሪያችን አይደለም። ከውስጥ የተቀባ ቀለም ማንበብ ስናቆም ቀለሙ
ይለቃል። ለምሳሌ ኮምፒውተር ሳይንስ ላይ የተመራመረ ሰው 15 ዓመት ጎጃም ወይም
ወለጋ ከርሞ ቢመጣ ‹‹ኮምፒውተር ምንድነው›› ሊል ይችላል።
አንዳንድ ጊዜ እኮ የሚገጥመን ነገር ዲግሪው ቤቱ ግድግዳ ላይ ተሰቅሎ ዕውቀቱ ግን
ጭንቅላቱ ውስጥ የለም። ዲግሪያቸውን ‹‹እዚህ ስመረቅ ነው፤ ከዚህ ቦታ ያገኘሁት ነው››
ይላሉ፤ ዕውቀቱ ግን ከውስጣቸው የለም። ዲግሪው ግድግዳ ላይ ቢሰቀልም ጭንቅላቱ
ውስጥ ያለው ዕውቀት ግን በየጊዜው ማሞቅ ያስፈልገዋል።
አባቶቻችን ዓድዋ ላይ እንደዚያ ተግባብተው፣ አርቀው አስበው፣ ጥቁር አፍሪካውያን
የሚኮሩበትን የጀግንነት መልስ የሰጡ በልብም በጉልበትም ሲመልሱ የ21ኛው መቶ ክፍለ
ዘመን እንዴት ምን ነካው? ‹‹ምን አገባህ!›› ማለት እንዴት አይችልም?
አባ መላ(ፊት አውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ) አንድ ፈረንጅ መጥቶ ሰገሌ(ሰሜን ሸዋ
ውስጥ ያለ) የወሎና የሸዋ ነገሥታት ተዋግተው ነበር። ነገር ካለፈ በኋላ አንድ ጣሊያን
መጥቶ ‹‹እናንተ የሸዋ ሰዎች እኮ እነዚህን ወሎዎችን ጉድ ሠራችኋቸው!›› አላቸው፤ እሱ
ጠብ ለመጫር ብሎ እንጂ አስቦበት አይደለም። ‹‹የወንድማማቾችን ስትል ለምን
የዓድዋውን አልነግርህም›› አሉት አባ መላ።
እሱ የነገራቸው የሸዋውንና የወሎውን ነው፤ መጋጨት ደግሞ ያኔም የነበረ ነው። አሁን
ሰሞኑን እየሰማሁ ነው፤ እገሌ የሚባለው ክልል ልሁን አለ የሚባል ነው። እነዚህ ዛሬ ክልል
እንሁን ክልል እንሁን እያሉ የሚጠይቁ የዛሬ ሰባት ዓመት ዕድሜ ሰጥቶት ያየ መከለያ
ይቸግራቸዋል። እርግጠኛ ሆኜ እነግራችኋለሁ መከለያ ይቸግራቸዋል። ሀገር እንደሹራብ
በዘዴ የተሠራ ነው። አንዱ ክር ሲመዘዝ ሁሉም ይመዘዛል። እዚህ አገር የወሰን ጥያቄ
የሌለበት የለም።
በአማራውና በትግራይ አለ፣ በኦሮሞና በሶማሌ አለ፤ እንደገና ደግሞ ተለጥጦ በአማራና
በአማራ መካከል አለ። እሱ ነው እኔ የሚገርመኝ! በኦሮሞና በኦሮሞ፣ በወለጋና በወለጋ
መካከል ይቀጥላል ገና! በሶማሌና በሶማሌ መካከል ይደረጋል። ጠብ የሆነ ቦታ ላይ
ካልተገደባችሁት ሰውነታችሁን ያበሰብሰዋል።
ይሄን ጥላቻ አሁን መገደብ ካልቻልን በጣም እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ አትራፊ የለም።
ልዩነቱ አየለ ሰኞ ይጎዳል፣ ከበደ ማክሰኞ፣ ሥዩም ረቡዕ፣ ተሾመ ሐሙስ፣ እስከ ዕሁድ ድረስ
ሁሉም ተጎድተው ጨርሰው ለቅሶ ደራሽም አይገኝም። ይሄንን እርግጠኛ ሆኜ ነው ምናገረው፣
ነብይ መሆን አያስፈልግም።
ወጣቶች በተለይ፤ አዲስ ሃሳብ ምታመነጩ ወጣቶች፤ ይሄን የተከበረ ጭንቅላት፣
እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠረውን ጭንቅላት፣ ማፍረስም መገንባትም የሚችለውን
ጭንቅላት እስኪ ለበጎ እናውለው!
107 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተመስርተዋል እዚህ አገር፤ አሁንም ግን ፈረንጆቹ በበሬ
እንደሚታረስ ለማየት ሙዚየም ገብተው ነው የሚያገኙት፤ እኛ አገር ግን ዛሬም በበሬ
ይታረሳል። ከአንድ ከዩኒቨርሲቲ ለተመረቀ ምሁር ገበሬን ወክያለሁ ብሎ ገበሬውን
ሲያፈናቅል ከገበሬው ያነሰ ሰው መሆኑን ያሳያል። እንዲያውም እዚህ አገር ገበሬ ውሎ
ይግባ! ምሁራኑ ምን አመጡ?
ምሁራኑ ምርጥ ዘር ላይ መመራመር ሲያቅታውቸው ሰውን በዘር ማባላት ተያያዙት! ገበሬው
እንዲያውም ምርጥ ዘር እየዘራ ሠርቶ እያበላ ነው። በትግራይ ብትሄዱ፣ በአማራ ብትሄዱ
መሬቱ የተበላ ነው፤ ከዚያ ከድንጋዩ ላይ ዘርቶ ግን፣ 24 ሰዓት እየሠራ ከጀንበሯ ጋር
ሽቅድምድም ነው። ማታ ሲተኛ አመስግኖ ነው። ‹‹ጌታዬ ያለ እኔ ማንን ፈጥረሃል?›› ብሎ
ነው። ሰው ጨረቃ ላይ እንደወጣ አልሰማም፤ ኧረ እንኳን ያልሰማ! እኛም ሰምተን ምንም
አልተጠቀምን፤ እብደት ነው ያተረፍንነው!
በዚህ ዘመን የማን አድናቂ ነህ ብትሉኝ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችና የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች
አድናቂ ነኝ፤ ፖለቲከኞቹን ንቁባቸው! በጣም ነው የገረመኝ። እኔ በ1998 ዓ.ም ጥቅምት ወር
ላይ ቅንጂት የሚባል ፓርቲ አሸንፎ ኢህአዴግ ያልተዘጋጀበት ሽንፈት፤ ቅንጂትም
ያልተዘጋጀበት ድል አጋጥሟቸው ሁለቱም ሰክረው ነበር። የቅንጅት የዚያን ጊዜ ችግር ዱብ
ዕዳ ድል ወረደበት! ለድልም ለሽንፈትም መዘጋጀት ያስፈልጋል።

የኛ ረዳት ቅዱስ ሩፋኤል!!!
እርዳን ቶሎ ና ከክፉ ጠላት ጠባቂያች ነህ ሊቀ መላእክት
ሩፋኤል ስሙ የእብራይስጥ ሁለት ቃላት ጥምረት “ሩፋ” እና “ኤል” የተመሰረተ ስም ነው ~ራፋ ማለት ፈውስ፣ መድኃኒት ማለት ነው ከ7ቱ ሊቃነ-መላእክት እንዱ።
ቅዱስ ሩፋኤል በስልጣኑ •☞ የቀንና የዓመታዊ የሰዎችን ሥራ ለእግዚአብሔር ዘገባ ማቅረብ፣ የሌሊት 3ሰዓት ተረኛ ጥበቃ •☞ሊቀመናብርት (የመናብርት አለቃ) •☞ ፈታሔ ማኅጸን (ማሕጸን የሚፈታ) •☞መራኄ ፍኖት (መንገድ መሪ) •☞ከሳቴ እውራን (የእውራንን ዓይን የሚያበራ) •☞ሰዳዴ አጋንንት (አጋንንትን የሚያባርር) •☞ፈዋሴ ዱያን (ድውያንን የሚፈውስ) •☞አቃቤ ኆኅት (የምህረትን ደጁ የሚጠብቅ) ተብሎ የተገለጠ ከሊቃነ መላእክቱ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ተከትሎ የሚነሳ መልአክ ራሱን እንዲህ በማለት ገለጠ « የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነት ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ» (ጦቢ.12÷15)
ቅዱስ ሩፋኤል የጦቢትን ዐይን ያበራበትና ወለተ ራጉኤልን ተቆራኝቷት የነበረውን ጋኔን ባወጣበት እግዚአብሔር በሰጠው በወሀቤ ብርሃንና መግረሬ ፀር የሚሆን በአስማተ መለኮቱ የእኛንም የጨለመ ኑሮአችንን ብርሃን ያድርግልን የኃጢአታችን ብዛት የሰይጣንን ክፉ ሥራ እንድንደግፍ እንዳያደርገን ከእኛ ዘንድ ያርቅልን አሜን❖❖❖

በሰማይ ሰልፍ ሆነ ውጊያው ተጀመረ
በሚከኤል ነገድ ሳጥናኤል አፈረ
ያቃጥላል ክንፉ የጠላትን ሰፈር
አያልቅም ቢወራ የሚካኤል ነገር
ዘንዶው ተወርውሮ ከምድር ወደቀ
የቀድሞውም እባብ በክንዱ ደቀቀ
ሚካኤል ሲነሳ ከሳሽ ይሸበራል
በአይለ መስቀሉ ተሰብሮ ተጥሏል
ዳቢሎስ አልቻለም ሚካኤል ፊት መቆም
በተማመነበት በነገዱ አልዳለም
የሰማዩን ስፍራ ለቀቀ ተመቶ
ሳጥናኤል ጨለመ ሚካኤል አብርቶ
የሐሴት አባቷ ዛሬ ስፍራ አቷል
መላካዊው አይሉን በትቢት ተነጥቋል
ሆኗል ምድረ በዳ እጅግ ተቅበዝብዞ
አብረው የወደቁት ነገዶቹን ይዞ
ስሙን እንጠራለን አይሉን እንዲሰጠን
የማሸነፊያውን ክብሩን እንዲያለብሰን
በመንገዳችን ላይ ሚካኤል ስላለ
ሁሉንም አለፍነው በእርሱ እየቀለለ
ቅዱስ ሚካኤል ከሚመጣብን ክፉ ነገር ይጠብቀን🙏
በሚከኤል ነገድ ሳጥናኤል አፈረ
ያቃጥላል ክንፉ የጠላትን ሰፈር
አያልቅም ቢወራ የሚካኤል ነገር
ዘንዶው ተወርውሮ ከምድር ወደቀ
የቀድሞውም እባብ በክንዱ ደቀቀ
ሚካኤል ሲነሳ ከሳሽ ይሸበራል
በአይለ መስቀሉ ተሰብሮ ተጥሏል
ዳቢሎስ አልቻለም ሚካኤል ፊት መቆም
በተማመነበት በነገዱ አልዳለም
የሰማዩን ስፍራ ለቀቀ ተመቶ
ሳጥናኤል ጨለመ ሚካኤል አብርቶ
የሐሴት አባቷ ዛሬ ስፍራ አቷል
መላካዊው አይሉን በትቢት ተነጥቋል
ሆኗል ምድረ በዳ እጅግ ተቅበዝብዞ
አብረው የወደቁት ነገዶቹን ይዞ
ስሙን እንጠራለን አይሉን እንዲሰጠን
የማሸነፊያውን ክብሩን እንዲያለብሰን
በመንገዳችን ላይ ሚካኤል ስላለ
ሁሉንም አለፍነው በእርሱ እየቀለለ
ቅዱስ ሚካኤል ከሚመጣብን ክፉ ነገር ይጠብቀን🙏
መድሃኒዓለም...........
✞ጌታ ሆይ...................
✞ኢየሱስ ሆይ..................
✞አማኑኤል ሆይ............
✞ጎዶልያስ ሆይ..............
✞ኤልሻዳይ ሆይ..............
✞እግዚአብሔር ሆይ........
•••••>አግዚአብሔር ወልድ ሆይ ሰዎች አላዩኝም ብዬ የሰራሁትን ገመናዬን ከአንተ በቀር ያየ እንደሌለ በሙሉ ልቤ አምናለሁ፡፡
••••••>አማኑኤል ሆይ ቻይ እንደሆንክ አዉቅ ሀሳብህም ሁሉ ይሆን ዘንድ ከቶ እንደማይከለከል በአለማት ላይ አንተ ብቻ እንደሰለጠንክ የሁሉ ፍጥረታት ስራ አስኪያጅ እንደሆንክ ያለጥርጥር በሙሉ ልቤ አምናለሁ፡፡
••••••>ዉዴ የህይወቴ አባት ካንተ ሌላ:-
☞ሳለቅስ እንባዬን የሚያብስ
☞ስወድቅ የሚያነሳኝ
☞ስራብ የሚያበላኝ
☞ስጠፋ የሚፈልገኝ
☞ስጨነቅ የሚደርስልኝ
☞አንገቴን ስደፋ ቀና የሚያደርገኝ
ካንተ በቀር ማንም እንደሌለኝ አዉቃለሁ፡፡
•••••••>መድሐኒዓለም ሆይ:-
ሌትተቀን እንደ ንስር እናት የምትጠብቀኝ እና የምታየኝ -አቤቱ እንዴት ባለ አንደበት ላመስግንህ....
በአንድ ነገር ተስፈ አለኝ እሱም አንተ ዘወትር ከኔጋ ነህ.
እዉነት ነዉ እግዚአብሔር ባስቀመጥነዉ ሁሉ አለ.

✝✝✝✝✝✝✝✝✝
“የቃልህ ፍቺ ያበራል፥ ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።”
— መዝሙር 118(119)፥130
🕎ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ላሉት ምንባባት አንድምታቸው ትንታኔና ማብራርያ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ
👉“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች...read more
👉መጽሐፍ ቅዱስ መቼ በአንድ ጥራዝ ተጠቀለለ? ከክ.ል.በ ይሁን በኋላ የተጻፉት ሁሉንም መጻሕፍቶች ለየብቻቸው ነበሩ፡፡ከ500ዎቹ ዓ.ዓ....read more
👉ኦሪት "ኦራይታ" ከሚል የሶርያ(አራማይክ) ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "ሕግ" ወይም "ትምህርት" ማለት ነው።የመጠሪያ ምንጩም....read more
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 65)
----------
11፤ በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።
12፤ የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ።
13፤ ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ፥ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤ በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉም። "
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ለሁላችሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመናን ወምእመናት እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።መጪውን ዘመን የሰላም የፍቅር የንስሐ ዘመን እንዲያደርግልን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን።
ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ እና መንፈሳዊ ጥንካሬያችንን እንድናበረታ የሚያግዙን መንፈሳዊ ቻናሎችን ይዘን ቀርበናል።እርስዎም ከእነዚህ መንፈሳዊ ቻናሎች የነፍስ ምግብ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እየተመገቡ መንፈሳዊ ሕይወትዎትን እንዲያጠናክሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን🙏
🙏ፈጣሪ ይባርከን🙏
ከነዚህ መፀሀፍት የተወጣጡበት
ትምህርትን መማር ይፈልጋሉ❔
እነሆ ብለናል :-
📚የባሕታውያን አባቶች ሕይወትና የመዝሙራት ተመስጦ
📖▓⇨ትምህርት በአባ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የድያቢሎስ ውግያዎች
📖▓⇨ትምህርት ⇨ክፈት
📚አምደ ሀይማኖት
📖▓⇨በአባታችን ቅዱስ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሕይወት
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚መንፈሳዊ ሰው
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
📚የአባቶች ሕይወት ንሮ እና ተመስጦ
📖▓⇨በአቡነ ሺኖዳ ⇨ክፈት
የመኖኮሳት ታሪክ እና ተመስጦ በብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ይቀርብበታል።

The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 11 months. If it remains inactive in the next 9 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.