tgoop.com/gGetem/2855
Last Update:
የሔርሞን_ማስታወሻ
ኡፍፍፍፍ መቼ በዚህ በቃና ብለሽ እታለም ከዚህ የእግር ብረት ከሆነ የአለም ፈተና ሲወድቁ ሲነሱ አልፈው በስንት እና ስንት እንግዳ ሀሳብ ሲናጡ ከርመው ለትዳር የበቁት ደግሞ ፊርማቸው ገና ቀለሙ በውል እንኳን ሳይደርቅ በበነጋው ለፍቺ ፊት እና ኃላ እየተማሩ ሰርክ የፍርድቤቱን ደጃፍ ከአፍ እስከ ገደፍ የሞሉት እነማን መሰሉሽ...?!......እኚው ትናትን "በሆታ" ተሞሽረው ዛሬ ጎጃቸውን በዋይታ የሚያጠናቅቁ የሁለት አለም ተጋሪዎች ናቸው።
እታለሜ መቼም ይህን ስታነቢ ትናንት በችግር ምክንያት ትተሻት የተሰደድሺው ያቺ ሚስኪን በባህሏ እና ፈሪሀ እግዚአብሔር የነበራት ያቺ ሀገር በእውን መሆኗን ለማመን ከራስሽ ጋር ሙግት እንደገጠምሽ እርግጠኛ ነኝ።
.....ግን በዚህስ ቢያበቃ ጥሩ አይደል ከላይ የገለፅኩልሽ ጥንድ ተጋሪዎች ይህን በጥረታቸው እና በፈጣሪ እርዳታ ቢሻገሩትም ዘመን ቀመስ በሆነ እንግዳ ትምህርት ሴቲቱ ተሰብካ አራርቆ መውለድ አልያም ቤት፣መኪና፣ንብረት፣ኮተት፣ወዘተ...መስፈርት ቀዳሚውን ቦታ ይይዙና አልኩሽ ያለ እኚህ መስረተ በሌላቸው ተልካሻ ምክንያቶች መላ አካላቷ እንደ ጦር ሜዳ መሬት እየተከፋፈተ ይቀበራል።በዚህም ዘረ-አዳም ለአራተኛ ጊዜ ከመፈጠር ደጅ ሳይሳካለት እንደመከነ ይቀራል እልሻለው።
መቼም ይህን ስልሽ ይህ ነገር ለወንድየውም የለውም ማለትሽ አይቀርም😭😭😀 እኔ እስካገባደድኩት እድሜ አልሰማሁም ምን አልባት አድሮ በነጋ ቁጥር የዚች ባልተኛ አለም ነገር መላ ቅጡ ስለማይታወቅ መፈብረኩ አይቀሬ ነው....
🛖ሔርሞን ነኝ የዳር ሀገሯ
🏙በስደት ላለሺው እታለሜ
#ፀሐፊ_ሊዮ_ማክ
(ይቀጥላል)👱♀
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
ለሒስ @sirak6
ለቤተሰባዊነት www.tgoop.com/gGetem
BY የሆሄያት ህብር📝📝
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/qaqq3zrLZrwD8X_qo5EUVuxRkB8qtrBLQ7AeBV--6RKYANT3PeuiwWL-tWfLohVhzw6ltztA682LfuadrXsLIOR5ADXtHBfuxqSt4oxtNqPaynhLg4fYQTQDOGTYtmFJvWgkAEJBXAx0WjK-hzl4S5TpcjYpH3Zt46sJ6Pf6UEZ1DFEIF6rW4z0t6Yqs460zh9STRuty0js7t9TgItClKz3nYxB29EiD3s6tRzyqmOE9w9s3jw5Nez38PXGV4uxCtfXTFRGKrxKO3L4RAGKq6XjZ82D5sw1m12Pdsyk2EwjDWf0wAkFE4xPQwuNVIKwafAVD-2Yaiwh__tSWRxvkyA.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/gGetem/2855