Telegram Web
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
.....ሚስቴ ማንን ትምሰል....
※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @yosikeman
እግዜር ግን ታያለህ?
እሷ እኛን ለመርዳት
መፈሸን ሳያምራት
በረዣዥም ቀሚስ ፣ እግሯን ብትሸፈን
ፀጉሯን በቀይ ሻሽ ፣ አግታ ብታፍን ፤
ብትመጥን ፣ ሳቋን
ብትሰበስብ ፣  ጣቷን
ብትሸሽ ፣ ብትሰወር
ቀን ባትወጣ ሰፈር
እኛን ላለመጣል
በውበቷ ዘገር …
ብትለፋ ብ’ተጋ
ለነፍሳችን ዋጋ
ከፈጠርካት ኋላ
ከስማም እንድታምር
ተሰናክለን ቀረን…
እሷ ምንም ብ’ጥር።


በማን ልትፈርድ ይሆን?

@gGetem
@gGetem
@gGetem
2
( መጋረጃ ... )
==============

የልብሽ በር መስታወት ነው
ሠርክ የሚያሳይ ትላንትሽን
ዘውትር ከእርሱ እያፈጠጥሽ
አታበላሽ ተይ ነገሽን ....

አትስበሪው አትቆልፊው
ከመታገል ላይቀር ፍርጃ
ተከልለሽ ምታርፊበት
እንኪ የፍቅሬን መጋረጃ  !!


@gGetem
@gGetem
ሰባራ ልብ

ሰባራ ልብ የፃፈው ከንቱ ግጥም
ስሜትን ሰቅዞ ባይዝም እንኳ ባይጥም
ያፍቃሪን ሰው ህይዎት ባይለውጥም
እኔ ግን እፅፋለሁ ፊደልን አያይዤ
ከተውሽኝ ቦታ ሰባራ  ልቤን  ይዤ

የጨረቃ የክዋክብት ድብቅ መረብ
ሰማይ ወርዶ ከምድር ጋር ቢቀራረብ
       የሌት ነፋስ
ብርድና ውርጭ ገላዬ ላይ ቢረባረብ
  በዶፍ ዝናብ  ምድር ቢጥለቀለቅ
እኔ እንደው ከተውሽኝ ከዛ ቦታ አለቅ
ታነሽኝ እንደው መተሽ አንሽኝ
   እባክሽ ከሰው አታነሽኝ
መልኬ ቢገረጣም ባንቺ ፍቅር ደዝዤ
ብዙ መንገድን  በሃሳቤ  ተጉዤ
እጠብቅሽ አለሁ ሰባራ ልቤን ይዤ



@gGetem
@gGetem
@gGetem
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
....ከሚላ 2....
#ገጣሚ_ሊዮ_ማክ
ልብ አንጥፎ መሬት
※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @yosikeman
@gGetem
ዛሬም....
🥰21👏1
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
የyohabi ደብዳቤ

😘የማይድን ናፍቆት.... 'የተረሳው ክፍል'😢

"ስትሄድ ያልከኝን መርሳት አቅቶኛል"
Audio
ተረት ተረት
ስብሁት ለአብ

አንባቢ ሱራፌል ጌትነት
ሱራቢራቢሮ🦋

@getem
@getem
@getem
በቀን እንደሞትኩ...

ከአፈሩ  አፈሩን ጥለነው
ከሰማዩ ሰማያቱን አልፈነው
ሄድን ሄድንና...
ከፈጣሪ የፍርድ መንበሩ ጋር ደረስን፤
ተረኛ ነበርና...
ደጃፉ ላይ ወንበር ስበን ተቀመጥን።
ተረኛ እስኪጠራ ፥ እስኪገባ ፈጣሪው ጋ
ትዝ ይለኛል ፥ ባንዲት ርዕስ ስናወጋ።

ሞትኩኝ...
የሚላስ የሚቀመስ አጥቼ
ሞትኩኝ...
"ትን" ብሎኝ ብፌ አሰናድቼ
ሞትኩኝ...
አልጋ ላይ ላመታት እንዳልነበርኩ ማቅቄ
ሞትኩኝ...
ስዝናና ውዬ ስመለስ ደክሞኝ መሪ ለቅቄ
ሞትኩኝ...
በተኛኹበት ወዳጄ ባልኩት በሰው ታንቄ
ሞትኩኝ...
ሞትኩኝ ሲሉ ፥ ኹሉ ኹሉም በየተራው
በቀኑ እንደሞተ ፥ ኹሉ ሰው ሚያወራው።

እኔ ግን...
እኔ ግን...
በቅጡ መኖሬን
በቅጡ መሞቴን ስላላወኩ
በቀኔ ሳይሆን በቀን እንደ ሞትኩ
አስታውሼ ነበር ፥ የተናገርኩ!


  

@gGetem
@gGetem
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
....ጠብቄሽ ነበር....

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @yosikeman
በመኖር  አጸድ ውስጥ
(በእውቀቱ ስዩም)

ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::

እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
-ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤

ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::

@gGetem
@gGetem
@gGetem
,           ዕ ድ ል

የት ነሽ ዕድል የትስ ብዬ ልፈልግሽ
ከሁሉም በላይ ነው እና ያንቺ ማዕረግሽ
እስኪ ላግኝሽና ለእኔም ይድረሰኝ ወግሽ
ዕድል የት ነሽ ዕድል የትስ ብዬ ልፈልግሽ

ፍጥረት በዕድሉ ሊኖር የተፃፈለትን ትቶ
ከማይሆነው ሊጋባ ከሚሆነው ተፋትቶ
ከአላህ ከእግዚሔሩ ጋር ተጋጭቶ
አንዱ ካንዱ ያለዕድል ከዕድል ተፋጭቶ
ተጎናትሮ ተሟሙቶ ላይፈጥር ዕድል
      ዕልህን
ታጥቆ ይዘምታል ፅናትን በቅናት ሊገድል
ዕድል ዕድል ዕድል የት ነሽ ዕድል
አንቺን ስፈልግ እኔ እራሴን እዳልገድል
ዕድል የት ነሽ ዕድል የትስ ብዬ ልፈልግሽ
ከሁሉም በላይ ነው እና ያንቺ ማዕረግሽ
እስኪ ላግኝሽና ለእኔም ይድረሰኝ ወግሽ



@gGetem
@gGetem
@gGetem
1
ባዶ እስኪሆን ድረስ


እንባውን ይሰፍራል ፣ ኑሮ ያሻመደው
ጥርሶቹን ይገልጣል ፣ ምቾት የታደለው።
ሰፍረን እናውቃለን ፣ እንባን በኩባያ
ሀጫ ጥርስ ዘግነናል ፣ ስጥ ሆኖ ገበያ ።

ይሄን እናውቃለን ፣ ጥንትም ነበር ድሮ
የሷ ግን ገረመን ፣ ውል ሳትን ዘንድሮ ።

ትስቅ ነበር እኮ ፣ ሆዷን በእጇ ይዛ
ከጨዋታ መኃል ፣ አንዱን ሰበዝ መ’ዛ
አንድም አልሰማንም ፣ ሀዘን እንጉርጉሮ
አንገት አልደፋንም ፣ ቀኖቿ ተቆጥሮ
እንዲህ በሳቅ ውሀ ፣ ገፅዋ ተሸርሽሮ…
እስክናጣት ድረስ ፣ ያቺን መልካም እንስት
ከቶም አላየንም ፣ ቁዝሚያ ና ምልክት
ሳቅ እንዴት ይሆናል ?
የመታመም ቅኔ
……………….  ዝግ ያለ ስንብት?

@gGetem
@gGetem
@gGetem
🥰2
እንቅልፌን ላውስሽ
እስከ ጠዋት ተኝ
ለችግርሽ እንደው
እኔ ልብከንከን ፣
ከቀን ባላድንሽ
የሌት ህልሜ ከሆን
ባንቺ ይታለም ፣

ከንፈርሽ ስር ያለች ነጥብ
ማሪያም ስማሽ ከሆነ ግን ፣
እንዴት አየህ አትበይ
ከእግሬ ስር ተኝተሽ
በሌሊት ወጋግን፣

(ነውና ያየሁሽ )

ካይንሽ ስር ላይ ገደል አለ
ግፋኝ ልውደቅ እያነባሽ ፣
እኔ ከታች ልውደቅ ቆይ
የዱር እሾህ እንዳይወጋሽ ፣

ደረቴ ጋር ጥብቅ በይ
ይጠፍሩኝ በልጥ ዛፍ ፣
ጡቶችሽ ጋር ካሳደረኝ
ከተራራው ጎጆ አፍ ፣

ከሰው መንጋ ተገንጥለን
ከጫጩት ድምፅ ተነጥለን ፣
በባዶ እግር ጫካ አልፈን
ተራራው ጫፍ ጎጆ ሰርተን
በጫካ ዛፍ ተከልለን ፣

ከሰሜን ንፋስ ሲ ነ ፍ ስ
ደመናው ሰማይ ሲ ወ ር ስ

በምስራቅ ጎን
የድንቢጥ ድምፅ
በምዕራብ ታች
የአንበሳም...፣
በቀስታ ተቃቅፈን
በዝምታ ስንሳሳም ፣

በጣቶቼ ወገብሽን
ክንዴ ሞልቶት ዞሮ ሲደርስ ፣
ከሰማዬ ነጫጭ ውሃ
ዝናብ ሚሉት ከእኛ ሲፈስ ፣

ተቃቅፈን ከአልጋችን
ዶፉ ሲወርድ ከጎጆ ውጭ ፣
በሳቅሽ እየታጀብኩ
በብልጭታው እያየሁሽ
በነጎድጓድ ስትደነግጭ ፣
በጣቶችሽ ጣቴን
በጭንቀት ስትጨብጭ ፣

ድንግጥ ስትይ አንገቴ ስር
ትንፋሽሽ ላይ ሙቀት ሳገኝ ፣
በግርብታ ያልጠበቀ
በቀ..ስ..ታ..ከንፈርሽ እንደሳመኝ

ከሩቅ ላይም የአራዊት ድምፅ
ከክንዴ ላይ ያንቺ ነፍስ ፣
ከንፈርሽ ስር ባለው ሀይቅ
ዋኝተንበት እንፍሰስ ፣

ከዚህ ጩኸት እንደበቅ
ከጫጫታው እንሰወር
በጨለማው ፍቅር ወበቅ
እንደ ድር እንደወር
ህልም ማለት..?እስኪ እንወቅ...?


የእኛን ኑሮ ካልጠበቁት
ከገፉን ስር ከሚስሙት
አድበስብሰው ከሚቀብሩት
ተራራ ስር ካለው ጎጆ
ዘላለም ነጥለን
ዘላለም ተቃቅፈን
ዘላለም እንሙት


@gGetem
@gGetem
@gGetem
🔥4
...ሊገለኝ ነው

ህይወት ሳታከትም  የእንባዬ ጠብታ
ትመጣ ከሆነ  የታመምኩኝ ለታ
አይህ እንደሆነ  ለደቂቃ ላፍታ
ናፍቆት ሊገለኝ ነው ታምሜያለው በቃ
             
  
@gGetem
@gGetem
@gGetem
ያለ ግጣም መግጠም
ሲቆይ ላያጣጥም
ጥቂት ግን ያስጉዛል
ትዝታና ፀፀት በደርዘን ያስይዛል
ልኩ የራቀው አካል ልኩ የራቀው ነፍስ
ሳይሰበር እንዲው መቼም ላይመለስ
ላይ ላዩን እያበራ ውስጡ እየዳመነ
ስንቱ ልብ በቁጭት ከስቶ መነመነ
ያለ ፍቅር ጥምረት የራስን ሰው ጥሎ
እራስን መቅጣት ነው ከናፍቆት ተዳብሎ
አዲስ ግንኙነት እንዲሁ ሰው ይዞ
ምክንያትን ያጣ መድረሻ ቢስ ጉዞ
አይን ወዲ ብሎ ልብ ወዲያ ካለ
ዋጋ የሚያስከፍል ትልቅ ጥፋት አለ



@gGetem
@gGetem
(...)

የምኞት መጨለም
የትዝታ መናድ
በወዳጅ መጠላት
ባመኑት ሰው መካድ
ሲኖሩት አይደለም
ሲያስቡት ነው ከባድ ።


@gGetem
@gGetem
👏1
( ዛሬም እንጉርጉሮ )
================

ይህ ልባችን
እስከ ስሩ እስከ ጥጉ ቢበረበር
ኩራታችን የገደለው ስንት ፍቅር
ውስጡ ነበር ....

ህይወታችን
በቅን ዳኛ በጥቂቱ ቢመረመር
ማፈራችን ያሳለፈው ስንት ጸጋ
ገጥሞት ነበር ...

በትነነው ስናበቃ
የሰጠንን ቁና ሰፍሮ
አይከብድም ወይ
አምጣ እያሉ ዛሬም ለእግዜር እንጉርጉሮ ??


@gGetem
@gGetem
#የእንቢታሽ ሱሰኛ!
(ሚካኤል አስጨናቂ)

አንቺን በማሰብ ውስጥ መደሰት ለምጄ
ፍቅርሽ ሱስ ሆኖብኝ ... ማንነቴን ክጄ
ባንቺ መወድስ ስም ክታብ አሰርቼ
ስምሽን  አንግቼ …

እንደ አሞራ ዙሬሽአንዣብቤ በላይ
አንቺን ሳይሽ ፣ ‘ዋይ ፣ ዋይ …’

አጃኢብ ነው መቼም!

ስትሄጅ ተራመድሁ... ስትቆሚ ቆሜ 
ባንቺ ስፍር ልኬት.. .በጠርዝ ተመድሜ
ከዕድሜ ከዘመኔዓመታት ቆንጥሬ
ከእንቢታሽ ጋራበእልህ ሰክሬ
ስንኞችን ጭሬ.. .
አንቺን በመጀንጀንጀንልማድ ተጠፍሬ
በሚጣፍጥ ህመም ...
ብቻዬን በአርምሞስብሰለስል ኖሬ

ከሀሳቤ ማግስት ... በስንኜ ድርድር 
ቃላት ድል ነስተውሽበኃይላቸው በትር
እኔም በተራዬ ፣ መፈቀር ስጀምር
“ፍቅርህን ተቀበልሁ” ያልሽኝ ጊዜለታ 
ፍቅርሽ ጥሎኝ ጠፋትዝታሽ ተረታ።

(እንቢ በይኝ ዳግም
እልህን ላጣጥም ። )

@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍1
እንደምትወዳት ንገራት,

(በእውቀቱ ስዩም)
ሕይወት የብድር በሬ፥መቼ ሁሌ ይጠመዳል
ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል
የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወሰዳል::

ቀለበት፥ አምባር አይደሉም
እጅህ ላይ ሁልጊዜ የሉም
-ቀናት ሳምንታት ወራት
ዛሬውኑ ፥አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት::

አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ
ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ
ያጸድ በሮች ሳይቆለፉ
በንቦች ጎዳና ላይ፥ተርቦች ሳይሰለፉ
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ
ሕይወት የላምባ መብራት
አሁንኑ ዛሬውኑ ፥እንደምትወዳት ንገራት፤

ርቃ ሳትገሰግስ
ገና ስንቋን ስትደግስ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደማትቀባው አመድ
ወደማትስበው አየር
ሳትቀየር
አንትም አንደበት ሳለህ፥ እሷም ጆሮ ሳያጥራት
ዛሬውኑ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት።

@gGetem
@gGetem
👌1
መናፈቅ ማለት …
ከወትሮው በድንገት
ከከተማ ግፊያ
ከሰፊው ገበያ
ከሰው ትርምስ
ከህይወት ግብስብስ
አረፍ ብለው ባልጋ
ከራስ ጋር ሲወጋ
የአስቴር እና ኤፍሬም
አባባይ ሙዚቃ ...
አንጀትንን ሲገርፍ
ትዝታን ሲያነቃ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት..
በቡሄ አመሻሽ
እርግት ባለ ሰማይ
ልጅነት ሲወያይ
ሲሸት የኩበት ጭስ
የአሪቲ ቃና መንደርን ሲዳብስ
ውብ አደይ አበባ ምድሪቷን ሲያነግስ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት ..
እኔና አንቺ አፍረን
ከዓይን ተሸሽገን
ከመስቀል ዳመራ
ሸሽተን ከጓደኞች
ፈልገን ሰዋራ ...
ተቃቅፈን እየሄድን
ውሎን ስንጋራ
ስትሰጪኝ ፖፖቲን
‘’ፖስት ካርዴስ ?’’ ብለሽ
ኪሴን ስትዳብሽኝ
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
ትምህርት ሊዘጋ ወቅት
ድራማ ተውነን
በሰኔ ሰላሳ  ለመታየት ደምቀን
በድራማው መኃል
ፈልገን ስህተት
ከልብ የሳቅን ዕለት
ከሳቅን በኋላ
ኩሪፊያ ሲከተለን ...
ድፍን ሶስት ወራትን
ያለመገናኘት ፍርሀት ሲውጠን
ስትሰናበችኝ  በጥልቁ ዝምታ
ዓይንሽን እያየሁ
ዓይኖቼን እያየሽ
የቆዘምን ለታ …..
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
የሽፍታ ፍርሀት
ነፍስያን ሳይንጣት
በ አራት እግር ጉዞ
የመኪናን መስኮት
በራስ ተመርኩዞ
የገጠርን መስመር
አንዱን መንገድ ይዞ
ተራራውን ማየት
እሸቱን መጎምዠት
ከገበሬ ቁና
በቆሎ መሸመት
የፀሀይዋን ግባት
አሻግሮ መቃኘት
እንዲህ ይመስለኛል።

መናፈቅ ማለት …

(ሚካኤል አ )


@gGetem
@gGetem
@gGetem
2025/07/12 21:47:06
Back to Top
HTML Embed Code: