Telegram Web
...ቃሌን
ውበት እረጋፊ  አላቂና አብቂ
ስስትን ማልሻ  አፍቃሪህ ናፍቂ
ገደብ የማላውቀው  እኔ ያንተ ጠባቂ
አርጅተን እስክንሔድ በሽበት ተከበን
ቃሌን አላጥፈውም አፈቅራለው አንተን
     

@gGetem
@gGetem
@gGetem
(እርቆ ለተኛ)

አትቀስቅሱት ከእንቅልፍ
አይውጣ ከእልፍኝ አይውረድ ከአልጋ
መሲሕ ካልሆነ
ወጀብ አይገስፅም መርከብ አያረጋ'
;
ተበላይ ተበላይ
ጧ! ብሎ የተኛ ስለምን ይፈራል
ሲቀርቡት ነው እንጂ
ርቆ ላየውማ ማዕበልኮ ያምራል።



@gGetem
@gGetem
.................ዮሐንስ✍️




ተይ አትከተይኝ
ላታስቆሚኝ መንገዴን አትዝጊው
ልቤ መች ፍቅር አዝሎ አሁን መተሽ ምፈልጊው

በቃ ሂጂ አልጠቅምሽም
ውስጤ ወና ድንጋይ ሆኗል የኔን ሀዘን አታብሺም

"ውዴ ሆዴ "አትበይኝ ውብ ቃላቶች አትምረጪ
ለፍቅራችን መለያ ስም አይጠቅምሽም ከቶ'አታውጪ
የልቤን ጉም ጥቁር ጭጋግ እንደ ፀሐይ መክፈት ካልቻሽ
የኔን ህመም በመታመም በኔ መዳን አንቺ ካልዳንሽ
ያንቺ ፍቅር ምን ሊጠቅመኝ ከቃል ውጪ ምን አትርፎ
እንደዚ አይነት የፍቅር ሂወት እስከዛሬስ መች ተፅፎ

አየሽ
ፍቅሬ ስትይኝ ዝም ያልኩሽ
ስትጠሪኝ ያልሰማውሽ

እንዳይመስልሽ ክፉ ሆኜ ከቶ አይደለም የጭካኔ
በኔ እምባ እንዳረጥቢነው የምገፊሽ ከጎኔ
በኔ ጥላ አንቺ ወድቀሽ በወንድ ልጅ ሳትጎጂ
ልብሽ ጠባሳ ሳያርፍበት እኔን ተይኝ አንቺ ሂጂ


@gGetem
@gGetem
💔1
አልሞትም!

(በእውቀቱ ስዩም)


ስሚ!
እኔ በዚህ ዐለም ፤ብዙ ብሰቃይም
አንድ ሀሙስ የቀረው፤ መስየ ብታይም
አምሮቴን ሳላገኝ፤ሱሴን ሳላከትም
በመሬት ከርስ ውስጥ ፤ገላየን አልከትም
አልሞትም!
ማንም ባልደፈረው፤ መንገድ ሳልገሰግስ
እንደ ንጉስ አይዙር፤ግማሽ ቀን ሳልነግስ
በጠገበው ሳልስቅ፤ ለራበው ሳልደግስ
አልሞትም!
ዝማሜን ሳላወልቅ፤ ያንድበቴን ግድብ
ዙፋን ላይ ሳልሸና፤ ጌቶቼን ሳልሰድብ
ከድሃ ሳላብር፤ ከገባር ሳልወግን
ከምድር በረከት፤ ድርሻየን ሳልዘግን
አልሞትም፤
ስሚ!
ልቤ እንደምኞቱ፤ ቢያገኝ እንደምርጫው
ያላማየ ማብቂያ፤ አንቺ ነሽ መቁዋጫው
እና
አገሬን ለቅቄ፤ ልብሽህ ላይ ሳልከትም
በውብ ከንፈርሽ ላይ፤ ከንፈሬን ሳላትም
አልሞትም!

@gGetem
@gGetem

        
ሢቃተ ሆሄ


   ጬኸት....
      ጬኸት
          ጬኸት
የሆሄያት ሲቃ
የሙሾ ድለቃ
ቃል ለዛውን ቢያጣ
ቅኔ ወዙ ቢነጣ
ሆሄያት ታመሙ
ሢቃ ድምጽ አሰሙ
       ያን ጊዜ
ገጣሚ ብእሩን ኣነሳ፤ከሆሄያት ድርድር
ከህመም ከሢቃ፤ስንኙን ሊያዋቅር
    ደራሲ ኣነባ
    የሆሄያት እንባ
ከወረቀቱ ላይ
ከነተበው ልቡ፤ከዘመኑ ሲሳይ
    ደራሲ ኣነባ
    የሆሄያት እንባ
ህይወቱን ሊገርፈው
በቅኔ ሊዘርፈው
ሆሄ ደረደረ
ቃላት ሰበጠረ
ሀረግ ኣዋቀረ
ሆሄያትም ታመሙ
ሢቃ ድምጽ ኣሰሙ
  ስንኙም ቤት መታ
  ግና የ ማታ ማታ
ሚስኪኑ ገጣሚ ቤት ለመታው ግጥሙ
በቆሰሉ ሆሄያት ህመም በሚያዜሙ
ፊደል ኣቀናብሮ በቃል በዘመነ
ቤት ለመታ ግጥሙ
ቤት መድፊያ እሱ ሆነ



@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍2
ሰላምን ፈለጋ
🦗🦗🦗🦗🦗🦗🦗
በሰወች መካከል ትልቅ ክፍተት መጣ
ትንሽ ተወድሶ ትልቅ ክብር አጣ
አገሬ ኢትዮጵያ ሰላም ላንች ይሁን
ፈቅር ይለግሰን ቸሩ አምላካችን
መሪና ተመሪ መገዱ ጠፍቷቸው
ተመሪ አወቀና መገድ ሊነግራቸው
መሪ አልሰማም አለ መች ተቀበላቸው
አተ መሪ ሁነህ ሰላምን ካሳጣህ
በምን ቀመር ሆኖ አተን ልከትልህ
የወድማችን ደም አተን እየጠጣህ
እናት ደስታን ስትል ሀዘን አሸክመህ
በልጆቿ ሀዘን እናት ደም አልቀሳ
በየትኛው መገድ ላተ እጅ ልሳ
አዉቃለው ታውቃለህ መገዱ መች ጠፋህ
አልገባኝም እኔ...
እናት መግደሉ ነው ?
እምነት ማጥፋቱ ነው?
ወይስ አገር መሸጥ..?
ነው ያተ ስልጣንህ?
አልገባኝም እኔ በምን ልጠይቅህ
ተምሪያለው ብለህ ማዕረግ ተሰጠሀል
እመራለው ብለህ ዳኝነት ይዘሀል
ግን እዴት መረሀው እስኪ ልጠይቅህ
ደምን እያፈሰስክ
እናት እያስለቅስክ
ሰላም ስጠን ሲሉህ ጀግናን እየረሸክ
ይህ ነው ሀላፊነት በምን ልጠይቅህ
ሰላምን ፍለጋ ቢመጣ ትልቁ ወድሜ
እረሽን እሚባል ትንሹ ወድሜ
በምን መልኩ ይሆን እርቁ የሚሆነው
ታናሽና ታላቅ እያጋደልክ ነው
ይህ ነዉ ወይ መሪነት?
እስኪ ልጠይቅህ
ተመሪነህ ብለህ አትናቀኝ እባክህ
ለህዝቤ ነጻነት መገዱን ልገርህ
ነፍጠኛነው ብለህ ወድም ከማሰረሸን
አዴ አድምጠኝና ሰላም ይሰፈንልን....

@gGetem
@gGetem
Audio
....አትፍረድ....
በሊዮ-ማክ
※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @yosikeman
<
<< ሳስ ተው ልሽ >>>

...........................................ሴናዬ
ዝም ብዬ ሳስተውልሽ ...
ኤሊያስ የገጠመላት ያቺን እፁብ አስታወሺኝ
በቃል ብቻ የማውቃትን በእውን መተሽ አሳየሺኝ
ባላውቃትም ባላያትም ፍፁም በቁም  ባልኖራትም
ኤሊያስ ግን ያሰባትን ሳይከትባት አልተዋትም
...........................................
ሳስተውልሽ እንዳመልሽ ስበት መልክሽ ወሰወሰኝ
ላንቺ ሲገጥም አንቺን ሲሰኝ ባይኔ መጣ አስታወሰኝ
የኖራትን ያወቃትን አጣጥሞ መቼ ቀረ
ገጠመላት አዜመላት ስሜት ምቱን በብራናው አጠቆረ
...........................................
ደሞ ደሞ..
ሳስተውልሽ ዘውድ አክሊልን ትጠሪያለሽ
ሀያል ስሜት በልብ ላይ ትጭሪያለሽ
ልክ እንደርሱ ሙቀት ውበት እስካርፕም ነሽ
የርሱን ግጥም ትመስያለሽ
.........................................
ሳስተውልሽ ....
የኬቢሻን ጥልቅ ግጥም
እንደ በላይ በቀለ ወያ የምትጥም
እንደ ጋሽ ደበበ ቀለም የሰፋች
እንደ ኤፍሬም ስዩም የረጋች
እንደ  ጋሽ ፀጋዬ ፅሁፍ የጦፈች
በውበት ደምቃ ነብስ ያጠፋች
                              ያለማች
ሁሉም የገጠመላት ሁሉም ያነበነባት
በቃል ቅኔ ግጥም አርጎ የፈጠራት
.......................................
ኤላን የናፈቀችው
አስቱን ያሸፈተችው
ዘውድን የማረከችው
ኬቢን የታመነቺው
በላይን ያሳመመችው
   ጋሽ ደቤን የናፈቀችው
   ጋሽ ፀጋዬን የጠበቀችው
እርሷን ሴት ትመስያለሽ ጠቢቦች የተቀኙላት በደስታ በሂወት ፍሬ
በምኞት በእምባና ናፍቆት ሀያሎች የወደቁልሽ  መሰልሺኝ ተበታኝ ጥሬ
በሀሳብ ቅዠት ነበልባል ታውረው የሚከተሉሽ
ዝም ብዬ ሳስተውልሽ ላንቺ ነው የሚገጥሙልሽ !
አንቺን ነው መሰል የፃፉሽ.....

           

@gGetem
@gGetem
🥰1
ውሸት ነው በይኝ፡፡
እንደሰው ተወድጄ ተከበሬ የኖርኩበት ቀን ትዝ አይለኝም፡፡
ከሰው ጋር ራሴን አላወዳድርም አልልሽም፡፡
ካልተወዳርኩ ደስታዬ ሀዘኔ ከየት ይመነጫል፡፡ ከሰው አነስኩ ይሉ የለ እናቶች እንኳን፡፡ ከሰው እንዳላንስ ተመክሬ ተዘክሬ ነው ከእናቴ ቤት የተሞሸረኩት ለዓለም የተዳርኩት፡፡


ያለንፅፅር ወደድኩህ ስትይኝ የደነገጥኩት ለዛም ነው፡፡ በምን አቅምሽ ቻልሽው፡፡ አለማወዳደርን አለማነፃፀርን፡፡ ወይስ Ego የሚሉትን ጣጣ እንደገላሽ እጣቢ ደፋሽው?
:
:
ውሸት ነው በይኝ፡፡ እኔን እየነካሽ የሰማሽው ሙዚቃ ምንድነው?
ትዝታ?
ገና መቼ ኖሬና፡፡
አንቺሆዬ?
እኔ ሆዬ የደረጃ ምረኮኛ የፉክክር ባርያ ነኝ፡፡
አምባሰል?
መብሰልሰል መቁሰል ....በነገር መብሰል፡፡
ባቲ?
እንደሆንኩ ታውቂያለሽ መዋቲ፡፡
.
.
ታዲያ ምን ሰማሽ ታዲያ ምን ነካሽና ወድሀለሁ አልሽ፡፡
ተይ አታስክሪኝ፡፡ የኖርኩበትን የእሽቅድምድም ሕይወት ፉርሽ አታርጊብኝ፡፡
እያፎካከርሽ ውደጅኝ፡፡
እያወዳደርሽ አልምጅኝ፡፡


አፈቅርሻለሁ
ከሁሉም አስበልጬ
እናፍቅሻለሁ
ከሁሉም መርጬ
እጠራሻለሁ
አንቺን ብቻ ውጬ፡፡


ያለውድድር ያለንፅፅር መውደድም መወደድም ዓለም አይችልበትም፡፡
አንቺ እንዴት

@gGetem
@gGetem
👏1
..............


የተራቡ ነፍሶች፤ፍቅርን የተጠሙ
የደከሙ ጆሮ፤ልብን የሚሰሙ
የታረዙ ኣይኖች፤ከውበት የሸሹ
የጎደፈ ቆዳ፤በኑሮ የቆሸሹ
ደብዛዛ ኮከቦች፤ያደመቁት ሰማይ
ከዚህ ሁሉ መሀል፤ቆንጆ ሴት ኣማላይ
ውበት ለራበው ዓይን
ሀሴት የምትመግብ
ፍቅር ለጠማው ጆሮ
የነፍስ ጥኡም ዜማ፤የህሊና ምግብ
ለጎደፈ ገላ፤የዘላለም ኣልባስ
ብርሀን እንደ ኮከብ፤ከጨለማው እራስ
     ብቻ ግን ቆንጆ ሴት
ከተመሳቀለ የህይወት ሸራ ላይ
ምንም ቢሸሽጓት፤ጎልታ የምትታይ
ብርሀን ያልሆነች፤ወይንም ጨለማ
ከሁሉም ለሁሉም፤ጋር የምትስማማ
ቆንጆ ሴት ኣማላይ
ጉድፍ ከበዛበት፤የኑሮ ሸራ ላይ
ኣልባስ ሆና ልትኖር
ከጎደፈ ገላው፤ከፈገግታው ሰማይ
.
..
ወደሱ ተጠጋች፤ወደ ግራ ጎኑ
ካለሷ ላለፈው፤ለባከነው ቀኑ
ዋስ እንኳ ባትሆን፤ለሀዘኑ ጠበቃ
ከእቅፋ እንዲደበቅ፤ኣቀፈችው ኣጥብቃ
ምን ኣይነት መክሊት ነው፤እንዴት ያለ ጸጋ
ህመሜ የሚፈወስ፤ከእቅፋ ስጠጋ
የምን ሀዘን ስቃይ
በፍቅር ልንሳፈፍ፤ከደመናው በላይ
ከኑሮ ሸራ ላይ
የምንመኘውን ስእል፤ስሎ ማየት
ከረሀብ
ከሀዘን
ከችግር መለየት
ምን ያለ ሀይል ነው፤እንጃ ግን ኣላቅም
ብቻ ግን እቅፋን፤ይዛለው ኣለቅም
ልክ እንደ ክርስቶስ
እንደ ሀዲስ ኪዳን
እንዴት መታደል ነው
በእቅፎቿ መዳን


      

@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍1
--------አልጋዬ--------

ሆድ ያባውን፣ ብቅል ያወጣዋል፣
እያሉ ፣ስንቱን ዘርጥጠዋል፣
ብሶት ንዴታቸውን፣ አውጥተዋል፣
የብቅሉ ትኩሳት፣ ነግቶ ሲያልፍላቸው፣
በሀፍረት አንገት፣ መድፋታቸው፣

እኔ ግን፣ እንዲ አልኩ
ምሳሌውን፣ ወደራሴ ቀየርኩ

ሆድ ያባውን፣ ዕንባ ያወጣዋል ብዬ
አነባለሁ ተሸሽጌ፣ ገብቼ ጓዳዬ
መከፋቴን ምታውቅ፣ የውስጤን ስብራት
ባዶነቴን ያየች፣ ብሶቴን ማወጋት
አልጋዬ ሚስጥረኛዬ፣ ጩኸቴን አድማጬ
በጣም እወድሻለሁ፣ ከሁሉ አብልጬ።

       
           


@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍2
............


ሳሚኝ እና ልዳን፤ዳሺኝ በመዳፍሽ
ፊደል አቁስሎኛል፤አትሸንግይኝ ባፍሽ
ነካኪው ገላዬን፤ያካሌን ጉዳንጉድ
ኣፌ ቃላት ይርሳ፤እንጩህ እንደጉድ
ዳሺኝ እና ልንቃ፤በድን ነው ህይወቴ
ኣዝምማ ከብዳለች፤የወረስኳት ቤቴ
ኣላወድስሽም በሽንገላ በቃላት
ሆድሽን ላያባባው፤ነፍሴን ላይደልላት
ሀጥያት ነው ቢሉንም፤ካህንና ቄሱ
ተይ ጽድቁን ለነሱ
ይልቅ ለኔና ኣንቺ
ሳሚኝ እና ልዳን፤ዳሺው ኣካላቴን
የልቡን ኣያቅም፤ኣትስሚ ኣንድበቴን
ቃሉን እንጠየፍ፤ልናቀው ትዛዙን
በነገና ዛሬ ቀናት ፍቺ የገዙን
ሆነው እስከሚያዩት፤ደርሰው በኛ ቦታ
ሀጥያትን እንውደድ፤ሰው እንሁን ላፍታ
ልዳሰው ገላሽን፤ያካልሽን ጉዳንጉድ
ሳሚኝ እና ልዳን፤ልሳምሽ እንደጉድ
ፍቅር የጸነሰው፤ዝሙት እንደማይወልድ
ተዳሩ ቢሉ እንኳ፤መዳራት ለነሱ
በረከሰ ኣንድበት፤ስምሽን ለሚያረክሱ
ባይገባቸው እንጂ የመሳምሽ ምሱ
ጽድቁን ተይ ለነሱ


   

@gGetem
@gGetem
@gGetem
ልጠብቅሽ?!
ትመጫለሽ ብይ ቆማለው ከመንገድ
በአንቺ ተስፋ ቆርጭ አልሄድ
የፍቅራችንን ትላንት እያሰብኩኝ
በትላንትናችን ነጋችንን እያለምኩኝ
ግን አንቺ ጥለሽኝ ሄድሽ
እጠብቅሻለው እያልኩኝ ትመጫለሽ
እዛው ነኝ ጥለሽኝ የሄድሽበት ቦታ
አለ ልቤ በፍቅርሽ እደተረታ
ትመጫለሽ እያልኩኝ ከዛሬ ነገ
እደምትመለሽ ልቤ ተስፍ እያደረገ 
እዛው ነኝ የቆምንበት ቦታ
ልቤ አንቺንስ በማንም አይተካ
ብያደክመኝም መቆሙ ከመንገድ
ብሉኝም ሄዳለች አንተ ሄድ
እጠብቅሻለው እዛው ቦታ ላይ ሁኝ
እደምትመለሽ መንገዱን አምኝ

    

@gGetem
@gGetem
@gGetem
.......


ተናነስን
ከል ለበስን
ለፍቅርን ብለን
ምኞትን ተከትለን
በደረቅ ቁስል  ነተብን
ነፍሳችን  ከሌላ ነፍስ አተብን
በዕንባ ነጠብጣብ ሆሄያት ከተብን
ፍቅር ሆኖ ጭብጡ  መውደድ ነበር ቅሉ
ሰከርን በድግሱ ጥንስሱ   ማጣት ሆኖ ብቅሉ



@gGetem
@gGetem
@gGetem
ትወደኝና ዋ!

እልህ ነው የያዘኝ ያለመገኘትህ
እኔ አንተን ስልህ ሌላውን ማለትህ
ስትገኝ አይደለም ሳጣህ ነው ምወድህ

ሁሉ ሲፈልገኝ ስላልፈለከኝ ነው
በፍቅር እንዳይመስልህ እንደዚህ ምሆነው
እልህ ነው!
አደራህን ውዴ ከወደድከኝ ጠላሃለው
ከፈለከኝ ርቅሃለው
አውቀዋለው እኔ አመሌን
ሲፈልጉኝ መጀነኔን
ፍቅር እንዳይመስልህ እንዲህ ሚያደርገኝ
እልህ ነው ካለህበት ሁሉ ሚያሽከረክረኝ
ልንገርህ አንተ ሰው ከቶ እንዳትወደኝ
እኔ አመል አለብኝ
ስለዚህ አደራ ወደህ አታስጠላኝ!


@gGetem
@gGetem
👍2
ተቁነጥንጣ ቀረበችኝ
ተቻኮለች እንዳፈቅራት ፣
ተጨነቀች ወዲያው ደሞ
ተቻኩየ ስላቀፍኳት ፣

ትፈጥናለች ለማግኜት
ልቤን አርጋው የቀበሌ  ፣
ታምር አርጋ ቆጠረችው
በእሷ ፍቅር መቸኮሌ ፣

መቸኮልን አስለምዳኝ
ተጣድፎ ዝግታየን
አቻኩላ አገባችኝ
እይ ስትል እድሜየን ፣


ተቻኩላ አስለምዳኝ
ረጋ ያለ አረማመድ  ፣
ተቻኩየ ጥያት ሄድኩኝ
ቀድማ ከእኔ እንዳትራመድ

@gGetem
@gGetem
@gGetem
-----------ድንገት-----------
ድንገት ሳላስበው፣ ልቤ ዘልቆ ገብቶ፣
ጣፋጭ በሆኑ ቃላት ፣እራሱ ወትውቶ፣
ዓለምን እንደ አዲስ ፣ለማየት ሚረዳ፣
ፍቅር መነፅር እንደሆነ እያስረዳ፣
ንፍገት የለሽ ፍቅሩን ፣በልቤ አነጓግዶ፣
ድንገት ተሰወረ፣ ክፉ አስለምዶ።

እኔ ምልህ ፍቅሬ...
እንደው ምን ገጥሞክ ነው? ከዐይኔ የራቅከው
ታስባለች ሳትል ከእኔ የሸሸኸው?

      

@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍2
የሰው ስህተት

ተቀይርክ አሉኝ ተገርመው
አፍ በእጅ ያዙ  ተደንቀው
አንተ አይደለህም ይሉኛል
አዎ አይደለውም እኔንማ ገለውኛል
መቀየሬ ገረማቸው
ገለው ክደው ሰባብረውኝ ምን ሆነሀል ጥያቄአቸው
እራሳቸው መልሴ ናቸው
አልናገር አልጋገር
ዝምም አልል እሰጣለው መልስ ነገር
አልነበርክም እንዲ አልሆንክም ለሚሉኝም
አዎ አልሆንኩም አልነበርኩም ግን አሁንም ባዶ አልሆንኩም
አዎ ነበርኩ ሳልሰበር
ለጥያቄው መልሴ ነበር
የለም ዳኛ ሀቃቢም ህግ
የኔን ስሜት ሚደነግግ
ማንም ምንም አይሰማው
ማንም ቢሆን የራሱን ነው የሚሰማው
የለም አንድም የበደልኩት
ነክሶኝ ሄዶ ያጎረስኩት
ደግሞ አማኝ እንደካድኩት
ትቶኝ ሄዶ ይናገራል እንደተውኩት
ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት አይጠፋም ግን ይመራል!
መሳሳቱም መዛዛጉም ከአንገት በላይ ግን ያቅራል
ሁሉም ፃድቅ ሁሉ በጎ
እኔን ክፉ ሰው አድርጎ
ሁሉም አለው የራሱ ልክ
ለፈፀመው ሰበብ ምክኒያት የሚያላክክ
ላንዱ በደል ላንዱ እውነት
ልክነት ነው የሰው ስህተት

         

@gGetem
@gGetem
👍3🗿1
ቋጠሮሽ


ዞሮ ዞሮ ከሀገር   ዞሬ ዞሬ ካንቺ
ካንቺ ሚስበኝን  ቋጠሮሽን ፍቺ

ከተሰደዱበት  ሀገር ቢመለሱ
እንደው ተጓዙ እንጂ  ድሮስ መች ደረሱ

እንደ አፈሯ ሽታ  እትብቴ ከተቀበረባት እኩል
እረቄ ከሄድኩት  ትጎትተኛለች በትዝታ በኩል

ሀገርስ እናት ነች  ብወድቅ ባላገግም
አልጋ ባትሰጠኝ   በረንዳን አትነፍግም

ያንቺ ግን ጥላ ነው  ወደ ፀሀይ ስዞር
  ከኋላ ይወድቃል
ተፈጥሮው ነውና  ስርቀው ይቀርባል
ስቀርበው ይርቃል

የኔ ፍላጎቴ  መራቅ ብቻ ካንቺ
በቃ ልሂድበት  ቋጠሮሽን ፍቺ

የታመመን ትናንት  ዛሬ ባማርርም
መድረስ ከሌለበት  ነገን አልገብርም



@gGetem
@gGetem
@gGetem
1💋1
..............


ከማበዴ በፊት፤ኣንድ ቃል ልንገርሽ
ላንቺ ብዬ ኣይደለም፤ጨርቅ የምቀድልሽ
ስለተውሺኝ ብዬ
መራቅ መገፋቴን፤መቻል ስላቃተኝ
ፍቅርሽ እንደ ቅዘት፤ስለሚያቃትተኝ
ከምቀደው ልብሴ፤ከገላዬ ካለው
ትዝታሽ ብቻ ነው፤በውብ የተሳለው
ጠረንሽ ነው ያለ፤ከገላ ከጨርቄ
የሄድሽ ቀን ጣልኩት፤ሀፍረቴን ኣውልቄ
    ከማበዴ በፊት
ኣንድ ቃል ለናገር፤ፍቅርዬ ባንቺ ፊት
  ኡ ኡ ብዬ ብጮህ
እንዳትጠብቂ ከጬኀቴ መሀል
ከቶም ስምሽ የለም
የኔ ውድ የኔ ኣለም
ለኔ ኣይነቱ ኣፍቃሪ
እብደት ጤንነት ነው ከእስሩ መፈቻ
ኣንቺን አንቺን ብቻ
ማለቱን እረስቶ
ፍቅርን እንደጨርቅ፤ከገላው ለይቶ
     ከገረባው መሀል
ተግቶ ሊፈልጋት፤የጠፋችው ፍቅሩን
ቅጠሏ ኣመርቅኖ
ግንዷ የበከለ ሰማይና ምድሩን
    ቅጠሏ ፍቅር ነው፤ሙትን የሚባብል
ግንዷ ደሞ ግፍሽ፤በቁም የሚገድል
  ለዚህ ይሆን ? እብድ ሁሉ
ገረባ የሚያነሳ፤ገረባ የሚጥለው
የጠፋችው ፍቅሩን፤ስለምትመስለው
       እናም ፍቅርዬ
    ላብድ ስለሆነ እንዳትጸጸቺ
ኣንቺን ፍለጋ ነው፤የማበዴ ፍቺ
ከሰው መሀል ባጣሽ፤ካትሮንስ ባትገኚ
ኣብጄ ፈለኩሽ፤ገረባ ስትሆኚ


   

@gGetem
@gGetem
@gGetem
🥰1
2025/07/10 05:31:31
Back to Top
HTML Embed Code: