Telegram Web
ፍቅርን ፈራን
(ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን)

ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነት ለመድን

“ፈራን”
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን

“ናቅን”
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን

“ናቅን”
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን

“ጠላን”
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ

“ራቅን”
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን

@gGetem
@gGetem
"ያ ባሏ ፈታት አሉ...ወስልታበት"
"አየህ አይደል ለክፉ ክፉ ሲያዝበት?"
"ኧረ ከሷ ውጭ ሴት አያውቅም ነበር"
"ሚስትህ ነግራኝ ባይሆን አላምንህም ነበር"


@gGetem
@gGetem
@gGetem
🔹🔹🔺🔹🔹🔺

ስንት ጊዜ ይፈጃል ምን ያህል አመታት
ስንት ሰዉ ይበቃል ትዝታን ለመርሳት

ምን የሚሉት ጂኒ ካንተ ጋር አሰረኝ💙
የትኛዉ መለኮት በፍቅርህ ጠፈረኝ

በየትኛዉ ጥበብ በየትኛዉ ዘዴ
በየትኛዉ ብልሀት አወከዉ የሆዴን

እንጃ................
ጊዜም መልሱ ጠፋበት መሰለኝ
ካንተ ጋር ይነጉዳል ጥያቄ እያጫረኝ

ስንት ዘመን ቀረኝ
ስንት እድሜ ይተርፈኝ
መቼ ያሳርፈኝ


ትዝታህ ጠቢቡ
ትዝታህ ብልሁ

ትዝታህ ብልጥ ወዳጅ🔻
እያሳሳቀ ነዉ አብሮ ሚያሳቅቀኝ
እያጫወተ ነዉ እድሜዬን የቀጨኝ

ወይ እሱ ይተወኝ ወይ አንተ ደግመህ ና
ትዝታህን ዉሰድ እኔን መልስና።❤️

┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
@gGetem
@gGetem
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
1👍1
አዝነህልኝ ይሆን
በገዛ ልቤ ስቀበር እያየህ
አይተኸኝስ ይሆን ሲገርፈኝ ትዝታህ
ህይወት ስታጎለኝ ከልብህ ነጥላኝ
አለም ስትጨልም ከአንተ ላይ አጥፍታኝ
አሳዝንህ ይሆን🥺🥺🥺
@gGetem
@gGetem
ግጥምና አበባ

በርግጥም በርግጥም
አትጨክኚም አይደል በአበባ በግጥም
ትወጃለሽ አይደል?
ሀቅን በቃል መግደል ?
ትፈቅጃለሽ አይደል ?
በስንኝ መደለል?

( እንግዲህ... )

እውነት እንኪገባሽ
ፍቅር በአፍሽ ጥላ
መውደድ በዓይንሽ ጥላ
ናፍቆት እንዲያረቅሽ
ህይወት በአንቺ ገላ
እስከዚያ ግን ድረስ
ተስፋ ተሞልቼ...
ባዶ እጄን ልመለስ
እየከፋኝ ልግባ
እስክሰጥሽ ድረስ ግጥምና አበባ!


@gGetem
@gGetem
👍1
#የጥምቀት_ስንብት
#ሊዮ_ማክ 💔
#የቀጠለ
#የጥምቀት_ስጦታ
"እ....አለኝ... አለኝ"ብዬ እጄን ወደ ኪሴ ስሰደው አንድ ባለ አምስት እና ባለ ሁለት ባለ ሀምሳ የብር ኖት ይዞ ወጣ:ወዲያውኑ አንዱን ሀምሳውን ብር ስሰጣት "አይ ከሌለህ ተወው አስር ብር ብቻ ነው የፈለኩት" አለችኝ፡እኔም ይህን ጥሩ አጋጣሚ ማለፍ ስላልፈለኩ ችግር የለውም አልኩኝ ከዘረጋችው እጇ ላይ እያኖርኩት:ግን በመሀል ምስጋና ይግባት እና በቀሩት አርባ ብሮች ፈንታ እንድቀላቀላቸው ስትጋብዘኝ አላመነታው ወዲያውኑ ነበር የተስማማሁት አብረንም ሔድን አታስተዋወቀችኝ ናርዶስ፣ሳባ፣ኤልሳ ከእኔ ልብ ላይ ደግሞ የቀረችው ቤዛ ነበር ስሟ እንደጨበጥኳት በዚያች ቅስፈት ሳለቃት እድሜ ልኬን እንደያዝኳት ለመኖር ለራሴ ቃል ኪዳን እየገባሁ ያለ ያክል በትኩረት ተመለከትኳት፡እርሷም ሴትነቷ ይዟት እንጂ አንዳች ነገር ውስጧ እንደተፀነሰ ታወቀኝ ከአይኖቿ ላይ....
እና በአንድ እይታ የተጀመረው ትውውቅ፡ እየዋለ ሲያድር አንዳች የጋለ ፍቅር ውስጥ ከተትን ብዙ ነገሮችም በመሀከላችን ለመፈጠር እና ለመከናወን አልፈጀብንም በሰዓቱ ለአመታት የምንተዋወቅ ጥንዶች የሆነን ያክል ተሰማን ግን ከአስራ አምስት ቀን በኃላ ፀብ በመሀከላችን ተፈጥሮ ተለያየን።በጓደኛዋ ምክንያት የተጀመረው ትውውቅ መልሶ በጓደኛዋ ተ...ለ...ያ....የ...ን....
www.tgoop.com/gGetem
እናም ዛሬ ከዚህ ሁሉ ነገር መፈጠር በኃላ እንደ ጨው ክምር ሀውልት አድርጎ ያስቀረኝ የእናቴ ንግግር እንዲህ ይል ስለነበረ ነው።
"ፍቄ አየሀት እህትህን የሟቹ የአጎቴ ኪዳን ልጅ እኮ ነች:ለበዓል የአሰላ መጥታለች ብላኝ ነበር እናቷ ና እናናግራት ብላ ልታናግራት መንገዱን ስታቋርጥ፡ እውነታውን ከሰማሁ አንስቶ የፈፀምነውን ያንን ሁሉ ነገር ሳስበው እርሷም ዘመዴ እህቴ መሆኗን ሳውቅ ወሽመጤ ቁርጥ ብሎ ባለሁበት ተተክዬ ቀረሁ ..............
(ጥቆማ👆😟)
ሀሳብ፣ቅሬታ፣ብርታት፣ነቀፌታ ካለ)👇
www.tgoop.com/gGetem
www.tgoop.com/leoyri
ንፍገት
ደራሲ ጆሲ
የሚሆነው አይታወቅምና በርህን አጥብቀህ አትዝጋ ብላ አያቴ ትነግረኝ ነበር። እኔም የእርሷን ምክር አንደ ዶግማ በልቤ ፅላት ፅፌው ይሀው ዛሬ ድርስ በራፌን አልዘጋም። ምሽት ከሆነና እቤት ከሌለው ብቻ ነው በራፌ የሚዘጋው።
ታዲያ  ይህ ባህሪዬ ከቤት አልፎ መስሪያ ቤትም ተከትሎኝ ከትሟል።  እንደተለመደው በራፌን ገርበብ አድርጌ ስራዬን እየሰራው ሳለ በራፌ   ተንኳኳ  መሰረት ነበረች። ምንግዜም እርሷ  በር  ስታንኳኳ  ለየት ያለ ስለተ ምት  ነበረው። ኳኳ ኳ ኳኳኳ ኳ ታደርግና ጥቂት ትታገሳለች ከዛም ከፍት ከሆነ ትገባለች አልያም ዝግ ከሆነባት ተመልሳ ትሄዳለች ትዕግስቷ የጠብታ ያክል ናት ። እኔም ፀባዮዋን ስለማውቅ መሲ ግቢ አልኩኝ አይኔን ከኮፒተሬ ላይ  ሳልነቅል። ለአፍታም የምሰራውን ገታ አድርጌ ቀና ስል   መሲ    ከክፍሉ ዘልቃ ኖሯል በፈገግታ እንደደመቀች ገዜ እንዴት ውልሃል አለችኝ በቆመችበት ሳለች ። ፈገግታዋ ልብ የሚሰርቅ ነው። መሰረት ከቁመቷ ዘለግ ያለች ቀይ  ብርቱካን የምትመስል አጠር ያለ  የስፌ ቀሚስ የምታዘወትር አላፊ አግዳሚ ሳይቀር በውበቷ  የሚማረክባት ውብ ሴት ናት። መሲ እንዴት ውለሻል ደግሞ ዛሬ ውብ ሆነሻል። ... አይደል አለችና ከእግሯ አንስታ እራሷን ተመልክታ አመሰግናለሁ አለች።

በሁለት እጇቿ  ደረታ ላይ ለጥፋ አንዳች መፅሔት የመሰለ የወረቀት ጥራዝ ይዛለች አትኩሬ ተመለከትኩት እውነትም መፅሔት ነበር። አረፍ በይ አልኳት በእጄ ወንበሩን አያመላከትኳት። ፈጥና ተቀመጠች በእጇቿ ይዛው የነበረውን መፅሔት ከፊት ለፊቷ ካለው ጠረፔዛ ላይ  አስቀመጠችው። ጥቂት የግል ወሬያችንን ስናወጋ ቆየንና እኔ ምልህ ገዜ አለች የወሬውን አቅጣጫ ለማስቀየር ቀጠለችና ትናንት ትልቅ እንግዳ ነው ያለን አላልኩህም ነበር። ማን እንደ ሆነ ገምት አለች አይን አይኔን እያየች። እኔም ሊሆኑ ይችላሉ  ብዬ ያስብኳቸውን ሰዎች ጠቀስኩ። ግን  መሳሳቴን ፊቷ ይናገራል። መፅሔቱን ከስቀመጠችበት በማንሳት ተመልከት የዚህ መፅሔት አዘጋጅ የሆነችው ሴት አወካት  አለችኝና መፅሔቱን ሰጠችኝ ተቀብያት ማገላበጥ ያዝኩ።  እንዴት የምታሳዝን ሴት መሰለችህ  በፊት የነበራት የሞራል ልዕልና ከስሞ የአዕምሮ መቃወስ ሁሉ ገጥሟት ሰራም ማቆሟን ባደረኩት ማጣራት ማወቅ ችያለሁ። ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ቀሚሷን ወደታች ወደታች እየሳበች ለመንኛውም ይሄንን ልነግርህ ብዬ ነው ብላኝ ወጣች። አፃፃፉም ሆነ የስዕልና የፎቶግራፎቹ አቀማመጥ ልጅ ሳለሁ እቤታች ያሸበርቅበት የነበረውን ጋዜጣ አስታወሰኝ። ትዝ ይለኛል ለሰዓታት የቤታችን ግድግዳ ላይ አፍጥጬ ነበር የምውለው።ፖለቲካ፣እስፖርት፣የሃራጅና የጨረታ እንዲሁም የስራ ቅጥር  ማስታወቂያው መዝናኛውም ቢሆን ለንባብ የሚጋብዝ አፃፃፍ ነበራቸው  የአዘጋጆቹም ብስለት ይሄ ነው የማይባል ነበር።ከሁሉም ከሁሉም መዝናኛ ላይ ያነበብኩት #ከገፅ 3የዞረ የአንድ ጫማ ሰፊ አሟሟትን  የሚያትት ፅሑፍ ጉዳይ መጨረሻውን ፍለጋ ግድግዳው ሳስስ የቆየሁበትን ጊዜ አልረሳውም እስገዛሬ ድረስ በውስጤ መጨረሻው ጥያቄ ሆኖ አለ ለሁሉ ግን ክብር ይገባቸዋል!#
ለሰዓታት ከተጓዝኩቀት የሃሳብ ጎዳና ወደ ዛሬ ተመለስኩ እውነት ነው ክብር ይገባቸዋል። ስንቱን መወደስ የሌለበትን ስናወድስ ክብር ለሚገባቸው ግን ክብርን ነፍገናቸው የት እንደ ወደቁ እንኳን አለማወቃችን ያሳፍራል

ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ!

ለሃሳብ አስተያየት
ጆሲ:@yosikeman
ለመቀላቀል
@gGetem
👍1
የናፈቀኝ ነገር
ያልኖርኩበት ሃገር!
ማንም ሰው ሳያውቀኝ÷ ከዜሮ መጀመር
ጠዋት የምሰማው
የማላውቃትን ወፍ፣ አዲስ አዘማመር።

የፈለግሁት ነገር
መኖሪያ መቀየር
ልብሴንም መቀየር
ለየት ቢልልኝ
የምጠጣው ውሃ÷  የምስበው አየር።

መራመድ የሚያምረኝ
በአዲስ ጎዳና ላይ  ÷ በኔ እግር የነቃ
ባገኝ አዲስ  ሃሳብ
አዲስ አይነት እውነት ÷ ወይም አዲስ ቋንቋ።

ማየት የምመኘው ÷ያልራቀ ወደላይ
ሰማያዊ ሳይሆን ÷አዲስ አይነት ሰማይ
በማላውቀው ቀለም ÷ አዲስ አይነት ፀሃይ።
.
.
.
የማውቀውን ሁሉ
መተካት በመሻት
ወደማይታወቅ
ህይወቴን ብሸሻት
የማልሰለቸውን ÷ አጣሁት ፈልጌው
(ስገምት ችግሩን)
አዲሱን የሚያስረጅ ÷ እኔ ነኝ አሮጌው።

በርግጥ እንኳን ማርጀት ÷ መኖር ይለመዳል?
መሰልቸትን መቻል÷ ከናፍቆት ይከብዳል?

በማውቀው  አኗኗር÷ መኖር ከከበደኝ
ወደማይታወቅ ÷ ልቤ ካሰደደኝ
እኔ የሌለሁበት ÷ ማንስ በወሰደኝ?
ወላጅ ባገኘሁኝ
በሆነ አይነት ታምር÷  ዳግም በወለደኝ??



@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍1
ጥለሺኝ እየሄድሽ
.....
መንገዷን ጨርቅ አርገው፣
ህይወቷንም ቀና፤
የምል አይነት እንከፍ,
የምል አይነት ጀዝባ ፡ አይደለውምና፦

ኋላ አደናቅፎኝ
ከፎቅ ላይ ብጥልሽ
ስለምትጎጂ፤
ከተፋታን ወዲህ
መንገዱ ያሰጋል
ተጠንቅቀሽ ሂጂ።

@gGetem
@gGetem
👍2
Audio
🙏🙏🙏
....... አጣብቂኝ
.............................🙏🙏🙏
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
@Leoyri
@gGetem
@gGetem
ነይ


በሰማያዊ ሰማዩ ላይ  አንሳፈፍ
በፍቅራችን ምናብ  እንበል እና ከፍ
መኖር ውልክፍክፉ  ሳያደናቅፈን
ነይ ሀሴት እናድርግ
              በመውደድ ተቃቅፈን
ነይ አብረን እንብረር
           ይህ መኖር ሳይጠልፈን

በህይወት ውበቷ  የመኖርን ክርታስ
ሰብረን እንጣለው   መኖርን አናስታውስ

በአብሮነታችን    አለምን እንራሳ  
ለኛ አይገባንም  ያለም ግሳንግሷ  
          መኖርን እንካድ
              ፍቅርን እናሳድ
እግዜር ይቀዬመን   ሀጥያታችን ይብዛ
አብረን እንጥፋ እና   አለምን  እንግዛ

ነይ

መዓት ይውረድብን  ሀጥያታችን በዝቶ
አንድ አንቺ ካለሺኝ  ምን ሊጎድለኝ ከቶ
ነይ....................





@gGetem
@gGetem
@gGetem
ናፍቃኛለች🥺❤️‍🩹
🍂     🍂     🍂     🍂      🍂
✍️ብሌን

🎤ናቢኦት🥰

                             
@gGetem
@gGetem
Join as
1
Audio
ምርጥ ግጥም
🎙🎙🎙ናትናኤል
ለሃሳብ እና አስተያየት @yosikeman
ለቤተሰብ ለመሆንና ለማጋራት @gGetem
Rip የኔ ጀግና ወንድም ስራህ በልቤ ከፍ ብሎ ይደመጣል።
Audio
ምርጥ ግጥም
🎙🎙🎙ናትናኤል
ለሃሳብ እና አስተያየት @yosikeman
ለቤተሰብ ለመሆንና ለማጋራት @gGetem
Rip የኔ ጀግና ወንድም ስራህ በልቤ ከፍ ብሎ ይደመጣል።
አንድ ወዳጄ ምን አለኝ መሰላችሁ "በጣም ከባዱ ነገር የሚወዱትን ማጣት ሳይሆን የሚወደንን ማጣት ነው"።
@gGetem
@gGetem
( ቆየን አይደል .. )
==============

ቆየን አይደል
:
የማለዳ አአዕዋፍ ድምጽ
ከእርጋታ ጋር ካደመጥን
ጀምበር ቀልታ ጎህ ስትቀድ
በተመስጦ ካደነቅን ...

ቆየን አይደል
:
እናት አባት ሲመርቁ
ከልባችን " አሜን " ካልን
ጨቅላ ሕጻናት በየሜዳው ሲቦርቁ 
በመደሰት ካስተዋልን ....

ቆየን አይደል
:
ዝናብ መቶን ጸሐይ ሞቀን
" እፎይ " ካልን
ጨረቃ እና ኮከብ ናፍቀን
ወደ ሰማይ ቀና ካልን ....

ቆየን አይደል ?



@gGetem
@gGetem
@gGetem
🔥1🥰1
መሳቀቅ
ካልወሉበት ዉለው ባለቤቱን ማነቅ
መደንገጥ
ያለርባን አሳቦ ልብ ምት ማቋረጥ
መታመም
አሜን ለማይል ልብ ሰርክ ሁሌም መሳለም
ማርገብገብ
ለነደደ እሳት ለዕፍታ መስገብገብ


ለማትረጋ እርግብ ጎጆ እየቀለስን
በበረረች ቁጥር ስንት ጊዜ አለቀስን
እያወቅን ስራችን እንደሌለው ጥቅም
በጨዋታ መሃል ስቀን አናስቅም
ማርገብገብ ለምዶብን ለጊዜ ተቀማጭ
እንራወጣለን እስክንሆን ተለዋጭ
መሆንን ሳናውቀው ኑረን በጉድ ሀገር
ደሃ አድርጎ አስቀረን ልማድ ሚሉት ነገር

ለመሆን ሳንጥር ስንት ጊዜ ፈጀን
       በማስሆን አረጀን
ለነዋሪ ጊዜ ሆነን አኗኗሪ
         አደረገን ቀሪ።


@gGetem
@gGetem
@gGetem
1👏1
የሆሄያት ህብር📝📝
@gGetem – የቢሆን ዓለም ክፍል 11
ቀጣዩ ነገ ስለዘገየን ይቅርታ እንጠይቃለን
ፍቅር በቃኝ
እኔ ልበ ስንኩል ማፍቀር የተሳነኝ
የወደድኩትን ውድ ጨርሼ ማልገኝ
መውደድን ለመውደድ ኃይል ያጠረኝ

ካቅሜ አንጠፍጥፌ ልጠቀለል
ባንድ ሰው ሥር አረፍ ልል
ብጥር ብጥር
ለጨዋታ ሆኗል አሉ የፍቅር ነገር 
እውነት ቀርቶ በትብብር

እንደውም
ሰዶ ማሳደዱም ደክሞኛል ሰጥቶ መቀበሉም እንዲሁ
የገባው ሰው እስኪመጣ የራሱ የፍቅር ትርጉሙ
መፅሐፉ ላይ የተፃፈው እንደዚህ ነው የተባልነው 
እርሱ ሰው ተገኝቶ እስከሚያሳርፈኝ
ፍቅር በቃኝ


@gGetem
2025/07/13 23:25:34
Back to Top
HTML Embed Code: