Telegram Web
የቢሆን ዓለም ክፍል 12
@gGetem | የሆሄያት ህብር
የቢሆን ዓለም ❉⎈
#ክፍል_12

ደራሲ - ደጉ ቁምቢ
ተራኪ - ተስፋሁን ገ/ዩሐንስ

ሁላችሁንም ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ የፍቅርና ሳይንሳዊ ነክ ልቦለድ።

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @yosikeman
የቢሆን ዓለም ክፍል 13
@gGetem | የሆሄያት ህብር
የቢሆን ዓለም ❉⎈
#ክፍል_13

ደራሲ - ደጉ ቁምቢ
ተራኪ - ተስፋሁን ገ/ዩሐንስ

ሁላችሁንም ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ የፍቅርና ሳይንሳዊ ነክ ልቦለድ።

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @yosikeman
አካል ቡጢን ፈርቶ
በምላሴ ሸጥኳት
እህቴ ናት ብዬ
እኔው ሚስቴን ዳርኳት



@gGetem
@gGetem
@gGetem
🏆1
አንቺን ነበር የፈለኩት
ላንቺ ነበር የተሳልኩት

ወይ አለችኝ ህልም ብላ
ጋኔል አለች ጨለም ብላ
መቼ ሰማች ወይብላ

የጠራናት ከአመት ቁስል
ሞተን ቆየን መጣሁ ስትል

ደከምኩኝ እስካለሽ
ተብከነከንኩ በየአፍ
ይቅናህ በይኝ እንዳገኝሽ
አልደረስኩም ስንቱን ባልፍ

ደሜን ማነው ያባከነው
ሞቴን ብቻ ሚመነዝር
አንቺን ከእኔ እያራቁ
ቃሉን ደግመው የሚያሰምር
ማነው አንቺን የሚያፈቅር ?
ማነው አንቺን አምኖ ሚያድር
ማነው ላንቺ የሚሰክር ?

ከእኔ ብቻ ዕንባ ዕንባ
ከእኔ ሌላ ህመም አለ?
ወይ'ብላም አጠራኝም
ኮሶ ብቻ መድን ካለ

ኑሮሽን እንድሸከም
ወንድሞቼን ፈለኳቸው
ተከዜ ላይ ጎርፉን ሆነው
ወድቀው ነው ያየኋቸው

ሶስት አይን ጥቁር ያላት
ሀዘን ጫንቃ የበዛባት
ይቺ ሀገር ሀገር ሳትሆን
የሲኦል በር ማለፊያ ናት !
       
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
@gGetem
@gGetem
የቢሆን ዓለም ክፍል 14
@gGetem | የሆሄያት ህብር
የቢሆን ዓለም ❉⎈
የመጨረሻው ክፍል
#ክፍል_14

ደራሲ - ደጉ ቁምቢ
ተራኪ - ተስፋሁን ገ/ዩሐንስ

ሁላችሁንም ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ የፍቅርና ሳይንሳዊ ነክ ልቦለድ።

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @yosikeman
🌿❤️እንዴት አደርሽ🌿
Yohannes_Lawgaw ስለ እኔ @sleenee Yohannes Lawgaw sle enee
🌿ዛሬ ማለዳ በዛሬ ህይወት ሰላም በሆነች ንጋት.. እልፍ #ተስፋ ባለባት...🕊🌿ያንቺ እንደሆንኩ ነቅቻለሁ ♥️ እንዴት አደርሽ🌿
🌿Yohannes Lawgaw 🌿
🌿#Morning_Queen #ጠዋት_ስትነቂ #ማለዳ #ፀሀይ
#ስጦታዬ #ፍቅር #ዕለተ_እሁድ
🦋••
@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍1
ማጉያ

ያንዳንዷ ቆንጆ ሴት:
ውበት የሚጎላው:
በምታስከትላት:
አስጠሊታ ሴት ነው::

By yisimak worku

@gGetem
@gGetem
#ለምን በህልሜ መጣሽ#
ለምን በህልሜ መጣሽ
ልረሳሽ ነበር.... ትዝታሽን ሁሉ ትናንት  ጋረ ጥዬ
አንቺን የሚያስታውስ ሰውን ወዲያ ብዬ
ልረሳሽ ነበረ....
ልቤ ጨክንና ከሌላ ተዛምድ
ትዳር ከምቶንህ  ከእርሷ ተዋደድ
ይህን ከማለቴ ቀናት ሳይቆጠር
ወራት ተደማምረው አመት ሳያስቆጥር
በህልሜ ጎዳና  ይሀው ዛሬ መጣሽ
Written by :Joy see(@yosikeman )
@gGetem
@gGetem
👏1
Audio
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
ምርጥ ግጥም
🎙🎙🎙ናትናኤል
ለሃሳብ እና አስተያየት
Rip የኔ ጀግና ወንድም ስራህ በልቤ ከፍ ብሎ ይደመጣል።🎙🎙🎙ናትናኤል
@gGetem
@gGetem
👍1💔1
ስንብት
-----------------                                                                   ተሰነባብተንም አይቆሮጥልኝ ፍቅርህ                                      በኔ ላይ ካስቻለህ ያው መንገዱ ይቅናህ ።                              ሁሌ ማወዛገብ ሁሌ ማስፈራራት                                           ሁልጊዜ መታመም ሁሌ መሰቃየት                                          ለኔ ካሰብክልኝ እስኪ ልቤን ያዛት ።                                    ጭንቀትህን ንገረኝ ህመምህን ልታመም                                 ልሞት ነው አትበለኝ ..........                                                    ፍቀድልኝ እና እንይ ይቺን አለም።                                    እጅህን ልያዛት                                                                 ከሞትንም አብረን ነው                                                        አይተን ያለም ግዛት።                                                       እየተሰናበትክ ነፍሴን አስጨነካት                                                        የኔ ፍቅር                                                       ፍቀድልኝ እና ነፍስህን ልያዛት ።                                                                               

@gGetem
@gGetem
#መሳቀቅ

ካልወሉበት ዉለው ባለቤቱን ማነቅ
መደንገጥ
ያለርባን አሳቦ ልብ ምት ማቋረጥ
መታመም
አሜን ለማይል ልብ ሰርክ ሁሌም መሳለም
ማርገብገብ
ለነደደ እሳት ለዕፍታ መስገብገብ


ለማትረጋ እርግብ ጎጆ እየቀለስን
በበረረች ቁጥር ስንት ጊዜ አለቀስን
እያወቅን ስራችን እንደሌለው ጥቅም
በጨዋታ መሃል ስቀን አናስቅም
ማርገብገብ ለምዶብን ለጊዜ ተቀማጭ
እንራወጣለን እስክንሆን ተለዋጭ
መሆንን ሳናውቀው ኑረን በጉድ ሀገር
ደሃ አድርጎ አስቀረን ልማድ ሚሉት ነገር

ለመሆን ሳንጥር ስንት ጊዜ ፈጀን
       በማስሆን አረጀን
ለነዋሪ ጊዜ ሆነን አኗኗሪ
         አደረገን ቀሪ

                                                       

@gGetem
@gGetem
ሆድ ለባሰው አንጀት
       እንባ እንደው አይገድም
ፍቅርንና ናፍቆት መለየት ያቃተው
        ለማፍቀር አይሄድም
ድም
      ድም
            ድም
                  ድም
  ማሰብ ማሰላሰል
   አስታወስኳት መሰል

ነጋሪት ቢጎሰም መለከት ቢነፋ
ከ'ሷ ዘንድ አድርሶ
ከ'ኔው ዘንድ ሚመልስ አንድ ዜማ ጠፋ
ሁሉም ወሳጅ ሆነ አድርሶ የሚያስቀር
ታድያ
የናፍቆት ነው እንጂ እንዲህ ሆነ ማፍቀር?
እንጃ
እንጃ
እንጃ
ከራስ ጋር ፍጥጫ

በምሰማው ዜማ እሷን ሚያስታውሰኝ
        አንድ ነገር አላት
     ቆይ እሷ ምንድን ናት

ብናፍቅ ሳልከጅል
እባላለው ወይ ጅል?
ብተክዝ ብፈዝም በሃሳብ ነበልባል
ናፈቃት ነው አፈቀራት ምባል?
አይ.....አይ አይ
ናፈኳትም አልናፈኳትም
ብቻ አላፈቀርኳት

@gGetem
@gGetem
@gGetem
ቀኝ ጉንጬን ቢመታኝ ግራ አቀረብኩለት
ያንገቴን ቢነጥቀኝ የእጄን ደገምኩለት
ተማምኜው ነበር መዳኔን በፍትህ
ዱላው ሲጠነክር አልዞር አለኝ ፊትህ
የወለዱትን ልጅ ነጥቆ እንደማስታቀፍ
ያቆሰለን ስቆ በእመነት እንደማቀፍ
ምን አለ የከበደ ?
ያልጸነሰ ሆዷ ቢያምጥ ምን ወለደ
ከደረቀ ጡቷ ምን አስጎነጨችው
የያዕቆብ ዘር ብላ ልጄን ነጠቀችው
በስምህ ነው አሉ
በደሉ በሙሉ
ነጻነቴን ነጥቆ ክቡሩን እያሻረ
ምነውሳ አብርሀም ቃልኪዳኑን ሻረ
ለመከነ መሀጸን ፍሬ ላላደለው
ከእቅፌ ነጠቁኝ የያዕቆብ ዘር ብለው
በስምህ ነው አሉ
ገራፊው በሙሉ
ቀኝ ጉንጬን ቢመታኝ ግራ ደገምኩለት
ግራዬን ቢደግመኝ ምኔን ላቅርብለት
ትግስትም ጡር አለው ለማመንም ገደብ
ከገራፊዋች አፍ ወንጌልህ ሲነበብ
ቃልህ አያጽናናም
ፍቅርህ አያጸናም
ሜቼም የናት አንጀት
ለወለደው እንጂ ላመለከው አይደላም
የእንባ ማድጋህን በንሰፍረው አይሞላም
ህግጋት አላቅም ቅኖናና ዶግማ
ትፈርድልኝ እንደው መበደሌን ስማ
በስምህ ነው አሉ
በዳዩ በሙሉ
ስለት ያበዛብን
ጭነት የጣለብን
ጋን ላቆመ ጠጠር
ጠብታ የመቆንጠር
ያህል ለወደደኝ
በክብሩ የማገደኝ
ሴትነቴን ንቆ
ጭኖቼን ፈልቅቆ
ሲደፍረኝ የዋለ
ለስምህ ነው አለ!



The Handmaids Tale : Nolite te bastardes carborundorum

By mad12titan

@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍1
.............

ትንሽ
ትንሽ
የቆጠብናትን ሳቅ
ነይ አብረን እንሳቅ
የእንባ ላቦት
ፊቱን አጥቦት
የኑሮ አለት ከሚጋፋ
በለቅሶ ጉም የሚጠፋ
የህመም ሲቃ የቋጠረ
ያንገቱ ክር የከረረ
አንቆ እስትንፋስ ለሚነጥቀው
እያላላ ከሚስቀው
የሰው መንጋ
ሳንጠጋ
ገሽሽ ላርግሽ
ካለምኩበት ልመሽግሽ
የፎረፍናት ከፈጣሪ
የደበቅነው ከአሳዳሪ
አለኝ ቦታ
ድረሽ ላፍታ
እዚህ ጋራ ባልልሽም
የማልመው አይጠፈሽም
ተገኚልኝ ከቀጠርኩሽ
ንገሺልኝ ከሰየምኩሽ
ካነገትነው የቀን ቀንበር
ከወረስነው የቂም መንበር
እሽቅድድም ከበዛበት
የደበቅናት አንዲት ዕለት
ለደም ቁርባን
የበግ መባን
ከለመደው
ከሚወደው
የሸሸግናት
የቀለስናት
አለች ቦታ
ድረሽ ላፍታ
የህይወት ምሰሶ
ቁልቁል ተደርምሶ
ጨፍልቆ እስኪገለን
ላፍታ ገሸሽ ብለን
ትንሽ
ትንሽ
የቆጠብናትን ሳቅ
ነይ አብረን እንሳቅ



@gGetem
@gGetem
............

በስሜት ተናንቀን
በስጋ ተዋውቀን
ገላሽን ስሞቀው
ወዝሽን ስጠምቀው
ጠረንሽ ሰንፍጦኝ
ጥፍርሽ ላመል ልጦኝ
የስሜት ጣረ ሞት
ውስጥሽን አፍሞት
ፍቅርን ስንሰራ
.....
........
............
ውል ከሌለው ስፍራ
ደከም ስትይ አርፈሽ
ክንዴን ተደግፈሽ
ፍቅርን ስታወጊኝ
በአሽሙር ስትወጊኝ
በህጻን ፈገግታ
ያዋቂ ጨዋታ
ብ........ዙ ስናወጋ
....
......
.........
እንደ ድንገት ነጋ
አይኔን አጨፍግጌ
ገላሽን ፈልጌ
ላቅፈው ብንጠራራ
ላወራሽ ብጠራ
ህልም ነው የለሽም
ያወጋሁሽ ሁሉ
ያደረግነው ሁሉ
ፍሬው አልደረሰሽም ?


@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍1
................

ዛሬም እንደትናትና
ናፈቅሺኝ ከንደገና
ተገዝ የበዛበት የቀናው ጎዳና
ውብ መልክሽን ሳለ
ከመንገዱ መሀል ላመል የበቀለው
ዘንባባና ጥዱ ሳቅሽን የመሰለው
ፈገግታሽን ኳለ!
የለማኝ የተሽከርካሪው የማቲው
ጫጫታ እራቀኝ
ከመንገድ መሀል ገትሮ
በህላዌ አመጠቀኝ
አካልሽ ከኔ ባያርፍም፤ጥላሽን ዳብሼ ጸናሁ
ዳናሽ ከከተበበት፤በጽናት ልቤን መራሁ
ደረስኩብሽ ስል ስትርቂኝ
ቀሚሽን ያዝኩ ስል ስትነጥቂኝ
ማፍቀር ሲያደናቅፈኝ
ተስፈ ሆኖኝ እንቅፋት
በበቀል እንዲሽርልኝ
የነፍሴን ስብር እጥፈት
ትናንት እንዳልነበረ
መዳፍሽ እንዳልዳበሰው
አላውቅም በሚል ቃል ክጄ
ፍቅርሽን እንዳላረክሰው
ትዝታሽ መግል ሆነብኝ ናፍቆትሽ የጊዜ ቁስል
ጎዳናው ይፈካልኛል ጫጫታው መልክሽን ሲስል
መከተል
መሄድ
መጓዝ ነው
ጥላዋን ያፈቀረ ሰው
መንገዱ የቀናለትን ልመና እንዳይመልሰው
ቃላት አይከጅሉትም ገላ ያልበቃውን ሰው
ጠልቼሽ እንደዲድንልኝ
የፍቅርሽ የነፍሴ ቁስል
ሸሽቼሽ እንዲሰምርልኝ
ህይወቴ ህልም እንዲመስል
ሀሞቴን አምርሬ
ሀጥያትሽን ደርድሬ
እረሳሁሽ ብዬ መንፈሴን ሳጽናና
ትናፍቂኝ ጀመር ዛሬም እንደገና

@gGetem
@gGetem
@gGetem
ቤት እማ ጨዋ ነሽ፣
እንኳን ሌላ ሌላ እኔንም አታይም፣
ግን እድሜ ለሱሱ፣
ወተሽ ወዳጅ ካየሽ አታልፊም አትተይም።

የሸመገለን ወንድ፣
በሰለቸ ዐይንሽ ዕያየሽ ወጠምሻ፣
የሱን መድሃኒት፣
አርገሽ ለቀን ያዝሽው የኔን ማስታገሻ 


@gGetem
@gGetem
@gGetem
መንገድ መሆን
-------------------------

ጠልቼሽ አይደለም
ጥላኝ ሄደች ብዬ: የማልጨነቀው
መንገድሽ ስለሆንኩ:
የመጣሽ ግዜ ነው:
መሄድሽን የማውቀው::

By belay bekele weya

@gGetem
@gGetem
እኔ እና አንቺ_ሊዮ_ማክ
<unknown>
👨‍❤️‍👨👩‍❤️‍👩💏 እኔ እና አንቺ👩‍❤️‍💋‍👩💏
#ገጣሚ_ሊዮ_ማክ
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@gGetem
@gGetem
@Leoyri
@Leoyri 👇👇👇
#ተፃፈ_03_05_2011_ዓ_ም
2025/07/13 14:41:41
Back to Top
HTML Embed Code: