መቼስ ልብ የለኝም
ልብ እንዳለው ስሆን
መቼስ ነፍስ የለኝም
ነፍስ እንዳለው ስሆን
መቼስ ህዝብ የለኝም
የጥንድ አልቃሽ ምሆን
እና ምኑ ይገርማል
እየኖርኩኝ እንኳ
እንዳልኖርኩኝ ስሆን
በትንንሽ ድምፆች አምላኬ በሚሉት
ሶቆቃ ብቻ ነው ምእመን ሚያሰሙት
በጨቅላ ህፃናት ቆመው በሚሰግዱት
ጫንቃቸው ሞትን ነው ነጠላ ያረጉት
ይሄ ሁሉ ምእመን
ለአምላክ የሚነግረው
ኑሮን አቅል ነው
ወይ መሪን ቀንሰው
እኔ ግን ደስታ ነው
ላንተ የማቀርበው
እኔ ስለት አለኝ
ልሞት ስለሆነ
ጥላ አለኝ ማስገባው
ኑሮ በሚያስፈራው
ዋይታ በደፈረው
በጭንቅ ለቅሶ ድምፅ
ዝምታ ይበላል
ያለምንም ፍትህ
ከኖረ እንደምስፅ
አለም ትንሽ ገብታኝ
ሀገር በደንብ ገብታኝ
እኛሳ ስላልናት
ስትጋረፍ አየሁ
በምእመን ልጇ
ጨካኝ ሁና እናት
እናት በጨከነች አባት በደበቃት
በግራ እግር ሀገር
ሞት ቀጠሮ ማወቅ
ደስታ ሆኖ ቀረ ተሳቆ ከማደር
እናማ ጌታዬ በዚህ ሺህ ምእመን
የጭንቅ መሃል ለቅሶ
አንዲት ነፍስ አለች
ደስታ ያፈነዳት የሞት ክሬም ልሶ
ኗሪው በሚፈራት
መሪው በሚንቃት
በግራ እግር ሀገር፣
ሞት ቀጠሮ ማወቅ
ደስታ ሆኖ ቀረ
ተሳቆ ከማደር ፣
@gGetem
@gGetem
@gGetem
ልብ እንዳለው ስሆን
መቼስ ነፍስ የለኝም
ነፍስ እንዳለው ስሆን
መቼስ ህዝብ የለኝም
የጥንድ አልቃሽ ምሆን
እና ምኑ ይገርማል
እየኖርኩኝ እንኳ
እንዳልኖርኩኝ ስሆን
በትንንሽ ድምፆች አምላኬ በሚሉት
ሶቆቃ ብቻ ነው ምእመን ሚያሰሙት
በጨቅላ ህፃናት ቆመው በሚሰግዱት
ጫንቃቸው ሞትን ነው ነጠላ ያረጉት
ይሄ ሁሉ ምእመን
ለአምላክ የሚነግረው
ኑሮን አቅል ነው
ወይ መሪን ቀንሰው
እኔ ግን ደስታ ነው
ላንተ የማቀርበው
እኔ ስለት አለኝ
ልሞት ስለሆነ
ጥላ አለኝ ማስገባው
ኑሮ በሚያስፈራው
ዋይታ በደፈረው
በጭንቅ ለቅሶ ድምፅ
ዝምታ ይበላል
ያለምንም ፍትህ
ከኖረ እንደምስፅ
አለም ትንሽ ገብታኝ
ሀገር በደንብ ገብታኝ
እኛሳ ስላልናት
ስትጋረፍ አየሁ
በምእመን ልጇ
ጨካኝ ሁና እናት
እናት በጨከነች አባት በደበቃት
በግራ እግር ሀገር
ሞት ቀጠሮ ማወቅ
ደስታ ሆኖ ቀረ ተሳቆ ከማደር
እናማ ጌታዬ በዚህ ሺህ ምእመን
የጭንቅ መሃል ለቅሶ
አንዲት ነፍስ አለች
ደስታ ያፈነዳት የሞት ክሬም ልሶ
ኗሪው በሚፈራት
መሪው በሚንቃት
በግራ እግር ሀገር፣
ሞት ቀጠሮ ማወቅ
ደስታ ሆኖ ቀረ
ተሳቆ ከማደር ፣
@gGetem
@gGetem
@gGetem
ቀጥረሽኝ....ፈላስፋ አደረግሽኝ
ላገኝህ ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፣ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፣ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፣ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፣ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡
ሰአቱ እስኪደርስ ፤ ሰአት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፣ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን...
እንዴት እንደምሔድ ፣ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፣ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዴ እግሬን ስጎትት፣ አንዴ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፣ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፣ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፣ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው...
ኒስትሮ ጋ ሔድኩኝ ፣ ጫማ ለማሰፋት፡፡
ሊስትሮው...
በወስፌ መንጠቆው ፣ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፣ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ...
"የህይወት ትንሽ ሽንቁር...
ጊዜና ግመልን ፣ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት ፣
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፣ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡
እየተጣደፍኩኝ...
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፣ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፣ "ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዲ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፣ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ...
መፈለግ ነው ብዬ ፣ የፍልስፍና አቅም፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፣ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፣ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፣ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፣ ስሔደው ይርቃል፡፡
ወደ ጫማዬ ሳይ ፣ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ....
ትቼው መጥቻለሁ ፣ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር...
ላይጠግን ይሰፋል ፣ በወስፌ ተቀዶ፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜ መጥቼ ፣ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ....
እጅጉን ይሻላል ፣ አርፍዶ የመጣ፡፡
ሰው የሚሉት ፍጡር...
ነፍስ ከስጋ ጋር ፣ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፣ ፍፁም የሚስተው፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜሽ መጥቼ ፣ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው ፣ መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፣ ማይጠነቀቀው!!!
@gGetem
@gGetem
ላገኝህ ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፣ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፣ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፣ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፣ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡
ሰአቱ እስኪደርስ ፤ ሰአት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፣ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን...
እንዴት እንደምሔድ ፣ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፣ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዴ እግሬን ስጎትት፣ አንዴ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፣ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፣ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፣ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው...
ኒስትሮ ጋ ሔድኩኝ ፣ ጫማ ለማሰፋት፡፡
ሊስትሮው...
በወስፌ መንጠቆው ፣ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፣ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ...
"የህይወት ትንሽ ሽንቁር...
ጊዜና ግመልን ፣ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት ፣
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፣ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡
እየተጣደፍኩኝ...
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፣ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፣ "ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዲ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፣ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ...
መፈለግ ነው ብዬ ፣ የፍልስፍና አቅም፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፣ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፣ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፣ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፣ ስሔደው ይርቃል፡፡
ወደ ጫማዬ ሳይ ፣ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ....
ትቼው መጥቻለሁ ፣ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር...
ላይጠግን ይሰፋል ፣ በወስፌ ተቀዶ፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜ መጥቼ ፣ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ....
እጅጉን ይሻላል ፣ አርፍዶ የመጣ፡፡
ሰው የሚሉት ፍጡር...
ነፍስ ከስጋ ጋር ፣ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፣ ፍፁም የሚስተው፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜሽ መጥቼ ፣ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው ፣ መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፣ ማይጠነቀቀው!!!
@gGetem
@gGetem
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝
በድቅድቅ ጨለማ ወንበሬን አውጥቼ
መሀል መሬት ላይ ጨረቃ እሞቃለው
ወፎች ሲዘምሩ ቁጭ ብዬ አደምጣለው
ወደ ላይ ቀና ስል...
የጨረቃ ብርሃን አይኔን ይወጋኛል
ሙቀቷ እሳት ሁኖ በላብ ያጠምቀኛል
''አ ዎ! አሁን ይበቃኛል''
''ከዚ በላይ ብቆይ ምቀልጥ ይመስለኛል''
ብዬ አሰብኩና...
ጥላውን ፍለጋ ወደ ቤቴ ገባው
ከቆጡ አልጋዬ ለመተኛት ሳስብ...
የ አልጋው ዝቅታ ሰላም ስላልሰጠኝ
ከፍ ካለው ቁርበት ከላይ ተንጋለልኩኝ..
አይኖቼን ገልጬ ድብን ብዬ ተኛሁ
ሰዉን እየረበሽኩ በደንብ አንኮራፋሁ
እንቅልፌ ሲመጣ ...
እንቅልፌ ሲመጣ ከ ሰመመን ነቃሁ;
ነግቷል መሰለኝ ሰማዩ ጨልሟል
ኮከቦችም አሉ ደመናም ደምኗል
ሊዘንብ ነው መሰል ልብሴን ቶሎ ላስጣ
ዝናብ ዘንቦ ሳያልቅ ፀሀይዋ ሳትመጣ::
@gGetem
@gGetem
@gGetem
መሀል መሬት ላይ ጨረቃ እሞቃለው
ወፎች ሲዘምሩ ቁጭ ብዬ አደምጣለው
ወደ ላይ ቀና ስል...
የጨረቃ ብርሃን አይኔን ይወጋኛል
ሙቀቷ እሳት ሁኖ በላብ ያጠምቀኛል
''አ ዎ! አሁን ይበቃኛል''
''ከዚ በላይ ብቆይ ምቀልጥ ይመስለኛል''
ብዬ አሰብኩና...
ጥላውን ፍለጋ ወደ ቤቴ ገባው
ከቆጡ አልጋዬ ለመተኛት ሳስብ...
የ አልጋው ዝቅታ ሰላም ስላልሰጠኝ
ከፍ ካለው ቁርበት ከላይ ተንጋለልኩኝ..
አይኖቼን ገልጬ ድብን ብዬ ተኛሁ
ሰዉን እየረበሽኩ በደንብ አንኮራፋሁ
እንቅልፌ ሲመጣ ...
እንቅልፌ ሲመጣ ከ ሰመመን ነቃሁ;
ነግቷል መሰለኝ ሰማዩ ጨልሟል
ኮከቦችም አሉ ደመናም ደምኗል
ሊዘንብ ነው መሰል ልብሴን ቶሎ ላስጣ
ዝናብ ዘንቦ ሳያልቅ ፀሀይዋ ሳትመጣ::
@gGetem
@gGetem
@gGetem
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Y€ŕi ወንጌላዊት)
My Song 1.ogg
15 MB
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝
መናፈቅ ማለት …
ከወትሮው በድንገት
ከከተማ ግፊያ
ከሰፊው ገበያ
ከሰው ትርምስ
ከህይወት ግብስብስ
አረፍ ብለው ባልጋ
ከራስ ጋር ሲወጋ
የአስቴር እና ኤፍሬም
አባባይ ሙዚቃ ...
አንጀትንን ሲገርፍ
ትዝታን ሲያነቃ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት..
በቡሄ አመሻሽ
እርግት ባለ ሰማይ
ልጅነት ሲወያይ
ሲሸት የኩበት ጭስ
የአሪቲ ቃና መንደርን ሲዳብስ
ውብ አደይ አበባ ምድሪቷን ሲያነግስ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት ..
እኔና አንቺ አፍረን
ከዓይን ተሸሽገን
ከመስቀል ዳመራ
ሸሽተን ከጓደኞች
ፈልገን ሰዋራ ...
ተቃቅፈን እየሄድን
ውሎን ስንጋራ
ስትሰጪኝ ፖፖቲን
‘’ፖስት ካርዴስ ?’’ ብለሽ
ኪሴን ስትዳብሽኝ
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
ትምህርት ሊዘጋ ወቅት
ድራማ ተውነን
በሰኔ ሰላሳ ለመታየት ደምቀን
በድራማው መኃል
ፈልገን ስህተት
ከልብ የሳቅን ዕለት
ከሳቅን በኋላ
ኩሪፊያ ሲከተለን ...
ድፍን ሶስት ወራትን
ያለመገናኘት ፍርሀት ሲውጠን
ስትሰናበችኝ በጥልቁ ዝምታ
ዓይንሽን እያየሁ
ዓይኖቼን እያየሽ
የቆዘምን ለታ …..
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
የሽፍታ ፍርሀት
ነፍስያን ሳይንጣት
በ አራት እግር ጉዞ
የመኪናን መስኮት
በራስ ተመርኩዞ
የገጠርን መስመር
አንዱን መንገድ ይዞ
ተራራውን ማየት
እሸቱን መጎምዠት
ከገበሬ ቁና
በቆሎ መሸመት
የፀሀይዋን ግባት
አሻግሮ መቃኘት
እንዲህ ይመስለኛል።
…
መናፈቅ ማለት …
(ሚካኤል አ )
@gGetem
@gGetem
@gGetem
ከወትሮው በድንገት
ከከተማ ግፊያ
ከሰፊው ገበያ
ከሰው ትርምስ
ከህይወት ግብስብስ
አረፍ ብለው ባልጋ
ከራስ ጋር ሲወጋ
የአስቴር እና ኤፍሬም
አባባይ ሙዚቃ ...
አንጀትንን ሲገርፍ
ትዝታን ሲያነቃ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት..
በቡሄ አመሻሽ
እርግት ባለ ሰማይ
ልጅነት ሲወያይ
ሲሸት የኩበት ጭስ
የአሪቲ ቃና መንደርን ሲዳብስ
ውብ አደይ አበባ ምድሪቷን ሲያነግስ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት ..
እኔና አንቺ አፍረን
ከዓይን ተሸሽገን
ከመስቀል ዳመራ
ሸሽተን ከጓደኞች
ፈልገን ሰዋራ ...
ተቃቅፈን እየሄድን
ውሎን ስንጋራ
ስትሰጪኝ ፖፖቲን
‘’ፖስት ካርዴስ ?’’ ብለሽ
ኪሴን ስትዳብሽኝ
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
ትምህርት ሊዘጋ ወቅት
ድራማ ተውነን
በሰኔ ሰላሳ ለመታየት ደምቀን
በድራማው መኃል
ፈልገን ስህተት
ከልብ የሳቅን ዕለት
ከሳቅን በኋላ
ኩሪፊያ ሲከተለን ...
ድፍን ሶስት ወራትን
ያለመገናኘት ፍርሀት ሲውጠን
ስትሰናበችኝ በጥልቁ ዝምታ
ዓይንሽን እያየሁ
ዓይኖቼን እያየሽ
የቆዘምን ለታ …..
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
የሽፍታ ፍርሀት
ነፍስያን ሳይንጣት
በ አራት እግር ጉዞ
የመኪናን መስኮት
በራስ ተመርኩዞ
የገጠርን መስመር
አንዱን መንገድ ይዞ
ተራራውን ማየት
እሸቱን መጎምዠት
ከገበሬ ቁና
በቆሎ መሸመት
የፀሀይዋን ግባት
አሻግሮ መቃኘት
እንዲህ ይመስለኛል።
…
መናፈቅ ማለት …
(ሚካኤል አ )
@gGetem
@gGetem
@gGetem
❤❤❤
ሳላውቅበት ሳልረዳ
አልገባኝ ወይ አልጠይቅ
እከፍላለው ትልቅ እዳ
አምላክ ሰቶኝ ልማርበት
እኔ ራሴን እዳውቅበት
ባምላክ ጥበብ እድመራ
እዳልወጣ ከሰው ተራ
መምር ሰጠኝ ባለአደራ
ያመምሩ ጠባአቂየ የሂወት መሰረቴ
ሊመልሰኝ ከስተቴ
እዳልጠፋ እኔ ልጁ
ደረሰልኝ አማላጁ
አቅፎ ያዘኝ በመዳፉ
አስቀመጠኝ ከእቅፉ
@gGetem
ሳላውቅበት ሳልረዳ
አልገባኝ ወይ አልጠይቅ
እከፍላለው ትልቅ እዳ
አምላክ ሰቶኝ ልማርበት
እኔ ራሴን እዳውቅበት
ባምላክ ጥበብ እድመራ
እዳልወጣ ከሰው ተራ
መምር ሰጠኝ ባለአደራ
ያመምሩ ጠባአቂየ የሂወት መሰረቴ
ሊመልሰኝ ከስተቴ
እዳልጠፋ እኔ ልጁ
ደረሰልኝ አማላጁ
አቅፎ ያዘኝ በመዳፉ
አስቀመጠኝ ከእቅፉ
@gGetem
ባአፍህ አግሰኸኝ
በልቤ አነገስኩህ
በጠቆረው ልብህ በፍቅር አይተኸኝ
ፍቅሬን አሰረከብኩህ
በውሸታም አይንህ በስስት አይተኸኝ
ሳይህ ሳሳውብህ
ሞልቸም አላይህ
ለስሜት ቀርበኸኝ
ፍቅርህ አሸነፈኝ
የልቤ ሰው ብየ በደማአቁ ጻፍኩህ
አተ የልቤ ጀግና የራሴ ነህ ያልኩህ
እድ ምክር ልስጥህ አድምጠኝ ለዛሬ
የፍቅሩ መምሬ
የሰጠኸኝ ፍቅር የውሸት ቢሆንም
አስቀምጨህ አለው በልቤ መሀተም
ስሜት ከሰአት ወጭ
አይቆይ አለመታት
ውሸት ለማምሻ እጅ
አይሆንም ለንጋት
ማምሻውን አትናፈቅ
እውነት ምረጥና ንጋቷን ተመልከት
@gGetem
@gGetem
በልቤ አነገስኩህ
በጠቆረው ልብህ በፍቅር አይተኸኝ
ፍቅሬን አሰረከብኩህ
በውሸታም አይንህ በስስት አይተኸኝ
ሳይህ ሳሳውብህ
ሞልቸም አላይህ
ለስሜት ቀርበኸኝ
ፍቅርህ አሸነፈኝ
የልቤ ሰው ብየ በደማአቁ ጻፍኩህ
አተ የልቤ ጀግና የራሴ ነህ ያልኩህ
እድ ምክር ልስጥህ አድምጠኝ ለዛሬ
የፍቅሩ መምሬ
የሰጠኸኝ ፍቅር የውሸት ቢሆንም
አስቀምጨህ አለው በልቤ መሀተም
ስሜት ከሰአት ወጭ
አይቆይ አለመታት
ውሸት ለማምሻ እጅ
አይሆንም ለንጋት
ማምሻውን አትናፈቅ
እውነት ምረጥና ንጋቷን ተመልከት
@gGetem
@gGetem
#አንቺ_ና_እኔ
ከአርዕያም ጥግ ከሰማያት በኩል
ወስደሽ የመለሺኝ ከጨረቃ እኩል
ጨርሰሽ የጣልሺኝ ከሰማይ ወደ መሬት
አዳፍንሽ አካሌን ልቤን ዘግተሺበት
...ከዚያ የምን ኮከብ
ገጥሜ ከራሴ ጋር ጠብ
ያለ አንዳች ሰበብ ያለ አንዳች ምክኒያት
ከሃሳብ ና ዝምታ ጋር ገጥሜ ወዳጅነት
ልንግርሽ ግን ውዴ
ቆርጦሎታል ያልኩት
የመመለስሽን ሃሳብ ክውስጤ ያጠፈዉት
አፈቅርሃለው ባልሺበት አንደበት
ማለትሽ አይደለም እረስቼሃለው
ይልቅስ ያዘንኩት ቅስሜ እስኪሰበር
የላክሺልኝ ወረቀት ላይ
ስትይኝ ነው ሰርጌ ላይ እንዳትቀር።
@gGetem
@gGetem
ከአርዕያም ጥግ ከሰማያት በኩል
ወስደሽ የመለሺኝ ከጨረቃ እኩል
ጨርሰሽ የጣልሺኝ ከሰማይ ወደ መሬት
አዳፍንሽ አካሌን ልቤን ዘግተሺበት
...ከዚያ የምን ኮከብ
ገጥሜ ከራሴ ጋር ጠብ
ያለ አንዳች ሰበብ ያለ አንዳች ምክኒያት
ከሃሳብ ና ዝምታ ጋር ገጥሜ ወዳጅነት
ልንግርሽ ግን ውዴ
ቆርጦሎታል ያልኩት
የመመለስሽን ሃሳብ ክውስጤ ያጠፈዉት
አፈቅርሃለው ባልሺበት አንደበት
ማለትሽ አይደለም እረስቼሃለው
ይልቅስ ያዘንኩት ቅስሜ እስኪሰበር
የላክሺልኝ ወረቀት ላይ
ስትይኝ ነው ሰርጌ ላይ እንዳትቀር።
@gGetem
@gGetem