tgoop.com/gibi_gubae/1080
Create:
Last Update:
Last Update:
የቅዱሳን አባቶች ወርቃማ አባባሎች
አባ ሙሴ ጸሊም
*መነኩሴ ለባልንጀራው መሞት ይገባዋል፤በምንም መንገድ እና በምንም ሁኔታ በወንድሙ ላይ መፍረድ የለበትም።
*መነኩሴ ማንንም እንዳይጎዳ ሥጋ መመገብ ከመተው በፊት ለማንኛውም ነገር መዋቲ መሆን አለበት።
*ሰው ወደ ልቡ የሚመጣውን ፍትወት እና ክፉ አሳብ ለመቋቋም ማልቀስ እና የእግዚአብሔርን ረዳትነት መለመን አለበት። ከዚያም በተረዳ ልቡና ሆኖ ከጸለየ ፈተናው ይታገሥለታል።
አባ መጣዕ
*ሰው ወደ እግዚአብሔር በቀረበ ቍጥር የራሱ ኃጢአት ይታየዋል።
*ልጅ እያለሁ አንደ ቀን መልካም ነገር አደርግ ይሆናል ብዬ ለራሴ እነግረው ነበር።እነሆ ሸመገልኩ እስከ አሁን መልካም የሚባል ነገር አላደረግሁም።
*አንድ አባት ወንድሙን ከራሱ አብልጦ ሲያመሰግን ስትሰማ እርሱ ራሱ ከትልቅ መዓርግ መድረሱን ተረዳ። ፍጹምነት ማለት ባልንጀራን ከራስ በላይ ማክበር ነውና።
*እግዚአብሔር የሚጸጸት ልቡና እና ትሑት ሰብእና እንዲሰጥህ ጸልይ፤ በደልህን አትዘንጋ፤ በሌሎች ላይ መፍረዱን ትተህ ራስህን የሁሉም የበታች አድርገህ ቍጠር።
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
BY ✞ግቢ ጉባኤ✟
Share with your friend now:
tgoop.com/gibi_gubae/1080