tgoop.com/gibi_gubae/1294
Last Update:
#በጸሎት_ጊዜ_ምን_እናድርግ?
#በጸሎት_ጊዜ_ምን_እያልን_እንጸልይ?
👉ዓምድ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ መቆም። (መዝ. 5:3)
👉ወገብን መታጠቅ ልብስን ዝቅ አድርጎ ማደግደግ ነው። (ሉቃ. 12:35 ፍት. መን አንቀጽ 14)
👉በጸሎት ጊዜ ፊትን ወደ ምስራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ ወደ ግራና ወደ ቀኝ ወደ ሌላም አለማለት በሰፊሐ እድ በሰቂለ ሕሊና ሁኖ መጸለይ ይገባል። (መዝ. 133:2፤ ዮሐ. 11:41)
👉ጸሎት ሲጀመርና ሲፈጸም አመልካች ጣትን ከሌሎች ጣቶች ጋር አመሳቅሎ በትእምርተ መስቀል አምሳል በጣት ማማተብ ነው። በዚህም የመድኃኔዓለምን መከራውን ማሰብ።
🙏የሚጸልይ ሰው በትህትናና በጸጥታ ሁኖ ለሌላ ሰው እንዳይሰማ ለራሱ ጆሮ ብቻ እንዲሰማ አድርጎ ኃጢአቱን እያሰበ መጸለይ ይገባዋል። ይህም የሚያደርገው ስለ አለፈው ኃጢአቱና በደሉ ነው። (1ኛ ሳሙ. 1:3)
🙏የሚጸልይ ሰው በጥቡዕ ልብ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገራል። አሳቡን በእግዚአብሔር ላይ ይጥላል። የዓለምን አሳብ ሁሉ ይተዋል።
🙏የሚጸልይ ሰው ሲያማትብ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አዐትብ ገጽየ ወኵለንታየ በትእምርተ መስቀል" እያለ ነው። ሁለተኛም "እግዚኦ መሐረነ እግዚኦ መሐከነ እግዚኦ ተሣሃለነ ወባርከነ አሜን" እያለ ያማትባል። ሦስተኛም "ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን እግዚኦ ረስየነ ድልዋነ ከመንበል በአኮቴት አቡነ ዘበሰማያት" የሚለውን ጸሎት 3 ጊዜ እየደገመና እየሰገደ በማማተብ በጸሎት መጀመርያና መጨረሻ ጊዜ ማድረግ አለበት። #እንዲሁም_መስቀልን_ከሚያነሳ_ቃል_ሲደርስ_ማማተብ_ስግደትንም_ከሚያነሳ_ቃል_ሲደርስ_መስገድ_ይገባዋል።
#የጸሎቱ_ቅደም_ተከተል_መጀመርያ_አቡነ_ዘበሰማያት_ሁለተኛ_መዝሙረ_ዳዊት_ውዳሴ_ማርያምና_ሌሎችም_ቀጥሎ_አቡነ_ዘበሰማያት_ጸሎተ_እግዚእትነ_ማርያም_ጸሎተ_ሃይማኖት_በመጨረሻም_አቡነ_ዘበሰማያት_ኬርያላይሶን_41_ጊዜ ይባላል።
-ሲጸልይ ማዘን ማልቀስ ይገባዋል። ሲያለቅስም በደሉንና ኃጢአቱን እያሰበ ለያንዳንዱ በደል ዕንባን ማፍሰስ ነው።
-የሚጸልይ ሰው በጸሎት ላይ አቋርጦ ከማንም ሰው ጋር ፈጽሞ መነጋገር የለበትም። ጸሎቱን ለማቋረጥ ችግር ቢገጥመው ግን በአቡነ ዘበሰማያት አሥሮ ንግግሩን ሲፈጽም ከአቋረጠበት ተነስቶ ጸሎቱን ሊጸልይ ይገባል። (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስርዓተ አምልኮና የውጪ ግንኙነት ገጽ 81፤ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ገጽ. 28-29: ሊቀ ካሕናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
BY ✞ግቢ ጉባኤ✟
Share with your friend now:
tgoop.com/gibi_gubae/1294