tgoop.com/gibi_gubae/1299
Last Update:
በግብፅ በረሀ አባ መቃርስ በሚኖሩበት ገዳም የሚኖር 1 መነኩሴ ነበር ያም መነኩሴ ሴቶችን ወደ ገዳሙ ያመጣ ነበር ይህን ተግባሩን ያዩ መነኮሳትም ወደ አባ መቃርስ በመሄድ ያደረገውን ነገር ይነግሯቸዋል አባ መቃርስም ልጄማ ይሄንን አያደርግም ይላሉ ። መነኮሳቱም ተበሳጭተው ይሄዳሉ ልጁም በሌላ ጊዜ ሴት ያስገባል እነዛ መነኮሳትም በድጋሚ ይሄዱ እና ለአባ መቃርስ ይነግሯቸዋል አባ መቃርስም አይ ልጄማ ይሄን አያደርግም ይላሉ በድጋሚ መነኮሳቱ ተበሳጭተው ይሄዱ እና ምን እናድርግ ? ብለው ይማከራሉ ከዛም በቃ ካሁን ቡሃላ ልክ ሴት ይዞ ሲመጣ እንነግራቸዋለን እስካሁን ያላመኑን እኛ ሴቶቹን ከሸኘ ቡሃላ ስለምንነግራቸው ነው በማለት ተማከሩ ። ያ መነኩሴም እንደ ለመደው ልክ ሌላ ሴት ይዞ ሲገባ መነኮሳቱ በሩጫ ሄደው ለአባ መቃርስ ይነግሯቸዋልአባ መቃርስም እንደ ተለመደው ልጄማ ይሄንን አያደርግም አሏቸው ። መነኮሳቱም አባታችን ልጅቷ አልወጣችም ኑ ወደ ባዕቱ እንሂድ እዛው እንይዛቸዋለን ብለው ወደ ባዕቱ መሄድ ጀመሩ መነኩሴውም ከሩቁ ሲመጡ አይቷቸው ደነገጠ ወይኔ ዛሬ ጉዴ ወጣ ብሎ ተጨነቀ ቅርጫቱንም ገልብጦ ልጅቷን በቅርጫት ከደናትአባ መቃርስም የበቁ አባት ነበሩና ባሉበት ሆነው የልጁን ድርጊት አወቁ ። ልክ እንደ ደረሱም ወደ ባዕቱ ሲገቡ አባ መቃርስ ቅርጫቱ ላይ ተቀመጡና በሉ ገብታለች ያላቹኝን ልጅ ፈልጋቹ አውጡልኝ አሉ ። መነኮሳቱ ቢፈልጉ ቢፈልጉ አጧት ወደ አባ መቃርስም ቀረብ ብለው አባታችን ይቅርታ እሱ ንፁህ ነው እኛ ነን ያጠፋነው አሉ አባ መቃርስም እኔኮ መጀመሪያም ነግሬያቹ ነበር ልጄ ንፁህ ነውያ መነኩሴም ደስ አለው ። አባ መቃርስም በል ና ወደ በዓቴ ሸኘኝ ብለውት መንገድ ላይ ወግ ይጀምሩለት እና ምንኩስና እንዴት ነው ይሉታል እሱም ጥሩ ነው ይላቸዋል ። እሳቸውም ያደረገውን ሁሉ እንደሚያውቁ እና ምን ማድረግም እንዳለበት መክረው ገስፀው ይልኩታል መነኩሴውም ልቡ ተነክቶ ከዛ ቡሃላ ታላቅ ተጋዳይ ሆነ ልጅቷም መነኮሰችእኛስ ዛሬ እንዴት ነው የሰዎችን እንከን ስናይ እንዳባ መቃርስ እንሸፍናለን ወይስ እንደ መነኩሴዎች ሮጠን ሄደን ለሌላ ሰው አቤት የእከሌ ጉድ በስምዓም ሲያዩት ሲያዩዋት ሰው ትመስላለች ሰው ይመስላል ... እንዲ እንዲ አርጎ እያልን የሰውን ገመና እንዘረዝራለን ? የሰውን ድካም ለሌላ ሰው አሳልፎ ከመንገር በፍቅር ቀርቦ ያንን ሰው ድካሙን ማገዝ የተሻለ ነው
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
BY ✞ግቢ ጉባኤ✟
Share with your friend now:
tgoop.com/gibi_gubae/1299