tgoop.com/gibi_gubae/2686
Last Update:
±±±ክብደት ለመቀነስ እንጹም!±±±
የታላቁ እስክንድር ሠራዊት ፋርስን /ፐርሺያን/ በድል እየተቆጣጠረ ነበር፡፡ አንድ ወሳኝ ቦታ ላይ ግን ወታደሮቹ እየተዳከሙ ሊሸነፉ ሆነ፡፡እነዚህ ወታደሮች ከዚህ ውጊያ
በፊት በነበራቸው ጦርነት ላይ የዘረፉትን ተሸክመው ስለነበር እንደልብ እንዳይንቀሳቀሱ ከብዷቸው በደንብ መዋጋት አቃታቸው፡፡
እስክንድር ይኼን ጊዜ የዘረፉትን ሁሉ አንድ ቦታ ላይ እንዲከምሩ አደረገና እሳት ለቀቀበት፡፡ ሁሉም ምርር ብለው ተበሳጩ፡፡ የንጉሡን ብልህነት የተረዱት ግን በኋላ ነው፡፡አንዱ ጸሐፊ ‹በፍጥነት እየሮጡ ሲዋጉ ክንፍ የተሠጣቸው ይመስሉ ነበር ›› ብሎ ጽፎአል፡፡ ድላቸውንም አረጋገጡ፡፡
እንደ አሜሪካ ባሉ ሀብታም ሀገራት ሁልጊዜ ከሚነሡችግሮች አንዱ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ነው፡፡ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በውፍረት ይቸገራሉ፡፡ ክብደታቸውንም ለመቀነስ ብዙ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ ፡፡ ለህክምናና ለአማካሪዎች ብዙ ገንዘብ ያወጣሉ፡
፡ አመጋገባቸውን ለመቀነስም ብዙ ትግል ያደርጋሉ፡፡ የስኳር ሕመም ፣ የልብ ሕመም ፣ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠንና ስትሮክ ያሰጋቸዋል፡፡ የሚሰቃዩትም ሆነ አመጋገባቸውን
መቆጣጠር የሚቸገሩት ከምግብ መከልከልን ስላልለመዱ ነው፡፡
ክርስቲያኖች የክርስቶስ ወታደሮች እንደመሆናችንከመንፈሳዊ ጠላታችን ከዲያቢሎስ ጋር በምናደርገው ውጊያ ላይ እንዳንቸገር የሚከብደንን ማንኛውንም ነገር ማስወገድ አለብን፡፡ ውጊያውን በሚገባ ለመዋጋት የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ እንዴት መታጠቅ እንዳለብን ማወቅ ያስፈልገናል፡፡ (ኤፌ. 6፡11-17) የውጊያችን መሪ ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በጾመና እኛንም እንድንጾም ባስተማረን ጊዜም ይህን ሃሳብ ነግሮናል፡፡ ከመጠን ያለፈ ምግብ ሆዳችንን ከሞላው ፣ ቁሳዊ ነገር ካበዛን ፣ በነፍሳችን ላይ ተጨማሪ ሸክም እንጨምራለን፡፡
በሰይጣን ወጥመድ ላይ የምናገኘውንም ድል ያስቀርብናል፡፡ ‹‹ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ ወገን ከጾምና ከጸሎትበቀር አይወጣም፡፡›› (ማቴ.17፡21)
መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲኖችን ከሯጮችም ጋርያመሳስላቸዋል፡፡ ሩጫን ለማሸነፍ
ደግሞ ወደ ኋላ የሚጎትተንን ‹ሸክምን ሁሉ ማስወገድ አለብን›› (ዕብ. 12፡1)
ይኼ ክብደት ገደብ የለሽ የሀብት ፍቅር ፣ በገንዘብ ፍቅር መማረክ ፣ ማለቂያ የሌለው እርካታን ፍለጋ ፣ ኃጢአት ለሆኑ ፍላጎቶች ባሪያ መሆን ፣ ሥጋዊ ምኞትና ስስት ሊሆንም ይችላል፡፡
አዎ ፤ መልካሙን የእምነት ውጊያ ልንዋጋና መንፈሳዊውን ሩጫ በጽናት ለመሮጥ የምናስብ ከሆነ መሪ ቃላችን መሆን ያለበት ‹ክብደት መቀነስ› ወይም ‹ጾም› የሚለው ነው፡፡‹‹እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና
ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ
ተቀምጦአልና።›› ዕብ. 12፡1
‹‹እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ ፤ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁምዕረፍት
ታገኛላችሁ ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።›› [ማቴ.11፡28]
ዲ\ን ሄኖክ ኃይሌ
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
BY ✞ግቢ ጉባኤ✟
Share with your friend now:
tgoop.com/gibi_gubae/2686