tgoop.com/gibi_gubae/2711
Last Update:
🕯''እግዚአብሔር በአሳባቸሁ ውስጥ እንዲኖር ስለእርሱ አብዝታችሁ አንብቡ።''🕯
~ምክር ዘአቡነ ሺኖዳ~
እግዚአብሔር በአሳባቸሁ ውስጥ እንዲኖር ስለእርሱ አብዝታችሁ አንብቡ። እርሱን ለማወቅ ስለእርሱ አንብቡ። እርሱን ካላወቃችሁት እንዴት እርሱን ልትወዱት ትችላላችሁ?
ስለእርሱ አንብቡ፤ ስታነቡ ግን በሳይንሳዊ ወይም በፍልስፍና ጠባይ አታንብቡ ወይም ደግሞ ስለእርሱ ጥናታዊ ጽሑፍ ወይም ትምህርት ለመስጠት አታንብቡ። ነገር ግን ወደ እርሱ ጥልቀት ለመግባት ወይም እርሱ ወደ እናንተ ጥልቀት እንዲገባ አንብቡ።
ለነፍሳችሁ ውድ የሆኑትን የእርሱን ባሕርያት ለማወቅ ስትሉ አንብቡ ይህ እውቀት አሳባችሁ ከእርሱ ጋር እንዲጣበቅና ፍቅሩ ከእናንተ ልብ ጋር እንዲቀናጅ ያደርግላችኋልና ። ስለ ስምምነቱ ስትሉም አንብቡ።
ከወደዱት ሰዎች ጋር ስላለው ግንኙነት በጠላቶቹ ላይ ስላለው አቋም ስትሉ አንብቡ! በጽሑፎች ውስጥ ስለእርሱ "ውበትህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል" (መዝ 44÷2) የሚለውን ቃል በማንበብ የእርሱን ውበት ታውቁ ዘንድ አንብቡ።
እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቀምሳችሁ ታዩ ዘንድ ስለእርሱ አንብቡ። ታዲያ ንባባችሁ ለልባችሁ ምግብ እንዲሆን እንጂ እንዲሁ ተራ ንባብ እንዲሆን አትፍቀዱ።
ስለ እግዚአብሔር ብዙ ካነበባችሁ በእርሱ ዘንድ ያለውን ፍጹምነት በሙሉ ታገኛላችሁ። እርሱን ስለምትወዱትም በሰሎሞን መዝሙር ውስጥ ካለችው ድንግል ጋር አብራችሁ "እርሱ ፈጽሞ ያማረ ነው" (መኃ. 5÷16) ትላላችሁ።
ከወደዳችሁት ስለእርሱ ማንበባችሁን ትቀጥላላችሁ። እግዚአብሔር ስለእርሱ የሚያነቡትን ስለእርሱ ዜና የሚጠይቁትን ከእርሱ ታሪኮች መካከል አንዱን ለማወቅ የሚናፍቁትንና እርሱን የሚያደንቁትን ሰዎች ይወዳቸዋል።
ስለእርሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከአባቶች ብሒሎች ወይም ከቤተክርስቲያንና ከቅዱሳን ታሪክ ልታነቡ ትችላላችሁ። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ ለመዳሰስ ስትሞክሩ በጥበቡ፣ በኃይሉና በርኅራኄው ውስጥ እንደምትወዱት ታውቃላችሁ።
💡አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ💡
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
BY ✞ግቢ ጉባኤ✟
Share with your friend now:
tgoop.com/gibi_gubae/2711