tgoop.com/gibi_gubae/2719
Create:
Last Update:
Last Update:
በግንቦት የርክበ ካህናት በተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መሠረት ሥርዓተ አምልኮ የሚፈጸምባቸው ይዞታዎቻችን ላይ የሚፈጸሙ የሁከት ድርጊቶች እንዲቆሙ እና ሕጋዊ ዋስትና እንዲሰጣቸው እንዲሁም በቤተክርስቲያናችን ፣ በሃይማኖት አባቶችና በምዕመናን ላይ የሚደርሱ መከራዎች እንዲቆሙና ተገቢው ካሳ እንዲሰጣቸው የሚጠይቅ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል። የመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ውሳኔውን እንዲፈጽሙ ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት በደብዳቤ አሳውቀዋል።
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
BY ✞ግቢ ጉባኤ✟
Share with your friend now:
tgoop.com/gibi_gubae/2719