tgoop.com/gibi_gubae/2726
Last Update:
አቡነ_ሐራ_ድንግል
🍂አባታቸው ካህን ዮሐንስ ሲባሉ
🍂 እናታቸው ወለተ ጊዮርጊስ ይባላሉ።
#ጥቅምት_19_የልደታቸው_መታሰቢያ
በ1574 ዓ/ም አሁን በስማቸው ወደሚጠራው
ገዳመ ወንያት መንነው ገብተዋል።
ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በጸሎት ላይ ሳሉ አንዲት ሚዳቋ ነብር ሲያባርራት ወደ እረሳቸው መጥታ ተጠጋቻቸው ነብሩም ተቆጥቶ ቆመ ። አሳቸውም ነብሩ እንዳይበላት ነግረውት አሷንም ነብሩ እንደማይበላት ነግረው አሰናብተዋቸዋል።
✤ 🙏 የቅዱሳን አባቶቻችን ሕይወት ኑሯቸው ከሰብአዊ ፍጥረት አልፎ ከ እንስሳት ጋር በሰብአዊ ቋንቋ እስከ መነጋገር ምን ያህል ይረቅ ።
ቅዱስ አባታችን ከመነኮሱበት ገዳም በተዐቅቦ ራሳቸውን ገዝተው ለ 14 ዓመት በዐት አጽንተው ኖረዋል።
የቅድስና ተጋድሏቸውንም ፈጽመው በተወለዱ በ 90 ዓመታቸው ጥር 11 ቀን 1624 ሊሄዱ ወደሚናፍቁት ወደ ጌታቸው ክብር ሄደዋል። በሥጋም ከዚህ ዓለም ፈተና አርፈዋል።
በመቃብራቸውም ላይ ለ 40 ቀን ያህል ብርሀን እንደታየ በገድላቸው ይነበባል።
አጽማቸውም በገዳማቸው አርፎ ይገኛል።
በጸሎታቸው ያፈለቁት ጸበል እንዲሁም እምነታቸው ከተለያዩ የስጋ ደዌ ህመምተኞችን በመፈወስ ላይ ይገኛል።
( ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል )
👉 ድንቅ የሆነው ተአምር ደግሞ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የጻድቁ ወዳጆች ተአምረኛውን እምነት በየቀኑ አይወሰዱ እየተቀቡ ፤ እምነቱ የሚወሰድበት ቦታ ግን ጎድሎ አያውቅም ።
👉 ⛪ የጻድቁ አባታችን የአቡነ ሐራ ድንግል ገዳማቸው ከባሕርዳር ወደ ጎንደር መንገድ ስንወጣ ዘንዘልማ የምትባል አነስተኛ ከተማ ያገኛሉ ፤ ከዘንዘልማ በስተ ቀኝ ታጥፎ በ 12.ኪሜ ይገኛል።
👉⛪ አሁን ላይ የሚታየውን በጻድቁ መካነ መቃብራቸው ላይ የተሳረውን የገዳሙን ህንፃ ያሰሩት አፄ ዮሐንስ 4ኛ በጽኑ ደዌ ነቀርሳ ( ካንሰር) ታመው በጻድቁ አማላጅነት አምነው ከመቀሌ ድረስ መጥተው በጻድቁ ጸበል ተጠምቀው እና አምነታቸውን ተቀብተው በመፈወሳቸው ስለ ማመስገናቸው ህንጻውን አሰርተዋል እንዲሁም የክብር ዘውዳቸውን አበርክተዋል።
የጻድቁ አባታችን ረድኤት በረከታቸው አይለየን
በቃል ኪዳናቸው ከመከራ ስጋ ከመራ ነፍስ ይጠብቁን
ሀገራችንን በጽኑ ቃልኪዳናቸው ከክፉ ይጠብቁልን።
🙏 🙏 🙏
( ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል)
( ከገድላት አንደበት በገ/ሥላሴ ከገጽ 125 - 128)
ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት
ዲ/ን ጌታባለው አማረ (ሰዐሊ)
@deacongetabalewamare
@deacongetabalewamare
BY ✞ግቢ ጉባኤ✟
Share with your friend now:
tgoop.com/gibi_gubae/2726