tgoop.com/gibi_gubae/792
Last Update:
🌴አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ🌴
"አምላክ ልብህን ይቀይረዉ ዘንድ፣እርሱን ለመከተል ታገል፡፡ እንደዚህ በለዉ “ጌታ ሆይ ከልቤ አድነኝ፤ከሃጢያቴና ከተፈጥሮአዊ ዝንባሌም አድነኝ፡፡ ከአንተ በመታረቅ መንገዴ ላይ፣እነዚህ ነገሮች ሁሉ መሰናክል አይሁኑ፡፡ብዙ ልቦችን፣ምናልባት ከእኔ በላይ የከፋ ሁኔታ ዉስጥ የነበሩትን፣ብዙ ሰዎችን ቀይረሃል፡፡ ከእነርሱ መሐል አንዱ እሆን ዘንድ እመኛለሁ፤ከቀየርካቸዉ ልቦች መሐል እንዱ አድርገኝ፤የሙሴ ጸሊምን፣እውጉስጢንን፣ግብ ጻዊቷ ማሪያምን፣አሪያኖስን ልብ ቀይረሃል፡፡ታዲያ እኔ ያለሁበትን ሁኔታ ለመቀየር ይከብድሃልን?
የእኔ ሁኔታ የተወሳሰበ መሆኑን ተመልከት!ነገር ግን በአንተ ወሰን በሌለዉ ሀይልህ ፊት ሲቀርብ ለመፍታት የሚያስቸግር አይሆንም፡፡
አምላኬ ሆይ የራሴን ልብ እንኳን ለመመለስና ሰላማዊ ለማድረግ አልችልም፡፡ነገር ግን ከአንተ ጋር ለመታረቅ መጀመሪያ የሚያስፈልገኝን፤እንደዚህ ያለዉን ልቤን መቀየር የምትችለዉ አንተ ነህ፡፡ ለዚህ እርቅ ወደሚገባዉ፣ ቅዱስ የሆነ ልብ መነካት ስሜት ልታመጣዉ የምትችለዉ አንተ ነህ፡፡
አምላክ ሆይ “ልጄ ልብህን ስጠኝ”(ምሳ.23፣26)በለኝ “ይሄዉ እንዳለ ዉሰደዉ” በሂሶጵ ረጭተህ አንፃኝ፤እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ፡፡(ዳዊ.50(51)፣7) ልቤን እንድትጠግነዉ አይደለም የምጠይቅህ፣ንጹህ ልብን እንድትፈጥርልኝ(መዝ.51)አዲስ መንፈስ እንድትሰጠኝ እንጂ፡፡ (ሕዝ.36፣26) ለአንተ በልቤ ዉስጥ ፍቅር ባታገኝ፣ እባክህ ይሄንን ፍቅር ስጠኝ፡፡ ለአንተ ፍቅር ቢጎድለኝ አትወቀሰኝ፤ እንደ ሐዋርያዉ ቃል ወደ ልቤ በመንፈስ ቅዱስ ፍቅርህን አፍስስብኝ እንጂ፡፡(ሮሜ.5፣5)
”የሚፈልግ” ነገር ግን የሚፈልገዉን ነገር እንዴት እንደሚያገኝ እነደማያዉቅ፤የሆነ ነገር የሚፈልግ ነገር ግን ማግኘት እንደማይችለዉ፤ህጻን ልጅ ቁጠረኝ፤ በየመንገዱ እደነቃቀፋለሁና”በመንገድህ ምራኝ”(ዳዊ.119) ለድህነቴ ጉዳይ፣ስለ ነፍሴ ድህነት እንደሚገባኝ የቆረጥሁ ካልሆንኩኝ፣ የአንተ የእኔን ነፍስ ለማዳን መቁረጥህ በቂ ነዉ፡፡
የእኔ ፈቃድ ሀይል የእኔን ነፍስ ለማዳን በቂ ካልሆነ የአንተ ጸጋ በእርግጠኝነት ነፍሴን ሊያድናት በቂ ነዉ፡፡በእኔ ክፉ ጸባዬ ከአንተ ጋር ለመኖር ፈቃደኛ ባልሆን አንተ ከእንተ ጋር እኖር ዘንደ መፍቀድህ በቂ ነዉ፤የአንተ ፈቃድ የሚያስፈገዉን ሁሉ ሊያደርግ ይችላልና፡፡
ጌታ ሆይ ለራሴ ፈቃድና ለድክመቴ ከተዉከኝ ግን እጠፋለሁ፡፡ ራሱን ለማከምም ሆነ ወደ ሀኪምም ዘንድ መሄድ እንደማይችለዉ ህመምተኛ ሰዉ ቁጠረኝ፤ቃል ብቻ ተናገር ብላቴና ይፈወሳል፡፡ (ማቴ.8፣8)”
🔥ከልብህ ሆነ ለአምላክህ ጸሎት አቅርብ ጥረትህ እንደሚገበዉ ጥንካሬ ቢያጣ፤ጸሎትህ የጎደለዉን ይሞለዋል፡፡“የጻድቅ ሰዉ ጸሎት በስራዋ እጅግ ሀይልን ታደርጋለችና፡፡”(ያዕ.5፣16)
🔥ከአምላክ ጋር በመታረቅ ዉስጥ በራስህ ማስተወል አትደገፍ ወይም በራስህ ሀይል ላይ“በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፡፡”(ምሳ.3፣5) ድካምህን የሚረዳ ሀይል ከአምላክ ጠይቅ!
🔥አምላክ ከአንተ የሚፈልገዉ
👉ልብህን
👉ፈቃድህንና
👉እምነትህን ነዉ፡፡
🔥“ፈቃድ” ማለት ሀይለኛ ብርታትና ቁርጠኝነት ማሳየት አይደለም ግን ወደ አምላክህ ለመቅረብ ያለ ፍላጎት ነዉ እንጂ፡፡የሰዉ ልጅ ደካማ ቢሆን እንኳን አምላክ ያደርግ ዘንድ ሀይል ይሰጠዋልና፡፡ በእርግጥ አምላክ ራሱ ያደርግ ዘንድ ጥንካሬ ይሰጠዋል፤አምላክ ራሱ በእርሱ ዉስጥ ይሰራል፤ ከእርሱ ጋርም ይሰራል፡፡
🔥ቅዱስ ሐዋርያ ጳዉሎስ እንዳለዉ “ስለ በጎ ፈቃድ መፈለግንም ማድርግንም በእናንተ ዉስጥ የሚሰራ እግዚአበሔር ነዉና”(ፊል.2፣13) አምላክ ከእርሱ ጋር ለመታረቅ ያለህን ፍላጎት ይፈልጋል፤ምክንያቱም ማንንም ከእርሱ ጋር ይታረቅ ዘንድ አያስገድድምና፡፡ ይሄንን ፍላጎትህን ካስታወቅሀዉ፤ከአንተ ጋር ሆኖ ይሰራል፤ለብቻዉ ያደርገዋል እያልኩኝ አይደለም፡፡እንደዚህ ከሆነ አንድን ሰዉ ምንም ጥረት እንዳያደርገ ያበረታተዋልና፡፡
🔥በሌላ በኩል ከእርሱ ጋር ለመስራት ያለህ ፍላጎት ለመታረቅ ምን ያህል የቆረጥክ መሆንህን ያሳያል፤እስካሁን ከእርሱ ጋር ለመታረቅ ከልብ ፍላጎት ሊኖርህ ይገባል ብለናል፡፡ለፍላጎትህ የቆረጥክ ስትሆን፣በጸሎት ተግባርህን ለመጀመር መሞከር አለብህ፡፡ ሊገጥሙህ የሚችሉትን የትኛዉንም መሰናክል ሁሉም ድል ታደርግ ዘንድ እንዲረዳ መጸለይ አለብህ፡፡
❤️የአባታችን በረከት ይደረብን፤ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለዘልዓለሙ አሜን፡!
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
BY ✞ግቢ ጉባኤ✟
Share with your friend now:
tgoop.com/gibi_gubae/792