Forwarded from 666( ኢልሙናቲ ) ሀይማኖት ምዝገባ ማእከል via @Josy_Button_Bot
የቤተ ክርስቲያኑ በር ነገ ወለል ብሎ ቢከፈትም ትናንት ግን ዝግ እንደነበር አንርሳው።
በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ቅዱስ ሲኖዶሱ እንባችንን ሊያብስ አድባራት ክፍት እንዲሆኑና አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ ወስኗል። አያይዙም የማስተባበሩን ሃላፊነት አድባራት እና ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንዲወስዱ አደራ ብሏል።
እናም.....
1 ትናንትና መዘጋቱን ረስተን ነገ መከፈቱን ብቻ አይተን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብተን እርስ በርስ ቡድን መድበን እገሌ እገሌ ለመባባል አንሂድ ከነገ ወዲያም ሊዘጋ እንደማይችል እርግጠኞች አይደለንምና!
2 ከምስጢራት ለመሳተፍ ማለትም ንስሃ ለመግባት ለመቁረብ ቀጠሮ አናስረዝም ትናንት ዝግ ነበር ከነገ ወዲያም ላለመሆኑ ፈጣሪ ብቻ ነው ማስተማመኛችን!
3 የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ የሚያስከብሩ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትን አንተች ጥንቃቄውን እንደ መጠራጠር አንውሰድ እምነታችንን ትናንት ቤተ ክርስቲያን ተዘግቶ ቤት ስንውል አይተነዋልና!
4 ምንም አይነት አገልግሎት ላይ ብንሆን ጸሎትንም ጨምሮ በቸልታ በማፌዝ አናድርገው ትናንት ባደረግነው ፌዝና ቸልታ ቤተ ክርስቲያን ተዘግቶ ነበርና!
5 ይሄን እድል ፈጥነን እንጠቀምበት ቤተ ክርስቲያናችንን እናክብራት የማይታዩ ጠባቂዎቿን መላእክትን ስንረሳ ፈጣሪ አለማውያኑን ከበሩ ላይ አቆመ ፣ በሰው መብዛት ስንመጻደቅ ቁጥራችን ምንም እንደማይረባው ሊያሳየን ቀነሰን ፣ እርሱ የሚፈልገውን ህይወት ሊያመለክተን ቆራቢ ብቻ እንዲገባ ተፈቀደ ፣ የእምነታችንን ድክመት ለሁላችንም ገለጸልን ፣ እንዲያ የቀበጥንበት የእግዚአብሔር ቤት እስኪናፍቀን ድረስ ባለመግባት ተቀጣን ፣ እንዲያ ለመታያ ብቻ ያደረግነው አገልግሎት ቆሞ መስዋዕትነት የሚጠይቅ አገልግሎት ሰጠን ፣ ብዙዎቻችንም ይሄ አገልግሎት ከብዶን ከቤተ ክርስቲያን ራቅን ጠፋን ፣ ራሴ ማለት ትተን ነበርና ራሳችንን እንድናይ ጊዜ ሰጠን ፣ በጣም ብዙ ነገር ተደረገልን
ይሄን ሁሉ ነገ ቤተ ክርስቲያን ሲከፈት እንዳንዘነጋው ቤተ ክርስቲያኑ ሲዘጋ አቁመንበት ከነበረው ሁኔታ ዛሬም ከቀጠልን ከነገ ወዲያም እንደሚዘጋ እርግጠኞች እንሁን። ያዘጋው ምንም አይደለም የኛ ችግር ነው።
ነገ እንዳይዘነጋ በተለይ ሰንበት ተማሪዎች እንደ ስማችን የቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች ሆነን የማስተባበሩን ስራ እንከውን። ይሄ እንደ ትናንቱ ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ውስጥ የምንፈልገውን ሰምተን ሰንበት ተማሪን የሚመለከተውን ውሳኔ ባላየ ማለፉ አይጠቅመንም።
እንደ ምዕመንም ወደ ሌላ ነገር አንግባ በቃ ምንም ስሌት አያስፈልገውም ትናንትና ተዘግቶ ነበር። ነገም ሊዘጋ ይችላል። ግን እንዳይዘጋ ቅዱስ ሲኖዶስ እንዳዘዘን የታዘዝነውን ጥንቃቄ እንፈጽም ስለ ተቀራረብን የውስጥ አንድነት አለን ማለት አይደለም ስለተራራቅንም እንዲሁ።
እኛ ልጆች ነን ልጅነታችን ደግሞ ለእግዚአብሔር ነው ሰማያዊው አባታችን እግዚአብሔር ደግሞ ምድራዊ አባት ጳጳሳትን ሰጥቶናል። ከዚያም ደግሞ አባትህን እና እናትህን አክብር ብሎናል።
ነገም ዳግመኛ የቤተ ክርስቲያን በሮች እንዳይዘጉ እኔም አንተም አንቺም ሁላችንም ከራሳችን የሚጠበቀውን ነገር እናድርግ።
ዲያቆን ዳዊት ናሁሠናይ (ዘብሥራት)
ግንቦት 5 2012 ዓ.ም
ወለቴ
👇👇👇👇👇
👉 @zebisrat 👈
👆👆👆👆👆

🌴አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ🌴
"አምላክ ልብህን ይቀይረዉ ዘንድ፣እርሱን ለመከተል ታገል፡፡ እንደዚህ በለዉ “ጌታ ሆይ ከልቤ አድነኝ፤ከሃጢያቴና ከተፈጥሮአዊ ዝንባሌም አድነኝ፡፡ ከአንተ በመታረቅ መንገዴ ላይ፣እነዚህ ነገሮች ሁሉ መሰናክል አይሁኑ፡፡ብዙ ልቦችን፣ምናልባት ከእኔ በላይ የከፋ ሁኔታ ዉስጥ የነበሩትን፣ብዙ ሰዎችን ቀይረሃል፡፡ ከእነርሱ መሐል አንዱ እሆን ዘንድ እመኛለሁ፤ከቀየርካቸዉ ልቦች መሐል እንዱ አድርገኝ፤የሙሴ ጸሊምን፣እውጉስጢንን፣ግብ ጻዊቷ ማሪያምን፣አሪያኖስን ልብ ቀይረሃል፡፡ታዲያ እኔ ያለሁበትን ሁኔታ ለመቀየር ይከብድሃልን?
የእኔ ሁኔታ የተወሳሰበ መሆኑን ተመልከት!ነገር ግን በአንተ ወሰን በሌለዉ ሀይልህ ፊት ሲቀርብ ለመፍታት የሚያስቸግር አይሆንም፡፡
አምላኬ ሆይ የራሴን ልብ እንኳን ለመመለስና ሰላማዊ ለማድረግ አልችልም፡፡ነገር ግን ከአንተ ጋር ለመታረቅ መጀመሪያ የሚያስፈልገኝን፤እንደዚህ ያለዉን ልቤን መቀየር የምትችለዉ አንተ ነህ፡፡ ለዚህ እርቅ ወደሚገባዉ፣ ቅዱስ የሆነ ልብ መነካት ስሜት ልታመጣዉ የምትችለዉ አንተ ነህ፡፡
አምላክ ሆይ “ልጄ ልብህን ስጠኝ”(ምሳ.23፣26)በለኝ “ይሄዉ እንዳለ ዉሰደዉ” በሂሶጵ ረጭተህ አንፃኝ፤እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ፡፡(ዳዊ.50(51)፣7) ልቤን እንድትጠግነዉ አይደለም የምጠይቅህ፣ንጹህ ልብን እንድትፈጥርልኝ(መዝ.51)አዲስ መንፈስ እንድትሰጠኝ እንጂ፡፡ (ሕዝ.36፣26) ለአንተ በልቤ ዉስጥ ፍቅር ባታገኝ፣ እባክህ ይሄንን ፍቅር ስጠኝ፡፡ ለአንተ ፍቅር ቢጎድለኝ አትወቀሰኝ፤ እንደ ሐዋርያዉ ቃል ወደ ልቤ በመንፈስ ቅዱስ ፍቅርህን አፍስስብኝ እንጂ፡፡(ሮሜ.5፣5)
”የሚፈልግ” ነገር ግን የሚፈልገዉን ነገር እንዴት እንደሚያገኝ እነደማያዉቅ፤የሆነ ነገር የሚፈልግ ነገር ግን ማግኘት እንደማይችለዉ፤ህጻን ልጅ ቁጠረኝ፤ በየመንገዱ እደነቃቀፋለሁና”በመንገድህ ምራኝ”(ዳዊ.119) ለድህነቴ ጉዳይ፣ስለ ነፍሴ ድህነት እንደሚገባኝ የቆረጥሁ ካልሆንኩኝ፣ የአንተ የእኔን ነፍስ ለማዳን መቁረጥህ በቂ ነዉ፡፡
የእኔ ፈቃድ ሀይል የእኔን ነፍስ ለማዳን በቂ ካልሆነ የአንተ ጸጋ በእርግጠኝነት ነፍሴን ሊያድናት በቂ ነዉ፡፡በእኔ ክፉ ጸባዬ ከአንተ ጋር ለመኖር ፈቃደኛ ባልሆን አንተ ከእንተ ጋር እኖር ዘንደ መፍቀድህ በቂ ነዉ፤የአንተ ፈቃድ የሚያስፈገዉን ሁሉ ሊያደርግ ይችላልና፡፡
ጌታ ሆይ ለራሴ ፈቃድና ለድክመቴ ከተዉከኝ ግን እጠፋለሁ፡፡ ራሱን ለማከምም ሆነ ወደ ሀኪምም ዘንድ መሄድ እንደማይችለዉ ህመምተኛ ሰዉ ቁጠረኝ፤ቃል ብቻ ተናገር ብላቴና ይፈወሳል፡፡ (ማቴ.8፣8)”
🔥ከልብህ ሆነ ለአምላክህ ጸሎት አቅርብ ጥረትህ እንደሚገበዉ ጥንካሬ ቢያጣ፤ጸሎትህ የጎደለዉን ይሞለዋል፡፡“የጻድቅ ሰዉ ጸሎት በስራዋ እጅግ ሀይልን ታደርጋለችና፡፡”(ያዕ.5፣16)
🔥ከአምላክ ጋር በመታረቅ ዉስጥ በራስህ ማስተወል አትደገፍ ወይም በራስህ ሀይል ላይ“በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፡፡”(ምሳ.3፣5) ድካምህን የሚረዳ ሀይል ከአምላክ ጠይቅ!
🔥አምላክ ከአንተ የሚፈልገዉ
👉ልብህን
👉ፈቃድህንና
👉እምነትህን ነዉ፡፡
🔥“ፈቃድ” ማለት ሀይለኛ ብርታትና ቁርጠኝነት ማሳየት አይደለም ግን ወደ አምላክህ ለመቅረብ ያለ ፍላጎት ነዉ እንጂ፡፡የሰዉ ልጅ ደካማ ቢሆን እንኳን አምላክ ያደርግ ዘንድ ሀይል ይሰጠዋልና፡፡ በእርግጥ አምላክ ራሱ ያደርግ ዘንድ ጥንካሬ ይሰጠዋል፤አምላክ ራሱ በእርሱ ዉስጥ ይሰራል፤ ከእርሱ ጋርም ይሰራል፡፡
🔥ቅዱስ ሐዋርያ ጳዉሎስ እንዳለዉ “ስለ በጎ ፈቃድ መፈለግንም ማድርግንም በእናንተ ዉስጥ የሚሰራ እግዚአበሔር ነዉና”(ፊል.2፣13) አምላክ ከእርሱ ጋር ለመታረቅ ያለህን ፍላጎት ይፈልጋል፤ምክንያቱም ማንንም ከእርሱ ጋር ይታረቅ ዘንድ አያስገድድምና፡፡ ይሄንን ፍላጎትህን ካስታወቅሀዉ፤ከአንተ ጋር ሆኖ ይሰራል፤ለብቻዉ ያደርገዋል እያልኩኝ አይደለም፡፡እንደዚህ ከሆነ አንድን ሰዉ ምንም ጥረት እንዳያደርገ ያበረታተዋልና፡፡
🔥በሌላ በኩል ከእርሱ ጋር ለመስራት ያለህ ፍላጎት ለመታረቅ ምን ያህል የቆረጥክ መሆንህን ያሳያል፤እስካሁን ከእርሱ ጋር ለመታረቅ ከልብ ፍላጎት ሊኖርህ ይገባል ብለናል፡፡ለፍላጎትህ የቆረጥክ ስትሆን፣በጸሎት ተግባርህን ለመጀመር መሞከር አለብህ፡፡ ሊገጥሙህ የሚችሉትን የትኛዉንም መሰናክል ሁሉም ድል ታደርግ ዘንድ እንዲረዳ መጸለይ አለብህ፡፡
❤️የአባታችን በረከት ይደረብን፤ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለዘልዓለሙ አሜን፡!
@gibi_gubae

+ የሞት ሞት +
‹‹ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰሎሞን
እጠይቀው ነበር በተገናኘን
ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?››
ነፍሳቸውን ይማርና ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል ይህችን ጥልቅ ስንኞች ያሏት አጭር ግጥም ጽፈው ነበር፡፡ ጋሽ ከበደ ምናልባት በዚያኛው ዓለም ጠቢቡ ሰሎሞንን የማግኘት ዕድል ገጥሟቸው ይጠይቁት ይሆናል፡፡ ሆኖም እርሳቸው ‹ሞት የሚሞትበት ጊዜው መቼ ነው?› ብለው ወደኋላ ዘመን ተጉዘው የብሉይ ኪዳኑን ሰው ጠየቁ እንጂ ሞት እንኳን ከሞተ ድፍን ሁለት ሺህ ዓመታት አልፈውታል፡፡ ለዘመናት ባለሥልጣን ሆኖ ሲገድል ብቻ የኖረው ሞት በዕለተ ዓርብ ግን ‹የሞት ሞቱ› በሆነው በመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ኃይል ሞት ራሱ ፍግም ብሎ ሞቷል፡፡ አሟሟቱ ደግሞ እንዲሁ አልነበረም ፣ ‹ከሞቱ አሟሟቱ› እንዲሉ አበው ሞት እንደ አረጀ አንበሳ ጥርሶቹ ረግፈው ጽኑ ሥቃይ ተሠቃይቶ ፣ ተዋርዶ ፣ በሆዱ ያለውን ሁሉ ተፍቶ ነበር የሞተው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የሞትን አሰቃቂ አሟሟት ከሆድ ሕመም ጋር ባለመሳሰለበት ‹ተምሳሌተ መብል ወከርስ› (Gastronomic Analogy) እንዲህ ይገልጸዋል ፡-
‹‹የክርስቶስን ሰውነት በመቀበሉ ሞት ታላቅ ስኅተት ሠራ፡፡ ይህ ሰውነት በእርሱ የገዥነት ሥልጣን ሥር ያለ ተራ ሰውነት ፣ ኃጢአተኛ የሆነና የሚሞት ሰውነት መስሎት ነበር፡፡ ከሰውነታቸው ጋር የማይስማማ ምግብን የበሉ ሰዎች ሲያስመልሳቸው የሚያወጡት አልስማማ ያላቸውን ምግብ ብቻ ሳይሆን የበሉትን ነገር ሁሉ ነው፡፡ በሞትም ላይ የሆነው ይኼው ነው፡፡ ሞት ፍጹም ንጹሕና የማይሞት የሆነውን የክርስቶስን ሥጋ ዋጠ ፤ የማይሞተው ሕያዉ ክርስቶስ ለአልጠግብ ባዩ ሞትና ሲኦል የሚመር እና የማይስማማ ምግብ ሆነበት፡፡ ሊስማማው ስላልቻለም ተፋው ፤ ከክርስቶስ ሥጋ ጋርም ሲኦል ሆድ ውስጥ ከጥንት ጀምሮ ውጦ የያዘውን ሙት ሁሉ አብሮ ተፋ፡፡ ለሞት የሚስማማው ብቸኛ ምግብ ኃጢአት ብቻ ነው፡፡ ኃጢአት የሌለበት የጌታ ሰውነት ለሲኦል የማይስማማ ምግብ ነው፡፡
ሞት ሊላመጥ የማይችልን ትልቅ ድንጋይ ዋጠ ፤ ይህ ድንጋይ የማይላመጥ ብቻ ሳይሆን በሆድ ውስጥ ቆይቶ የሚያፈራርስና የሚሰባብር ነው፡፡ ስለዚህ ሞት ‹የማዕዘን ድንጋይ› የሆነውን የክርስቶስን ፍጹም ቅዱስ የሆነ ሥጋ በዋጠ ጊዜ በታላቅ ሥቃይና ድካም ውስጥ ሆኖ ጥንካሬዎቹን ሁሉ አጣ፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ጴጥሮስ ‹ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለም› ያለው፡፡ (ሐዋ.፪፥፳፬) የትኛዋም ሴት ልጅ ለመውለድ ምጥን ባማጠች ጊዜ ሞት የክርስቶስን ሥጋ ይዞ የተጨነቀው ያህል ተጨንቃ አታውቅም ”
ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ደግሞ በሰውኛ ዘይቤ (Personification) በጻፈው ውብ ድርሰቱ ሞትን ስለ ክርስቶስ ከራሱ ጋር እንዲህ ያናግረዋል፡-
‹‹ሞት እንዲህ አለ ፡- ‹‹ይህ ማን ነው? የማንስ ልጅ ነው? እኔን ድል የነሣኝ ይህ [ኢየሱስ የተባለ] ሰው ከየትኛው ቤተሰብ የተገኘ ይሆን? የትውልዶች ሁሉ የዘር ሐረጋቸው የተዘረዘረበት መጽሐፍ በእጄ ላይ አለ፡፡ ከአዳም ጀምሮ የነበሩት ሰዎች ስም አንድ በአንድ ማንበብ ጀመርሁ፡፡ ከእኔ ያመለጠ [ያልሞተ] አንድም ሰው የለም፡፡ ነገድ በነገድ ሁሉም በክንዶቼ ላይ ተጽፈዋል…
…. በእርግጥ አልዋሽም ፤ የሁለት ሰዎች ስም ብቻ ከእኔ ዘንድ የለም ፤ ሄኖክና ኤልያስ ወደ እኔ አልመጡም … በመላው ምድር ሁሉ ዞሬ ፈለግኋቸው ፣ ዮናስ እስከ ወረደበት የዓሣ አንበሪው ሆድ ድረስ ወርጄ ፈለግኋቸው፡፡ በገነት ውስጥ ተሸሽገው ከሆነ እንዳልፈልጋቸው የሚያስፈራ ኪሩብ ጠባቂ ሆኖ ቆሟል፡፡ ያዕቆብ መሰላልን ተመልክቶ ነበር ፤ ምልባት ወደ ሰማይ የወጡት በዚያ መሰላል ይሆንን?››
ከዚህ ሁሉ መዘላበዱ በኋላም ሞት በሶርያዊው ብዕር እንዲህ ሲል የክርስቶስን ሞት ያማርራል፡-
‹‹ሞት እንዲህ አለ ፡- ወደ ሙሴ ዘመን ብመለስ ሳይሻለኝ ይሆን? ሙሴ እኮ በዓልን ደግሶልኝ ነበር፡፡ በግብፅ ፋሲካ የታረደው በግም ከእያንዳንዱ ግብፃዊ ቤት የበኩር ልጅን ሠጥቶኝ ነበር፡፡ በሙት ላይ ሙት በሲኦል ደጃፍ ተከምረውልኝ ነበር፡፡ ይኼኛው የፋሲካ በግ [ክርስቶስ] ግን ሲኦልን በዘበዘው ፣ ሙታንንም ከእጄ ነጥቆአቸው ወጣ፡፡ ሙሴ ያሳረደው የቀደመው በግ መቃብሮችን ሞላልኝ ፤ ይኼኛው በግ ክርስቶስ ግን ሞልተው የነበሩትን መቃብሮች ባዶ አደረገብኝ››
‹‹የኢየሱስ ሞት ለእኔ ሥቃይ ነው ፤ ከሞቱ ይልቅ ለእኔ በሕይወት እንዲቆይ በተውሁትና ወደ እርሱ ባልቀርብሁ ይሻለኝ ነበር፡፡ በሌሎች ሰዎች ሞት ደስ ይለኝ ነበር ፤ የእርሱን ሞት ግን ጠላሁት፡፡ በሕይወት ሳለ የሞቱ ሰዎችን አስነሥቶ ነበርና እርሱም ከሞት እንደሚነሣና ወደ ሕይወት እንደሚመጣ ገምቼ ነበር፡፡ እርሱ ግን በሞቱ ሙታንን ወደ ሕይወት ወሰዳቸው ፤ ይዤ ላስቀራቸው ስሞክርም በሲኦል ደጃፍ አሽቀንጥረው ጥለውኝ ሔዱ … ገና አሁን እኔም ስለ ወዳጆቻቸው ሞት የሚያለቅሱ ሰዎችን የኀዘናቸውን ጣዕም ቀመስሁት … ከሰዎች ላይ የሚወዷቸውን በመቀማት የማመጣባቸው ሥቃይ በተራው በእኔም ላይ ወደቀ …›› እያለ ሞት ‹እግዚአብሔር ያጽናህ› የማይባል ኀዘንን አዘነ፡፡
ተስፋ የቆረጠ መቼም ከሁሉ ጋር ጠበኛ መሆኑ አይቀርምና ሞት በደረሰበት ውርደት ከወዳጁ ከዲያቢሎስም ጋር ተጣላ፡፡ ዲያቢሎስ ሰውን ለሚያሠራው ኃጢአት ደሞዙ ሞት ቢሆንም በክርስቶስ ሞት ምክንያት ግን ሰይጣን ከደሞዝ ከፋዩ ሞት ጋር ተጣላ፡፡ ሶርያዊው ንብ ኤፍሬም በንጽቢን እያለ በጋገረውና ሳናካትተው ልናልፈው በማንችለው ውብ የኦርቶዶክሳዊ ሥነ ጽሑፍ የማር እንጀራ በመሰለ ዝማሬው ላይ እንዲህ ይላል ፡-
‹‹ሞትና ሰይጣንን ‹ከእኔና ከአንተ በሰው ላይ ኃይለኛ የሆነ ማን ነው?› እያሉ እየጮኹ ሲነታረኩ ሰማኋቸው፡፡ ሞት ሰዎችን ሁሉ መማረኩን በመግለጽ ኃይለኛነቱን አስረዳ ፤ ሰይጣን ደግሞ ሰዎችን ሁሉ ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግበትን ተንኮሉን አስረዳ፡፡
ሞት ፡- አንተ ክፉ ሆይ ፤ ለአንተ የሚታዘዙልህ እኮ መታዘዝ የፈለጉ ሰዎች ብቻ ናቸው ፤ ለእኔ ግን ወደዱም ጠሉም ይታዘዙልኛል፡፡
ሰይጣን ፡- አንተ እኮ በጉልበት አስገድደህ ነው የምትይዛቸው ፤ እኔ ግን የምይዛቸው የሚማርኩ ማማለያዎችንና ወጥመዶችን ተጠቅሜ ነው፡፡
ሞት ፡- ስማኝ አንተ ክፉ ፣ የአንተን ወጥመዶች ብርቱ ሰው ሊሰባብራቸው ይችላል ፤ ከእኔ ቀንበር ግን ማንም አያመልጥም ፤ ማንም!
ሰይጣን ፡- አይ ሞት! አንተ እኮ ጉልበትህን የምታሳየው በታመሙ ሰዎች ላይ ነው ፤ እኔ ግን በጤነኞቹም ላይ ኃይል አለኝ!
ሞት ፡- አንተ እኮ የሚቃወሙህን ሰዎች ትሸሻለህ እንጂ ድል የማድረግ ሥልጣን የለህም ፤ እኔ ግን በሚረግሙኝ ላይም ሥልጣን አለኝ ፤ የሰው ልጅ እየረገመኝ እንኳን እጄ ላይ ይወድቃል!
ሰይጣን ፡- ሞት ሆይ! አንተ እኮ ይህን ሥልጣን ያገኘኸው ከእግዚአብሔር ነው ፤ እኔ ግን ሰዎችን ወደ ኃጢአት ስመራ ማንም አይረዳኝም፡፡
ሞት ፡- እኔ እንደ ንጉሥ ሥልጣኔን ስጠቀም አንተ ግን ሥራህን የምትሠራው በደካማነትና በመልከስከስ ነው፡፡
ሰይጣን ፡- አይ ሞኙ! ምን ያህል ታላቅ እንደሆንሁ አታውቅም አይደል? እኔ እኮ ከፍተኛውን ሥልጣን ነጻ ፈቃድን ለመማረክ ብቃት ያለኝ እኮ ነኝ!
ሞት፡- አንተ እኮ ተንኮልህን የምትሠራው እንደ ሌባ በመሬት እየተሳብክ ነው ፤ እኔ ግን እንደ አንበሳ ሳልፈራ ሰባብሬ እጥላለሁ!
ሰይጣን ፡- ሞት ሆይ ፤ እስቲ ንገረኝ አንተን የሚያገለግልህና የሚያመልክህ ማን ነው? እኔን ግን ነገሥታት ሳይቀሩ እንደ አም

ላክ ያመልኩኛል!
ሞት ፡- ሞታቸውን እንደ መልካም ነገር የሚናፍቁኝና የሚጠሩኝ ብዙዎች ናቸው ፤ አንተን ግን ፈልጎ የጠራህም የሚጠራህም የለም፡፡
ሰይጣን ፡- ብዙ ሰዎች በሥራቸው እንደሚጠሩኝና እጅ መንሻም እንደሚያቀርቡልኝ አላስተዋልክም እንዴ? አይ ሞት!
ሞት ፡- ስምህ እኮ የተጠላ ነው አይ ሰይጣን! ሁሉ ይረግምሃል ፤ ስምህን ልታነጻውና መጠላትህን ልትሸሽገው አትችልም፡፡
ሰይጣን ፡- ጆሮህ ሳይደፈን አይቀርም ፤ ሰዎች በአንተ ላይ ምን ያህል በምሬት እንደሚጮኹ አትሰማም እንዴ? ይልቅ ብትደበቅ ሳይሻልህ አይቀርም…››
የሞትና የሰይጣን ክርክር ረዥም ነው ፤ ክርክሩ ከሲኦልም ጋር ይቀጥላል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ከሁሉ በመጨረሻ :- ‹‹አንድ ልብ ሆነው የነበሩትን ሞትና ሰይጣንን የከፋፈላቸው እርሱ የተመሰገነ ይሁን ፤ ተከፋፍለን የነበርነውን እኛንም አንድ ልብ ያደረገን እርሱ የተመሰገነ ይሁን›› ብሎ ውብ ድርሰቱን ያጠናቅቃል፡፡
‹አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል› እንደሚባለው ሞት በአሟሟቱና በመዋረዱ የተነሣም እኛ ክርስቲያኖች እጅግ ንቀነው ‹መውጊያህ የታለ?› እያልን መዘበት የጀመርን ሲሆን ሰማዕታቱ ደግሞ እንኳንስ ሊፈሩት የአንገታቸውን ኮሌታ ለመታረድ እየሰበሰቡ በደስታ የሚጠጡት ጽዋ ሆነላቸው፡፡ ስንቱን እንዳላስለቀሰና በጣር እንዳላስጨነቀ ዛሬ ሙቱ ሞት ተንቆ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ለፍትሐት ጸናጽልና ከበሮ ይዛ የምትዘምርበት ፣ በኀዘን ፈንታ ማኅሌት የምትቆምበት ፣ እየተደገሰ ከነዳያን ጋር የሚበላበት ክስተት ሆኖ አረፈው፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 28 2012 ዓ ም
ሕማማት - ገጽ 500

አስደናቂዋ ፍሬ
አለም ሲፈጠር በርካታ አስደናቂ ፍጥረታት ተፈጥረዋል። የሰው ልጅም ፍጡር በመሆኑ ስለ ፍጥረታት አውቆ ሊጨርስ አይቻለውም። ነገር ግን ከፍጥረታት ግን መማር ያለበትን ነገር ሊማር ይገባዋልና ስለ ፍጥረታት እናነሳለን።
አሁን የምነግራችሁ ስለ አንድ አስደናቂ ፍሬ ነው። ይህችን ፍሬ የያዘው ትላቁ ዛፍ አጠገብ ሆነው ከሚያስጎበኙኝ አባት ጋር ሆነን በአስደናቂዋ ፍሬ እንደነቃለን። መደነቅም ብቻ ሳይሆን እናማማራለን። አስጎብኚያችን አባት ንግግራቸውን የጀመሩት ወደ ዛፏ በእጃቸው እየጠቆሙ ነው።
አየሃት ያቺን ዛፍ ርዝመቷን ፥ መርዘሟ ደግሞ የሚጎላው ፍሬዋ ያለበትን ቦታ ስታየው ነው። አስደናቂዋ ፍሬ ከላይ ነው ያለቺው። ፍሬዋ የተንጠለጠለችበት ሁኔታ ፣ የፍሬዋ ቅርጽ ፣ የፍሬዋ ቀለም አጓጊ እንድትሆን ያደረጓት ነገሮች ውስጥ የተወሰኑት ናቸው። ደግሞ በዚህ ያለፈ ያገደመ ሁሉ ይህቺን ፍሬ ሳያያት አያልፍም። ያያት ደግሞ ሳይጎመጅ አይቀርም።
ከጎመጁት ውስጥ አንዳንዶች አስደናቂዋን ፍሬ በማየት ብቻ ሲያልፏት ተመልክቻለሁ። ሌሎቹም ተመኝተዋታል። እኔን የሚያስገርሙኝ ግን ሁለት አይነት ሰዎች ናቸው። የመጀመሪያዎቹን አደንቃቸዋለሁ ሁለተኞቹን ደግሞ አፍርባቸዋለሁ።
የመጀመሪያዎቹ የማደንቃቸው እዚህ ለመውጣት ከባድ የሆነ ዛፍ ላይ ወጥተው ያቺን የምታስጎመጅ ፍሬ አውርደው የሚበሉት ናቸው። ግን እነዚህን እንደማደንቃቸው ሁሉ ሞክረው የሚያቅታቸውንም ፣ የአቅማቸውን ሞክረው የሚሄዱትንም አደንቃቸዋለሁ። ይህን ያስተማረኝ ይህች አስደናቂ ፍሬ ናት። በአንድ ወቅት አንዱ ብዙ ጥሮ ሲያቅተው ፍሬዋ ራሷ ወደቀችለትና በላት። በአንድ ወቅት ደግሞ ይህችን ፍሬ ለመብላት ተጋግዘው ሁለት ሆነው ሲወጡ ላይ ከደረሱ በኋላ ፍሬዋ ሁለት ሆነችና ለሁለቱም ሆነች። ይህች ፍሬ አስደናቂዋ ፍሬ እየተባለች መጠራት የጀመረችው ከዚያ በኋላ ነው።
ሌሎቹ የማፍርባቸው ደግሞ ከላይ የሚያወርድ ሰውን በመቀማት ፍሬዋን ለመብላት የሚጥሩ ሰዎች ናቸው። ግን ይህች አስደናቂ ፍሬ ለእንደዚህ አይነት ሰዎች አትሆንም። በአንድ ወቅት ሁለት ሰዎች መጡና አንዱ ወደላይ ወጣና ይህችን ፍሬ አውርዶ ሊበላ ሲል አብሮት የመጣው ጓደኛው ሲቀማው ይህች ፍሬ ተበላሸች። እኛ ይህች ፍሬ አስደናቂነቷ በብዙ መልክ ነው።
ይህን ያህል ስለ አስደናቂዋ ፍሬዋ ከነገርኩህ ስለ ፍሬዋ አስተማሪነት ልንገርህ እያሉ ወደ መቀመጫ ወሰዱኝ እና ንግግራቸውን ቀጠሉ።
ይህች አስደናቂ ፍሬ ሕይወት ናት። ብዙዎች ይህችን ፍሬ ሊበሉ ስኬታማ ሕይወት ሊኖሩ ይፈልጋሉ። ነገር ግን ከነዚህ ብዙ ስኬታማ ሕይወት መኖር ከሚፈልጉ ሰዎች መካከል መከፈል ያለበትን ዋጋ መክፈል ዛፉን መውጣት የሚፈልጉ ጥቂቶቹ ናቸው። ይህች ዛፍ ስር በሕይወት መስመር ላይ ሆነህ ስኬታማ ለመሆን ከፈለክ ስለ ስኬታማነት ብዙ ማሰብ ሳይሆን ጥቂት ሞክረህ ዛፉን መውጣት ነው የሚሻለው።
ስለዚህች አስደናቂ ፍሬ ያነሳነው ነገር ሁሉ ሕይወትን ይመለከታል። ሕይወት ጥረትን ትፈልጋለች በምኞት አትሳካም። ለሰው ሁሉ ተመሳሳይ ጣዕም ላይኖራት ይችላል። ለተባበሩ ትቀላለች። የተባበሩትም በመተባበራቸው አይጎዱም። ለምቀኞች አትሆንም እጃቸው ብትገባም ጣዕሟን አትሰጥም።
በሕይወትህ መልካም ነገርን ለማግኘት በቅድሚያ ዋጋን ልትከፍል ብዙ ልትደክም እንደምትችል መርሳት የለብህም። ሕይወት እንድትመችህ ያሰብክ ለታ የዚህን ዛፍ ርዝማኔ ተመልከት በዛፉ ርዝማኔ ደግሞ ተስፋ እንዳትቆርጥ የፍሬዋን መልክ አስተውለህ ጣፋጭነቷን ገምት። ያኔ ሁሉንም አመጣጥነህ መሄድ አለብህ። በአንተ አስተሳሰብ ሕይወት ልትሆን የምትፈልገው ነገር ሳይሆን ሕይወት እንዳለችው ነው የምትሆነው። እያሉ ከተቀመጡበት ተነሱና እኔን ለማሰናበት ሽር ጉድ ማለት ጀመሩ። እኔም ተሰናብቼ በአስደናቂዋ ፍሬ እየተደነኩ ተለየኋቸው።
ዲያቆን ዳዊት ናሁሠናይ (ዘብሥራት) @zebisrat
ግንቦት 10 2012 ዓ.ም

📚የተለያዩ የብራና መጽሐፍት
📚መጽሐፈ ሔኖክ
📚 መዝሙረ ዳዊት
📚 መመጽሐፈ ኩፋሌ
ግዕዙን መመርመር ለምትሹ ሊቃውንት እና ጠበብት እንዲሁም ጥበብ ፈላጊዎች በሙሉ!
በብራና የተዘጋጁ የጥንት መጽሐፍቶችን በቴሌግራም ላይ በ PDF ለማግኘት ይቀላቀላሉ።
👉 https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAFkIxjZXhdZg59k2Nw
👉🏽"መፀሐፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ።" ማቴ 22፥29
➡️ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍቶችን በPDF & ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን የያዙ አፖች የሚለቀቁበት ቻናል ነው ይቀላቀላሉ↘️
█████████████████
█▓▒░░ JOIN ░░▒▓███
█▓▒░░ OPEN ░░▒▓███
█████████████████ 📚
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል"
📖ሆሴዕ 4፥6
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን የሚያገኙበት ቻናል ነው።
✝ ይቀላቀላሉ ✝
✝ JOIN JOJN ✝

ምድረ-ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም
#ምድረ_ከብድ_ገዳም ፡– ከአዲስ አበባ ቡታጅራ መስመር ሲመጡ 100 ኪ,ሜ የአስፓልት መንገድ እንደተጓዙ በጉራጌ ዞን የምትገኘውን ቡኢ ወረዳን ያገኛሉ ። ከተማዋን ወጣ እንዳሉ ወደግራዎ እንዲታጠፉ የሚያመለክተውን ምልክት{ታቤላ} ያያሉ : ከዚያ 20ኪ,ሜ የጠጠር መንገድ ተጉዘው ያገኙታል።በምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም ፡—
1ኛ † ,,,, የአቡየ ቤተክርስቲያን ።
2ኛ † ,,,, በምልጃዋ ለነፍሳችን ነፍሷ የሆነችው የእመቤታችን ልደታ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ።
3ኛ † ,,,,የጻድቁ አባታችን የእረፍታቸው ቦታ።
4ኛ † ,,,,ዋሻ ሰረገላ ማለት ፡– በዓታቸው ከሆነችና ዳግማዊት ኢየሩሳሌም ተብላ ከተሰየመችው ምድረ ከብድ ገዳም ወደ………
- በደብረ ታቦር ወደተሰየመው በዓታቸው ዝቋላ ገዳም ።
- ኢየሩሳሌም ።
- አረብ ምድርና ፡ ብሔረ ብጹሀን
ወደ ተለያዩ ገዳማት ይሄዱበት የነበረ በምድር ውስጥ ለውስጥ ጉዟቸው ጊዜ በራፏ (ደጃፏ) ይገኛሉ።
በነዚህ ቅዱሳት መካናት በመገኘትና በመማጸን ለርዕሰ ባሕታዊ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቸሩ አምላካችን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አትረፍርፎ ከሰጣቸው ጸጋና በረከት ለመሳተፍ በቃል ኪዳናቸው ለመጠቀም
《ኑ》በዓላቸውን አብረን እናክብር።
የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት
የእመቤታችን አማላጅነት
የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸሎትና ልመና
ይህን ቅዱስ ቦታ ረግጣችሁ ከበረከቱ ተሳታፊ ያድርጋችሁ። ከሚመጣውም መቅሰፍት ፡ አሁን ከመጣብን ወረርሽኝ ይጠብቁን ፡ ይሰውሩን ፡ ከአለም ከኢትዮጵያ ያጥፉልን። አሜን,,,

የቅዱሳን አባቶች ወርቃማ አባባሎች
አባ ሙሴ ጸሊም
*መነኩሴ ለባልንጀራው መሞት ይገባዋል፤በምንም መንገድ እና በምንም ሁኔታ በወንድሙ ላይ መፍረድ የለበትም።
*መነኩሴ ማንንም እንዳይጎዳ ሥጋ መመገብ ከመተው በፊት ለማንኛውም ነገር መዋቲ መሆን አለበት።
*ሰው ወደ ልቡ የሚመጣውን ፍትወት እና ክፉ አሳብ ለመቋቋም ማልቀስ እና የእግዚአብሔርን ረዳትነት መለመን አለበት። ከዚያም በተረዳ ልቡና ሆኖ ከጸለየ ፈተናው ይታገሥለታል።
አባ መጣዕ
*ሰው ወደ እግዚአብሔር በቀረበ ቍጥር የራሱ ኃጢአት ይታየዋል።
*ልጅ እያለሁ አንደ ቀን መልካም ነገር አደርግ ይሆናል ብዬ ለራሴ እነግረው ነበር።እነሆ ሸመገልኩ እስከ አሁን መልካም የሚባል ነገር አላደረግሁም።
*አንድ አባት ወንድሙን ከራሱ አብልጦ ሲያመሰግን ስትሰማ እርሱ ራሱ ከትልቅ መዓርግ መድረሱን ተረዳ። ፍጹምነት ማለት ባልንጀራን ከራስ በላይ ማክበር ነውና።
*እግዚአብሔር የሚጸጸት ልቡና እና ትሑት ሰብእና እንዲሰጥህ ጸልይ፤ በደልህን አትዘንጋ፤ በሌሎች ላይ መፍረዱን ትተህ ራስህን የሁሉም የበታች አድርገህ ቍጠር።

የመነኩሴው ፈሊጥ
መጾም ያቃተውን ሰው ጹም፣ መመጽወት የተሳነውን መጽውት፣ መራመድ የማይችለውን ሩጥ የሚሉ መካሪዎች ብዙ ናቸው፡፡ መራመድ የማይችል እንዴት መሮጥ እንዳለበት ከማሳየት ይልቅ ቀንበር ማክበድ ጠባያችን ሆኗል፡፡ ይህ የሚያሳየው ቃሉ እንጂ ተግባሩ የተለየን መሆኑን ነው፡፡ በተግባር መግለጥ ብንችል ኖሮ፣ ማገዝ ቢያቅተን እናሯሩጠውና ሰውነቱ ሞቆ ተጋድሎ ሲጀምር እናፈገፍግ ነበር፡፡ እኛ ግን ልምድ የሌለውን ሁሉ ተሸከም ማለት ይቀለናል፡፡ ከባለ ግመሉ ከአባ ቆሪር ምክር ለመመጽወት የሄደ ክርስቲያን ግመሉ ከሚችለው በላይ ስለጫነው አንተ አቅም አጥተህ ምክር ለመቀበል መጥተህ ሳለ ግመሉን ካለ አቅሙ ለምን ጫንከው ተብሏል፡፡
ከአቅማቸው በላይ ተሸክመው የከበዳቸውን ሰዎች በማገዝ ሸክሙ ሳይከብዳቸው፣ ከክርስቲያናዊ ተጋድሎ ሳያፈገፍጉ በእምነት እንዲኖሩ ማገዝ ከዘመናችን የሃይማኖት ሰዎች የሚጠበቅ መሆኑን ለማስታወስ የአባ ዳንኤልን ፈሊጥ በአብነት እጠቅሰዋለሁ፡፡ አንድ አባ ዳንኤል የሚባል መነኩሴ ነበር፡፡ የደከመ ባገኝ አግዛለሁ እያለ በጨረቃ ከበዓቱ ወጥቶ ገዳማውያን በሚገኙበት በረሃ ይዞር ነበር፡፡
በአንድ ወቅት የማትሠራው ኃጢአት ያልነበር፣ ከጽድቅ ተግባር የማትተዋወቅ ሴት አገኘ፡፡ አባ ዳንኤልም ሴቲቱን ወደ ሴቶች ገዳም ወስዶ ልብላ ካለች ትብላ፣ ልተኛ ካለች ትተኛ፣ የፈቀደችውን ሁሉ ታድርግ፣ የገዳሙ ሕግ አይፈቅድም በማለት ቀንበር አንዳታከብዱባት ብሎ ለእመምኔቷ አስረክቧት ሔደ፡፡ እመምኔቷም እንደታዘዘችው አደረገች፡፡ ሴቲቱ በፈለገች ጊዜ ትበላለች፣ ስትፈልግ ትተኛለች፡፡ ያሰኛትን ታደርጋለች፡፡ ግን ደስታ የላትም፤ አብረዋት የሚኖሩት መነኮሳት ቤተ ክርስቲያን አድረው፣ በሥራ ተጠምደው ሲኖሩ ተመለከተች፡፡ እሷ በልታ ይርባታል፡፡ እነሱ ሳይበሉ አይራቡም፣ እሷ ተኝታ ይደክማታል፣ እነሱ ቆመው ውለው፣ ቆመው አድረው ድካም አያውቁም፡፡ ቀስ በቀስ መገረም፣ ከዚያም በሕይወታቸው መቅናት ጀመረች፡፡
ምግብ ሲያቀርቡላት እስከ ሦስት ሰዓት ልቆይ ማለት ጸሎት አድርጋ መብላት ተለማመደች፡፡ ቆየችና እስከ ስድስት ልቆይ አለቻቸው ከዚያም እስከ ዘጠኝ፣ ከዚያም በ24 ሰዓት አንድ ጊዜ መመገብ ጀመረች፡፡ ከዚያም ከሳምንት አንድ ቀን ብቻ መቅመስ በመጨረሻም በዓቷን ዘግታ በሦስት ሳምንትም፣ በወርም በሕይወት ለመቆየት ያህል መቅመስ ደረሰች እንዲህ ድክመታችን ታግሠው ለክብር የሚያበቁን ባለ ፈሊጥ መምህራን ማግኘት ለዚህ ዘመን እንዛዝላ ተሸካሚ ከዕንቊ የበለጠ ስጦታ ነው እላለሁ፡፡

🕯ጉባኤ ትርጓሜ ሊቃውንት🕯
🕯የሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ
ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችን ከባረከችው በኋላ ምስጋናውን የጀመረው #“ፈቀደ እግዚእ…” ብሎ ነው፡፡
፩. በመቅድመ ወንጌል “ወአልቦቱ ካልእ ሕሊና ዘንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢያቱ - በኃጢአቱ ከማዘን፣ ከማልቀስ በቀር ሌላ ግዳጅ አልነበረውም” እንዲል ጌታ ፭ ሺህ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ ያዝን ይተክዝ የነበረ አዳምን ነጻ ያደርገው (ያድነው) ዘንድ ወደደ፡፡ ምድራዊ ንጉሥ የተጣላውን አሽከር “ሰናፊልህን (ልብስህን) አትታጠቅ፤ እንዲህ ካለ ቦታም አትውጣ” ብሎ ወስኖ ያግዘዋል፡፡ በታረቀው ጊዜ ግን ርስቱን፣ ጉልበቱን፣ ቤቱን፣ ንብረቱን እንደሚመልስለት ኹሉ ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርም “ጥንቱንም መሬት ነህና ወደ መሬት ተመለስ” /ዘፍ.፫፡፲፱/ ብሎ ፈርዶበት የነበረ አዳምን ይቅር ብሎ ወደ ቀደመ ቦታው ወደ ገነት፣ ወደ ቀደመ ክብሩ ወደ ልጅነት ይመልሰው ዘንድ ወደደ /ሉቃ.፳፫፡፵፫/፡፡
🪔ሊቁ (ቅዱስ ኤፍሬም) በኦሪ. ዘፍ ፫፥፱ ያለውን ኃይለ ቃል ሲተረጕምም እንዲህ ይላል፡- “ቸር ወዳጅ የኾነው እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን ወዲያው እንደተሳሳቱ ፍርዱን አላስተላለፈባቸውም፤ ታገሣቸው እንጂ፡፡ ይኸውም ምኅረት ቸርነቱን ይለምኑት ዘንድ ነው፡፡ እነርሱ ግን አልለመኑትም፡፡ እግዚአብሔርም ምንም ሳይናገራቸው በገነት ውስጥ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱን ቀጠለ፡፡ አዳምና ሔዋን ግን አሁንም አልመለስ አሉ፡፡ በመጨረሻም አምላክ ድምፁን ማሰማት ጀመር፡፡ ‘አዳምን ወዴት ነህ?’ ይላቸው ጀመር፡፡ አስቀድሞ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱ መንገድ ጠራጊው ዮሐንስን እንደሚልክላቸው፣ ቀጥሎ ድምፅ አሰምቶ ወዴት ነህ ብሎ መፈለጉም ወልደ እግዚአብሔር ራሱ በተዋሕዶ ፍጹም ሰው ኾኖ ሊያድናቸው እንደ ፈቀደ ያጠይቃል” ይላል /St. Ephrem the Syrian, Commentary on Genesis/፡፡
🪔ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ኦሪት ዘልደትን በተረጐመበት በ፲፯ኛው ድርሳኑ ላይ፡- “በዚህ ንግግሩ የእግዚአብሔር ከአእምሮ የሚያልፈውን ፍቅሩን እንመለከታለን፡፡ አንድ አባት ልጁ የማይረባውን ነገር በማድረግ ከክብሩ ቢዋረድም አባቱ እጅግ እንዲወደውና ወደ ቀደመ ክብሩ ይመልሰው ዘንድ እንዲደክም፤ እግዚአብሔርም ከሰው ልጆች ጋር ይህን የመሰለ ፍቅር ሲያሳይ እናስተውላለን፡፡ አንድ ሐኪም ወደ ታማሚው አልጋ ጠጋ ብሎ በሽተኛውን እንዲጠይቀውና አስፈላጊውን ኹሉ እንደሚያደርግለት፣ ሰው ወዳጁ እግዚአብሔርም ወደ አዳም ጠጋ ብሎ ሲያነጋግረው እንመለከታለን” ይላል፡፡
ዳግመኛም #በሌላ አንቀጽ “አዳም ሆይ ወዴት ነህ” ማለቱ፣ ለአቅርቦት መኾኑን ሲገልጥ፡- “አዳም ሆይ! ምን ኾንክብኝ? በመልካም ቦታ አስቀምጬህ ነበር፤ አሁን ግን ቦታህ ተለወጠብኝ፡፡ ብርሃን ተጐናጽፈህ ነበር፤ አሁን ግን ጨለማ ውስጥ አይሃለሁ፡፡ ልጄ! ወዴት ነህ? ይህ ኹሉ እንደምን ደረሰብህ? በአንተ ውስጥ ያኖርኩት መልኬ ማን አበላሸብኝ? በዚህ ያህል ፍጥነት የጸጋ ልብስህን ገፎ የጽልመት ልብስ ያከናነበህ ማን ነው? ውዴ! ባለጸጋ አድርጌ ፈጥሬህ አልነበረምን? ታድያ አሁን ድኽነት ውስጥ የከተተህ ማን ነው? ያን የግርማ ልብስህን ሰርቆ ዕራቆትህ ትኾን ዘንድ ያደረገህ ማን ነው? እኮ የጸጋ ልብስህን እንድታጣ ያደረገህ ማን ነው? ይህን የመሰለ ቅጽበታዊ መለወጥ ከወዴት መጣብህ? የከበረ ዕንቁህን እንድትጥል ያደረገህ ምን ቢገጥምህ ነው? አክብሮ በተወደደ ቦታ ካስቀመጠህና ኹል ጊዜ በስስት ዐይን ሲያነጋግርህ ከነበረው አምላክህ ተደብቀህ እንድትሸሸግ ያደረገህ ምንድነው? ማንም የወቀሰህ ሳይኖር፣ እንዲህ እንዲህ አድርገህ በድለሃል ብሎ የመሰከረብህ ሳይኖር ይህን ያህል በፍርሐት መናጥ ከወዴት አገኘህ?” ይላል /Daily Readings of St. John Chrysostom/፡፡
🪔ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ሆይ! ፭ ሺሕ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ የነበረ አዳምን ነፃ ካደረገው ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡ #“ቅድስት” ማለቱ ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት ልዩ ሲል ነው፡፡ ይኸውም፡-
· ሌሎች ሴቶች ከነቢብ ከገቢር ቢነጹ ከሐልዮ አይነጹም፡፡ እሷ ግን የዕንቆራው #ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ቴዎዶጦስ “ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል በሕሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ- ከፈጠራት ጀምሮ በምንም በምን (በሕሊናዋም በሥጋዋም) ከድንግልናዋ አልተለወጠችም” /ሃይ.አበ.፶፫፡፳፪/ እንዲል ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከሐልዮ ኃጢአት ንጽሕት ናትና፡፡
· 🪔ጽንዕትም አለ፡፡ ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፤ ኋላ ተፈትሖ አለባቸው፡፡ እሷ ግን ቅድመ ፀኒስ ጊዜ ፀኒስ፤ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ ጽንዕት (ወትረ ድንግል) ናትና፡፡
· 🪔ክብርትም አለ፡፡ ሌሎችን ሴቶች ብናከብቸው ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን፣ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንትን ወለዱ ብለን ነው፡፡ እሷን ግን ወላዲተ አምላክ ወልዳልናለች ብለን ነውና፡፡
· 🪔ልዩም አለ፡፡ እናትነትን ከድንግልና፣ አገልጋይነትን ከእናትነት፣ ወተትን ከድንግልና ጋር አስተባብራ የተገኘች፤ በድንግልናም እያለች ከጡቶቿ ወተት ተገኝተው በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግብ መጋቤ ፍጥረታት አምላክን የወለደች፤ እሳታውያን የሚኾኑ ኪሩቤል ሱራፌልም በፍርሐት በረዐድ ኹነው ዙፋኑን የሚሸከሙት እሳተ መለኮት ጌታን ፱ ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመች፣ በክንዷ የታቀፈች፣ በዠርባዋ ያዘለች ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችምና፡፡
🪔“ለምኚልን” ሲልም ልክ በዚህ ምድር እንደነበረው ዓይነት ልመና ከዚያ በኋላ ኖሮባት አይደለም፡፡ ስንኳን በሷና በሌሎችም የለባቸውም፡፡ በቀደመ ልመናዋ የምታስምር ስለ ኾነ እንዲህ አለ እንጂ፡፡ ይኸውም በቃል ኪዳኗ ማለት ነው፡፡ አንድም በቁሙ ይተረጐማል፡፡ ማዘከር (ማሳሰብ) አለና፡፡
🪔“ሰአሊ ለነ ቅድስት” የሚለው ቅዱስ ኤፍሬም የተናገረው አይደለም፡፡ “ታድያ ይህን የጨመረው ማን ነው?” በሚለው ላይም ኹለት ዓይነት አመለካከለት አለ፡፡ “ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መከፈያ ተናግሮታል” የሚሉ አሉ፤ “የኋላ ሊቃውንት ተናግረውታል” የሚሉም አሉ፡፡
ሊንኩን ተጭነው ቀጣዩን ያንብቡ

💡የማክሰኞ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓ
ሜ💡
🪔ለምስጋና ኹለተኛ፣ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን በሚኾን በዚህ ቀንም እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኾናም፡- “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም” ትለዋለች፡፡ እርሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ይቆማል፡፡ ክርክር በዕለተ ሰኑይ አልቋልና “ባርክኒ” ብሎ ተባርኮ “አክሊለ ምክሕነ” ብሎ ምስጋናውን ይጀምራል፡፡
፩. ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት ቢባል የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለውም /፩ኛሳሙ.፲፮፥፲፫/፡፡ ኢያሱ ምንም የስሙ ትርጓሜ መድኃኒት ቢኾንም የደኅንነታችን መጀመሪያ መኾን አልተቻለውም፡፡ ኤልያስም ምንም ንጹሕ፣ ድንግል ቢኾንም የንጽሕናችን መሠረት መኾን አልተቻለውም፡፡ የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችን መጀመሪያ፣ የንጽሕናችን መሠረት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የመመኪያችን ዘውድ “አክሊለ ሰማዕት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የደኅንነታችን መጀመርያ “ጥንተ ሕይወት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የንጽሕናችን መጀመርያም ኹሉ በእጁ የተጨበጠ፣ ዓለምንም በመዳፉ የያዘ፤ በጠፈር ላይ የሚቀመጥ ፣ ዳግመኛም መሠረቱን ከታች የሚሸከም “መሠረተ ዓለም” የሚባል ጌታችን ነው /ቅዳ.ማር. ቁ.፶፩/፡፡ እርሱም አካላዊ ቃልን በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን፡፡ እኛን ስለማዳን ሰው ኾነ፤ ሰውም ከኾነ በኋላ ግን ፍጹም አምላክ ነው፡፡ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ እንደ ወለደችው ኹሉ እርሱም አምላክነቱ ሳይለወጥ ሰው ኾነ፡፡ እርሷ “ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም)” ስትባል እንደምትኖር ኹሉ እርሱም “አምላክ ወሰብእ (ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው)” ሲባል ይኖራል /ሃይ.አበ.፷፯፡፯/፡፡ ተፈትሖ ሳያገኛት (ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ) እንደምን እንደወለደችው ግን የማይመረመር አንድም ሊነገር የማይችል፣ ከኅሊናት ኹሉ የሚያልፍ ድንቅ ነው፡፡
*በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፪. “ቃል ሥጋ ኾነ” እንዲል በእርሱ ፈቃድ /ዮሐ.፩፡፲፬/፣ “ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና” እንዲል በአባቱ ፈቃድ /ዮሐ.፫፡፲፮/፣ “በመንፈስ ቅዱስ በኀይልም እንደ ቀባው” እንዲልም /ሐዋ.፲፡፴፰/ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሰው ኾኖ አዳነን፡፡ ሊቁ እንዲህ ማለቱ “ወልድ ያለ ፈቃዱ ሰው ኾነ” የሚሉ መናፍቃን ስላሉ ነው፡፡ ሌሎች ሊቃውንትም፡- “የእግዚአብሔር ልጅ ያለ ፈቃዱ ሰው እንደ ኾነ የሚያምን፤ የሚያስተምር፤ ወይም የአብ ፈቃድ ሌላ ነው፤ የወልድ ፈቃድ ሌላ ነው፤ የመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ሌላ ነው የሚል ቢኖር፤ ፈቃዳቸው አንድ፤ መንግሥታቸውም አንድ እንደኾነ የማያምን ሰው ቢኖር ውጉዝ ይኹን” ብለው አስተምረዋል /ሃይ.አበ.፻፳፫፡፪/፡፡
🪔 በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ፍጽምት የምትኾኚ እመቤታችን ሆይ! በድንግልና ጸንተሽ ብትገኚ ላንቺ የተሰጠሸ ጸጋ ፍጹም ነው፡፡ እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ባሕርይ ቢኾን አንድም በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሸልና ለአንቺ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ ይህ ከቃላት በላይ የሚያልፈው ባለሟልነቷ ቅዱስ ባስልዮስ ከሌሎች ቅዱሳን ጋር እያነጻጻረ ሲያብራራው፡- “የዚህ ዓለም ነገር ኹሉ አይመጥናትምና የሚመጥናትን ምን ዓይነት ምስጋና እናቅርብላት? ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን ሲናገር ዓለም አልተገባቸውም /ዕብ.፲፩፡፴፰/ ካላቸው ከከዋክብት በላይ ኾና እንደምታበራው ፀሐይ ለኾነችው ለአምላክ እናትማ ምን ልንል እንችል ይኾን?... ምን ምሥጢር እንደተከናወነ ተመልከት፤ ኅሊናን አእምሮን የሚያልፍ ነገር እንደኾነም አስተውል፡፡ ታድያ የአምላክ እናት ታላቅነት እንደምን ኹሉም ሰው አይናገር? ማንስ ነው ከቅዱሳን ኹሉ በላይ እንደኾነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፣ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈጸመለት፣ ጴጥሮስ በጥላው ካዳነ /ሐዋ.፭፡፲፭/፣ የጳውሎስ የልብሱ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ /ሐዋ.፲፱፡፲፩/ ለእናቱማ ምን ዐይነት ሥልጣንና ኀይል ተሰጥቷት ይኾን? በምን ዓይነትስ ሥጦታ አስጊጧት ይኾን? ጴጥሮስ፡- ክርስቶስ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ስላለው ብፁዕ ነህ ከተባለና የመንግሥተ ሰማያት ቁልፍ ከተሰጠው /ማቴ.፲፮፡፲፮-፲፱/ እርሷማ ከኹሉም ይልቅ እንዴት ብፅዕት አትኾን? /ሉቃ.፩፡፵፭/ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸከሙ ምርጥ ዕቃ ከተባለ /ሐዋ.፱፡፲፭/ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይኾን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች እርሷ ምን ዓይነት ልዩ ዕቃ ትኾን? … ነገር ግን ስለ እርሷ ብዙ እናገራለሁ ብዬ ስለ ክብሯ ጥቂት በመናገር ራሴን በኀፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለኁ፡፡ ስለዚህ ከአሁን ወዲህ የንግግሬን መልሕቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጫለሁ” ይላል /መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፣ ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፣ ገጽ ፺-፺፩ ይመልከቱ/፡፡
🪔 ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ፣ በላይዋ ዙፋን ተነጽፎባት በዚያ ላይ ንጉሥ ተቀምጦባት፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያያት የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ /ዘፍ.፳፰፡፲፰-፲፱/፡፡ መተርጕማኑ ይህ ምን ማለት እንደኾነ ሲያብራሩ፡- “ከምድር እስከ ሰማይ መድረሷ የልዕልናዋ፣ በላይዋ ላይ ዙፋን ተነጽፎባት ንጉሥም ተቀምጦባት ማየቱ ፱ ወር ከ፭ ቀን በማኅፀኗ ለመሸከሟ፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ማየቱ ደግሞ ጌታችን ከእመቤታችን ሰው ከመኾኑ አስቀድሞ ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ለማሳረግ አይወጡም አይወርዱም ነበር፤ ጌታችን ከእመቤታችን ሰው ከኾነ በኋላ ግን ለተልእኮ የሚወጡ የሚወርዱ ኾነዋልና ሲል ነው” ይላሉ /ሉቃ.፪፡፲፬፣ ሐዋ.፲፡፫-፬፣ የኦሪት ዘልደትን ትርጓሜ ይመልከቱ/፡፡
🪔 ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በአምሳለ ንጉሥ ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
ሊንኩን ተጭነው የቀጣዩን ዕለት ያንብቡ
👇 👇👇
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
👆👆👆
🕯JOIN 🕯

#በጸሎት_ጊዜ_ምን_እናድርግ?
#በጸሎት_ጊዜ_ምን_እያልን_እንጸልይ?
👉ዓምድ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ መቆም። (መዝ. 5:3)
👉ወገብን መታጠቅ ልብስን ዝቅ አድርጎ ማደግደግ ነው። (ሉቃ. 12:35 ፍት. መን አንቀጽ 14)
👉በጸሎት ጊዜ ፊትን ወደ ምስራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ ወደ ግራና ወደ ቀኝ ወደ ሌላም አለማለት በሰፊሐ እድ በሰቂለ ሕሊና ሁኖ መጸለይ ይገባል። (መዝ. 133:2፤ ዮሐ. 11:41)
👉ጸሎት ሲጀመርና ሲፈጸም አመልካች ጣትን ከሌሎች ጣቶች ጋር አመሳቅሎ በትእምርተ መስቀል አምሳል በጣት ማማተብ ነው። በዚህም የመድኃኔዓለምን መከራውን ማሰብ።
🙏የሚጸልይ ሰው በትህትናና በጸጥታ ሁኖ ለሌላ ሰው እንዳይሰማ ለራሱ ጆሮ ብቻ እንዲሰማ አድርጎ ኃጢአቱን እያሰበ መጸለይ ይገባዋል። ይህም የሚያደርገው ስለ አለፈው ኃጢአቱና በደሉ ነው። (1ኛ ሳሙ. 1:3)
🙏የሚጸልይ ሰው በጥቡዕ ልብ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገራል። አሳቡን በእግዚአብሔር ላይ ይጥላል። የዓለምን አሳብ ሁሉ ይተዋል።
🙏የሚጸልይ ሰው ሲያማትብ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አዐትብ ገጽየ ወኵለንታየ በትእምርተ መስቀል" እያለ ነው። ሁለተኛም "እግዚኦ መሐረነ እግዚኦ መሐከነ እግዚኦ ተሣሃለነ ወባርከነ አሜን" እያለ ያማትባል። ሦስተኛም "ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን እግዚኦ ረስየነ ድልዋነ ከመንበል በአኮቴት አቡነ ዘበሰማያት" የሚለውን ጸሎት 3 ጊዜ እየደገመና እየሰገደ በማማተብ በጸሎት መጀመርያና መጨረሻ ጊዜ ማድረግ አለበት። #እንዲሁም_መስቀልን_ከሚያነሳ_ቃል_ሲደርስ_ማማተብ_ስግደትንም_ከሚያነሳ_ቃል_ሲደርስ_መስገድ_ይገባዋል።
#የጸሎቱ_ቅደም_ተከተል_መጀመርያ_አቡነ_ዘበሰማያት_ሁለተኛ_መዝሙረ_ዳዊት_ውዳሴ_ማርያምና_ሌሎችም_ቀጥሎ_አቡነ_ዘበሰማያት_ጸሎተ_እግዚእትነ_ማርያም_ጸሎተ_ሃይማኖት_በመጨረሻም_አቡነ_ዘበሰማያት_ኬርያላይሶን_41_ጊዜ ይባላል።
-ሲጸልይ ማዘን ማልቀስ ይገባዋል። ሲያለቅስም በደሉንና ኃጢአቱን እያሰበ ለያንዳንዱ በደል ዕንባን ማፍሰስ ነው።
-የሚጸልይ ሰው በጸሎት ላይ አቋርጦ ከማንም ሰው ጋር ፈጽሞ መነጋገር የለበትም። ጸሎቱን ለማቋረጥ ችግር ቢገጥመው ግን በአቡነ ዘበሰማያት አሥሮ ንግግሩን ሲፈጽም ከአቋረጠበት ተነስቶ ጸሎቱን ሊጸልይ ይገባል። (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስርዓተ አምልኮና የውጪ ግንኙነት ገጽ 81፤ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ገጽ. 28-29: ሊቀ ካሕናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ

በግብፅ በረሀ አባ መቃርስ በሚኖሩበት ገዳም የሚኖር 1 መነኩሴ ነበር ያም መነኩሴ ሴቶችን ወደ ገዳሙ ያመጣ ነበር ይህን ተግባሩን ያዩ መነኮሳትም ወደ አባ መቃርስ በመሄድ ያደረገውን ነገር ይነግሯቸዋል አባ መቃርስም ልጄማ ይሄንን አያደርግም ይላሉ ። መነኮሳቱም ተበሳጭተው ይሄዳሉ ልጁም በሌላ ጊዜ ሴት ያስገባል እነዛ መነኮሳትም በድጋሚ ይሄዱ እና ለአባ መቃርስ ይነግሯቸዋል አባ መቃርስም አይ ልጄማ ይሄን አያደርግም ይላሉ በድጋሚ መነኮሳቱ ተበሳጭተው ይሄዱ እና ምን እናድርግ ? ብለው ይማከራሉ ከዛም በቃ ካሁን ቡሃላ ልክ ሴት ይዞ ሲመጣ እንነግራቸዋለን እስካሁን ያላመኑን እኛ ሴቶቹን ከሸኘ ቡሃላ ስለምንነግራቸው ነው በማለት ተማከሩ ። ያ መነኩሴም እንደ ለመደው ልክ ሌላ ሴት ይዞ ሲገባ መነኮሳቱ በሩጫ ሄደው ለአባ መቃርስ ይነግሯቸዋልአባ መቃርስም እንደ ተለመደው ልጄማ ይሄንን አያደርግም አሏቸው ። መነኮሳቱም አባታችን ልጅቷ አልወጣችም ኑ ወደ ባዕቱ እንሂድ እዛው እንይዛቸዋለን ብለው ወደ ባዕቱ መሄድ ጀመሩ መነኩሴውም ከሩቁ ሲመጡ አይቷቸው ደነገጠ ወይኔ ዛሬ ጉዴ ወጣ ብሎ ተጨነቀ ቅርጫቱንም ገልብጦ ልጅቷን በቅርጫት ከደናትአባ መቃርስም የበቁ አባት ነበሩና ባሉበት ሆነው የልጁን ድርጊት አወቁ ። ልክ እንደ ደረሱም ወደ ባዕቱ ሲገቡ አባ መቃርስ ቅርጫቱ ላይ ተቀመጡና በሉ ገብታለች ያላቹኝን ልጅ ፈልጋቹ አውጡልኝ አሉ ። መነኮሳቱ ቢፈልጉ ቢፈልጉ አጧት ወደ አባ መቃርስም ቀረብ ብለው አባታችን ይቅርታ እሱ ንፁህ ነው እኛ ነን ያጠፋነው አሉ አባ መቃርስም እኔኮ መጀመሪያም ነግሬያቹ ነበር ልጄ ንፁህ ነውያ መነኩሴም ደስ አለው ። አባ መቃርስም በል ና ወደ በዓቴ ሸኘኝ ብለውት መንገድ ላይ ወግ ይጀምሩለት እና ምንኩስና እንዴት ነው ይሉታል እሱም ጥሩ ነው ይላቸዋል ። እሳቸውም ያደረገውን ሁሉ እንደሚያውቁ እና ምን ማድረግም እንዳለበት መክረው ገስፀው ይልኩታል መነኩሴውም ልቡ ተነክቶ ከዛ ቡሃላ ታላቅ ተጋዳይ ሆነ ልጅቷም መነኮሰችእኛስ ዛሬ እንዴት ነው የሰዎችን እንከን ስናይ እንዳባ መቃርስ እንሸፍናለን ወይስ እንደ መነኩሴዎች ሮጠን ሄደን ለሌላ ሰው አቤት የእከሌ ጉድ በስምዓም ሲያዩት ሲያዩዋት ሰው ትመስላለች ሰው ይመስላል ... እንዲ እንዲ አርጎ እያልን የሰውን ገመና እንዘረዝራለን ? የሰውን ድካም ለሌላ ሰው አሳልፎ ከመንገር በፍቅር ቀርቦ ያንን ሰው ድካሙን ማገዝ የተሻለ ነው
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae