🌹ትዕቢተኛ አትሁን -- እንደ ሰናክሬም ትወድቃለህ ።
መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 2//19÷35//
🌹ዓለምን አትመልክት -- እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዐምድ ሆነህ ትቀራለህ ።
ዘፍጥረት //19÷ 22-23//
🌹ክፋ ባልንጅራን አትያዝ -- እንደ ሶምሶን በጠላት እጅ ትወድቃለህ።
መጽሐፈ ምሳሌ //16÷ 15//
🌹አትመኝ -- እንደ አዳም የዲብሎስ ባሪያ ትሆናለህ ።
ዘፍጥረት //3÷1-8//
🌹አትዘሙት -- እንደ ሰሎሞን አምላክህን አስረስቶ ጣዖትን እንድታመልክ ያደርግሃል ።
መጽሐፍ ነገሥት ካልዕ 1//11÷1-8 //
🌹ሥልጣንን አትውደድ -- እንደ አቤሴሎም በአባትህ ላይ ትነሣለህ ።
መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 2//15÷13-17 //
🌹ገንዘብን አትውደድ --እንደ ይሁዳ ጌታህን ያስክድሃል ።
ማቴዎስ ወንጌል //26÷14-16//
🌹አትቅና-- እንደ ቃየል ወንድምህን ትገላላህ ።
ዘፍጥረት // 4÷1//
🌹አትስከር-- አዕምሮ አሳጥቶ የማይገባ ሥራ ትሠራለህ ።
ዘፍጥረት //19÷30-38//
🌹በአባትህ አትሳቅ -- እንደ ካም ትረገማለህ ።
ዘፍጥረት //9÷20 -21//
🌹በሐሰት አትመስክር -- እንደ ሐማ ባዘጋጀኸው ጉድጓድ ትገባለህ ።
መጽሐፈ አስቴር//7÷1//
🙏💚❤💛

💵ዓሥራት
1፡- አሥራት ማለት ምን ማለት ነው?
- አሥራት ማለት ከአሥር አንድ በሚለው መገለጫነት ከመቶ አሥር፤ ከሺህ መቶ የሚሉትን ሁሉ የሚያመለክት ነው፡፡ ስለዚህ የሰውልጅ ፈጣሪ ከሰጠው ላይ ሩቡን ለአምላኩ ቀሪውን ለርሱ
መገልገያ ያደርግ ዘንድ በፈጣሪ በተሠራለት ሕግ መሰረት የሚፈጽመው ነው፡፡ ፈጣሪያችን ከሰው ልጅ አስራትን መቀበሉ የሚጠቀምበት ሆኖ አይደለም ነገርግን በመጀመሪያ ሀብታችን ይባረክልን ዘንድ ፤ የተሻለ ነገርን ሊሰጠን ፤ ለርሱ ያለንን ታማኝነት እና መውደድ ይገለጥ ዘንድ ነው፡፡ በቅዱስ ዮሐንስ
ወንጌል ላይ የምናገኛት ሳምራዊቷን ሴት ጌታችን ምድራዊ ውኃ ስጪኝ እኔም አንዴ ጠጥተውት ዳግመኛ የማያስጠማውን የዘለዓለም ሕይወት የሚያሰጠውን የሕይወትን ውኃ እሰጥሻለሁ እንዳለው ነው፡፡ (የቅ.ዮሐ.ወን4-1)
✞ አሥራት የሚወጣው ለማን ነው?
- አንዳንዶች አሥራትን ለንስሓ አባታቸው በቤተክርስቲያን ለሚሠራ ህንጻ ለማሠራት ለሰንበት ትምህርት ቤት ለማኅበር የአባልነት መዋጮ እንዲሆን ይሰጣሉ ይህ ግን ስህተት ነው፡፡
በመጀመሪያ አሥራት የሚወጣው ለማን ነው ለሚለው ለእግዚአብሔር ነው የሚለው መልስ ነው፡፡ ይኸውም ለቤተመቅደስ ለሚፈጸመው አገልግሎት ማለት ለመሥዋዕቱ ማቅረቢያ እንዲውል ነው የምንሰጠው፡፡ ካህናትም የእግዚአብሔር እንደራሴዎች ሆነው ከምዕመናን የሚመጣውን አሥራት ይቀበሉለታል ለመሥዋዕቱ የሚሆነውን ካቀረቡ በኋላ የቀረውን እነርሱ ይጠቀሙበታል ይኸውም የካህናቱ ርስታቸው አምላክ በመሆኑ ነው፡፡
ለምሳሌ በኦሪቱ ስንመለከት ታላቁ መሥፍን ኢያሱ እስራኤላውያንን እየመራ ርስት ከነዓን ካደረሳቸው በኋላ ለአሥራ አንዱ ነገድ ርስትን ከፍሎ ሲሰጣቸው የካህናት ነገድ ለሆነው ለሌዊ ነገድ ግን ለእነርሱ እና ለንብረቶቻቸው መኖሪያ ከሚሆን በቀር አርሰው ዘርተው እህል የሚያገኙበትን መሬትን አልሰጣቸውም ይህም የሆነበት ምክንያት ነገደ ሌዊ ለቤተመቅደስ አገልግሎት የተመረጡ እንደመሆናቸው ይህንን አገልግሎታቸውን ትተው ሌላ ሥራ በመሥራት ሕዝቡ ከአምላኩ ጋር የሚያገናኘው እንዳይታጣ እና የቤተመቅደስ አገልግሎት እንዳይስታጎል ነበር ስለዚህም አስራ አንዱ ነገዶች ለእግዚአብሔር ብለው የሚያመጡትን አሥራትን… ሌዋውያን ለእግዚአብሔር እንደራሴዎች እንደመሆናቸው ተቀብለው ለመሥዋዕቱ የሚገባው ካቀረቡ በኋላ የቀረውን ይወስዱት ነበር የካህናት ርስታቸው እግዚአብሔርን ነው የተባለውም ለዚህ ነው፡፡ አንባብያን አስቀድመን እንደገለጥነው ካህናት አሥራትን የሚያወጡ እንደሆነ የተገነዘባችሁ ይመስለናል ካህናት ከሕዝቡ አሥራትን ካስወጡ በኋላ እነርሱም የአሥራት አሥራትን ያወጣሉና፡፡ በአጠቃላይ አሥራትን ለፈጣሪ ነው የምንሰጠው ስንል በተዘዋዋሪ ለካህናት እንሰጣለን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከአሥራት አሥራት ካወጡ በኋላ የቀረውን የወር ደሞዝ እንዲሆናቸው ለሚከፈላቸው ካህናት በግል ለንስሓ አባት አሥራትን መስጠት አይገባም፡፡ ነገርግን ደሞዝ በሌለበት በተለይ በገጠር ባሉ አድባራትና ገዳማት ለሚያገለግሉ ካህናት ምዕመናን በግላቸው ለንስሓ አባታቸው ይሰጣሉ፡፡ ከአሥራት ውጨ የሆነ ስጦታን ግን ደሞዝተኛ ለሆነም ላልሆነም ለንስሓ አባት ሆነ ለማንኛም ካህን በግል መስጠት ይቻላል፡፡ ከዚህ በተረፈ ከላይ አሥራትን ለማህበር መርጃ ለሰንበት ት/ቤት የአባልነት መዋጮ በቤተክርሰቲያን ለሚሠሩ ሕንጻዎች ማሠሪያ እንዲሆን ለመስጠት ግድ የሚሆንበት አጋጣሚ ካለ ግን ከንስሐ አባት ጋር መመካር ይገባል፡፡
✞ አሥራትን የምንሰጠው ለአጥቢያ ቤተክርስቲያን ነው ወይስ ለወደድነው ሌላ ገዳም ነው ?
☞ ሀብተ ወልድ (ታላቅ ሀብት የሆነውን የእግዚአብሔር ልጅነት) ላገኘንበት፤ ስመ ክርስትና ለተሰየምንበት ወይም በአርባ በሰማንያ ዕለትታችን ለተጠመቅንበት አድባር ወይም ገዳም እንሰጣለን፡፡
☞ አገልግሎትን ለምናገኝበት በአጥቢያችን ላለ ቤተክርስቲያን እንሰጣለን፡፡ በተለይ በተለያየ ምክንያት የልጅነት ጥምቀትን ካገኘንበት ቤተክርስቲያን ስንርቅ (መኖሪያችንን በመቀየራችን ርቆን አገልግሎትን በሌላ ቤተክርስቲያ ልናደርግ ከቻልን እኛን እያገለገሉ ያሉ ካህናት በምንገለገልበት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ያሉ አገልጋዮች በመሆናቸው አሥራታችንን ለዚህ ቤተከርስቲያን እንሰጣለን፡፡)
☞ የንስሓ አባታችን ላሉበት ቤተክርስቲያን እንሰጣለን፡፡ ከዚህ ውጪ ግን ተአምር ተደርጎልኛል፣ ጸሎቴ ተሰምቶበታል፣ እኔ ካለሁበት አጥቢያ ይልቅ ካለበት ችግር የተነሳ አገልግሎትን መስጠት ስለማይችል ለገጠር ለተቸገሩ አድባራት እና ገዳማት መሥጠት ይሻለኛል ያለ ግን አስቀድሞ ለንስሓ አባቱን አሳውቆ ፈቃድንም ካገኘ በኋላ መሥጠት ይችላል፡፡ ይህ ዓይነቱ በጎ ምግባር የሚበረታታ ነው ሆኖም ግን አንድ ሰው ብቻ በግሉ ለተቸገሩ ቤተክርስቲያናት በመሥጠት የሚያመጣው ለውጥ እንብዛም በመሆኑ በማኅበር በኩል በመሰባሰብ ሁሉም የንስሐ አባታቸውን ፈቃድ በማግኘት አሥራታቸውን ቢሰጡ ጥሩ ነው፡፡
🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
☞ የእናንተ አስተያየት ብዙ እንድንሰራ ይጠቅመናልና አስተያየታችሁን አትንፈጉን
ለጥያቄ እና አስተያየት
@gibi_gubae
@gibi_gubae
#ይሄንን ጽሑፍ ሌሎች ክርስቲያን እህት ወንድሞቻጅን እንዲደርስ👉 Share ያድርጉ...

#ውሻ_ነኝ +
ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ ባለ ብዙ ታሪክ ሊቀ ጳጳስ ነበር፡፡
በእርሱ ዘመን ታዲያ ብዙ ሰዎች ወደ ክርስትና እየተመለሱ
ይጠመቁ ነበር፡፡ ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ታዲያ አንዳንዶች
የማትደገመዋን አንዲት ጥምቀት እንደ ጠበል ደጋግመው
መጠመቅ ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ለዚህ መላ አበጀ፡፡ አንድ ሰው
ከተጠመቀ በኋላ #በአንገቱ_ላይ_የማይወልቅ_ክር_እንዲያስር
አደረገ፡፡ በሒደትም ይህን ክር ያሰረ ሰው የተጠመቀ ክርስቲያን
መሆኑ ምልክት ሆነ የኋላ ሊቃውንትም ይህንን የማዕተብ ሥርዓት
ከኦሪት እስከ ሐዲስ አጣቅሰው አስፋፍተው አስተማሩበት፡፡
# ያዕቆብ_በክርስቲያኖች_ላይ_ይህንን_ክር_በማሰሩ_ታዲያ_
የክርስትና_ተቃራኒዎች_ዘበቱበት
‘ብለህ ብለህ ደግሞ እንደ ውሻ በየሰዉ አንገት ላይ ክር ማሰር
ጀመርህ?’ ብለው ተሳለቁበት
ቅዱስ ያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ ፦
‘ውሻ ለጌታው ታማኝ ነው ፤ እኔ ለክርስቶስ ታማኝ ውሻው ነኝ’
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ ባለ ብዙ ታሪክ ሊቀ ጳጳስ ነበር፡፡
በእርሱ ዘመን ታዲያ ብዙ ሰዎች ወደ ክርስትና እየተመለሱ
ይጠመቁ ነበር፡፡ ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ታዲያ አንዳንዶች
የማትደገመዋን አንዲት ጥምቀት እንደ ጠበል ደጋግመው
መጠመቅ ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ለዚህ መላ አበጀ፡፡ አንድ ሰው
ከተጠመቀ በኋላ #በአንገቱ_ላይ_የማይወልቅ_ክር_እንዲያስር
አደረገ፡፡ በሒደትም ይህን ክር ያሰረ ሰው የተጠመቀ ክርስቲያን
መሆኑ ምልክት ሆነ የኋላ ሊቃውንትም ይህንን የማዕተብ ሥርዓት
ከኦሪት እስከ ሐዲስ አጣቅሰው አስፋፍተው አስተማሩበት፡፡
# ያዕቆብ_በክርስቲያኖች_ላይ_ይህንን_ክር_በማሰሩ_ታዲያ_
የክርስትና_ተቃራኒዎች_ዘበቱበት
‘ብለህ ብለህ ደግሞ እንደ ውሻ በየሰዉ አንገት ላይ ክር ማሰር
ጀመርህ?’ ብለው ተሳለቁበት
ቅዱስ ያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ ፦
‘ውሻ ለጌታው ታማኝ ነው ፤ እኔ ለክርስቶስ ታማኝ ውሻው ነኝ’
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
🌻🕯#ጉባኤ፦መንፈሳዊ አበረታች መድኃኒት🕯🌻
🌼💡ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ💡🌼
🌻💡ወዳጄ አንተ ወደዚህች ምድር የመጣህ አንተን የሚመስል ብቸኛው
ሰው ነህ:: የማያልቅበት ፈጣሪ የአንተን ዓይነት ሰው ፈጥሮ
አያውቅም ድጋሚም አይፈጥርም:: ምድርም የአንተ ዓይነት ሰው
አይታ አታውቅም:: ዕድሜ የተሠጠህ ለአንተ ብቻ የተሠጠህን
ነገር አበርክተህ እንድትሔድ ነው:: በአንተ ብቻ የሚፈታ ችግር
በአንተ ብቻ የሚፈጠር ብዙ መፍትሔ አለ::
ሌሎች ከአንተ በሀብት በእውቀት በሥልጣን ወዘተ በልጠው
ልታይ ትችላለህ:: ሕይወት ፍትሐዊ አይደለችም:: ፈጣሪ ያደላል
ወይ ልትል ትችላለህ::
ከሀብታሙም ከአዋቂውም ከኃያሉም እኩል ለአንተ የተሠጠህ
ፍትሐዊ ሥጦታ ግን ጊዜ ነው:: ሁሉም ቀንና ሌሊቱ ሃያ አራት
ሰዓት ነው:: በብራቸው ሰዓት ያስጨመሩ የሉም:: አጠቃቀምህ
ነው እንጂ ጊዜ በእኩልነት ተሠጥቶሃል::
ዐዲስ ዓመት ሊገባ ነው:: ፀሐይ እያየችን ስታልፍ ሌላ ዓመት
ሆናት:: 2012 አይቻልም እንጂ በድንጋይ ፈንክተን ብንሸኘው ደስ
የሚለን ዓይነት ከባድ ዓመት ነበር:: አሁን ሌላ በቸርነቱ ሌላ
ዘመንን አቀዳጀን:: ፈጣሪ የሠጠን ያተጻፈበት አዲስ ደብተር ነው::
ብዕሩ እጃችን ላይ ነው:: ምን እንጽፍበት ይሆን? ካለፈው ደብተር የቀጠለ ታሪክ እንጽፍ ይሆን? ወይስ አዲስ ነገር?
🌻መልካም አዲስ ዓመት🌻
🌼💡ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብን ለመፍጠር
👇👇👇👇
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae🌻
🌻🕯🕯🌻

+ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል +
የመላእክት አንድነት ኹሉ ያመሰግኑሻል በንፅህና ሥርዓት እነርሱን ትመስያለሽና።
የነቢያት አንድነት ያመሰግኑሻል ተስፋ ትንቢታቸው እውን ሆኖ በአንቺ ተፈፅሟልና።
የሐዋርያት አንድነት ሁሉ ያመሰግኑሻል የተወደደው ልጅሽ ወንድሞች አድርጓቸዋልና።
ድለ መልካሞች ሰማዕታት ያመሰግኑሻል የልጅሽ
መከራ አንድነት በሥጋቸው ተሸክመዋልና
ደናግልና መነኮሳት ያመሰግኑሻል ሕይወታቸውን ለንፅሕናሽ ምሳሌ ብፅዕት አድርገዋልና።
ሊቀ ጳጳሳትና ኢጲስ ቆጶሳት ያመሰግኑሻል ለማዕረገ
ክህነታቸው ልጅሽ አለቃ ሆኗልና።
አንባቢዎችና መዘምራን ያመሰግኑሻል ልጅሽን ለማመስገን እንደ ወርቅ ጸናጽሎች በቤተ መቅደስ ይጮኻሉና።
የክርስቲያን አንድነት ኹላቸው ያመሰግኑሻል ከልጅሽ
ጎን በፈሰሰው ውሃ የጥምቀት መጎናጸፊያን ለብሰዋልና።
(አርጋኖን - ሊቁ አባ ጊዮርጊስ)

+ የሠላሳ ሦስት ዓመታት ዕንባ +
የዮሐንስ ወንጌል ‹ቃል ሥጋ ሆነ በእኛም አደረ› ብሎ ስለ አምላክ ሰው መሆን ፤ ስለ ሰው አምላክ መሆን ምሥጢር በግልፅ የሚናገር ነገረ መለኮታዊ ወንጌል ነው፡፡ ይህ ወንጌል ከሌሎቹ ወንጌላት እጅግ ዘግይቶ የተጻፈ ቢሆንም ‹በመጀመሪያ ቃል ነበረ ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ› ብሎ ስለሚጀምር ከኦሪት ዘፍጥረትም የሚቀድም አሳብን የያዘ ነው፡፡ ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን ሲጽፍ ‹ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ ልጽፍ መልካም ሆኖ ታየኝ› ብሎ ቢጽፍም ‹ለመጀመሪያም መጀመሪያ አለውና› ከእርሱ በኋላ የጻፈው ዮሐንስ ወንጌሉን ከምድር አንሥቶ ወደ ቅድመ ዓለም ወሰደው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ከሥር ከመሠረቱ ጀምሬ ላንብብ ብሎ የሚነሣ ሰው መነሣት ያለበትም ከዚህ ዓረፍተ ነገር ነው፡፡ (ዮሐ. ፩፥፩)
ወንጌላዊው ‹‹ያ ቃል ሥጋ ሆነ በእኛም አደረ›› ብሎ ቀጥታ ወደ አምላክ ሰው መሆን ጉዳይ ከመግባቱ በፊት ‹በመጀመሪያ ቃል ነበረ ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ› የሚለውን ማስቀደም ነበረበት፡፡ ስለዚህ የወንጌሉን መግቢያ በሆነው ከ፩‐፲፰ ክፍለ ንባብ ውስጥ ከ፩‐፲፫ ያለውን ክፍል የእግዚአብሔር ቃል ከቅድመ ዓለም ጀምሮ እንደነበረ፣ ዓለምን እንደፈጠረ ፣ ወደ ዓለም ይመጣ እንደነበረ ፣ በዓለሙም እንደነበረ ወዘተ በሚገልጹ ቃላት ተሞልተዋል፡፡ ይህንን አብራርቶ መሠረት ከጣለ በኋላ ‹ቃል ሥጋ ሆነ ፤ በእኛም አደረ› ብሎ ወደ ምሥጢረ ሥጋዌ መጥቷል፡፡
‹ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቀለ› ብለን ለመናገር ስንነሣም ይህንን የወንጌላዊውን የአጻጻፍ ስልት ልንከተል ግድ ይለናል፡፡ ወንጌላዊው ‹ቃል ሥጋ ሆነ› ከማለቱ ፊት ‹በመጀመሪያ ቃል ነበረ ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ› ማለት አስፈልጎት ነበር፡፡ እኛም ‹ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቀለ› ለማለትም ‹በመጀመሪያ ሕጻን ነበረ ፤ ሕጻኑም በማርያም ዘንድ ነበረ› ብለን ከመነሻው መጀመር ያስፈልገናል፡፡
የክርስቶስ የማዳን ሥራው በመስቀል ላይ ፍጻሜውን አገኘ እንጂ ከተፀነሠበትና ከተወለደበት ጊዜ አንሥቶ የሚያደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ለእኛ መዳን እጅግ ወሳኝ ነበሩ፡፡ የሰው ልጅ መዳን የተከናወነው በዕለተ ዓርብ መስቀል ላይ በተፈጸመው ካሣ ብቻ አይደለም፡፡ እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ሳይወለድ ፣ በጥቂቱ ሳያድግ እንደ መጀመሪያው አዳም ከመሬት የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተገኝቶ ፣ ሦስት ዓመትዋን አስተምሮ በተሰቀለ ነበር፡፡
የክርስቶስ የማዳን ሥራ ግን በድንግልና ከመፀነሱና ከሕፃንነቱ ጊዜ የሚጀምር የካሣና የመሥዋዕትነት ሥራ ነበር፡፡ ለዚህም ነው ክርስቶስ ሲሰቀል በዓይኑ ያላየው አረጋዊው ስምዖን በሥጋ ተወልዶ ስላየው ብቻ ‹‹ዓይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና ባርያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ›› ያለው፡፡ (ሉቃ. ፪፥፴፩) በዚህ ምክንያት ስለመዳናችን ስንናገር ‹‹የመመኪያችን ዘውድ የመድኃኒታችን መጀመሪያ የንጽሕናችንም መሠረት እኛን ስለማዳን ሰው የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን›› ብለን እንጀምራለን፡፡
እመቤታችን አምላክ ከእርስዋ እንዲወለድ ነጻ ፈቃድዋን ከሰጠችበት ቅጽበት ጀምሮ ወልዳ ያሳደገችበት ሒደት ሁሉ በሰው ልጅ የመዳን ታሪክ ውስጥ እጅግ ወሳኝ ሥፍራ ያለው ነው፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ራሱን ይሠጥ ዘንድ አስቀድማ ‹እነሆኝ የጌታ ባሪያ› ብላ ራስዋን ለእግዚአብሔር የሰጠችው የዓሥራ አምስት ዓመትዋ ብላቴና ያለ ወንድ ዘር ትወልጃለሽ የሚለውን የመልአኩን ቃል ከማመንዋ ጀምሮ ለሰው ልጅ ድኅነት ዕድሜዋን የሰጠች ፣ ስደትንና ኀዘንን ለመታገሥ ወስና ራስዋን ለፈጣሪዋ ያስረከበች ነበረች፡፡
በነቢያት የተነገረለትን አምላክ እንደምትወልድ ፣ እርሱም ሕዝቡን ከኃጢአታቸው እንደሚያድናቸው የተነገራት ድንግል ፣ በቤተ መቅደስ አድጋ ስለ መሲሑ የተነገሩ ትንቢቶችን የሰማችው ድንግል ፣ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ ስላለፈው ብቻ ሳይሆን ለወደፊት ስለሚነሡት ‹ትውልድ ሁሉ› አውቃ ትንቢትን የተናገረችው ድንግል የልጅዋን የማዳን ዕቅድ ባወቀችበት መጠን ያለፈችበት የኀዘን መንገድም ከባድ ነበር፡፡ ስለዚህም ጌታችን ከተወለደበት ጀምሮ እስከተቀሰለበት ድረስ ያሉት ሠላሣ ሦስት ዓመታትም ለእናቱ ለድንግል ማርያም የዕንባና የጭንቀት ዓመታት ነበሩ፡፡
የእመቤታችን ኀዘን የሚጀምረው ጌታችንን ይዛ ወደ ቤተ መቅደስ ከሔደችበት ከስምንተኛው ቀን ጀምሮ ነው፡፡ በዚያች ዕለት በቤተ መቅደስ ክርስቶስን ሳያይ ሞትን እንዳያይ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ የነበረው አረጋዊው ስምዖን ጌታችንን ተቀብሎ ካቀፈው በኋላ አንድ ትንቢት ተናገረ ፡-
‹‹እነሆ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ምልክት ሆኖ ተሾሞአል ፤ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል›› (ሉቃ. ፪፥፴፭) ብሎ ልጅዋ ለብዙዎች ማመንና መካድ ምልክት እንደሆነና በሚደርስበት የመስቀል ላይ መከራ ምክንያትም በእርስዋም ላይ ስለሚደርሰው እንደ ሰይፍ ልብ የሚከፍል ኀዘን ጨምሮ ነገራት፡፡ እመቤታችን ካዘነቻቸው ታላላቅ ኀዘናት አንዱም በዚህ ቀን ያዘነችው ኀዘን ነበረ፡፡
እዚህ ላይ ለአፍታ ቆም ብለን ሁኔታውን ለማገናዘብ እንሞክር፡፡ ሕጻን ልጅ ታቅፋ የሔደች ማንኛዋስ እናት ብትሆን አንድ ሽማግሌ ልጅዋን ታቅፎ ይዞ ልጅዋ ብዙ መከራ እንደሚደርስበትና እርስዋም ኀዘን እንደሚደርስባት ሲነግራት ምን ያህል ትደነግጥ ይሆን? ምናልባትም ከሽማግሌው እጅ ልጅዋን በቁጣ ነጥቃ እንደ አቤሜሌክ ‹አእምሮውን ያጣ ሽማግሌ ባልኩህ ነበር› ብላው ትሔድ ይሆናል፡፡
ድንግል ማርያም ልጅዋን ለአረጋዊው የሰጠችው ግን በመንገድ ላይ ሳይሆን በቤተ መቅደስ ውስጥ ነበር፡፡ ስምዖንም የተነገረላትን ድንግልን ከምትወልደው አማኑኤል ጋር ለማየት ለብዙ ዘመናት ሲጠባበቅ የነበረ መንፈስ ቅዱስ የሚያናግረው ጻድቅ ሰው እንጂ ተራ ሽማግሌም አልነበረም፡፡ ስለዚህ ስለ ልጅዋ መከራም ሆነ ስለ እርስዋ ኀዘን የተናገረው በመንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ታውቃለች፡፡ ይህን አረጋዊ ከሸመገለና ካረጀ በኋላ ትንቢት ያናገረው ኤልሳቤጥን ከሸመገለችና ካረጀች በኋላ በታላቅ ድምፅ ጮኻ ‹‹አንቺ የተባረክሽ ነሽ ፤ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው›› ብላ እንድትናገር ያደረጋት መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡
ስለዚህ እመቤታችን ስለ ልጅዋ ሞት ትንቢትን ከሰማችበት ከዚያች ዕለት ጀምሮ የኀዘን ጉዞዋን ጀመረች፡፡ ንጉሥ ዳዊት እንኳን ስለ ልጁ ‹‹የተወለደልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞታል›› ተብሎ ሲነገረው እጅግ ኀዘን ወድቆበት ነበር፡፡ ‹‹ዳዊትም ጾመ ፤ ገብቶም በመሬት ላይ ተኛ፡፡ የቤቱም ሽማግሌዎች ተነሥተው ከምድር ያነሡት ዘንድ ከአጠገቡ ቆሙ ፤ እርሱ ግን እንቢ አለ ፤ ከእነርሱም ጋር እንጀራ አልበላም›› (፪ሳሙ. ፲፪፥፲፬) ንጉሥ ዳዊት በዝሙት ስለወለደው ልጁ ሞት ሲነገረው እንዲህ በኀዘን ኩርምት ካለ እመቤታችን በድንግልና ስለወለደችው ልጅዋ ሞት ስትሰማ ምንኛ ትጨነቅ ይሆን?
ምናልባት የዳዊት ልጅ ወዲያው የሚሞት በመሆኑ ገና ከሠላሳ ሦስት ዓመታት በኋላ ልጅዋ ከሚሰቀለው እናት ጋር ኀዘኑ አይነጻጸርም ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ይህ እውነታ ኀዘንዋን ከዳዊት ኀዘን የበለጠና የከፋ ያደርገዋል፡፡ በዚህ መጽሐፍ አራተኛ ምዕራፍ መግቢያ ላይ የተመለከትነውን የአብርሃምና ይስሐቅን ታሪክ እስቲ መለስ ብለን እናስታውስ፡፡ አብርሃም ልጁን ይስሐቅን እንዲሠዋ ከተነገረው በኋላ እስከ ሞርያ ተራራ ድረስ ሦስት ቀናትና ሦስት ሌሊቶች ከልጁ ጋር ተጉዞ ነበር፡፡ ልጁ እን

ደሚሞት እያሰበ ከሚያሳሳው ልጁ ጋር የተጓዘባቸው እነዚያ ሦስት ቀናት ለአብርሃም እጅግ አስጨናቂ ቀናት ነበሩ፡፡
ልጅዋ በመስቀል ላይ እንደሚሞት እያወቀች ለሠላሳ ሦስት ዓመታት አብራው የቆየችው ድንግል ምንኛ ትጨነቅ ይሆን? ዕድሜው በጨመረ ቁጥር ወደ መስቀሉ እየቀረበ እንደሚመጣ እያወቀች ፣ እንደ ሐዋርያቱ እንኳን አትሰቀል አትሙት ሳትለው የቆየችው ድንግል ምን ያህል ትጨነቅ እንደነበር ማሰብ አያዳግትም፡፡ ሆኖም የእመቤታችን ታላቅ ኀዘን የልጅዋን መከራ ከስምዖን ትንቢት ውስጥ በመስማትዋ ብቻ ያበቃ አልነበረም፡፡ ትልቁ ሄሮድስ ‹‹ሕጻኑን ሊገድለው ይፈልጋል›› በተባለችበት ጊዜስ ምን ሆና ይሆን?
ጨካኙ ንጉሥ ሄሮድስ የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ ለመግደል በጭካኔ በተነሣ ጊዜ መንገድ ወጥታ የማታውቀው የገሊላዋ ብላቴና እርስዋ ሕጻን ሆና ሕጻንዋን ታቅፋ ለስደት በወጣች ጊዜ የነበራትን ኀዘንስ በምን እንገልጸዋለን? አባ አርከ ሥሉስ እንዳለው ልጅዋን በጉያዋ ሸሽጋ በምትሸሽበት ጊዜ ከጭንቀትዋ የተነሣ ገሊላዊትዋ ድንግል ማርያም መሬት ጠብባት መድረሻ አጥታ ነበር፡፡
መውጫ መግቢያውን ሳታውቅ በቤተ መቅደስ ውስጥ ያደገችው ድንግል ወደ ግብፅ በረሃ እንደ ወፍ የተንከራተተችው መንከራተት ፣ እንደ አንበሳ የሚያስፈሩት የነዳዊትና የነሰሎሞን ልጅ ድንግል ልጅዋን ታቅፋ መሸሽዋ ፣ የደረሰባት ኀዘን ፣ ረሃብና ጥም ፣ ያፈሰሰችው ዕንባ እስከዛሬ ድረስ በቤተ ክርስቲያናችን የጥልቅ ተመሥጦ ምንጭ ነው፡፡ የስደትዋን ነገር በጾም ለማሰብ የፈቀዱ ክርስቲያኖች በሚጾሙበትና በውብ ማኅሌት ስለ እነዚያ የስደት ወራት በሚታሰብበት በዘመነ ጽጌ ስለ ኀዘንዋ ብዙ ይባላል፡፡
‹‹ርኢክሙኑ ወለተ ደክታመ
ሐዚላ ሕጻነ ትጎይይ ገዳመ
አኀሥሠኪ ወእብል እንዘ አዐይል አድያመ
ማርያም ጸዋሪተ ኃይል ዘኢለመድኪ ድካመ
አንደደኒ ሥራሕኪ ከዊኖ አፍሐመ››
‹‹አንዲት የደከማት ታናሽ ብላቴና ሕጻን ታቅፋ ወደ ምድረ በዳ ስትሸሽ አይታችኋልን? እያልኩ በየከተማ እየዞርሁ እፈልግሻለሁ! ኃይልን የተሸከምሽ ፣ ድካምን ያልለመድሽው ማርያም ሆይ መንከራተትሽ እንደ ፍሕም እሳት ሆኖ አቃጠለኝ!››
‹‹አይቴ ኀለፈት እምዕያማ ማርያም ጣዕዋ
ኀሠሥክዋ በቤተልሔም ወኢረከብክዋ
እሴአለክሙ ሰብአ ገሊላ እመ ርኢክምዋ
ንግሩኒ ዜናሃ ወአርእዩኒ ፍናዋ
ኀበ ሖረት በብካይ እትልዋ
‹‹ታናሽዋ ጊደር ማርያም ወዴት አለፈች? በቤተ ልሔም ፈለግኳት ግን አላገኘኋትም፡፡ የገሊላ ሰዎች ሆይ እለምናችኋለሁ ፤ ካያችኋት ንገሩኝ የሔደችበትንም መንገድ አመልክቱኝ! ወደ ሔደችበት በለቅሶ እከተላታለሁ!›› ይላል የድንግሊቱ ኀዘን ዘልቆ የተሰማው የሰቆቃወ ድንግል ደራሲ አባ አርከ ሥሉስ
ያዕቆብ ወደ ግብፅ ሲሰደድ ልጅህ ዮሴፍ በግብፅ ተሾሟል ተብሎ ተነግሮት ፣ ልቡ በደስታ ተሞልቶ ፣ ረሃቡን ሊያስታግሥና በምቾት ሊኖር ነበር፡፡ ጉዟቸውም ከግብፅ ፈርዖን በተላከላቸው ልዩ የቤተ መንግሥት ሰረገላ ነበር፡፡ (ዘፍ. ፵፮፥፭) የያዕቆብ ዘመድ ድንግል ማርያም ግን ወደ ግብፅ የሔደችው አንድም የሚያውቃት ሰው ሳይኖር ነበር፡፡ በኀዘንና በዕንባ ተሞልታ ፣ ወደ ረሃብ ምቾት በሚነሣ የአህያ ጀርባ ላይ ተጭና ነበር ፡፡
ባለቅኔው ‹‹ሐሜትን የማትፈራው ማርያም የሕይወት እንጀራን (ክርስቶስን) ተሸክማ በመንገድ ላይ የእንጀራን ፍርፋሪ ለመነች›› (ማርያም ድንግል ዘኢትፈርህ ሐሜተ ፤ ፍርፋራተ ኅብስት ሰአለት በፍና እንዘ ትፀውር ኅብስተ››) እንዳሉት አምላክን በእጆችዋ ታቅፋ በረሃብና ጥም እስከ ልመና ደርሳለች፡፡ በአጠቃላይ በእነዚያ ሦስት ዓመታት ዲያብሎስ ያሳደዳት ሴቲቱ ድንግል ማርያም የሕጻናትን ደም እንደወንዝ ከኋላዋ ያፈሰሱት የሄሮድስ ወታደሮች ልጄን እንዳይገድሉብኝ በሚል ጭንቀትን ፣ ረሃብንና ጥምን ፣ መራራ ኀዘንን አሳልፋለች፡፡ (ራእ. ፲፪፥፲፬‐፲፮)
በእነዚህ የስደት ወራት ድንግል ማርያም የደረሰባት ጭንቀትና ኀዘን በቅዳሴያችን እንዲህ እያልን ከልጅዋ እንድታማልደን እንለምናታለን፡፡
‹‹ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ ጋራ ካገር ወደ ሀገር ስትሸሺ ካንቺ ጋራ መሰደዱን አሳስቢ፡፡ ድንግል ሆይ ከዓይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር ዕንባ አሳስቢ ፤ ድንግል ሆይ ረሃቡንና ጥሙን ችግሩንና ኀዘኑን ከርሱ ጋራ የደረሰብሽን ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ›› (ቅዳሴ ማርያም ኀዳፌ ነፍስ)
የእመቤታችን ኀዘንና ጭንቀት ከስደት ከተመለሰች በኋላም አላበቃም፡፡ ጌታችን የዓሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ሳለ ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው ነበር፡፡ ‹
‹ሲመለሱ ግን ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር ፤ ዮሴፍና እናቱም አላወቁም ነበር፡፡ ከመንገደኞች ጋር የነበረ ስለመሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፈለጉት ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡
ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ አገኙት፡፡ የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ፡፡ ባዩትም ጊዜ ተገረሙ ፤ እናቱም ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው፡፡ እርሱም ፡- ስለ ምን ፈለጋችሁኝ በአባቴ ቤት እኖር ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን? አላቸው›› (ሉቃ. ፪፥፪‐፵፱)
ተሰድዳ ከሰይፍ ያተረፈችው ልጅዋ ከስደት ይዛው በተመለሰች በጥቂት ዓመታት ልዩነት ሲጠፋባት በአርኬላዎስ ወገኖች እጅ ገብቶ ይሆን ብላ በጽኑ ተጨንቃ ነበር፡፡ ‹ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን› እያለችም ልጅዋን ፍለጋ ለሦስት ቀናት ያህል ተንከራትታ ነበር፡፡ ልጅ ጠፍቶበት የሚያውቅ ሁሉ ይህንን ጭንቀት ይረዳዋል፡፡ በሕይወትዋ ሁሉ ለእኛ ምሳሌ የምትሆነው ድንግል ክርስቶስ ለሦስት ቀናት ብቻ ከእርስዋ ቢጠፋባት ፍለጋ መውጣትዋም የሚያስተምረን ነው፡፡
ከብዙዎቻችን ሕይወትና ልብ ውስጥ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ከጠፋ ስንት ቀን ሆኖት ይሆን? እኛስ ከውስጣችን ያጣነውን ጌታችንን መፈለግ የለብንም ትላላችሁ? እመቤታችን ከመንገደኞች ጋር ወይም ከዘመዶች ጋር ፈልጋ አላገኘችውም ፤ በመጨረሻ ግን በቤተ መቅደስ አገኘችው፡፡ ክርሰቶስን በዘርና በዘመድ አናገኘውም፡፡ የእርሱ መገኛ በቤተ መቅደስ ነው፡፡
‹‹የሚፈልጉት የት ሊያገኙት እንደሚችሉ ተማሩ ፤ የትም ሳይሆን በቤተ መቅደስ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ፈልጉት ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ካሉ መምህራን ዘንድ ፈልጉት›› እንዳለ ሊቁ መድኃኔ ዓለምን በየመንገዱ ማግኘት አይቻልም ፤ በቤተ መቅደስ ከአባቶች ዘንድ ግን ይገኛል፡፡
በእውነት ክርስቶስን ያገኘ ጌታን ካገኘሁ ይበቃኛል ብሎ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሊርቅ አይችልም ፤ ይልቁንስ ‹‹ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት ፤ ወደ እናቴም ቤት ወደ ወላጅ እናቴ እልፍኝ እስካስገባው ድረስ አልተውሁትም›› ሊል ይገባዋል፡፡
የእናት ቤት የወላጅ እናታችን እልፍኝ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን የምናገኝባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ የሚገኝ ክርስቶስ ወይም ከቤተ ክርስቲያን የሚያስወጣ ክርስቶስ እርሱ እውነተኛው ክርስቶስ አይደለም፡፡ ‹‹ማንም ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ ፤ ሐሰተኞች ክርስቶሶች ይነሣሉና፤ እነሆ አስቀድሜ ነገርኳችሁ እነሆ በበረሃ ነው ቢሏችሁ አትውጡ ፤ እነሆ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ አትመኑ›› ብሎ ነግሮናልና፡፡ (መኃ. ፫፥፬ ፤ ማቴ. ፳፬፥፳፫‐፳፮)
እመቤታችን ልጅዋን በቤተ መቅደስ ባገኘችው ጊዜ ጌታችን በአ

ይሁ
ድ መምህራን ሥር በትሕትና ተቀምጦ ነበር፡፡ በመልሱ ብቻ ሳይሆን እንደ ሕጻናት ልማድ በጥያቄው ያስደንቃቸውና ያስተምራቸው ነበር፡፡ እናቱ ወደ እርሱ ስትቀርብ እንደ ሌሎች ወላጆች በቁጣ አልጮኸችበትም፡፡ ከጸሎት በማይተናነስ እርጋታና በሚያራራ ቃል ‹‹ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን›› አለችው፡፡
ትሕትናዋ የማያቆመው ድንግል እኔና አባትህ ብላ ራስዋን አላስቀደመችም:: በመጀመሪያ እርሱን አስቀድማ ‹እነሆ አባትህና እኔ› ብላ ጻድቁ ዮሴፍን ‹አባትህ› ብላ ጠራችው፡፡ ይህንን ያለችው ቅዱስ ኤፍሬም እንዳለው ክርስቶስ የዮሴፍ ልጅ እንደሆነ ለሚመስላቸው በዚያ ለተቀመጡት አይሁድ ሕሊና እና እንደ አባት ያሳደገውን ዮሴፍንም ለማክበር ብላ እንጂ እንደ ፊልጶስ ባለማወቅ አይደለም፡፡ (ዮሐ. ፩፥፵፮) ይህንን የእመቤታችንን ንግግር ይዘው ክርስቶስ የዮሴፍ ልጅ ነው የሚሉ እንዳይኖሩ ግን ጌታችን እዚያው ሥፍራ ላይ ‹በአባቴ ቤት እኖር ዘንድ እንዲገባኝ አታውቁምን› በማለት አባቱ ዮሴፍ ሳይሆን እግዚአብሔር አብ መሆኑን አመልክቷል፡፡
ጌታችን ለሦስት ቀናት ያህል የጠፋው ለምንድር ነው? ‹ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?› የሚለው ጥያቄ መልሱ ምን ይሆን? ይህን ያደረገው ‹‹የተወለደው በማርያምና በዮሴፍ ቤት ሊቀመጥ ሳይሆን የእውነትን እውቀት ያስተምር ዘንድ ሥርዓትን ይፈጽም ዘንድ እንደሆነ ለማስረዳት ነው›› (ወከመ ያለቡ ውእቱሰ ኢተወልደ ከመ ይንበር ውስተ ቤተ ማርያም ወዮሴፍ አላ ባሕቱ ከመ ይምሀር አእምሮተ ጽድቅ ወይፈጽም ሥርዓተ››) እንዲል፡፡ ከዚያም በኋላ ‹ከእነርሱም ጋር ወርዶ ይታዘዝላቸውም ነበር› ተብሎ መጻፉ ደግሞ የቱንም ያህል መንፈሳውያን ብንሆን ለወላጆቻችን መታዘዝን ማስቀደም እንዳለብን የሚያስተምር ነው፡፡ (ሉቃ. ፪፥፶፩)
ጌታችን ለሦስት ቀናት ጠፍቶ መገኘቱ እንደ ቅዱስ አምብሮስ ያሉት ሊቃውንት ትንሣኤውን ያመለክታል ይላሉ፡፡ የደብረ ገሪዛን ጉንዳጉንዲ ትርጓሜ ወንጌልም ጌታችን ይህንን ያደረገው በመቃብር ሦስት ቀናት መቆየቱን የሚያስረዳ ትንቢት እንደሆነና በሦስተኛው ቀን ለማርያምና ለዮሴፍ መገለጡም ከትንሣኤው በኋላ ለመግደላዊት ማርያምና ለደቀ መዛሙርቱ የሚገለጥ መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ በውብ መንገድ አነጻጽሮ አስቀምጦታል፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 28 2013 ዓ ም
ለዘመነ ጽጌ ከሕማማት ገጾች

✝✝የብዙ ሰው ጥያቄ የሆነዉ እንዴት ኅሊናዬን ሰብስቤ ልጸልይ✝✝
ልቡናውን ሰብስቦ መጸለይ አልችል ያለው ደቀመዝሙር አረጋዊውን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- “አባቴ! የጸሎት መጽሐፍ ይዤ ሳነብ ልቡናዬ አይሰበሰብልኝም፡፡ አፌ ቢያነብም ልቡናዬ አይተረጕምም፡፡ እርስዎ እንደነገሩኝ ደግሞ ቅዱሳን በፍጹም አሳባቸው እያሰቡና እያራቀቁ እንባንና ጸጸትን እየጨመሩ የደረሱትን እኛ በልባችን ሌላ እያሰብን በአፋችን ብቻ እንደነርሱ ብንናገር እንደ ገደል እንደ ዋሻ ሆነን በእግዚአብሔር እንደመቀለድ ነው፡፡ ጸሎትም አይሆንልንም፡፡ እንግዲህ ያፍ ጸሎቴ ቅድመ እግዚአብሔር የማይደርስ ከሆነ ጸሎቴን ብተወው ይሻላል ወይስ ባልተወው ይሻላል?” እርሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፡- “ዕውር ሰው በዘንጉ ምድር እየመታ ሲሄድ ከመንገድ ላይ ያለ እባብ ለጊዜው ድምጹን ሰምቶ ይመታኛል ብሎ እንደሚሸሽለት ሁሉ አንተም አስተውለህ ባትጸልይም ባፍህ ውስጥ የቃለ እግዚአብሔርን መንኳኳት እየሰሙ አጋንንት መሸሻቸው አይቀርምና ምንም ቅድመ እግዚአብሔር ባይደርስም ጸሎትህን አትተው፡፡ አጋንንትንም ማባረር ጥቅም ነውና፡፡ ብዙ ከምትጸልየውም አንዳንድ ጊዜ ልብህ የሚወድቅባት ቃል ተጠራቅማ ወደ እግዚአብሔር እንድትደርስልህ ምንም ዝርወ ልብ ብትሆንም አፍህም ፍጥረቱ ነውና አንተው በዳይ አንተው አኵራፊ እንዳትሆን ባፍህም ብቻ ቢሆን መነጋገሩን አትተወው፡፡”
👍ሌሎች ትምህርቶችን እና ምክሮችን ለማግኘት

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ኅዳር ፲፭ (15) ❖
+"+ ቅዱስ ሚናስ ምዕመን ሰማዕት +"+
=>ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) በምድረ ግብጽ ተወዳጅ
ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው:: ልክ በሃገራችን ቅዱስ
ጊዮርጊስ ልዩ ቦታ እንዳለው ሁሉ ግብፃውያን ማር
ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም::
+ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም
ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ
ነው:: በተለይ ለታመመ: ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ
ደራሽ: ባለ በጐ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው::
+"ግብጽ ውስጥ ቅዱሱን የማያውቅ ሰው ካገኛችሁ
እርሱ ኦርርቶዶክሳዊ አይደለም ማለት ነው" ሲባልም
ሰምተናል:: በነገራችን ላይ ለቅዱሳን ተገቢውን ክብር
በመስጠት: ታሪካቸውን በመጻፍ: በማጥናት: በመጽሔት:
በፊልምና በመሳሰሉት ለሕዝብ በማስተዋወቅ
ግብጻውያኑ ከእኛ ብዙ ርቀት ሒደዋል:: ዛሬ እንኩዋ
የምንጠቀምበትን ስንክሳር 80 ከመቶ እጁን ያዘጋጁት
እነርሱ ናቸው::
+አባቶቻችንና እናቶቻችን ኢትዮዽያውያን ቅዱሳን ግን
አብዛኞቹ ተረስተው ቀርተዋል:: መጽሐፈ ገድላቸውንም
ብል በልቶታል:: ዛሬም የቤት ሥራው የእኛ ብቻ ነው::
+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ሚናስ (ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው):-
*በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች
ልጅ::
*በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ::
*በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ::
*ሃብትን: ክብርን: ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት
የተወሰነ::
*በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ አላውያን የገደሉት
ሰማዕት ነው::
+እርሱ ሰማዕት ከሆነ ከበርካታ ዘመናት በሁዋላ
ምዕመናን ክቡር አካሉን ፈልገው ያጡታል::
የሚገለጥበት ጊዜ ሲደርስ ግን እርሱ የተቀበረበት ምድረ
በዳ የበጐችና የእረኞች መዋያ ነበርና ተአምራትን
አደረገ::
+አንድ እረኛ በጐቹ ድውያን ሆኑበት:: በዚያ ሰሞን
ከቅዱሱ መቃብር ላይ ጸበል ፈልቆ ነበርና እረኛው ተርታ
ውሃ ነው ብሎ በጎቹን ሲያጠጣቸው አንዱ ድውይ በግ
ወደ ጸበሉ በመዘፈቁ ዳነ::
+በዚህ የተገረመው እረኛ ሁሉንም የታመሙ በጐቹን
አምጥቶ ነከራቸው:: እነርሱም ተፈወሱ:: ይህ ዜና
በምድረ ግብፅ ሲሰማ ድውያን ሁሉ እየመጡ ይፈወሱ
ገቡ:: ግን እነሱም ሆነ እረኛው ምክንያቱን ማወቅ
አልቻሉም:: ነገሩ በሮም ንጉሥ ዘንድ ሲሰማ ሴት ልጁን
ከሠራዊቱ ጋር ላካት::
ምክንያቱም እርሷ ከብዙ ዘመን ጀምራ መጻጉዕ ነበረችና
ፈውስን አጥታ ነበር::
+መጥታ ተጠመቀች: ፈጥናም ተፈወሰች:: እርሷ ግን
እንደ ሌሎች ያዳናትን ማንነት ሳታውቅ መሔድ
አልፈለገችምና ሱባዔ ገባች:: ቅዱስ ሚናስ በሌሊት
ራዕይ መጥቶ ሥጋው እንዳለ ነገራት:: እርሷም መሬቱን
አስቆፍራ የቅዱሱን አካል በክብር አስወጣች::
+ከዚያም በንጉሡ ትዕዛዝ ምድረ በዳው ከተማ
እንዲሆን ተቀየረ:: ስሙም "መርዩጥ" ተባለ:: ጸበሉ
የነበረበት ቦታም ላይ የማር ሚናስ ቤተ ክርስቲያን
ታንጾበት ቅዳሴ ቤ ተከብሯል::
+"+ ቅዱስ ቂርቆስ ሕጻን +"+
=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካሏት ዐበይት ሰማዕታት አንዱ
ቅዱስ ቂርቆስ ነው:: በተለይ በዘመነ ሰማዕታት ተነስተው
እንደ ከዋክብት ካበሩትም አንዱ ነው:: ቅዱስ ወንጌል
እንዲህ ይላል:- "መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን
ያፈራል::" (ማቴ. 7:17)
+መልካም ዛፍ ቅድስት ኢየሉጣ መልካም ፍሬ ብጹዕ
ቂርቆስን አፍርታ ተገኝታለችና ክብር ይገባታል:: ቡርክተ
ማሕጸንም እንላታለን:: የተባረከ ማሕጸኗ የተባረከ ልጅን
ለ9 ወር ተሸክሟልና::
+በዚያ ክርስቲያን መሆን መከራ በነበረበት ዘመን ይህንን
ደግ ሕጻን እርሷን መስሎ: እርሷንም አህሎ እንዲገኝ
አስችላለችና:: አበው በትውፊት እንዳቆዩልን ከሆነ
በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በዚህች ቀን እናታችን ቅድስት
ኢየለጡ ብጹዕ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስን ወልዳለች::
+ፈጣሪ ቢያቆየን የሰማዕትነት ዜናቸውን ጥር 15 ቀን
የምንመለከት ነንና የዚያ ሰው እንዲለን እንማጸነዋለን::
=>አምላከ ሰማዕታት በምሕረቱ ይማረን:: በይቅርታው
ኃጢአታችን ይተውልን:: ከበረከተ ሰማዕታትም ይክፈለን::
=>ኅዳር 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
2.ልደተ ቅዱስ ቂርቆስ
3.ብጽዕት ኢየሉጣ
4.አባ ሚናስ ዳግማይ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
2.ቅድስት እንባ መሪና
3.ቅድስት ክርስጢና
=>+"+ አሁንስ ይላል እግዚአብሔር:: በፍጹም ልባችሁ
በጾምም: በለቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ:: ልባችሁን
እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ:: አምላካችሁም
እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ: ቁጣው የዘገየ: ምሕረቱም
የበዛ: ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ:: +"+ (ኢዩ. 2:12)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

አባት የሌለው ቤት
ታክሲ ውስጥ ከመጨረሻው ቀጥሎ ከሚገኘው መቀመጫ ላይ ተቀምጬ ነው ጉዞዬን የጀመርኩት ከእኔ ጀርባ ሶስት ጎልማሳ ወንዶች ይነጋገራሉ። የንግግራቸው ጭብጥ (ይመስለኛል አንድ ግቢ ውስጥ የሚኖሩት) በግቢ ውስጥ ያጋጠማቸው አንድ ቤተሰብ ባህሪ አስቸጋሪ መሆኑን ነው። ይህ ቤተሰብ የቴሌቪዥን ድምጽ በመጨመር ብሎም ሌሎች አብሮ የመኖር እሴትን ሊያፈርሱ የሚችሉ ተግባራትን እየፈጸመ ማስቸገሩን ነው። ይህንን ቤተሰብም ሲገልጹት "ድሮም አባት የሌለበት ቤት" ሲሉ ተናገሩ።
በርግጥ በሃገራችን አባት ቤተሰብን ቀጥ አድርጎ በስርአት በመምራት በኩል በርካታ ስራዎችን ይሰራል። አባት ይፈራል ፥ ይከበራል ይወደዳልም። ምናልባት አባት እናትን በመፈራት ሲበልጣት እናት ደግሞ በአንጻራዊነት በመወደድ ትበልጠዋለች።
ከእነዚህ ወንድሞቼ ንግግር ይሄ "አባት የሌለው ቤት" የሚለው አገላለጽ እንደ ኦርቶዶክሳዊ ያለንበትን ሁኔታ የሚገልጽ ስለመሰለኝ ውስጤ ቀረ። ዛሬ ብዙዎቻችን አባት እንደሌለው ቤት ስርዓት እያለን ያለ ስርዓት ህግ እያለን ያለ ህግ እየሄድን ነው። አባታችን ቢኖር እርሱን ፈርተን ህጉን እናከበር ነበር። ዛሬ ህጉን ስርአቱን እናውቀዋልውን ግን አንመራበትም።
ጻድቁ ዮሴፍ የጲጥፋራ ሚስት ህግን እንዲፈርስ ስትጠይቀው እንደዚህ ነበር ያላት "በአባቴ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ይሄንን ኃጢአት እሰራለሁ"። የዮሴፍ ቤት አባት የሌለው ቤት አለመሆኑን በይፋ ነበር ያስመሰከረው። ሐዋርያው ጴጥሮስ ደግሞ ፈጣሪውን እንደማያውቅ ተናግሮ ኃጢአትን ከሰራ በኋላ "አባት የሌለው ቤት መሆኑን" ሲረዳ ከልቡ አለቀሰ ተጸጸተና አባቱን ወደ ቤቱ ይመጣለት ዘንድ ለመነው። ክርስቶስም በምህረት ወደርሱ መጥቶ ታላቅ ክብርን ሰጠው።
እነዚህ ሁለቱ ቅዱሳን "አባት ያለው ቤት" ሆነው የተገኙ ሰዎች ናቸው። ዛሬ በነሱ እግር ስር የተገኘን እኛ ግን "ቤታችን አባት የሌለው ቤት" ሆኗል። አባታችን እግዚአብሔርን ትተን ህግን አፍርሰን ስርዓትን ጥሰን እየኖርን ነው። በዚህም ምክንያት ብዙ ችግር እያጋጠመን ባዶነት እየተሰማን ቢሆንም እንደ ሐዋርያው ጴጥሮስ ባዶነታችንን በአባታችን በእግዚአብሔር ለመሙላት አልታደልንም።
እስቲ አባታችንን ቤታችን ውስጥ እንፈልገው ነገር ግን አባታችንን የምናገኘው ከደጃችን ቆሞ በራፋችንን እየመታ ነው። ይሄ ደግሞ መሆን የለበትምና አባታችንን በህይወታችን እንግለጸው። አባት ያለበት ቤት መገለጫው የአባትየው በቤት ውስጥ መገኘት ጥቅሙ የቤቱ በስርዓት መያዝም ነውና አባታችን ከኛ ጋር ካለ በስርዓት መኖር አያቅተን።
ዲያቆን ዳዊት ናሁሠናይ (ዘብሥራት)
ታህሳስ 09 2013 ዓ.ም
ፒያሳ @zebisrat

“እያንዳንዱ ስለ ክርስቶስ የሚነገረው ነገር ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከፍ ከፍ የሚያደርጋት ነው፡፡ ከክብሯ ሁሉ ከፍ ያለው ክብር ግን በመስቀሉ የተደረገው ድንቅ ነገር ነው፡፡ ሐዋርያው ይህን ቢያውቅ “ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክሕት ከእኔ ይራቅ” አለ ገላ.6፡14፡፡
ሲወለድ ጀምሮ ዕውር የነበረው ሰው በሰሊሆም ውኃ ታጥቦ እያየ መምጣቱ ድንቅ ነው፡፡ ሆኖም ዓለም ከታወረበት ዕውርነት አውጥቶ ብርሃን እንዲያይ ካደረገው ከመስቀሉ ጋር ሲነጻጸር ይህ ምንድነው? ከሞተ አራት ቀን የሆነው በመቃብርም ያደረው አልዓዛር እንደገና መነሣቱ ታላቅ ነገር ነው፡፡ ሆኖም በኃጢአት የሞተውን ዓለም ነፍስ ዘርቶ እንዲነሣ ካደረገው ከመስቀሉ ኃይል ጋር ሲነጻጸር ይህ ምንድነው? አምስቱ እንጀራዎች አምስት ሺሕ አባዎራዎችን ማጥገባቸው ድንቅ ነው፡፡ ሆኖም ዓለም ሁሉ ነግሦበት ከነበረው ረኀብ በዕውቀት ብርሃን እንዲጠግቡ ካደረገው ከክርስቶስ ኃይል ጋር ሲነጻጸር ይህ ምንድነው? ሰይጣን ለዓመታት ሲያሰቃያት የነበረችው ሴት ከእስራት መፈታትዋ ታላቅ ነገር ነው፡፡ ሆኖም ሁላችንን በኃጢአታችን ምክንያት ተጠላልፈን እንድንታሰር የሆንበትን የኃጢአት ሰንሰለት ከበጣጠሰው ኃይል ጋር ሲነጻጸር ምንድነው?
ዓለም ስለዳነ የምታደንቁ አትሁኑ! ይልቁን የሞተው ዕሩቅ ብእሲ ሳይሆን የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ በመሆኑ ይህንን አድንቁ እንጂ፡፡”
ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም

እግዚአብሔር ሕግን ወይም ትዕዛዝን ከመስጠቱ በፊት ሰንበትን የባረከውና የቀደሰው መሆኑ ነው። በሥነ ፍጥረት እግዚአብሔር ብዙ ድንቆችን አድርጓል እርሱ ብርሃናትን፣ ሰማያትን፣ ቀላያትን፣ ምድርን፣ ዕጽዋትን፣ እንስሳትን፣ የሰውን ልጅ ሁሉ ፈጥሯል። እነዚህን ሁሉ ፍጥረታት ከፈጠረባቸው ዕለታት መካከል እግዚአብሔር ባርኮታል ቀድሶታልም የተባለለት ከሰንበት በቀር ሌላ ቀን የለም። ስለ ሁሉም ዕለታት የተነገረ ቢኖር "ያ መልካም እንደሆነ አየ "የተባለው ብቻ ነው (ዘፍ 1፥12)።
ከሳምንቱ ሰባት ቀናት መካከል ለዕረፍት የተቀደሰው የተባረከውም ዕለት ሰንበት ብቻ ነው ። ሌሎቹ ቀናት የተባረኩት ለሥራ ነው እርሱ ሠርቶባቸው እኛም ልንሰራባቸው ሰጥቶናል። ይህም ሰው በየፊናው የግል ሥራውን የሚያከናውንባቸው ሌሎች ዕለታት ከእግዚአብሔር ጋር ከሚነጋገርበት በስብሐት እግዚአብሔር ከሚጠመድበት መንፈሳዊና ሰማያዊውን ነገር ብቻ በማሰብ ከሚውልበት ዕለት ሰንበት ጋር የሚስተካከል ቅድስናና በረከት እንዲሁም ክብር የሌላቸው መሆኑን የሚያስረዳ ነው።
በዚህ መሠረት ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብትም ሁሉ ከተፈጠሩበት ዕለት ይልቅ አንድ ሰንበት የዕረፍት ቀን የበለጠ መሆኑን እናስተውላለን ። ማርታ ደስ እያላት ያለ አንዳች እረፍት የሠራችው ሥራ ማርያም ከጌታ እግር ስር ተቀምጣ በጸጥታ ቃለ እግዚአብሔርን ከመስማቷ የበለጠ ክብር አልነበረውም። (ሉቃ 10፥40)
በመሆኑም ዕለተ ሰንበት ዐርፈው ቃለ እግዚአብሔርን የሚሰሙበት በተዘክሮተ እግዚአብሔር የሚያሳልፉት መንፈሳዊውን ተግባራትን የሚሠሩበት በመሆኑ ከሌሎቹ ዕለታት የከበረ ነው ።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

ፆመ ገሃድ ምንድነው?
ጾመ ገሃድ
ይህ ጾም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት በማሰብ
የጥምቀት ዋዜማ የሚፆም ፆም ነው፡፡ ይህም ማለት በጥምቀት ዋዜማ ከምግብ መከልከል ነው፡፡ የሚቆርብ ሰው አክፍሎ የሚያድር ስለሆነም የጥምቀትን ድራር መጾም ነው፡፡ ሐዋርያት
«ልደት ጥምቀት ዓርብ ረቡዕ ቢውል በሌሊት ቀድሰው ሥጋውን ደሙን ይቀበሉ፤ ከሌሊቱ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጹሙ ብለው አይፍረዱ» ብለዋል /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15/፡፡ የልደትና
የጥምቀት በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ሃምሳ የሚበላውን የጥሉላት ምግብ በጠዋት በመብላት ምእመናን በዓሉን እንዲያከብሩ ታዟል፡፡
ይህም እነዚህ ሁለቱ ታላላቅ የእግዚአብሔር በዓላት
በመሆናቸው ነው፡፡ የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ በሚውልበት ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ ማክሰኞንና ሐሙስን
በመጾማችን ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል፡፡ በዚህም የጾምና የበዓል ማክበር ሥራ ይከናወናል፡፡ የጥምቀትን ዋዜማ ጥሉላት መባልዕትን መተው ነው፡፡ ይህንንም እንደ ዘይቤው ገሀድ ይለዋል፣ መገለጫ፣ ግልጥ፣ ይፋ መሆን ማለት ነው፡፡
እንዲሁም ጋድ ይለዋል፣ ለውጥ፣ ልዋጭ ማለት ነው፡፡ ጥምቀት ረቡዕ ዓርብ ሲውል በዚያ ለውጥ ማክሰኞ ሐሙስ ይጾማልና ጋድ አለው፡፡ እንዲሁም አንድ ጊዜ ሲጾም አንድ ጊዜ ሲቀር
እንዳይረሳና ቅዳሜ ወይም እሑድ በሰንበት ቀን ይጾሙ ዘንድ አይቻልም፣ ነገር ግን እህል ውኃ እንጂ ጥሉላት ከመብላት መጠበቅ ይገባል፡፡
ልደት የሚውልባቸው ረቡዕና ዓርብ ቢሆኑ የፍሥክ /
የሚበላባቸው/ ቀናት ሆነው እንዲከበሩ ሐዋርያት ያዘዙ ቢሆንም በዋዜማው የሚገኙት ማክሰኞና ሐሙስ ከጾመ ነቢያት ጋር የተያያዙ ስለሆኑ መጾማቸው ግድ ነው፡፡ ሆኖም የነቢያትን ጾም
የማይጾሙ ሰዎች በመላው የጾሙ ቀናት ሲበሉ ቆይተው
በዋዜማው ብቻ ገሀድ ነው ብለው ይጾማሉ፡፡ ነገር ግን ይሄ ትክክል አይደለም። ጾሙ የጥምቀት ብቻ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ አባቶቻችን በፆም በጸሎት በረከት እንዳገኙ እኛም ከእግዚአብሔር በረከት እናገኛለን እና መፆምን ቸል አንበል ለዚህም አምላካችን ይርዳን አሜን፡
(ምንጭ ከገድላት አንደበት)

#ጾመገሀድ #በየኔታ_ዘለዓለም_ሐዲስ
ከዘጠኙ ዓበይት የጌታ በዓላት ሁለቱ የልደትና የጥምቀት በዓላት ተጠቃሾች ናቸው በሁለቱ በዓላት ቀን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በኀዘን ማሳለፍ እንደሌለበት ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራሉ ምክንያቱም የክርስቶስ ልደትና ጥምቀት የዕዳ ደብዳቤያችን የተቀደደባቸው የድኅነታችን መሠረት የተጣለባቸው ዐበይት በዓላት ስለሆኑ ነው።
እነዚህ በዓላት በረቡዕና በዓርብ ቀን ከዋሉ አስቀድመን በዋዜማው ለውጥ አድርገን እንጾማቸዋለን ልደት ረቡዕ ከሆነ ማግሰኞ በዋዜማው፣ ዓርብ ከሆነ ሐሙስ በዋዜማው እስከምሽቱ አንድ ሰዓት (13 ሰዓት) እንጾማቸዋለን በሌሎችም ቀናት በዋዜማቸው በየዓመቱ ይጾማሉ ቀናቱ ሁለት ቢሆኑም ቁጥራቸው ግን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተብለው ነው የሚቆጠሩት፡፡
ገሀድ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት ገሀድና ጋድ፡፡ #ገሀድ ማለት መገለጥ መታየት መታወቅ ማለት ነው ተገለጠ ታየ ታወቀ የተባለውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ምንም ከዚያ በፊት አምላክነቱ የተገለጠባቸው ብዙ መንገዶችና ተአምራት ቢኖሩም አብ በደመና ሁኖ የምወደው ልጄ ይህ ነው በማለት፣ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በመቀመጥ የክርስቶስ አምላክነት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ ገሀድ መገለጥ ተብሎ ተሰይሟል።
በሌላም በኩል #ጋድ ማለት ለውጥ ማለት ነው ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዓርብ ሲሆኑ ለውጥ ሁኖ የሚጾምበት ማለት ነው ስለዚህ ገሀድ ስንል የክርስቶስን አምላክነት በዕለተ ጥምቀት መገለጥ፣ ጋድ ስንል ደግሞ ለዓርብና ለረቡዕ ጾም ለውጥ ሁኖ የተጾመውን ጾም ማለታችን ነው፡፡ ይህንን ጾም ጥር 10 ቀን የሚነበበው ስንክሳር እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡፡
ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ከመ ይደሉ ንጹም እሎንተ ክልኤተ ዕለታተ ዘእምቅድመ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት እስመ እላ ዕለታት ህየንቴሆሙ ለረቡዕ ወዓርብ ሶበ ይከውን ላዕሌሆሙ በዓለ ልደት ወጥምቀት ወበዝንቱ ይትፌጸም ለነ ክልኤቱ ግብር ግብረ ጾም ወግብረ በዓል ወከመዝ ሥሩዕ ውስተ አብያተ ክርስቲያኖሙ ለግብፃውያን
ወለእመ ኮነ ዕለተ በይረሙን ዘውእቱ አስተርእዮ በዕለተ እሑድ አው በዕለተ ሰንበተ አይሑድ ይጹሙ በዕለተ ዐርብ እምቅድሜሁ እስከ ምሴት በከመ ተናገርነ ቅድመ ወለእመ ኮነ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት በዕለተ ሰኑይ ኢይትከሀል ከመ ይጹሙ በዕለተ ሰንበት ዳዕሙ ይትዐቀቡ እምነ በሊዕ ጥሉላተ፡፡
ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው በይረሙን (መገለጥ፣ ገሀድ) በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥር ቀን ነው በዋዜማው ዓርብ እስከምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ በማለት ይገልጸዋል፡፡
ከላይ እንዳየነው ጥምቀት ወይም ልደት እሑድና ቅዳሜ ከዋሉ ጾሙ መጀመር ያለበት ዓርብ መሆኑን ተመልክተናል ይህንም መነሻ በማድረግ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት ሰኞ ሲሆን ዓርብ እስከ አንድ ሰዓት፣ ቅዳሜ እስከ ስድስት፣ እሑድ እስከ ቅዳሴ መውጫ እስከ ሦስት በመቁጠር የጾሙን ሰዓት 13 ሰዓት ያደርጉታል ይህም ከላይ የተገለጠውን ስንክሳር መነሻ በማድረግ የመሚናገሩት ስለሆነ አክብረን እንቀበለዋለን ቅዳሜ እስከ ስድስት ለመጾሙም ሃይ ምዕ 20 ተጠቃሽ ነው።
በሌላ በኩልም ጋድ አንድ ቀን ነው ሰኞ ሲሆን እሑድን ብቻ ከጥሉላት እንከለከላለን እንጅ ቅዳሜን አይጨምርም በማለት ይህን የሚቃወሙ አሉ ስንክሳር የተናገረውን ምን እናድርገው ተብለው ሲጠየቁም ስንክሳር የታሪክ እንጅ የሥርዓት መጽሐፍ አይደለም የሚል መልስ ነው የሚሰጡት፡፡
ይህ ጥያቄ ወደሌሎች ሊቃውንት ሲቀርብ የሚሰጡት መልስ ደግሞ ስንክሳር ታሪክ ብቻ ሳይሆን ሥርዓትም የተካተተበት መጽሐፍ መሆኑን ይናገራሉ በእርግጥ ስንክሳር ማለት እስትጉቡእ ስብስብ ማለት ስለሆነ ሥርዓተ ቤተ ክርስተቲያንን ከሠሩ አበው ታሪክ የተሰበሰበ መሆኑን መዘንጋት የለብንም ከላይም እንዳየነው ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ስለዚህ አባቶቻችን አዘዙን በማለት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጻፉ አበው አዘዙን አለ እንጅ ስንክሳርን የጻፉ ሰዎች የራሳቸውን ሐሳብ ያንጸባረቁበት አይደለም ስንክሳርም ቢሆን ምንም ቁጥሩ ከአዋልድ መጻሕፍት ቢሆን የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ነውና ጥምቀትና ልደት ሰኞ ከሆኑ ቅዳሜና እሑድን ከጥሉላት ተከልክለን ቅዳሜንም እስከ ስድስት ሰዓት ጹመን የአበውን ትዕዛዝ ማክበር አለብን፡፡
በሌላም በኩል ጋድ አንድ ነው እሱም የጥምቀት ዋዜማ ብቻ ነው የልደት ዋዜማ የለውም የሚሉም አሉ እንዲህ ለሚሉት መልሱ አጭር ነው ጾመ ነቢያት ስንት ነው የሚል ጥያቄ ማንሣት ነው እንደሚታወቀው ጾመ ነቢያትን ስንጾም ቀናቱ አርባ አራት ናቸው 40 ጾመ ነቢያት፣ 3ቱ የፊልጶስ ደቀ መዛሙርት የጾሙትና አብርሐም ሦርያዊ ተራራ ያፈለሰበት ጾም፣ አንዱ ጾመ ገሀድ ነው ስለዚህ በበዓለ ልደት ዋዜማ የምንጾመው ገሀድ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡
ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በተግሳፁ አንዳስቀመጠው "ስለ ፆም ክርክር በተነሳ ጊዜ ሁሌም ቢሆን ለፆም አድሉ "
"" መልሱ እንዲህ ከምስክር መምህራን ሲሆን ይሻላል፡፡ እኛ ከምንናገረው፡፡
የኔታ ዘለዓለም ሐዲስ ማለት የክቡር ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ምክትልና የ፬ቱ መጻሕፍተ ትርጓሜ መምህር ናቸው፡፡ (እንዲያው የኔ ብጤ የፌስቡክ አርበኛ እንዳይመስሉህ ብዬ ነው!)
DN YORDANOS ABEBE
❤️ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ❤️
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

ቂርቆስና ኢየሉጣ በሰማዕትነት የጸኑ ቅዱሳን
በዛሬ ዕለት ቅዱስ ቂርቆስ ከእናጹ ጋር ሰማዕትነት ተቀብለው ከዚህ ዓለም የተለዩበት ነው። አገራቸው አንጌቤን ነው። መምለኬ ጣዖት የነበረው የአገራቸው ንጉሥ እለ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን “ለጣዖቴ ስገጂ” ባላት ጊዜ ሰማይንና ምድርን ለፈጠረው ለእግዚአብሔር እንጂ ለጣዖት አልሰግድም አለችው። ኢየሉጣም የሦስት ዓመት ሕፃን ፈልግና እርሱ የተናገረውን እፈጽማለሁ አለች። ንጉሡም የሦስት ዓመት ልጅ ፈልጉ ብሎ አዘዘ። ወታደሮቹ ሕፃን ሲፈልጉ ከከተማ ውጭ ቅዱስ ቂርቆስን አግኝተው ወደ ንጉሡ ወሰዱት። ንጉሡ ሊሸነግለው ቢፈልግም ቅዱስ ቂርቆስ ግን ለጣዖት መስገድ እንደማይገባ ነገረው።
ቅዱስ ቂርቆስም በከሐዲው ንጉሥ ፊት የአምላኩን ክብር ገለጠ። ንጉሡ እለ እስክንድሮስ ቂርቆስና ኢየሉጣ የሚሰቃዩበትን መሣሪያ እንዲዘጋጅ አዘዘ። ወታደሮችም ማሰቃያ መሣሪያው ተሠርቶ እስከሚያልቅ ቂርቆስንና እናቱን ኢየሉጣን ከእስር ቤት አስገቧቸው፡፡ የተዘጋጀውን ማሰቃያ መሣሪያ ስትመለከት ቅድስት ኢየሉጣ በጣም ስለፈራች ንጉሡ አድርጊያ ያላትን ለመፈጸም ደርሳ ነበር። በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቂርቆስ"እናቴ ሆይ የተዘጋጀውን መሣሪያ አትፍሪ” በማለት አረጋጋት። እናቱን ከማረጋጋት በተጨማሪ የእናቱን ልቡና እንዲያጸናላት እግዚአብሔርን በጸሎት ጠየቀው። እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ፍርሃቷን አስወገደላት። ቅድስት ኢየሉጣም “ልጄ ስትሆን የጽድቅ መሪ ሆንከኝ። ለመንግሥተ ሰማያት አበቃኸኝ” አለችው። ሁለቱ ቅዱሳን እጅ ለእጅ ተያይዘው ወደ ነደደው እሳት ቢገቡም እሳቱ አልጎዳቸውም።
ሕፃኑ ቂርቆስና ኢየሉጣ ለብዙ ጊዜ መከራ ሲቀበሉ ቆዩ። በመጨረሻም ተጋድሏቸውን ፈጽመው ጥር 15 ቀን ሰማዕትነትን ተቀበሉ፡፡ ከቅዱሱ አንገት ደም፣ ውኃና ወተት ወጣ። ስለተጋድሎውም ሦስት አክሊሎች ወረዱለት፡፡ ጌታችንም ቅዱሱ የተቀበለውን የመከራ ጽናት፣ የትዕግሥቱን ብዛት አይቶ ቃልኪዳን ገባለት። “ስምህ በተጠራበት፣ ቤተመቅደስህ በታነፀበት፣ ሥዕልህ ባለበት ቦታ ሁሉ የሕፃናት ሞት፣ የእንስሳት እልቂት፣ የእህል መታጣት፣ አባር፣ ቸነፈር አይደርስም” አለው፡፡ በዘመኑም ዓሥራ አንድ ሺሕ አራት የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር አብረው ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡ የቅዱስ ቂርቆስ አብረውት ሰማዕትነትን የተቀበሉ በረከት ይደርብን፤ ጸሎታቸው በሃይማኖት እንድንጸና ያግዘን። አሜን!!

+ አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ! +
እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ መሐሪ ነው ፣ ይቅር ባይ ነው፡፡ ፍቅር ይቆጣል ወይ? ይቅር ባይስ ይቀጣል ወይ? ብዙዎቻችን ስለ ክርስቶስ ሲነገረን መሐሪነቱና ፍቅሩ ብቻ ቢነገረን አንጠላም፡፡ ጨርሶ የማንፈራው እግዚአብሔር እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አታድርግ! የሚለን ሲመጣ ‘አትፍረድ’ እንላለን ፤ ቆይተን ግን የሰማዩን ዳኝም አትፍረድ ማለት ይቃጣናል፡፡ ቅጣት የሌለበት ክርስትና እንሻለን፡፡
ይህ ዓይነቱን ክርስትና ‘ጣፋጭ ክርስትና’ {የስኳር ክርስትና ይሉታል} ምንም ምሬት የሌለበት ሁሌም ማር ማር የሚል ሕይወት አድርገው ክርስትናን የሚሰብኩም ብዙ ናቸው፡፡ ‘አይዞህ ብትታመም ትፈወሳለህ ፣ ቤትህ ይሞላል ፣ ቀዳዳህ ይደፈናል ፣ ብትበድልም አትቀጣም’ ብቻ የሚሉ ስብከቶች የስኳር ክርስትና ስብከቶች ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ የሚያጮሁ ሰዎች ክርስቶስ ‘የምድር ጨው ናችሁ’ ያለውን ትተው የምድር ስኳር ለመሆንና ዓለምን ለማስደሰት የሚፈልጉ ናቸው፡፡
በእርግጥ እግዚአብሔር ይቆጣል ወይ? አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ
‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6
‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10
‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’ መዝ. 90፡7
እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡
ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ "ቁጣው ለዘላለም ነውና" አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡
‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12
‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5
‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31
የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን መሐሪ ነህና ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’ ብሎ የፈጣሪን ቁጣ አበረደ፡፡ /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’ ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24
አንድ ሠዓሊ በጣም ብዙ ደክሞ የተጠበበትን ሥዕሉን የፈለገ ቢበሳጭ ለረዥም ጊዜ ያንን ሥዕል ለመሳል የተጠበበትን ጥበብ አስቦ ሥዕሉን ወደ እሳት አይጨምረውም፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ሲል ይለምናል ‘ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋል ወይ? [ጌታ ሆይ እኔን ስትፈጥር የተጠበብክበትን] የቀደመ ጥበብህን አስብ እንጂ! አስበህም ማረኝ! [ያጠፋዖኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ ፤ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ]
ይቅርታውን በንስሓ ለሚለምኑ ሁሉ ምሕረቱ ቅርብ ነው፡፡ በቀኝና በግራው ወንበዴዎች በተሰቀሉበት በዕለተ አርብ የግራው ወንበዴ ሲሰድበው ጌታ መልስ አልሠጠም፡፡ የቀኙ ወንበዴ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ በገነት ትሆናለህ አለው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ እርሱ የራበው ሰው ለምግብ የሚቸኩለውን ያህል ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡ ‘ምሕረትን ይወድዳልና ቁጣውንም ለዘላለም አይጠብቅም ተመልሶ ይምረናል ፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ፤ ኃጢአታችንንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል’ ሚክ 7፡18
ልጆች ሳለን ጥፋት ስናጠፋ ከወላጆቻችን እንደበቃለን፡፡በተደበቅንበት ሰዓት ውስጣችን በፍርሃት ይርዳል፡፡ ‘ዛሬ ገደለኝ’ ‘ዛሬ መሞቴ ነው’ ብለን እንጨነቃለን፡፡ የሚደርስብንን ቅጣት እጅግ አጋንነን ከመፍራታችን የተነሣ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠን አንጠላም፡፡ በዚያ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ግን ወላጆቻችንም እስኪያገኙን ይጨንነቃሉ፡፡ እግዚአብሔርም እንዲህ ነው፡፡ አጥፍቶ በገነት ዛፎች መካከል የተሸሸገ አዳምን ወዴት ነህ ብሎ የፈለገ እርሱ እኛንም ይፈልገናል፡፡ አዳም ከገነት ሳይባረር ገነት ውስጥ እንደጠፋ ፈጣሪ ሳያባርረን ራሳችንን በኃጢአት ተሸማቅቀን ያባረርን እኛን ይፈልገናል፡፡ እርሱ ስለመጥፋትህ ይጨነቃል አንተ ‘ዛሬስ አይምረኝም’ ትላለህ፡፡
የሚገርመው በጥፋታችን ከተደበቅንበት ወላጆቻችን ካገኙን በኋላ ሁለተኛው ዙር ጭንቀታችን ‘ምን አጥፍተህ ነው የተደበቅከው’ መባል ነው፡፡ ጥፋታችንን ሲያውጣጡን እንንቀጠቀጣለን፡፡ ያጠፋነውን ስለምናውቀው ስንት እንደሚያስገርፈንም እናውቀዋለን፡፡ ‘ብትናገር ይሻላል? ግዴለህም!’ ብለው አግባብተውም አስፈራርተውም ወላጆቻችን ጥፋታችንን ያውጣጡናል፡፡ እየፈራን ያጠፋነውን ጥፋት ስንናዘዝ ግን ወላጆቻችን በጥፋታችን ቅጥል ብለው ‘አልመታህም ተናገር’ ያሉንን ረስተው የዱላ ዝናም ያዘንቡብናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ጥፋትህን ስትነግረው ቁጣው የሚገነፍል አባት አይደለም፡፡
’’ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው’ 1ዮሐ 1፡9