❖❖❖❖❖በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ❖❖❖❖❖
❖እንኳን ለእመቤታችን ንጽሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
❖❖ዕረፍተ_ድንግል❖❖
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር:: ከነገር ሁሉ በፊት እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር::
ዓለም ተፈጥሮ: አዳምና ሔዋን ስተው: መርገመ ሥጋና መርገመ ነፍስ አግኝቷቸው: በኃዘን ንስሃ ቢገቡ "እትወለድ እም ወለተ ወለትከ - ከ5 ቀን ተኩል (5500 ዘመናት) በሁዋላ ካንተ ባሕርይ ከምትገኝ ንጽሕት ዘር ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ተስፋ ድኅነት ሰጠው::
ከአዳም አንስቶ ለ5500 ዓመታት አበው: ነቢያትና ካህናት ስለ ድንግል ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናገሩ:: መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት:: ምሳሌም መሰሉላት:: ከሩቅ ዘመን ሁነውም ሊያገኟት እየተመኙ እጅ ነሷት::
"እምርሑቅሰ ርእይዋ: ወተአምኅዋ" እንዲል::
የድንግል ማርያም ሐረገ ትውልድ
- ከአዳም በሴት
- ከያሬድ በሔኖክ
- ከኖኅ በሴም
- ከአብርሃም በይስሐቅ
- ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ
- ከይሁዳ በእሴይ: በዳዊት: በሰሎሞንና በሕዝቅያስ ወርዳ ከኢያቄም ትደርሳለች::
ከሌዊ ደግሞ በአሮን: አልዓዛር: ፊንሐስ: ቴክታና በጥሪቃ አድርጋ ከሐና ትደርሳለች::
አባታችን አዳም ከገነት በወጣ በ5,485 ዓመት ወላዲተ አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ ኢያቄም ወሐና ትወለዳለች:: (ኢሳ. 1:9, መኃ. 4:7) "ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ:: (ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራ)
ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለ3 ዓመታት ቆይታ ወደ ቤተ መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለ12 ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና እያገለገለች: እርሷን ደግሞ መላእክተ ብርሃን እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየመገቧት ኑራለች:: 15 ዓመት በሞላት ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት::
በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማሕጸንዋ ጸነሰችው:: ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር: ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ:: (ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ለብሐዊ)
ወልደ እግዚአብሔርን ለ9 ወራት ከ5 ቀናት ጸንሳ: እንበለ ተፈትሆ (በድንግልና) ወለደችው:: (ኢሳ. 7:14) "ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በገሊላ ለ2 ዓመታት ቆዩ::
አርዌ ሔሮድስ እገድላለሁ ብሎ በተነሳበት ወቅትም ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም: በላበትና በድካም: በዕንባና በኃዘን ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ከገሊላ እስከ ኢትዮዽያ ተሰዳለች:: ልጇ ጌታችን 5 ዓመት ከ6 ወር ሲሆነው: ለድንግል ደግሞ 21 ዓመት ከ3 ወር ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ::
በናዝሬትም ለ24 ዓመታት ከ6 ወራት ልጇን ክርስቶስን እያሳደገች: ነዳያንን እያሰበች ኑራለች:: እርሷ 45 ዓመት ልጇ 30 ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን ተጠምቆ በጉባኤ ትምሕርት: ተአምራት ጀመረ:: ለ3 ዓመታት ከ3 ወራትም ከዋለበት እየዋለች: ካደረበትም እያደረች ትምሕርቱን ሰማች::
የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም የመጨረሻውን ፍጹም ሐዘን አስተናገደች:: አንጀቷ በኃዘን ተቃጠለ:: በነፍሷም ሰይፍ አለፈ:: (ሉቃ. 2:35) ጌታ በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሳኤውን አየች:: ለ40 ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች::
ከልጇ ዕርገት በሁዋላ በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትን ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች:: በጽርሐ ጽዮንም ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ15 ዓመታት ኖረች:: በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ: ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል: ሐዋርያትን ስታጽናና: ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች::
ዕድሜዋ 64 በደረሰ ጊዜ ጥር 21 ቀን መድኃኒታችን አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ:: ኢየሩሳሌምን ጨነቃት:: አካባቢውም በፈውስ ተሞላ:: በዓለም ላይም በጐ መዓዛ ወረደ:: እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት ባልተደረገ: ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ: ክብርና ተአምራት ዐረፈች:: ሞቷ ብዙዎችን አስደንቁአል::
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ::
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ::" እንዲል::
ከዚህ በሁዋላ መላእክት እየዘመሩ: ሐዋርያቱም እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ: በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው ወሰዱ:: ይሕንን ሊቃውንት:-
"ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ::
እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ::
ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ" ሲሉ ይገልጡታል::
በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ ቅዱስ ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው) እነርሱን ቀጥቶ: እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል:: በዚያም መላእክት እያመሰገኗት ለ205 ቀናት ቆይታለች::
ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ 1 ሱባኤ ጀመሩ:: 2ኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል ማርያምን ንጹሕ ሥጋ ሰጣቸው:: እየዘመሩም በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል::
በ3ኛው ቀን (ነሐሴ 16) እንደ ልጇ ባለ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: ትንሳኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ አይቶ: መግነዟን ተቀብሏል:: ሐዋርያቱም መግነዟን ለበረከት ተካፍለው: እንደ ገና በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ገቡ::
ለ2 ሳምንታት ቆይተው: ሁሉንም ወደ ሰማይ አወጣቸው:: በፍጡር አንደበት ተከናውኖ የማይነገር ተድላ: ደስታና ምሥጢርንም አዩ:: ጌታ ራሱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የበዓሉን ቃል ኪዳን ሰምተው: ከድንግል ተባርከው ወደ ደብረ ዘይት ተመልሰዋል::
ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን: ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::
#ቅዱስ_ጐርጐርዮስ_ሊቅ
ለዚህ ቅዱስ አባት ብጹዕ መባል ተገብቷል:: ክቡር: ምስጉን: ንዑድ ሰው ነውና:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቂሣርያ ቀዸዶቅያ የተወለደው ቅዱሱ ሰው ለደሴተ ኑሲስ ብርሃኗ ነው:: አባቱ ኤስድሮስ: እናቱ ኤሚሊያ: ወንድሞቹ ቅዱሳን "ባስልዮስ: ዼጥሮስ: መክርዮስና መካርዮስ" ይባላሉ::
የተቀደሰች እህቱም ማቅሪና ትባላለች:: ከዚህ የተባረከ ቤተሰብ ለቅድስና ያልበቃ አንድም ሰው የለም:: ሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስም ከማር በጣፈጠ ዜና ሕይወቱ እንደ ተጻፈው:-
በልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል::
ሥጋውያን ጠቢባንን ያሳፍር ዘንድም የግሪክን ፍልሥፍና በልኩ ተምሯል:: በታላቅ ወንድሙ ቅዱስ ባስልዮስ መሪነት ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል:: በመንኖ ጥሪት ተመስግኗል::
ተገብቶትም በኑሲስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኗል:: እርሱ ሲሔድ በከተማው የነበሩ ክርስቲያኖች 11 ብቻ የነበሩ ሲሆን እርሱ ሲያርፍ ክርስቶስን የማያመልኩ ሰዎች ቁጥር 11 ብቻ ነበር:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ ፍጹም ሊቅ ነበርና ከቁጥር የበዙ ድርሳናትን ደርሷል:: ታላቁን ጉባኤ ቁስጥንጥንያን (በ381 ዓ/ም) መርቷል:: ብዙ መናፍቃንንም አሳፍሯል::
ከንጽሕናው የተነሳ መላእክት ያቅፉት: እመ ብርሃንም ትገለጥለት ነበር:: ለ33 ዓመታት እንደ ሐዋርያት ኑሮ በዚህ ቀን ድንግል ጠራችው:: ቀድሶ አቁርቦ: ሕዝቡን አሰናብቶ: የቤተ መቅደሱን ምሰሶ እንደ ተደገፈ ዐርፎ ተገኝቷል:: በዝማሬና በፍቅር ቀብረውታል::
@gibi_gubae

++ አበው ስለ እመቤታችን ዕረፍት እንዲህ አሉ ++
‹ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች 'ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
‹‹ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው … በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው … በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው … በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ … አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [የተለያየ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ›› ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ (Homily on the Dormition)
‹‹የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በሥጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍትና እርስዋን የሚመለከቱ የመጨረሻዎቹን ምሥጢራትም ማየት ነበረባቸው፡፡ ይህም የሆነው የክርስቶስ የዕርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው ዓለም ለሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው›› ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ (aka Doctor of Dormition)
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
አስተ ር እዮ ማርያም
ጎተበርግ ስዊድን

VALENTINE'S DAY
ሼር በማድረግ ትውልዱን ከጥፋት እንታደግ❗
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ቤዛ ሆኖ በፍቅሩ የገዛን እጃችንን ለጣኦት እንድንሰጥ አይደለም ብዙ ዋጋ የተከፈለብን እስከ ሞት እንከን በሌለው ፍቅሩ የወደደን መንግስቱን እንድንወርስ እንጂ እንድንጠፋ አይደለም።
የቫላንታይ ቀን ድብቅ እውነታ ስንቶቻችን እናውቃለን? ይህን የቫላታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) ብለን ስንቶቻችን ነን የምናከብረው ? ወይስ ሰው ስላከበረውና የስልጣኔ መገለጫ መስሎን ነው የምናከብረው ???
ከክርስቶስ ልደት በፊት በባቢሎን ፤ቤልዘቡል ፤በግሪክ ፓን ፤ ሮማ ሞሎቅ ፤ በላቲን ሳተርን ለሚባሉት ሰይጣኖች ያላገቡ ሴቶች ደም የሚፈስላቸው ቀይ ልብስ የሚለበስላቸው ጣኦቶች ናቸው ይህ ዛሬ ቫለንታይን ተብሎ የመጣው ማለት ነው።
የሚገርመው ደሞ ሴቶቹ በዚህ ቀን ለመደፈር ብለው እራቁታቸውን ጫካ መግባታቸው ነው በዚህ ቀን የተደፈረች እና ደሟን ያፈሰሰች ሴትም ሆነ ወንድ በጣኦቱ የተመረጠ እና የተባረከ ነው መባሉ ነው ይበልጥ ነገሩን ሰይጣናዊ የሚያደርገው።
ግሪክ አርኬዲያ ብለው በሚጠሩት አስቀያሚ ትርጉም ባለው ተራራቸው ላይ በዚህ ቀን ላይ ነው ያላገቡ ወንድ እና ሴቶቻቸውን ጣኦቱ ስር ወሲብ በመፈጸም ገላቸውን አርክሰው ለሰይጣን የሚገብሩት።
ይህ የሰይጣን ቀን ነው ክርስትና ይሄን ትከለክላለች ታወግዛለች። (ሁሉም ቀን የእግዚአብሔር ነው ግብሩ ነው የሰይጣን የሚያደርገው)
ኢየሱስ ክርስቶስ ከመውለዱ ከዘመናት በፊት አረማውያን ሮማውያኖች Feb 14 ማታ እና ለ Feb 15 ንጋት አጥቢያ የተኩላ አዱኚ ለሚሉት ሉፐርካልያ (luperkalya ) ጣኦት የሚዘጋች ክብረ በአል ነው፡፡
ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ክርስትና ተቀብሎ እውነተኛ የጽድቅ ሃይማኖት መሆኑን በማውጁ ማንኛውም የጣኦት አምልኮ እንዲቀር ቢያስጠነቅቅም የተውሰኑ የሮማውያን ሰዎች ግን በአሉን ማክበር አልተውም።
እንዴት ይህ አረማዊ ባህል ቫለንታይን የሚል ሰያሜ ተሰጠው? ቫለንታይን የሚል ስም በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ስያሜ ነው፡፡ ቫለንታይን የጥንታዊ ታዋቂው ሉፐርኩስ ጣኦት ነው።
ሉፐርኩስ በግሪካዎያን ፓን (pan) ተብሎ ሚጠራው ከወገቡ በታች በግ አናቱ ላይ ቀንድ ያለው ጣኦት ነው። በጥንታውያን አይሁድ ደግሞ ይህ ፓን ባል (baal) በሚል ስያሜ ይታወቃል።
ጥንታውያን ሮማውያን ከባቢሎናውያን የቀዱት አረማዊ የልብ (heart) ምልክት ይጠቁማሉ፡፡ በባቢሎናውያን ባል (bal) ልብ የሚል ፍች ነው ያለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህ አረማዊ የልብ ምልክት ለቫለንታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) የምንለው መግለጫነት እንጠቀምበታለን። ባል የባቢሎናውያን ጣኦት ነበር።
በዚህ የሃጥያት ቀን በትንቹ ይህ ይሆናል
1. በዚህ ቀን February 14 በብዙ የሚቆጠሩ እህቶቻችንን ክብረ ንጽህናቸውን (ድንግልናቸውን) ያጣሉ❗
2. በርካታ ወጣቶች በስካር ምክንያት በሚያሽከረክሩት መኪና ህይወታቸውን እና አካላቸውን ያጣሉ❗
3. በአለማችን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የአልኮል መጠጥ ሽያጭ የሚከናወንበት ቀን ነው በአጠቃላይ የዝሙት እና ስካር መንፈስ የሚነግስበት በከፍተኛ ሁኔታ ሰይጣን በደም የሚረካበት ቀን ነው።
Valentine day ማለት ሰይጣን በጥልቅ እና ረቂቅ ሃሳብ ብዙዎችን የሚያጠምድበት ቀን ነው አስተውሉ ሰይጣን ከ7ሺህ አመት በላይ የክፋት ልምድ አለው።
እንግዲህ ምርጫው ያንተ/ቺ ነው :- የእግዚአብሔር ወይም የሰይጣን ልጅ መሆን???
" ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ። "
(ትንቢተ ሆሴዕ 4 : 6)
እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ያድለን። አሜን
ምንጭ : ዝማሬ ዳዊት ቻናል

የአለም እውነታወች
------------------------------------//
የሰው ዋጋው እየቀነሰየዶሮእናየእህልዋጋ
እየጨመረሲመጣ በርትተህፀልይ፡፡
የውሻቡችላእየተሸጠ ሰውንግነበነጻየሚፈልገው
ሲታጣ ዘመኑመክፋቱንአንተም አብረህመክፍትህን
እወቀው ፡፡
ስለብርቅየእንስሳትብዙዎችእያለቀሱይናገራሉ
በምግብእጥረትስለሚሞቱትህጻናትግንቃል
አይናገሩም ፡፡
ስለጠፈርሳይንስብዙይወራል(ይሰራል)የምድር
ኑሮግንሲተራመስያስተዋለየለም ፡፡
ስለወደቁሐውልቶችብዙይባላልበየጎዳናው ዳር
ስለወደቁትምስኪንህጻናትግንምንም አይባልም ፡፡
የለማኝገቢይጠናልይታወቃልየባለስልጣናት
ስርቆትግንታይቶእንዳልታየይታለፋል፡፡
ስለአየርመበከልዓለም በሙሉይጮሃልስለሰው
ልጆችመርከስግንዝም ይባላል፡፡
ውሾችእናድመቶችአልጋህላይእንዲዘሉ
እየፈቀድክድሆችግንየግቢህድንጋይላይእንዲቀመጡ
ባለመፍቀድህየፈጣሪህንምህረትጠይቅ፡፡
የፈጣሪስዕልእያልክስትስም ራሱፈጣሪአክብሮ
የፈጠረውንሰውንግንረግጠህበማለፍህየወጣልህ
አስመሳይመሆንህንእወቀው ፡፡
ከዚህአፍእናልብከተለያዩበትቲያትረኛማንነትህ
ፈጥነህውጣ ፡፡
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
------------------------------------//
የሰው ዋጋው እየቀነሰየዶሮእናየእህልዋጋ
እየጨመረሲመጣ በርትተህፀልይ፡፡
የውሻቡችላእየተሸጠ ሰውንግነበነጻየሚፈልገው
ሲታጣ ዘመኑመክፋቱንአንተም አብረህመክፍትህን
እወቀው ፡፡
ስለብርቅየእንስሳትብዙዎችእያለቀሱይናገራሉ
በምግብእጥረትስለሚሞቱትህጻናትግንቃል
አይናገሩም ፡፡
ስለጠፈርሳይንስብዙይወራል(ይሰራል)የምድር
ኑሮግንሲተራመስያስተዋለየለም ፡፡
ስለወደቁሐውልቶችብዙይባላልበየጎዳናው ዳር
ስለወደቁትምስኪንህጻናትግንምንም አይባልም ፡፡
የለማኝገቢይጠናልይታወቃልየባለስልጣናት
ስርቆትግንታይቶእንዳልታየይታለፋል፡፡
ስለአየርመበከልዓለም በሙሉይጮሃልስለሰው
ልጆችመርከስግንዝም ይባላል፡፡
ውሾችእናድመቶችአልጋህላይእንዲዘሉ
እየፈቀድክድሆችግንየግቢህድንጋይላይእንዲቀመጡ
ባለመፍቀድህየፈጣሪህንምህረትጠይቅ፡፡
የፈጣሪስዕልእያልክስትስም ራሱፈጣሪአክብሮ
የፈጠረውንሰውንግንረግጠህበማለፍህየወጣልህ
አስመሳይመሆንህንእወቀው ፡፡
ከዚህአፍእናልብከተለያዩበትቲያትረኛማንነትህ
ፈጥነህውጣ ፡፡
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
±±±ክብደት ለመቀነስ እንጹም!±±±
የታላቁ እስክንድር ሠራዊት ፋርስን /ፐርሺያን/ በድል እየተቆጣጠረ ነበር፡፡ አንድ ወሳኝ ቦታ ላይ ግን ወታደሮቹ እየተዳከሙ ሊሸነፉ ሆነ፡፡እነዚህ ወታደሮች ከዚህ ውጊያ
በፊት በነበራቸው ጦርነት ላይ የዘረፉትን ተሸክመው ስለነበር እንደልብ እንዳይንቀሳቀሱ ከብዷቸው በደንብ መዋጋት አቃታቸው፡፡
እስክንድር ይኼን ጊዜ የዘረፉትን ሁሉ አንድ ቦታ ላይ እንዲከምሩ አደረገና እሳት ለቀቀበት፡፡ ሁሉም ምርር ብለው ተበሳጩ፡፡ የንጉሡን ብልህነት የተረዱት ግን በኋላ ነው፡፡አንዱ ጸሐፊ ‹በፍጥነት እየሮጡ ሲዋጉ ክንፍ የተሠጣቸው ይመስሉ ነበር ›› ብሎ ጽፎአል፡፡ ድላቸውንም አረጋገጡ፡፡
እንደ አሜሪካ ባሉ ሀብታም ሀገራት ሁልጊዜ ከሚነሡችግሮች አንዱ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ነው፡፡ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በውፍረት ይቸገራሉ፡፡ ክብደታቸውንም ለመቀነስ ብዙ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ ፡፡ ለህክምናና ለአማካሪዎች ብዙ ገንዘብ ያወጣሉ፡
፡ አመጋገባቸውን ለመቀነስም ብዙ ትግል ያደርጋሉ፡፡ የስኳር ሕመም ፣ የልብ ሕመም ፣ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠንና ስትሮክ ያሰጋቸዋል፡፡ የሚሰቃዩትም ሆነ አመጋገባቸውን
መቆጣጠር የሚቸገሩት ከምግብ መከልከልን ስላልለመዱ ነው፡፡
ክርስቲያኖች የክርስቶስ ወታደሮች እንደመሆናችንከመንፈሳዊ ጠላታችን ከዲያቢሎስ ጋር በምናደርገው ውጊያ ላይ እንዳንቸገር የሚከብደንን ማንኛውንም ነገር ማስወገድ አለብን፡፡ ውጊያውን በሚገባ ለመዋጋት የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ እንዴት መታጠቅ እንዳለብን ማወቅ ያስፈልገናል፡፡ (ኤፌ. 6፡11-17) የውጊያችን መሪ ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በጾመና እኛንም እንድንጾም ባስተማረን ጊዜም ይህን ሃሳብ ነግሮናል፡፡ ከመጠን ያለፈ ምግብ ሆዳችንን ከሞላው ፣ ቁሳዊ ነገር ካበዛን ፣ በነፍሳችን ላይ ተጨማሪ ሸክም እንጨምራለን፡፡
በሰይጣን ወጥመድ ላይ የምናገኘውንም ድል ያስቀርብናል፡፡ ‹‹ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ ወገን ከጾምና ከጸሎትበቀር አይወጣም፡፡›› (ማቴ.17፡21)
መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲኖችን ከሯጮችም ጋርያመሳስላቸዋል፡፡ ሩጫን ለማሸነፍ
ደግሞ ወደ ኋላ የሚጎትተንን ‹ሸክምን ሁሉ ማስወገድ አለብን›› (ዕብ. 12፡1)
ይኼ ክብደት ገደብ የለሽ የሀብት ፍቅር ፣ በገንዘብ ፍቅር መማረክ ፣ ማለቂያ የሌለው እርካታን ፍለጋ ፣ ኃጢአት ለሆኑ ፍላጎቶች ባሪያ መሆን ፣ ሥጋዊ ምኞትና ስስት ሊሆንም ይችላል፡፡
አዎ ፤ መልካሙን የእምነት ውጊያ ልንዋጋና መንፈሳዊውን ሩጫ በጽናት ለመሮጥ የምናስብ ከሆነ መሪ ቃላችን መሆን ያለበት ‹ክብደት መቀነስ› ወይም ‹ጾም› የሚለው ነው፡፡‹‹እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና
ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ
ተቀምጦአልና።›› ዕብ. 12፡1
‹‹እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ ፤ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁምዕረፍት
ታገኛላችሁ ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።›› [ማቴ.11፡28]
ዲ\ን ሄኖክ ኃይሌ

+ ዕጣንና አለመታዘዝ +
ዕጣን መቅሠፍትን ያርቃል : ደዌን ይገሥጻል::
ሳይንሱ ሳይቀር ድብታን (depression) ያርቃል እስከማለት የደረሱ ጥናታዊ ምስክርነቶችን ይሠጥበታል::
ዕጣንን መቅሠፍት እንዲያርቅ የሚያደርገው ንጥረ ነገሩ ብቻ ሳይሆን በካህናት የሚደረገው ጸሎተ ዕጣን ነው::
በእስራኤላውያን ታሪክ የተፈጸመው ይህ ነው::
"አሮንም ሙሴ እንደ ተናገረው ጥናውን ወስዶ ወደ ጉባኤው መካከል ሮጠ፤ እነሆም፥ መቅሠፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር፤ ዕጣንም ጨመረ፥ ለሕዝቡም አስተሰረየላቸው" ኦሪት ዘኍልቍ 16 :47
በዕጣን ምክንያት ብዙ ሺህ ሰው ካለቀበት መቅሠፍት እስራኤላውያን ዳኑ:: ይህ ታሪክ ዕጣን መቅሠፍት እንደሚያርቅ ያሳያል::
በተያያዘ ዜና :-
የብዙ ሰው ሞት ምክንያት የነበረው መቅሠፍት ግን መነሻው ምን ነበር? ስንል የሚከተሉት ነጥቦችን ማስተዋል ይገባናል::
1ኛ የመቅሠፍቱ ዋነኛ መነሻ ቆሬ ዳታንና አቤሮን የተባሉ ሰዎች ለሌዋውያኑ ካህናት ለሙሴና ለአሮን ትእዛዝ አንገዛም ማለታቸውና ክህነትን በማቃለላቸው ነበር
2ኛ ካህን ከመናቅ አልፈው እኛ ከማን እናንሳለን ብለው ያለ ሥልጣናቸው እሳት አንድደው ዕጣን ለማጠን በመሞከራቸው የተነሣ መቅሠፍት ነበር
3ኛ መቅሠፍቱ ከመነሣቱ በፊት እግዚአብሔር ለሕዝቡ መቅሠፍቱ እንዳይነካችሁ ፈቀቅ በሉ ብሎ ነበር:: ከዚያ መቅሠፍት ከዳኑት መካከል የሚበዙት ይህን ትእዛዝ ከሙሴ አፍ ሲሰሙ አክብረው መሸሽ የቻሉ ሰዎች ብቻ ነበሩ:: አልሰማ ያሉና ከኑግ ጋር የተገኙ ሰሊጦች ግን አብረው ተወቅጠዋል::
የአሮንን ክህነት የናቁት ግን ዕጣኑን ራሳቸው ይዘው ቢያጥኑም መቅሠፍቱ የጀመረው ከእነርሱና ከቤተሰባቸው ነበር:: ይህ እንግዲህ ቃል በቃል የተጻፈው ነው::
አባቶቻችንን እንስማ! በእኛ ቸልታ ምክንያትም ብዙ ሊቃውንትዋ አረጋውያን የሆኑላትን ቤተ ክርስቲያን አንጉዳት:: ታምመህ ከምትሰቃይና ለሌሎችም ሥቃይ ምክንያት ከምትሆን "ሳትታመም ዳን" "ተፈወስ እምቅድመ ትሕምም":: ተጠንቅቆ ከቤቱ የሚውለውን ሰው አንተ ወጥተህ በሽታ ሸምተህለት ማምጣትህ አያሳዝንም?
"አዬ ጉድ! ጠቢብ ከሰነፍ ጋር እንዴት ይሞታል!" መክ 2:16
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት ቂርቆስ 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ ባሕርን ተናገረው
እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት
ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር
እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር"
ልብ አድርጉ :-
ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል
ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል
ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል:: ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው::
ይህንንም እናስታውስ
ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው::
ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :-
"ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም"
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር 23 2013 ዓ ም
Translated from Mighty arrows publication

🕯"አቤቱ በምድር ላይ ብዙ ዘመን ከመኖር በገነት አንዲት ቀን ደስ መሰኘት ይሻላል"
መጽሐፈ መቃብያን ካልእ 13፥1_6
"የአመኑ እሊያ አምስቱ የመቃቢስ ልጆች ግን ለጣዖት የተሠዋውን መሥዋዕት መብላትን እምቢ ብለው ሰውነታቸውን ለሞት ሰጡ።
ይህ ዓለም እንደሚያልፍ እንደሚያረጅ ተድላውም ለዘለዓለም እንደማይኖር ዐውቀው በሰማይ ከአለው እሳት ይድኑ ዘንድ ሰውነታቸውን ለእሳት ሰጡ። ሰውን ከመገዳደር እግዚአብሔርን መገዳደር እንደሚከፋ፥ከንጉሥም ቁጣ የእግዚአብሔር ቁጣ እንደሚከፋ አውቀዋልና።
"አቤቱ በምድር ላይ ብዙ ዘመን ከመኖር በገነት አንዲት ቀን ደስ መሰኘት ይሻላል፤ ከብዙ ዘመኖችም የአንዲት ሰዓት ይቅርታህ ይሻላል፤ የእኛ የሰዎች ዘመናችን ምንድን ነው? እንደጥላ የሚያልፍ፥በእሳት ዳርም አንደአለ ሰው አይደለምን? አቤቱ አንተ ግን ለዘለዓለም ትኖራለህ ፤ ዘመንህም የማይፈፀም ነው፤ ስም አጠራርህም ልጅ ልጅ ነው።"

ጥያቄ
በሉቃስ ወንጌል "መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፡፡ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል" ሉቃ 1:35 ላይ ይጸልልሻል የተባለው ""መንፈስቅዱስ በማርያም ላይ አስቀድሞ መምጣት ያስፈለገበት ምክንያት ለመጽለል ( ለመጋረድ፣ ለማጥለል) ሲሆን ቀጥሎም ከተጋረደው ወይም ከተጠለለው ማንነቷ ውስጥ የሚወለደው ክርስቶስ " ቅዱሱ" የእግዚአብሄር ልጅ እንዲሆንና እንዲባል ነው።"" በማለት እመቤታችን ኃጢአት ነበረባት በማለት ተቃዋሚ መናፍቃን ያስተምራሉ::
መልስ
👉 ቃሉን አስተውለን ከተመለከትነው እመቤታችን "ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል" ሉቃ. 1:34 በማለት ለጠየቀችው ጥያቄ ነው መልአኩ "መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፡፡ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል" ሉቃ 1:35 በማለት የመለሰው በደል ኖሮባት ከዚያ ሊያነጻት አይደለም፡፡ ኃጢአት እንደሌለባትማ ከፍ ብሎ በሉቃ. 1:28 ላይ "ጸጋን የሞላብሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፡፡ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት፡፡" በማለት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በረከት ሳይሆን መርገም በነበረበት ዘመን ብሩክት ብሎ አመስግኗታል፡፡ ጸጋ በጎደለበት ዘመን ጸጋን የተሞላሽ በማለት ኃጢአትና መርገም ያላገኛት እንደሆነች ተናግሯል፡፡
እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምስ "ከሴቶች ተለይታ ጸጋን የተመላችና ከሴቶች ተለይታ የተባረከች" ናት፡፡ ሊቃውንትም ይህን ክፍል "ያንቺማ ጽንስ መቼ እንደሌሎች ሴቶች ጽንስ ነዋ መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል ኃይለ ልዑል ወልድ ሥጋሽን ይለብሳል፡፡" በማለት ተርጉመውታል፡፡
ሁለተኛው ተቃዋሚዎች "ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ የሆነው መንፈስ ቅዱስ ወዳንቺ ይመጣል" የሚለው ቃል ከተነገረ በኋላ ነው በማለት ይህ ግን በባህሪይው ቅዱስ የሆነ ጌታ ቅድስናን ስጋ ከለበሰ በኋላ ነው ያገኘው የሚለው የክህደት ትምህርት ነው፡፡ "በመጀመርያ ቃል ነበር ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር፡፡ ቃልም እግዚአብሔር ነበር፡፡" ዮሐ 1:1 በማለት ቅድመ አለም ቃል (ወልድ) እግዚአብሔር እንደሆነ ተናግሯል፡፡ ቅድስናው የባህሪይው ከእመቤታችን ሲወለድ ያገኘው አልነበረም፡፡
የቀጠለ...👆👇👆👇
👉 ሌላው 'ጸለለ' ለሚለው ግዕዙ በራሱ ሁለት አይነት ፍቺ (ትርጉም) አለው ጠብቆና ሲላላ "ጸለለ" ላልቶ ሲነበብ "መጥለል፣ መጥራት፣ በአየር ወይም በውኃ ላይ ተዘርግቶ መሄድ... አጽለለ ደግሞ አጠራ፣አጠለለ፣አሰፈፈ ፣ አንጓለለ" ተብሎ ይፈታል፡፡ ላልቶ ሲነበብ በግዕዝ አረባብ "ጸለለ፣ ይጸልል፣ ይጽልል፣ ጸሊል ሲሆን ግሱን በቅርብ የሴት አንቀጽ ሲረባ "ጸለለኪ፣ ይ'ጸ'ልለኪ፣ይጽልልኪ..." ይሆናል፡፡ በሉቃ. 1:35 ላይ ግን የተጠቀሰው ቃል በግዕዙ "መንፈስ ቅዱስ ይመጽዕ ላዕሌኪ ወኃይለ ልዑል ይ'ጼ'ልለኪ" ነው የሚለው፡፡ ከላይ እንደተመለከተው ግን ቃሉ ሲላላ ያለው የአረባብ መንገድ በሉቃስ ወንጌል ላይ ያለውን "ይ'ጼ'ልለኪ" አያስገኝም፡፡
"ጸለለ" ሲጠብቅ ደግሞ ትርጓሜው "መጽለል፣ በላይ ሆኖ ማጥላት፣ ጥላ መሆን፣ ማልበስ፣ መክደን፣ መሸፈን፤ መከለል፤ መጋረድ" ተብሎ ይፈታል፡፡ ጠብቆ ሲነበብ ባለው የአረባብ መንገድ ነው በሉቃስ ወንጌል ላይ የተጻፈውን ይ'ጼ'ልለኪ የሚለውን የሚያስገኘው፡፡
👉 ስለዚህ ጠብቆ ሲነበብ ካለው ትርጉም ጋር የሚሄድ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ይህንም በሉቃ 1:35 ተክተን ስናነበው "የልዑል ኃይል ይጋርድሻል፣ በላይ ሆኖ ያጠላልሻል፣ ጥላ ይሆንሻል፣ ያለብስሻል፣ ይከድንሻል፣ ይሸፍንሻል፣ ይከልልሻል" የሚል ትርጉም ይሰጣል፡፡ "ማንጓለል፣ ማጥራት፣ ማጥለል፣ የሚል ግስ እና በሁለተኛ አንቀጽ ለእመቤታችን አልተነገረም፡፡
በእንግሊዘኛው መጽሐፍ ቅዱስም "The Holy Ghost Shall come up on thee, and the power of the highest shall 'overshadow' thee" luke 1:35 ገልጾታል፡፡ ይጸልልሻል የሚለውን "Overshadow" በማለት ነው የሚያስቀምጠው፡፡ ይህም ቃል "To shelter, to protect " ጥላ መሆን (አስቀድሞ) መጋረድ ተብሎ ይፈታል፡፡
ስለዚህም ቃሉ በኃይለ ልዑል መጋረድ መጠበቋን ፣ መሸፈኗን ከኃጢአት መከልከሏን ነው፡፡" የሚያሳየው:: በማር. 9:7፣ ሉቃ 9:34፣ ማቴ 17:5 ላይም Overshadow የሚለው መጋረድ ወይም መከለል በሚል የተፈታ ነው፡፡ ጸለለ የሚለውም ይህን የተከተለ ነው፡፡
ዋቢ፦ ሐውልተ ስምዕ (መምህር ኃይለ ማርያም ላቀው)
- ወልታ ጽድቅ (በአማን ነጸረ)

+ ለንስሓ የሚቀሰቅስ ዶሮ +
🐓🐓🐓🐓🐓
ጴጥሮስን ለታላቅ ንስሓ የቀሰቀሰው የዶሮ ጩኸት ነበር ... ‹የዶሮ ጩኸት ጴጥሮስን ለንስሓ አበቃው› የሚለው ታሪክ ከዶሮ ጩኸት አልፎ እልፍ ሰባኪያን ‹ንስሓ ግቡ› እያሉ ሲጮኹ እየሰማን ምንም ለማይመስለን ለእኛ ለልበ ደንዳኖቹ መልእክቱ ምን ይሆን? የዶሮዎቹን ጩኸት ሰምቶ በመመለስ ፈንታ የዶሮዎቹን የአጯጯህ ስልት እያወዳደርን ሰባኪያን ለምናማርጥ ለእኛ መልእክቱ በእርግጥ ምን ይሆን?
በእርግጥ የዶሮውም እድል የሚያስቀና ነው፡፡ አንድ ጊዜ ጮኾ የወደቀውን ጴጥሮስ እንዲነሣ መቀስቀስ መቻሉ የታደለ ሰባኪ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ስንጮኽ ውለን አንድ ሰው ለንስሓ ማብቃት ላልቻልን ሰባኪያን ይህ ዶሮ ምንኛ የሚያስቀና ነው? ለነገሩ በልማዱ ዶሮ ጮኾ ሌሎቹን ከማስነሣቱ በፊት እሱ ተነሥቶ ክንፉን እያርገበገበ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ እኛ ግን ራሳችን በኃጢአት ተኝተን ሌላውን ለንስሓ ለመቀስቀስ የምንሞክር እንቅልፋም ዶሮዎች ስለሆንን በጩኸታችን የረበሽነው እንጂ የቀሰቀስነው ሰው የለም፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
"ሕማማት" ከተሰኘው መጽሐፍ 2ኛ ምዕራፍ የተወሰደ
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
🐓🐓🐓🐓🐓
ጴጥሮስን ለታላቅ ንስሓ የቀሰቀሰው የዶሮ ጩኸት ነበር ... ‹የዶሮ ጩኸት ጴጥሮስን ለንስሓ አበቃው› የሚለው ታሪክ ከዶሮ ጩኸት አልፎ እልፍ ሰባኪያን ‹ንስሓ ግቡ› እያሉ ሲጮኹ እየሰማን ምንም ለማይመስለን ለእኛ ለልበ ደንዳኖቹ መልእክቱ ምን ይሆን? የዶሮዎቹን ጩኸት ሰምቶ በመመለስ ፈንታ የዶሮዎቹን የአጯጯህ ስልት እያወዳደርን ሰባኪያን ለምናማርጥ ለእኛ መልእክቱ በእርግጥ ምን ይሆን?
በእርግጥ የዶሮውም እድል የሚያስቀና ነው፡፡ አንድ ጊዜ ጮኾ የወደቀውን ጴጥሮስ እንዲነሣ መቀስቀስ መቻሉ የታደለ ሰባኪ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ስንጮኽ ውለን አንድ ሰው ለንስሓ ማብቃት ላልቻልን ሰባኪያን ይህ ዶሮ ምንኛ የሚያስቀና ነው? ለነገሩ በልማዱ ዶሮ ጮኾ ሌሎቹን ከማስነሣቱ በፊት እሱ ተነሥቶ ክንፉን እያርገበገበ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ እኛ ግን ራሳችን በኃጢአት ተኝተን ሌላውን ለንስሓ ለመቀስቀስ የምንሞክር እንቅልፋም ዶሮዎች ስለሆንን በጩኸታችን የረበሽነው እንጂ የቀሰቀስነው ሰው የለም፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
"ሕማማት" ከተሰኘው መጽሐፍ 2ኛ ምዕራፍ የተወሰደ
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
🕯"አቤቱ በምድር ላይ ብዙ ዘመን ከመኖር በገነት አንዲት ቀን ደስ መሰኘት ይሻላል"
መጽሐፈ መቃብያን ካልእ 13፥1_6
"የአመኑ እሊያ አምስቱ የመቃቢስ ልጆች ግን ለጣዖት የተሠዋውን መሥዋዕት መብላትን እምቢ ብለው ሰውነታቸውን ለሞት ሰጡ።
ይህ ዓለም እንደሚያልፍ እንደሚያረጅ ተድላውም ለዘለዓለም እንደማይኖር ዐውቀው በሰማይ ከአለው እሳት ይድኑ ዘንድ ሰውነታቸውን ለእሳት ሰጡ። ሰውን ከመገዳደር እግዚአብሔርን መገዳደር እንደሚከፋ፥ከንጉሥም ቁጣ የእግዚአብሔር ቁጣ እንደሚከፋ አውቀዋልና።
"አቤቱ በምድር ላይ ብዙ ዘመን ከመኖር በገነት አንዲት ቀን ደስ መሰኘት ይሻላል፤ ከብዙ ዘመኖችም የአንዲት ሰዓት ይቅርታህ ይሻላል፤ የእኛ የሰዎች ዘመናችን ምንድን ነው? እንደጥላ የሚያልፍ፥በእሳት ዳርም አንደአለ ሰው አይደለምን? አቤቱ አንተ ግን ለዘለዓለም ትኖራለህ ፤ ዘመንህም የማይፈፀም ነው፤ ስም አጠራርህም ልጅ ልጅ ነው።"
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
መጽሐፈ መቃብያን ካልእ 13፥1_6
"የአመኑ እሊያ አምስቱ የመቃቢስ ልጆች ግን ለጣዖት የተሠዋውን መሥዋዕት መብላትን እምቢ ብለው ሰውነታቸውን ለሞት ሰጡ።
ይህ ዓለም እንደሚያልፍ እንደሚያረጅ ተድላውም ለዘለዓለም እንደማይኖር ዐውቀው በሰማይ ከአለው እሳት ይድኑ ዘንድ ሰውነታቸውን ለእሳት ሰጡ። ሰውን ከመገዳደር እግዚአብሔርን መገዳደር እንደሚከፋ፥ከንጉሥም ቁጣ የእግዚአብሔር ቁጣ እንደሚከፋ አውቀዋልና።
"አቤቱ በምድር ላይ ብዙ ዘመን ከመኖር በገነት አንዲት ቀን ደስ መሰኘት ይሻላል፤ ከብዙ ዘመኖችም የአንዲት ሰዓት ይቅርታህ ይሻላል፤ የእኛ የሰዎች ዘመናችን ምንድን ነው? እንደጥላ የሚያልፍ፥በእሳት ዳርም አንደአለ ሰው አይደለምን? አቤቱ አንተ ግን ለዘለዓለም ትኖራለህ ፤ ዘመንህም የማይፈፀም ነው፤ ስም አጠራርህም ልጅ ልጅ ነው።"
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
🕯''እግዚአብሔር በአሳባቸሁ ውስጥ እንዲኖር ስለእርሱ አብዝታችሁ አንብቡ።''🕯
~ምክር ዘአቡነ ሺኖዳ~
እግዚአብሔር በአሳባቸሁ ውስጥ እንዲኖር ስለእርሱ አብዝታችሁ አንብቡ። እርሱን ለማወቅ ስለእርሱ አንብቡ። እርሱን ካላወቃችሁት እንዴት እርሱን ልትወዱት ትችላላችሁ?
ስለእርሱ አንብቡ፤ ስታነቡ ግን በሳይንሳዊ ወይም በፍልስፍና ጠባይ አታንብቡ ወይም ደግሞ ስለእርሱ ጥናታዊ ጽሑፍ ወይም ትምህርት ለመስጠት አታንብቡ። ነገር ግን ወደ እርሱ ጥልቀት ለመግባት ወይም እርሱ ወደ እናንተ ጥልቀት እንዲገባ አንብቡ።
ለነፍሳችሁ ውድ የሆኑትን የእርሱን ባሕርያት ለማወቅ ስትሉ አንብቡ ይህ እውቀት አሳባችሁ ከእርሱ ጋር እንዲጣበቅና ፍቅሩ ከእናንተ ልብ ጋር እንዲቀናጅ ያደርግላችኋልና ። ስለ ስምምነቱ ስትሉም አንብቡ።
ከወደዱት ሰዎች ጋር ስላለው ግንኙነት በጠላቶቹ ላይ ስላለው አቋም ስትሉ አንብቡ! በጽሑፎች ውስጥ ስለእርሱ "ውበትህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል" (መዝ 44÷2) የሚለውን ቃል በማንበብ የእርሱን ውበት ታውቁ ዘንድ አንብቡ።
እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቀምሳችሁ ታዩ ዘንድ ስለእርሱ አንብቡ። ታዲያ ንባባችሁ ለልባችሁ ምግብ እንዲሆን እንጂ እንዲሁ ተራ ንባብ እንዲሆን አትፍቀዱ።
ስለ እግዚአብሔር ብዙ ካነበባችሁ በእርሱ ዘንድ ያለውን ፍጹምነት በሙሉ ታገኛላችሁ። እርሱን ስለምትወዱትም በሰሎሞን መዝሙር ውስጥ ካለችው ድንግል ጋር አብራችሁ "እርሱ ፈጽሞ ያማረ ነው" (መኃ. 5÷16) ትላላችሁ።
ከወደዳችሁት ስለእርሱ ማንበባችሁን ትቀጥላላችሁ። እግዚአብሔር ስለእርሱ የሚያነቡትን ስለእርሱ ዜና የሚጠይቁትን ከእርሱ ታሪኮች መካከል አንዱን ለማወቅ የሚናፍቁትንና እርሱን የሚያደንቁትን ሰዎች ይወዳቸዋል።
ስለእርሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወይም ከአባቶች ብሒሎች ወይም ከቤተክርስቲያንና ከቅዱሳን ታሪክ ልታነቡ ትችላላችሁ። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ ለመዳሰስ ስትሞክሩ በጥበቡ፣ በኃይሉና በርኅራኄው ውስጥ እንደምትወዱት ታውቃላችሁ።
💡አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ💡

የሰሙነ ሕማማት ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
#######################
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
ብዙ ጊዜ በየዓመቱ ሕማማት ሲመጣ ክርስቲያኖች ጥያቄ ያበዛሉ።ጥያቄውም ባለማወቅ እንዲሁም በራስ ፍላጎት የሚነሱ ናቸው።ለነዚህ ጥያቄዎች ደግሞ መልስ መስጠት ይገባል።
በዚህም መሠረት እንደሚከተለው እናቀርባለን።
1.የማይፈጸሙ ተግባራት
ማማተብ፣መስቀል መሳለም አይቻልም።በብሉይ መስቀል አርማችን አልነበረምና።ማህበር፣ቁርባን፣ሰንበቴ፣ፍትሓት፣ጥምቀት፣ቅዳሴ፣ንስሓ መስጠትና መቀበል የለም።ካሳ የተፈጸመልን ከትንሳኤው በኃላ ነው።መሳሳም መጨባባጥ የለም።ይሁዳን ጌታን በመሳም አሰልፎ ሰጥቷልና ያንን ለማሰብ።
በዚህ ሳምንት በቤተክርስቲያን እየተገኙ መጸለይ መስገድ ግብረሕማማትን መስማት ይገባል።
2.የተለመዱ ግን አግባብ ያልሆኑ ተግባራት
መስቀልያ አትልበሱ
ማህተብ አውልቁ
ሥዕለት ከተሰቀሉበት ይውረዱ
ልብስና ሰውነትን አትታጠቡ የሚሉት ከቤተክርስቲያን ሕግ ውጪ ናቸው።ጫማን ከእግር ማውለቅም ግዳጅ አይደለም።
3.ስግደት
በሰሙነ ሕማማት ውስጥ 21 :12: 29 ቢውሉ ይሰገዳል ወይ የሚሉም አሉ።መልሱ አዎ ይሰገዳል ነው።ምክንያቱም ወቅቱ የክርስቶስን መከራ የሚናስብበት ነውና።ድንግል ማርያምም ቅዱስ ሚካኤልም በሐዘን ነበሩና።
4.ቅዳሜ ይታረዳል ወይ?????
ይህ የብዙ ወገኖቻችን ጥያቄ ቢሆንም ከሰዓት ይታረዳል የሚሉ ቢኖሩም እንኳ ፈጽሞ አይታረድም።ምክንያቱም ቅዳሜ ከ55ቱ የአብይ ጾም ቀናት አንዱ ናትና።በዚህ ቀን ስመ ሥላሴን ጠርቶ መባረክም አይቻልምና።በዕለቱ ከቅባት ለራቀ ሰውነት እንደቅቤ አይብ ተልባ ማር ወተት ያሉትን መጠቀም ይገባል።ክርስቶስ ተንስኣ እሙታን ሳይባል መታረድ የለበትም።ለነድያንም ከሆነ ጠዋት ታርዶ ይደርሳልና።
ክርስቶስ መከራ ተቀበለ በመከራውም አዳነን!!!!!!!!
ቀሪ ጥያቄዎች ካሉ በውስጥ ማቅረብ ይቻላል።
በእርሱ ቁስል እኛም ተፈወስን
ኢሳ 53:6
ከመ/ር እሸቱ

“ማግባት ለሚሹ” የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር
ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው፤ እንዲህ ያለውን፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" (1ኛ ቆሮ.7፥2)። "ከድህነት ይወጣ (ትወጣ) ዘንድ" ነው የሚለውን? ወይስ "ሀብት ለማግኘት ሲባል" ነው የሚለውን? አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡
ስለዚህ ልጆቼ! እማልዳችኋለሁ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡ የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡
አባቶች ሆይ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት፦ ሀብትን አላየም፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡
እናቶች ሆይ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡
እናንተ ማግባትን የምትሹ ወጣቶች ሆይ! ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡
እናንተ ልጃገረዶች ሆይ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡
የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡

ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች
👉 የመስቀል አደባባይ ጉዳይ አሁንም #ትኩረትን ያሻል!
👉 አሁንም እጃቸውንም አይናቸውንም ከመስቀል አደባባይ ላይ አላነሱም!! ይባስ ብለው በGoogle map ላይ "መስቀል አደባባይ ወይም ኢድ አደባባይ" በማለት ነገሩን የማወሳሰብ ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።
😇 ከምንግዜውም በላይ አንድነታችን የሚያስፈልግበት ሰዓት ላይ እንገኛለን። ይህንን "ኢድ አደባባይ" ለማለት ዳር ዳር የተባለለትን ሴራ ለማክሸፍ በጋራ እንቁም!
ይህንን ያድርጉ!
1)Google map ይክፈቱ
2)ቦታ በመፈለጊያው ላይ "Meskel square" ብለው ይፈልጉ
3)"Direction" ከሚለው ስር ወደላይ በማድረግ "Suggest an edit" የሚለውን ይጫኑ
4)"መስቀል አደባባይ ወይም ኢድ አደባባይ" የተባለውን በመምረጥ "መስቀል አደባባይ" በማለት ያስተካክሉ
5)"Category" ከሚለው ምርጫ ውስጥ "place of worship" የሚለውን ይምረጡ
6) በመጨረሻም ከላይ ▶️ የNext ምልክቷን ይጫኑ
ከዚህ በኃላ ለGoogle የስም ማስተካከያ እንዲደረግ መልዕክት መላክዎን የሚገልጽ ማረጋገጫ ይመጣልዎታል።
ስለቤተክርስቲያንና ማምለኪያ ቦታዎቿ ዝም አንልም!!!
ስለቤተክርስቲያን ስትሉ ለምታውቋቸው ኦርቶዶክሳዊያን በሙሉ መልዕክቱን ከዚህ በላይ ከተያያዘው ምስል ጋር ያጋሩ!

ያልሰማህ ስማ የሰማህ አሰማ። በዓለ ዕርገትን በመስቀል አደባባይ።አላየሁም የለ አልሰማሁም የለ።ብቻ ሰኔ 3/2013 ዓ/ም ከቀኑ ስድስት ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ እንገናኝ።ጨለማን፣ባርነትን፣ሲኦልን፣የሰው ዘር ሁሉ ገዳይ የሆነውን ሞትን በሞቱ ሽሮ፣በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ሞትን ድል አድርጎ ከሞት የተነሳውን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ፣ የዕርገት በዓል በመስቀል፣በመስቀል አደባባይ፣በአንድነት ሆነን እናክብር።ስለሀገራችን እንጸልይ፣ከሰላም አምላክ ሰላምን እንለምን፣ዘረኝነትንና መለያየትን እናውግዝ፣ፍቅርና አንድነትን፣እናንግስ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሼር ሼር ሼር አደራ ሼር አድርጉት። ሰኔ 3/2013/ዓ/ም በመስቀል አደባባይ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ጀምሮ፣ ታላቅ ሀገር አቀፍ ኦርቶዶክሳዊ ጉባኤ ይደረጋል።ይህንን መልዕክት ሰምቶ በማናቸውም መንገድ የማያስተላልፍ እንዳይኖር። አደራው ጥብቅ ነው። አሁን ያለፈውን ሁሉ በይቅርታ ሽረን ለቤተክርስቲያናችንና ለሀገራችን ህልውና አንድ ሆነን ዘብ የምንቆምበት ሰዓት ነው።የኢትዮጵያም ትንሣኤ እሩቅ አይደለም።ተስፋዋ እግዚአብሔር አይተዋትም፣አይረሳትም፣ አይጥላትም፣የኢያሪኮን ቅጽር በጩኸት ያፈረሰ፣የኛ እግዚአብሔር ፣ ዛሬም ከፊትዋ የተደቀነባትንና ወደ ከነአን አላስስገባት ያለውን የመከራ ግንብ ሁሉ በኃይሉ ይደረምሰዋል።ብቻ ወደላይ እንጩህ፣የኢትዮጵያ መፍትሄ ያለው፣ኃያላን ነገሥታትጋ ሳይሆን መድኃኔዓለም እጅ ላይ ብቻ ነው።
በግንቦት የርክበ ካህናት በተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መሠረት ሥርዓተ አምልኮ የሚፈጸምባቸው ይዞታዎቻችን ላይ የሚፈጸሙ የሁከት ድርጊቶች እንዲቆሙ እና ሕጋዊ ዋስትና እንዲሰጣቸው እንዲሁም በቤተክርስቲያናችን ፣ በሃይማኖት አባቶችና በምዕመናን ላይ የሚደርሱ መከራዎች እንዲቆሙና ተገቢው ካሳ እንዲሰጣቸው የሚጠይቅ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል። የመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ውሳኔውን እንዲፈጽሙ ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት በደብዳቤ አሳውቀዋል።
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae