tgoop.com/hebre_muslim/2247
Last Update:
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
🛌 ከመኝታ በፊት የሚባሉ
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ ﴿١﴾ اللَّهُ الصَّمَدُ ﴿٢﴾ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ ﴿٣﴾ وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ ﴿٤﴾
(1) በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ (1) «አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡ (2)«አልወለደም፤አልተወለደምም፡፡ (3) «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡» (4)
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ ﴿١﴾ مِن شَرِّ مَا خَلَقَ ﴿٢﴾ وَمِن شَرِّ غَاسِقٍ إِذَا وَقَبَ ﴿٣﴾ وَمِن شَرِّ النَّفَّاثَاتِ فِي الْعُقَدِ ﴿٤﴾ وَمِن شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ ﴿٥﴾
በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ፡፡ (1) «ከፈጠረው ፍጡር ሁሉ ክፋት፡፡ (2) «ከሌሊትም ክፋት ባጨለመ ጊዜ፤ (3) «በተቋጠሩ (ክሮች) ላይ ተፊዎች ከኾኑት (ደጋሚ) ሴቶችም ክፋት፡፡ (4) «ከምቀኛም ክፋት በተመቀኘ ጊዜ፤ (እጠበቃለሁ በል)፡፡» (5)
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ ﴿١﴾ مَلِكِ النَّاسِ ﴿٢﴾ إِلَٰهِ النَّاسِ ﴿٣﴾ مِن شَرِّ الْوَسْوَاسِ الْخَنَّاسِ ﴿٤﴾ الَّذِي يُوَسْوِسُ فِي صُدُورِ النَّاسِ ﴿٥﴾ مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ ﴿٦﴾
(1) በል «በሰዎች ፈጣሪ እጠበቃለሁ፡፡ (1) «የሰዎች ሁሉ ንጉሥ በኾነው፡፡(2) «የሰዎች አምላክ በኾነው፡፡ (3) «ብቅ እልም ባይ ከኾነው ጎትጓች (ሰይጣን) ክፋት፡፡ (4) «ከዚያ በሰዎች ልቦች ውስጥ የሚጎተጉት ከኾነው፡፡ (5) «ከጋኔኖችም ከሰዎችም (ሰይጣናት እጠበቃለሁ በል)፡፡»(6)
‘\ነብዩ(ሶ.ዐ.ወ) ዘወትር ከመተኛታቸው በፊት ሁለት መዳፎቻቸውን በማጋጠም ከላያቸው ላያ ትፍ ትፍ ይሉባቸዋል፡፡ ከዛም ከላይ ያሉትን ሶስቱን ሱራዎች ያነባሉ፡, በመቀጠልም በመዳፎቻቸው ከአካላቸው የቻሉትን ያክል ያብሱ ነበር፡፡ ከራሳቸው በመጀመሪያ ፊታቸውንና በፊታቸው በኩል ያሉ የአካል ክፍሎቻቸውን ይደባብሳሉ፡፡ ከዚያም ሌሎችን የአካል ክፍሎቻቸውን፡፡ ይህንኑ ሦስት ጊዜ በመደጋገም ይፈጽማሉ፡፡ ’
اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ مَنْ ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِنْدَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِنْ عِلْمِهِ إِلَّا بِمَا شَاءَ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلَا يَئُودُهُ حِفْظُهُمَا وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ
አልሏሁ ላኢላህ ኢልላ ሁወል ሐይዩል ቀይዩም፣ ላተእኹዙሁ ሱነቱን ወላ ነውም፤ ለሁ ማፊስማዋቲ ወማ ፊል አርድ፤ ወንዘልለዚ የሸፈዑ ዒንደሁ ኢልላ ቢኢዝኒሂ ያዕለሙ ማበይነ አይዲይሂም ወማ ሀኸልፈሁም ወላ ዩሒጡና ቢሸይኢን ሚን ዒልሚሂ ኢልላ ቢማሻአ፤ ወሲዐ ኩርስዩዑሰማዋቲ ወል አርድ ወላ የኡዱሁ ሒፍዙሁማ ወሁወል ዐልዩል ዐዚም
አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡ (255).
{ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنْزِلَ إِلَيْهِ مِنْ رَبِّهِ وَالْمُؤْمِنُونَ كُلٌّ آمَنَ بِاللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِنْ رُسُلِهِ وَقَالُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ } { لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا لَهَا مَا كَسَبَتْ وَعَلَيْهَا مَا اكْتَسَبَتْ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِنْ نَسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَا رَبَّنَا وَلَا تَحْمِلْ عَلَيْنَا إِصْرًا كَمَا حَمَلْتَهُ عَلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِنَا رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِ وَاعْفُ عَنَّا وَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا أَنْتَ مَوْلَانَا فَانْصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ }
አመነርረሱሉ ቢማ ኡንዚለ ኢለይሂ ሚንረቢሂ ወልሙእሚኑን ኩሉን አመነ ቢልላሂ ወመላኢከቲሂ ወኩቱቢሂ ወሩሱሊሂ ላኑፈሪቁ በይነ አሐዲን ሚን ሩሱሊህ ወቃሉ ሰሚእና ወአጠእና ጉፍራነከ ረብበና ወኢለይከል መሢር፣ ላዩከሊፋልላሁ ነፍሰን ኢልላ ውስአሃ ለሃ ማከሰበት ወዐለይሃ መክተሰበት ረብበና ላቱአኺዝና ኢንነሲና አው አኸጠእና ረብበና ወላ ተህሚል ዐለይና ኢስረንከማ ሐመልተሁ አለልለዚይነ ሚን ቀብሊና ረብበና ወላ ቱሐምሚልና ማላጣቀተ ለና ቢህወዕፋ እና ወግፊር ለና ወርሃምና አንተ መውላና ፈንሱርና አለል ቀውሚል ካፊሪን››
‹‹መልእክተኛው ከጌታው ወደርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖችም (እንደዚሁ)፤ ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጽሐፍቱም፣ በመልዕክተኞችም ከመልዕክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም (የሚሉ ሲሆኑ) አመኑ፡፡ ሰማን፤ ታዘዝንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ምህረትህን (እንሻለን)፡፡ መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው፡፡ አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳት፤ ለርሷ የሰራችው አላት በርሷም ላይ ያፈራችው (ኃጢያት) አለባ፡፡ (በሉ)፡- ጌታችን ሆይ! ብንረሳ፣ ወይም ብንስት አትያዘን፤ (አትቅጣን)፤ ጌታችን ሆይ!! ከባድ ሸክምን ከኛ በፊት በነበሩት ላይ እንደጫንከው በእኛ ልይ አትጫንብን፤ ጌታችን ሆይ! ለእኛም በእርሱ ችሎታ የሌለንን ነገር አታሸክመን፤ ከኛም ይቅርታ አድርግ፤ ለኛም ምህረት አድርግ፤ እዘንልንም፤ ዋቢያችን አንተ ነህና፤ በከሃዲዎች ህዝቦች ላይም እርዳን፡፡›› (አል-በቀራህ: 285 to 286) .”
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
BY ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣﷽
Share with your friend now:
tgoop.com/hebre_muslim/2247