HELANSANE Telegram 4568
Forwarded from ሄላንሳን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
👉 ከምኩራብህ ግባ ! 👈

ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬ #ከምኩራብ ግባ! በሚል ርዕስ እግዚአብሔር አምላክ ያስተምረናል።በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምዕሮ ሦስት ነገሮች ቤተክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ። #ህንጻ ቤተክርስቲያኑ #የክርስቲያን ምዕመናን ህብረት እንዲሁም ደግሞ #የእኛ የገዛ አካላችን ቤተክርስቲያን ይባላል። ስለዚህ የእኛን ቤተመቅደስ(ቤተክርስቲያን) ወይም ምኩራብ እንዴት አድርገን እናቅናት? ፈጽመን እናሰናዳትና የምኩራባችንን አለቃ ና ግባ!!! እንበለው። (🙏 በፍጹም ትጋት እስከ ፍጻሜው ጸንታችሁ አንብቡ🙏 )
@helansane
👉 አባታችን ባሕታዊው ቴዎፋን የተናገሩትን ነገር መሠረት አድርገን ወደ እኔና እናንተ ቤተመቅደስ እናምራ። #የሰው ነፍስን በንጉሥ የሚመስሉት ሲሆን ሥጋውን ደግሞ በንጉሡ ቤተ መንግሥት ይመስሉታል። ይህ ቤተ መንግሥት #አምስት መስኮቶች አንድ በር አለው። እነዚህ አምስት መስኮቶች አምስቱ የስሜት ሕዋሳት ናቸው። በሩ ደግሞ #አእምሮ ነው። ታድያ የእኛ ቤተመቅደስም አወቃቀሩ እንዲኹ ነው። #በር በተሰኘው አእምሮአችን ቅድሚያ ማንን ይሆን አስገብተን ከውስጣችን ያነገስነው ንጉሥ ? በውስጣችን ላነገስነው ንጉሥ ምን ይሆን አምስቱን መስኮቶች ከፍተን ከውጪ ልንቀበል የከጀልነው?
👉 እኛ ደካሞች ሁለት ንጉሦችን በአንድ ቤተ መንግሥታችን አንግሰን ግራ እየተጋባን አለን። #ዘለዓለማዊውን ንጉሥ ክርስቶስን በአእምሮአችን ዙፋን አስቀምጠን በጎን ደግሞ የዚህች የከንቱ ዓለም ገዢ (የክፋት ሃሳቦች ሁሉ ንጉሥ) የሆነውን የዲያብሎስን #ሃሳብ በውስጣችን ጨምረን እያነገስን እንገኛለን። ምክንያቱም ደግሞ እኛ በምንውልባቸው ቦታዎች መስኮት በተባሉት የስሜት ሕዋሶቻችን ፊት ለፊት የኃጥአት ነጋዴ ዲያብሎስ ልዩ ልዩ ልምምዶችንና ነፍስን የሚያስደስቱ ስሜቶችን ያመጣል። በዚህም የተነሳ #ክርስቶስን በቅጡ ያላነገስንባት አእምሮ ከመስኮቱ ማይረባትን ሁሉ ትሸምታለች። መቼም ሁለት ንጉሥ በአንድ ቤተ መንግሥት አንግሳ እንደማትኖር ዘለዓለም እንደማትጸና ታውቃለች።
👉 አሁን ከምኩራባችን (ከቤተመቅደሳችን) ቅድሚያ እኛ ገብተን ውስጡዋን በመስኮት በኩል በምንቀበላቸው ከሄላንሳን ማዕድ ከምንሸምታቸው የቅዱሳን አባቶች ምክርና ተግጻጾች እናዘጋጃትና የምኩራባችንን አለቃ #ከምቡራብህ ግባ! እንለው ዘንድ እንውጣ።(#የምኩራብ አለቃ ሉቃ 13፥14) ኤርምያስ በትንቢቱ ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ አዳራሻችንም ውስጥ ገብቶአል። (9፥21) ብሎ እንደተናገረ የዘለዓለማዊ ሞት ምክንያቶችን በስሜት ሕዋሶቻችን ወደ ነፍሳችን ከምናስገባ ይልቅ እውነተኛ ብርሃን የሆነውን ሕይወትና መንፈስ የሆነው የክርስቶስን ቃል እናስገባ ዘንድ እንዘጋጅ።
፥- ዓይናችንን መቆጣጠር
ቤተ መቅደሳችንን በብርሃን ሆነን ለማስተካከል ተቀዳሚው ነገር ዓይናችንን መቆጣጠር ነው። በማቴ 6፥22-23 < #የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል። ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል።> በእዚህች አይን በተባለችው መስኮት ከፍተህ የምታስገባው ነገር ጨለማ ብቻ ከሆነብህ መክፈቻ እንዳላት ሁሉ መዝጊያም አላችና ዝጋት። በማቴ ላይ #ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት ሙሉ መቅደስህን ጨለማ ከምታደርግብክ አንድም በሲዖል እሳት ከምትማግድህ ዛሬ ዝጋት ጠርቅማት ሲል ነው።
(#ቢቻልህስ በእያንዳንዱ ሰውና በእያንዳንዱ ነገር ውስጥ አምላክን መፈለግና ማየት ልመድ ተለማመድ። )
፥- ጆሮን መቆጣጠር
የጆሮአችን ዋነኛ ጠላቶች ዘፈን ስድብና ነቀፋን የተሞሎ ግጥሞች ቀልዶች ወሬዎች ናቸው።ሁሉም ከጆሮአችን አልፈው ዓይኖቻችንን በፍትወታዊ ትርዒቶታቸውም ጭምር ያሳድፋብናል። አልፎም ፍጹም ጥፋትን ያስከትሉብናልና ስለዚህ ቅድሚያ ምንሰማውን መምረጥን አስከትለን ደግሞ ፍጹም ወደ መተው ማደግ አለብን። ወደ ቤተ ክርስቲያን ስታመሩ ድንገት የሰማችኹት ዘፈን ቤተ ክርስቲያን ደርሳችኹ እንኳን እየጸለያችኹ በውስጣችኹ እንደሚመጣ አስተውሉ። ዳግመኛም #ሽንገላን መቀበል ኃጢአት ነው። ሰዎች ሁሉ መልካም ሲናገሩላችሁ ወዮላችሁ። (ሉቃ 6፥26 ት.ዳን 11፥21-34 ተመልከቱ)
(#ቢቻልህስ አሉባልታ/ሐሜትን/ ከመስማት መቆጠንብ ልምድ አድርግ! ያን ጊዜ ተናጋሪው ይጠፋልና።)
፥- ምላስን መቆጣጠር
በምላሳችን #ጥምር ስህተቶችን (ኃጥያቶችን) ነው ምንሰራው ይበልጥ እንጠንቀቅ በነገሮች ሁሉ እናስተውል። እናታችን ሔዋንን አንዴ ብቻ ዕፀ በለስ በመቅመሷ ምን ያክል ክፋት ውድመትን አስከትሏል። የዓለም ከንቱ የሆነውን ነገር ሁሉ #አታጣጥም ማንኛውንም ምግብ ማጣጣምን ለምላስህ አስለምድ ነገር ግን ወሬን ማስለመድ ግን ፈጹሞ አቁም። <<እኔ እላችኃለሁ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል።ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።(ማቴ 12፥36) >>
👉 ከአበው ቅዱሳን መካከል አንዱ የማውራት ፍላጎት ሲፈትነው በአፋ ውስጥ ጠጠሮችን እስከመጨመር ደርሶአል።
፥- አፍንጫን መቆጣጠር
በምናሸተው ነገር የፍትወት ሐሳቦችንና ስሜቶችን ሊያነቃቃ ይችላል።ጥሩ አሽተን ምንፈጽማቸው ከንቱ ስሜቶች አልፈው በሽቱ ፈንታ ግማት እንዳይሆንባችሁ ተጠንቀቁ። (ኢሳ 3፥24) የሚያውድህ ሽታ ወደ ዝሙት ሐሳብ ከመራህ እየተመኘኸው ያለኸው ሥጋ ኢሳይያስ እንዳለው እንደሚበሰብስና ወደ ከፋ ሽታ እንደሚለውጥ አስታውስ። ይልቅ አንተ ዘወትር የቅዱሳንን መዓዛ ለማሽተት ከእቤትህ ውጣ መስኮትህንም ክፈት።
(#በመንገድ ሳለህ በጎ መዓዛ አፍንጫህን ባወደው ጊዜ ልዩ መዓዛ ባለው ውድ ሽቱ ጌታዋን የቀባችውን ማርያምን አስባት።<ቤቱም ከናርዶስ ሽቱ ሞላ> ዮሐ 12፥3
፥- የምንነካውን ነገር መቆጣጠር
እግዚአብሔርም አለ፥- #እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ #አትንኩትም። ስለዚህ ለመውደቅዋ ምክንያት ቀዳሚው ነገር መንካትዋ እንደሆነም ተመልከት። በመንካት የሚሰማን ስሜት ቢያስደስትም ኅሊናችንን ግን ወዳልተቀደሱ ሃሳቦች መምራቱ አይቀርምና እንጠንቀቅ።(በጾታዊ ጉዳዮች ላይ ይበልጡኑ ተጠንቀቁ)።
ቅዱስ ይሁዳም በመልዕክቱ ላይ 1፥23 #አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ። ይህም ማለት እርቃንን ከሚያሳዩ ከሚያጎሉ ልብሶች ፍላጎትና ንክኪም ፈድማችሁ ራቁ ተጠበቁም። እርሱን አመንዝራዎች እርቃናቸውንና ኅፍረታቸውን ለማሳየት ያደርጉትማል ኃጥያትንም ይፈጽሙበታልና እናንተ ግን መልካሙን ልብስ ተሸለሙ። መቅደሳችሁን ውስጡን እንዳሳመራችሁት ሁሉ ገጽታውም ፍጹም ያማረና በቅዱሳን ዘንድም የተወደደ ወደ መልካም ሃሳብ ብቻ የሚስብ ይሁን ዘንድ ተሰሩ።
@helansane
ውድ ቤተሰቦቻን አሁን ቅድሚያ ወደ ምኩራባችን ገብተን ውስጡን አስተካክለን የልቡናችንን ወጣ ገባ(#በውስጤ እንዳላኖርክ የልቤ ግርግዳዎች ይጎረብጡሃል) ብለው እንደተናገሩ ቅዱሳን አባቶቻችን እኛም ይህን አባጣ ጎርባጣችንን አቅንተን የመስኮቶቻችንን አከፋፈት አስተካክለን እደ አእምሮአችንን አዘጋጅተን #ከገባ ላናስወጣው አንተ የምኩራባችን አለቃ ንጉሥ ሆይ ግባ!!! እንለው ዘንድ ዛሬ ከኃጥአት ወጥመድ እንወጣ!!!

🙏ሳምንቱን የሰላም የፍቅር የጤና ያድርግልን።🙏
ሼር በማድረግ ማካፈል የዘወትር ተግባራችሁ ይሁን።
።ቸር ያቆየን።

tgoop.com/helansane/4568
Create:
Last Update:

BY ሄላንሳን

Share with your friend now:
tgoop.com/helansane/4568

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Telegram iOS app: In the “Chats” tab, click the new message icon in the right upper corner. Select “New Channel.” Joined by Telegram's representative in Brazil, Alan Campos, Perekopsky noted the platform was unable to cater to some of the TSE requests due to the company's operational setup. But Perekopsky added that these requests could be studied for future implementation. Judge Hui described Ng as inciting others to “commit a massacre” with three posts teaching people to make “toxic chlorine gas bombs,” target police stations, police quarters and the city’s metro stations. This offence was “rather serious,” the court said. Users are more open to new information on workdays rather than weekends. Private channels are only accessible to subscribers and don’t appear in public searches. To join a private channel, you need to receive a link from the owner (administrator). A private channel is an excellent solution for companies and teams. You can also use this type of channel to write down personal notes, reflections, etc. By the way, you can make your private channel public at any moment.
from us

Telegram ሄላንሳን
FROM American