Warning: mkdir(): No space left on device in /var/www/tgoop/post.php on line 37

Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/hollypoem/--): Failed to open stream: No such file or directory in /var/www/tgoop/post.php on line 50
ግጥም ፍቅር ቅኔ@hollypoem P.10668
HOLLYPOEM Telegram 10668
ካንቺጋማ
አብረን በላን  አብረን ጠጣን
አብረን ገባን  አብረን ወጣን

ካንቺጋማ
ተደባደብን  ተቃቀፍን
አንዴ ዳበስ   አንዴ እፍን
አንዴ ቦረሽ  አንዴ ምጥጥ
አንዴ ፈገግ  አንዴ ፍጥጥ

ካንቺጋማ
ተለያየን  ተራራቅን
ተኮራረፍን  ተታረቅን
ተፋቀርን  ተዋደድን
ጅራፍ ፈታን  ሳር ገመድን
እንደ አዲስ ተኮራረፈን
እንደገና ልንታረቅ
አንቺ ከኔ ስታነቢ
እኔ ካንቺ ስነፋረቅ
ተለያይተን ላይሆንልን
አብረን ሆነን ላንስማማ
ስንታደል ሁሉን ባንዴ
ከዛን ሁሉን ስንቀማ

ካንቺጋማ
ሰማይ ወጣን ፥ በደመና
እስከ ጠረፍ ተመጠቅን
ተለማመድን እሳት ማቀፍ
ጉምን በጣት  መሰንጠቅን
ተዘዋወርን እስከ አለም ጫፍ
የሚታይን አየን  ሁሉን
የኮረፈን በሣቅ መጣል
የተከፋን ማባበሉን
ካበባ ጋር ፈነደቅን
ከእፉዬ ጋር ሰማይ ወጣን
ሁሉን ጣዕም አጣጣምነው
ተጋራነው ሁሉን ስልጣን

ካንቺጋማ  - የኔ ብርሃን
ብርሃን ላይ ስንቴ አበራን
ጠሃዩዋ ላይ አንፀባረቅን
ጨረቃ ላይ መንገድ ሰራን

ልታጎርሺኝ ስትዘረጊ
ስትመልሺ ልጎርስ ስል
ተደብቄሽ ስታነቢ
አይንሽ እሳት እስኪመስል
አንዴ አብረን ስንጨፍር
አንዴ አብረን ስንመለኩስ
በፀሎት ጧፍ እንደችቦ
ደማቅ ፍቅር ስንለኩስ
ስንመፀውት ከሰው ዘርፈን
እኔ እና አንቺ አብረን ሆነን
አንዴ ፊቱ ስንፀድቅ
አንዴ ደግሞ ስንኮነን

ተኳረፍን  ተታረቅን
ተፋቀርን ካንቺጋማ
ተለያይተን ላይሆንልን
አብረን ሆነን ላንስማማ
ሁሉም ጣዕም አጣጣምነው
ተጋራነው ሁሉን ስልጣን
ዳግም መሬት ልንለጠፍ
ከጠፈር ላይ እየወጣን

ካንቺጋማ

❴❴❴❴❴                    ❵❵❵❵❵
       ሚኪያስ ፈይሣ



tgoop.com/hollypoem/10668
Create:
Last Update:

ካንቺጋማ
አብረን በላን  አብረን ጠጣን
አብረን ገባን  አብረን ወጣን

ካንቺጋማ
ተደባደብን  ተቃቀፍን
አንዴ ዳበስ   አንዴ እፍን
አንዴ ቦረሽ  አንዴ ምጥጥ
አንዴ ፈገግ  አንዴ ፍጥጥ

ካንቺጋማ
ተለያየን  ተራራቅን
ተኮራረፍን  ተታረቅን
ተፋቀርን  ተዋደድን
ጅራፍ ፈታን  ሳር ገመድን
እንደ አዲስ ተኮራረፈን
እንደገና ልንታረቅ
አንቺ ከኔ ስታነቢ
እኔ ካንቺ ስነፋረቅ
ተለያይተን ላይሆንልን
አብረን ሆነን ላንስማማ
ስንታደል ሁሉን ባንዴ
ከዛን ሁሉን ስንቀማ

ካንቺጋማ
ሰማይ ወጣን ፥ በደመና
እስከ ጠረፍ ተመጠቅን
ተለማመድን እሳት ማቀፍ
ጉምን በጣት  መሰንጠቅን
ተዘዋወርን እስከ አለም ጫፍ
የሚታይን አየን  ሁሉን
የኮረፈን በሣቅ መጣል
የተከፋን ማባበሉን
ካበባ ጋር ፈነደቅን
ከእፉዬ ጋር ሰማይ ወጣን
ሁሉን ጣዕም አጣጣምነው
ተጋራነው ሁሉን ስልጣን

ካንቺጋማ  - የኔ ብርሃን
ብርሃን ላይ ስንቴ አበራን
ጠሃዩዋ ላይ አንፀባረቅን
ጨረቃ ላይ መንገድ ሰራን

ልታጎርሺኝ ስትዘረጊ
ስትመልሺ ልጎርስ ስል
ተደብቄሽ ስታነቢ
አይንሽ እሳት እስኪመስል
አንዴ አብረን ስንጨፍር
አንዴ አብረን ስንመለኩስ
በፀሎት ጧፍ እንደችቦ
ደማቅ ፍቅር ስንለኩስ
ስንመፀውት ከሰው ዘርፈን
እኔ እና አንቺ አብረን ሆነን
አንዴ ፊቱ ስንፀድቅ
አንዴ ደግሞ ስንኮነን

ተኳረፍን  ተታረቅን
ተፋቀርን ካንቺጋማ
ተለያይተን ላይሆንልን
አብረን ሆነን ላንስማማ
ሁሉም ጣዕም አጣጣምነው
ተጋራነው ሁሉን ስልጣን
ዳግም መሬት ልንለጠፍ
ከጠፈር ላይ እየወጣን

ካንቺጋማ

❴❴❴❴❴                    ❵❵❵❵❵
       ሚኪያስ ፈይሣ

BY ግጥም ፍቅር ቅኔ


Share with your friend now:
tgoop.com/hollypoem/10668

View MORE
Open in Telegram


Telegram News

Date: |

As five out of seven counts were serious, Hui sentenced Ng to six years and six months in jail. According to media reports, the privacy watchdog was considering “blacklisting” some online platforms that have repeatedly posted doxxing information, with sources saying most messages were shared on Telegram. Don’t publish new content at nighttime. Since not all users disable notifications for the night, you risk inadvertently disturbing them. Telegram message that reads: "Bear Market Screaming Therapy Group. You are only allowed to send screaming voice notes. Everything else = BAN. Text pics, videos, stickers, gif = BAN. Anything other than screaming = BAN. You think you are smart = BAN. Those being doxxed include outgoing Chief Executive Carrie Lam Cheng Yuet-ngor, Chung and police assistant commissioner Joe Chan Tung, who heads police's cyber security and technology crime bureau.
from us


Telegram ግጥም ፍቅር ቅኔ
FROM American