tgoop.com/hollypoem/10669
Last Update:
ዳዳ ነኝ
ቆንጆ ነኝ
.
ስላንቺ ቁንጅና
ስላንቺ ቁመና
ከንፈር እና ዳሌ
ጥርስና ተረከዝ ፣ ፀጉር ገለመሌ
ለጡት ለወገብሽ ፣ ለፀባይሽ ጭምር
በግጥም በዝርው ፣ ባድናቆት ስዘምር
እስከዛሬ ድረስ...
ውበትሽን አግንኜ ፣ ሰርክ መለፈፌ
እኔ ስለራሴ ...
አንዳች ቀን እንኳን ፣ ግጥም አለመፃፌ
ሲትጠዪኝ ቆጨኝ
ቢሆንም ቆንጆ ነኝ፡፡
ፓፓራራም ላላላላም
ፓፓራራም ላላላላም
ፓፓራራም ላላላላም
ፓፓራራም ላላላላም
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እርግጥ ነው ብዙዎች...
ስለኔ ሳወራ ፣ ድንገት ያኮርፉኛል
ያንተን ሌሎች ያውሩ ፣ ብለው ይነግሩኛል
እኔን ከኔ በላይ...
እርግጠኛ ሆኖ ፣ ሌላ እንዴት ያውቀኛል?!
ፓፓራራም ላላላላም
ፓፓራራም ላላላላም
።።።።፣፣
እናም እኔ ማለት...
ቁመቴ ከአክሱም ፣ በእጥፍ ይረዝማል
ጣፋጭ አንደበቴ...
መስማት ለተሳነው ፣ ለስልሶ ይሰማል
ውብ አረማመዴ...
እንኳን መንገደኛን ፣ መንገድን ያቆማል፡፡
፡፡፡፡፡፡
የከንፈሬ ወዙ ፣ ጥፍጥናው አያልቅም
ጥርሴ ሺ ገዳይ ነው!
ሺ ሟች ላለማየት ፣ ኗሪ ፊት አልስቅም፡፡
ከአይኔ ብሌን ውስጥ ፣ ብርሐን ይፈልቃል
አይኔን ያየ ሁሉ
ልቡን አሳውሮ ፣ በፍቅር ይወድቃል፡፡
፡፡፡፡፡
የገላዬ ጠረን ፣ ከሽቱ እጥፍ ነው
መልካም ጠረን ሁሉ...
አለ ባሉት ስፍራ ፣ እኔ አለሁ ማለት ነው፡፡
ፀባየ ትሁት ነኝ ፣ ምጡቅ ነው እውቀቴ
ግርማ ሞገሳም ነው ፣ ተክለ ሰውነቴ
ያየኝ ይወደኛል
የወደየኝ ሁሉ ፣ መቼም አይጠላኝም
ከዚ በላይ እንኳን...
ብዙም ስለራሴ ፣ የማውቀው የለኝም፡፡
እንደውም እንደውም...
አልጎርርም እንጂ ፣
ያፈር ሰውነቴን ፣ በቁንጅና አብየው
ቆንጆ ማየት ሲያምረኝ ፣ ራሴን ነው ማየው፡፡
ብቻ ግን ቆንጆ ነኝ!!!
ዳዳ ነኝ ፓፓራራም ላላላላም
___
BY ግጥም ፍቅር ቅኔ
Share with your friend now:
tgoop.com/hollypoem/10669